Addis Ababa City land Development And Administration Bureau
5.42K subscribers
8K photos
76 videos
20 files
331 links
Download Telegram
በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ ሴቶችን ያከበረች ከተማ አዲስ አበባ!

በአዲስ አበባ ከተገነቡ ግዙፍ ፕሮጀክቶች ሁሉ የተለየና የላቀ ትርጉም ያለው ለነገዋ የሴቶች ተሃድሶና ክህሎት ማበልፀጊያ ማዕከል በአስቸጋሪና በምስቅልቅል ሁኔታ ውስጥ የነበሩ ሴችን ህይወት የቀየረ ለብዙዎች የመንፈስ እርካታን ያጎናፀፈ ዘመን ተሻጋሪ ስራ ነው፡፡

ማዕከሉ ከዚህ ቀደም ትኩረት የተነፈጋቸው እና በጎዳና ላይ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ይኖሩ የነበሩ በተለይም በወሲብ ንግድ ላይ የተሰማሩና ለጾታዊ ጥቃት ተጋላጭ የነበሩ ሴቶችን ከነበሩበት አሰቃቂ ህይወት በማላቀቅ በመንከባከብና መጠለያ በመሆን ህይወታቸው እንዲቀየርና ገቢ እንዲያገኙ ብሎም እራሳቸውን እንዲችሉ በማድረግ ከፍተኛ አስተዋጾ እያበረከተ ይገኛል፡፡

በመዲናችን አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የሚገኘውና በከተማ አስተዳደሩ መልካም እሳቤ የተገነባው የነገዋ የሴቶች ተሀድሶ እና ክህሎት ማበልጸጊያ ማዕከል በአንድ ጊዜ እስከ 2 ሺህ በዓመት ደግሞ እስከ 10 ሺህ የሚደርሱ ሴቶችን የመቀበል አቅም አለው ፡፡

ይህ ግዙፍና ለብዙዎች የመንፈስ እርካታን ያጎናፀፈ ፕሮጀክት በአስቸጋሪ ህይወት ይኖሩ የነበሩ ሴቶችን ከነበረባቸው ሁለንተናዊ ችግር በማላቀቅ ኑሯቸውን በማሻሻል የሥነ ልቦና ድጋፍ እና የጤና እንክብካቤ እንዲያገኙ በማድረግ በስነ-ውበት፣ በፋሽንና ጨርቃ ጨርቅ፣ በምግብ ዝግጅት እንዲሁም በሌሎች 18 የሙያ ዘርፎች የተሟላ ዕውቀት እንዲያገኙ በማድረግ በቀጥታ ወደ ስራ እንዲገቡ እያደረገ ይገኛል፡፡

በአጠቃላይ ከተመሠረተ ጀምሮ በድምሩ 3258 ሰልጣኞችን በማብቃት ወደ ስራው ዓለም እንዲቀላቀሉ በማድረግ ህይወታቸውን በተሻለ መንገድ እንዲመሩና ለሌሎችም አርዓያ እንዲሆኑ በማድረግ ላይ ይገኛል ።

ለነገዋ የሴቶች ተሃድሶና ክህሎት ማበልፀጊያ ማዕከል በከተማ አስተዳደሩ የሚተገበሩ ግዙፍ ፕሮጀክቶች የሰው ህይወት ላይ መሰረት ያደረጉ የብዙዎችን እንባ ያበሱ እንዲሁም ታሪክን በደማቁ የፃፉ ስለመሆናቸው ይህ ታላቅ ስራ ህያው ምስክር ነው፡፡
2👏1
በቅርቡ ስራ ላይ የዋለው የካሳ ሞጁል ልማት ተነሺዎች ፍትሐዊ የካሳ ክፍያ እንዲያገኙ ከማስቻል ባለፈ በአተገባበር ወቅት ይስተዋል የነበረውን ብልሹ አሰራር መግታቱን የየካ ክፍለ ከተማ መሬት ልማትና አስተዳደር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ገለፀ።

ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ በተጠናቀቀው 2018 በጀት ዓመት ለ1ሺ 226 የልማት ተነሺዎች 2.5 ቢሊየን ብር የካሳ ክፍያ ስለ መፈፀሙም ተመላክቷል ፡፡

ነሀሴ 06/2018 (መልአ)

************

የአዲስ አበባ ከተማ መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ያለ ፕላን የተሰሩና የተጎሳቆሉ የከተማዋን ክፍል መልሶ በማልማት ፤ ከተማዋን ምቹ የመኖሪያ እና ተመራጭ የኢንቨስትመንት መዳረሻ ለማድረግ የተያዘው ውጥን እንዲሳካ የበኩላን አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል ፡፡

ቢሮው በተለይ ባለፉት የለውጥ ዓመታት በኮሪደር ልማትና በወንዝ ዳርቻ ፕሮጀክቶች ምክንያት ለሚነሱ ህጋዊ የልማት ተነሺዎች ምትክ ቤት ፣ ቦታ እና የካሳ ክፍያ በመፈፀም አካባቢው መልሶ እንዲለማ ክትትልና ድጋፍ እያደረገ ይገኛል፡፡

የየካ ክፍለ ከተማ መሬት ልማትና አስተዳደር ቅርንጫፍ ጽ/ቤትም ጫካ ፕሮጀክትን ጨምሮ በክፍለ ከተማ እየተተገበረ ባለው የኮሪደር ልማትና የወንዝ ዳርቻ ፕሮጀክት ምክንያት ከአከባቢው ለተነሱ 1ሺ 226 የግልና የቀበሌ ቤቶች 2.5 ቢሊየን ብር የካሳ ክፍያ በመፈፀም ፕሮጀክቶቹ በተያዘላቸው የጊዜ ገደብ እንዲጠናቀቁ መደላድል መፈጠሩን የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ኃላፊ አቶ ቢሆነኝ አበጋዝ ተናግረዋል፡፡

ከተከፈለው ካሳ 38.55 ሚሊየኑ ለ581 የቀበሌ ቤቶች ለዕቃ ማጓጓዣ ትራንስፖርት የተፈፀመ መሆኑንም ኃላፊው አብራርተዋል፡፡

በበጀት ዓመቱ የልማት ተነሺዎች መረጃ አሰባሰብና የካሳ ትንተና ስራዎችን ለማዘመን ስራ ላይ የዋለው የካሳ ሞጁል ፤ የልማት ተነሺዎች ፍትሐዊ የካሳ ክፍያ እንዲያገኙ ከማስቻል ባለፈ ብልሹ አሰራርን መሉ ለሙሉ ማክሰም ያስቻለ መሆኑን አቶ ቢሆነኝ ጨምረው ገልፀዋል ፡፡

ለበለጠ መረጃ ትስስር ገፆቻችንን Like, Follow, subscribe በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ።
👇👇👇👇👇👇
Website: - https://www.aalb.gov.et
https://linktr.ee/addisabababacityland
Email :-addisabababacityland@gmail.com
4
የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በ2019 በጀት ዓመት ለልዩ ልዩ ፕሮጀክቶች 1ሺ ሄክታር የለማ መሬት አዘጋጅቶ ለማስተላለፍ ማቀዱን ገለፀ።

ይህ የተገለፀው ቢሮው በ2019 በጀት ዓመት ረቂቅ እቅድ ላይ በተወያየበት መድረክ ላይ ነው ።

ነሀሴ 07/2018(መልአ)
****

ዘመናዊ የመሬት አስተዳደር ስርዓት የተዘረጋበትና የላቀ አገልግሎት የሚሰጥበት ተቋም ለመፍጠር ራዕይ ሰንቆ የተቋቋመው የአዲስ አበባ ከተማ መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በየደረጃው የሚገኙ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት የዘርፉን የ2019 በጀት ዓመት ረቂቅ እቅድ እና የሰው ተኮር ተግባራትን በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ገምግሟል ።

የግምገማ መድረኩን በንግግር የከፈቱት የቢሮው ኃላፊ አቶ መላኩ ታምሩ መድረኩ የ2019 በጀት ዓመት ረቂቅ እቅድ የተሟላ እንዲሆን ግብዓት ለመሰብሰብ ታስቦ መዘጋጀቱን ገልፀው ጥራት ያለው አገልግሎት በመስጠት ብቁና ተወዳዳሪ ተቋም ለመፍጠር አመራሩ ከምንጊዜውም በላይ የመሪነት ሚናውን እንዲወጣ አሳስበዋል።

በየደረጃው ተጠያቂነትን በማስፈን ሌብነትን ማክሰም እንደሚገባም በማከል ።

የበጀት ዓመቱን ረቂቅ እቅድ ሪፖርት ያቀረቡት የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ካሳሁን ዓለሙ በበኩላቸው በተጠናቀቀው 2018 በጀት ዓመት ለተለያየ አገልግሎቶች 929 ሄክታር መሬት ተዘጋጅቶ መተላለፉን አስታውሰው ፤ በተያዘው 2019 በጀት ዓመት ሀገራዊ ፋይዳ ያላቸው ፕሮጀክቶችን ጨምሮ 1ሺ ሄክታር የለማ መሬት አዘጋጅቶ ለማስተላለፍ ውጥን መያዙን ተናግረዋል ።

አያይዘውም በተመቻቸው ኦንላይን አገልግሎት በመታገዝ ከ1988 እስከ 1997 አግባብ ባለው አካል ሳይፈቀድ የተያዙ 10,500 ሰነድ አልባ ይዞታዎችን የባለቤትነት ማረጋገጫ ካርታ አዘጋጅቶ ለማሰራጨት እና አገልግሎት አሰጣጥን በማሳለጥ ከይዞታና ከሊዝ 36.7 ቢሊየን ብር ለመሰብሰብ መታቀዱንም አብራርተዋል ።

በዚሁ መድረክ በ2018 በጀት ዓመት የላቀ አፈፃፀም ላስመዘገቡ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች፣ የማዕከል ሰራተኞች እና የተቋሙ አገልግሎት አሰጣጥ እንዲሻሻል አስተዋጽኦ ላበረከቱ የመማክርት ጉባኤ አባላት እውቅናና የማበረታቻ ሽልማት ተሰጥቷል ።

ለበለጠ መረጃ ትስስር ገፆቻችንን Like, Follow, subscribe በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ።
������
Website: - https://www.aalb.gov.et
https://linktr.ee/addisabababacityland
Email :-addisabababacityland@gmail.com
10
የኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ የድህረ ምረቃ ተማሪዎች እና የዩኒቨርሲቲው ምሁራን በአዲስ አበባ ጉብኝት አደረጉ

የኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ የድህረ ምረቃ ተማሪዎች እና የዩኒቨርሲቲው ምሁራንን ያካተተ የልዑካን ቡድን በአዲስ አበባ የተለያዩ የቱሪዝም መዳረሻዎችን ጎበኙ::

የልዑካን ቡድኑ የአብርሆት ቤተ መጽሀፍ፣ የሳይንስ ሙዚየም፣ የአራዳ ፓርክ፣ የወንዝ ዳር ልማት እና የአንድነት ፓርክን ጎብኝተዋል:: በጉብኝታቸው ባዩት የቱሪዝም ሀብትና በአዲስ አበባ ፈጣን የልማት ጉዞ እጅግ መደነቃቸውን ገልጸዋል::

አዲስ አበባ በሚኖራቸው ቆይታም በከተማዋ የሚገኙ ሌሎች የቱሪዝም መዳረሻዎችንና የልማት ስራዎችን የሚጎበኙ ሲሆን ጉብኝቱ የከተማዋን የቱሪዝም ሀብት በአለም አቀፍ ደረጃ ለማስተዋወቅ፣ የቱሪዝም ኢንቨስትመንት ዕድሎችን ለማስፋት እና የጋራ ትብብርን ለማጠናከር ትልቅ አስተዋጽኦ ይኖረዋል።
2