Addis Ababa City land Development And Administration Bureau
5.42K subscribers
7.99K photos
76 videos
20 files
329 links
Download Telegram
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ስለ ወዳጅነት ፓርክ ካስተላለፉ መልዐክት፦

“በአዲስ አበባ መሐል የሚገኘው የወዳጅነት ፓርክ ባለፉት ስምንት ዓመታት በመደመር መንግሥት ከተገነቡት የመጀመሪያዎቹ ዘርፈ-ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው የሕዝብ መገልገያ ቦታዎች አንዱ ነው። ይህ ፓርክ ባለፉት አራት ዓመታት ብቻ ወደ አንድ ቢሊዮን ብር ገደማ ገቢ ያስገኘ ሲሆን፣ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የሥራ ዕድሎችንና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትን ፈጥሯል።”

Prime Minister Abiy Ahmed’s message about Friendship Park:

“Friendship Park, located in the heart of Addis Ababa, is one of the first multifunctional public spaces built by the Medemer Government over the past eight years. In the past four years alone, the park has generated close to one billion birr in revenue, while creating employment opportunities and economic benefits both directly and indirectly.”

#PMOEthiopia
#EthiopiaDelivers
ኢትዮጵያን ከወጣቶቿ ነጥሎ ማየት አይቻልም!

የህዝባችን የእድሜ ስብጥር እንደሚያመላክተው ወጣቶች ከፍተኛውን "ቁጥር መያዛቸው፣ ብልጽግናን ለማረጋገጥና ለማፅናትም ታላቅ እድል ነው።

‎የኢትዮጵያ ወጣት መልካም ዓላማን አንግቦ የሚንቀሳቀስ፣ የለውጥ ዋነኛ ሞተርና የሉዓላዊነታችን ጽኑ ማገር ነው! የኢትዮጵያ ወጣት የሀገሩን ታሪክ በአዲስ ብዕርና ብራና እየጻፈ ይገኛል። ሀገራችንን የኋሊት ጠፍንገው የያዟትን አጓጉል ልማዶች፣ አላስፈላጊ ንትርኮች፣ ጭቅጭቅ እና ግጭቶች በመራቅ የአሁን ወጣት በልማት ላይ አተኩሯል፣ ድህነትን ተጠይፏል።

የመደመር መንግሥት የወጣቶችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነትና የአመራርነት ሚና ለማጠናከር በትኩረትና በቁርጠኝነት እየሰራ ይገኛል።

‎ሀገራዊ ርዕያችንን ዕውን ለማድረግ ሁላችሁም በንቃት እየተጋን፣ በፍቅር እንድንመላለስ ጥሪዬን አቀርባለሁ።"

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
2
ለውበት፥ ለኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እድገት
አስተዋፅኦ እያደረገ ያለው የቆሻሻ አስተዳደር ስርዓት!

አዲስ አበባ በደረቅ እና ፈሳሽ ቆሻሻ አስተዳደር የከተማዋን ገጽታ የለወጡ መጠነ ሰፊ ሥራዎችን አከናውናለች። ከተማ አስተዳደሩ የተገበረው የተቀናጀ የቆሻሻ አስተዳደር ሥርዓት ከተማዋን ለነዋሪዎቿ ጽዱና ተስማሚ አካባቢን ከመፍጠር ባለፈ የማህበረሰቡ ጤና እንዲጠበቅ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክቷል።

ባለፉት አምስት አመታት የዘመነ የቆሻሻ አስተዳደር ስርዓት ተግባራዊ በመደረጉ እጅግ ከፍተኛ ቶን የደረቅ ቆሻሻ እና ፈሳሽ ቆሻሻ በመልሶ መጠቀም ኡደት ውስጥ ውሏል፡፡

የቆሻሻ አስተዳደር ሥርዓቱ ከንጽህና ባሻገር ለከተማዋ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እድገት የማይናቅ ሚና እየተጫወተ ይገኛል። በዘርፉ በተደራጁ ወጣቶች፣ ሴቶችና ማህበራት አማካይነት ሰፊ የሥራ እድል ከመፍጠሩም በላይ ቆሻሻን ወደ ሀብት የመቀየር (Recycling) አሰራር ተተግብሯል። ከዚህ በፊት ለከተማ ብክለትና ለጤና ስጋት የነበረው ቆሻሻ ዛሬ ሃብት እንዲሆን ተደርጓል፡፡ በየዓመቱ በከተማችን ከደረቅ ቆሻሻ በብዙ ቶን ኮምፖስት ለከተማ ግብርና ይመረታል፡፡ እንዲሁም ከደረቅና ፈሻስ ቆሻሻ ለኃይል ማመንጫ መቅረቡ የቆሻሻ አስተዳደር ከመሰብሰብና ከመጣል ወደ ኡደት፣ ኢኮኖሚያዊ ጥቅም እና ኃይል ምንጭነት እየተሸጋገረ ከተማችንን ውብ እና ፅዱ ማድረግ ተችሏል።

ይህ የተቀናጀ የቆሻሻ አስተዳደር ስርዓት አዲስ አበባን ውብ፡ ጽዱ እንድትሆንና ዓለም አቀፍ እውቅናን እንድታገኝ አድርጓታል፡፡ ስኬቱ ከተማዋ ለአገር ውስጥና ለውጭ ሀገር ጎብኚዎች ሳቢ፣ ምቹና ጽዱ እንድትሆን ያስቻለ ሲሆን ይህም አዲስ አበባን በአፍሪካ ደረጃ ከ10 ጽዱ ከተሞች አንዷ አድርጓታል።

በመሆኑም የጽዳቱ ውጤት አዲስ አበባ የአህጉራችን የዲፕሎማሲ ማዕከልነቷን የሚያረጋግጥ የጽዳትና የመሰረተ ልማት ደረጃ ላይ መድረሷን ያረጋግጣል።
በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ ሴቶችን ያከበረች ከተማ አዲስ አበባ!

በአዲስ አበባ ከተገነቡ ግዙፍ ፕሮጀክቶች ሁሉ የተለየና የላቀ ትርጉም ያለው ለነገዋ የሴቶች ተሃድሶና ክህሎት ማበልፀጊያ ማዕከል በአስቸጋሪና በምስቅልቅል ሁኔታ ውስጥ የነበሩ ሴችን ህይወት የቀየረ ለብዙዎች የመንፈስ እርካታን ያጎናፀፈ ዘመን ተሻጋሪ ስራ ነው፡፡

ማዕከሉ ከዚህ ቀደም ትኩረት የተነፈጋቸው እና በጎዳና ላይ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ይኖሩ የነበሩ በተለይም በወሲብ ንግድ ላይ የተሰማሩና ለጾታዊ ጥቃት ተጋላጭ የነበሩ ሴቶችን ከነበሩበት አሰቃቂ ህይወት በማላቀቅ በመንከባከብና መጠለያ በመሆን ህይወታቸው እንዲቀየርና ገቢ እንዲያገኙ ብሎም እራሳቸውን እንዲችሉ በማድረግ ከፍተኛ አስተዋጾ እያበረከተ ይገኛል፡፡

በመዲናችን አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የሚገኘውና በከተማ አስተዳደሩ መልካም እሳቤ የተገነባው የነገዋ የሴቶች ተሀድሶ እና ክህሎት ማበልጸጊያ ማዕከል በአንድ ጊዜ እስከ 2 ሺህ በዓመት ደግሞ እስከ 10 ሺህ የሚደርሱ ሴቶችን የመቀበል አቅም አለው ፡፡

ይህ ግዙፍና ለብዙዎች የመንፈስ እርካታን ያጎናፀፈ ፕሮጀክት በአስቸጋሪ ህይወት ይኖሩ የነበሩ ሴቶችን ከነበረባቸው ሁለንተናዊ ችግር በማላቀቅ ኑሯቸውን በማሻሻል የሥነ ልቦና ድጋፍ እና የጤና እንክብካቤ እንዲያገኙ በማድረግ በስነ-ውበት፣ በፋሽንና ጨርቃ ጨርቅ፣ በምግብ ዝግጅት እንዲሁም በሌሎች 18 የሙያ ዘርፎች የተሟላ ዕውቀት እንዲያገኙ በማድረግ በቀጥታ ወደ ስራ እንዲገቡ እያደረገ ይገኛል፡፡

በአጠቃላይ ከተመሠረተ ጀምሮ በድምሩ 3258 ሰልጣኞችን በማብቃት ወደ ስራው ዓለም እንዲቀላቀሉ በማድረግ ህይወታቸውን በተሻለ መንገድ እንዲመሩና ለሌሎችም አርዓያ እንዲሆኑ በማድረግ ላይ ይገኛል ።

ለነገዋ የሴቶች ተሃድሶና ክህሎት ማበልፀጊያ ማዕከል በከተማ አስተዳደሩ የሚተገበሩ ግዙፍ ፕሮጀክቶች የሰው ህይወት ላይ መሰረት ያደረጉ የብዙዎችን እንባ ያበሱ እንዲሁም ታሪክን በደማቁ የፃፉ ስለመሆናቸው ይህ ታላቅ ስራ ህያው ምስክር ነው፡፡
2👏1
በቅርቡ ስራ ላይ የዋለው የካሳ ሞጁል ልማት ተነሺዎች ፍትሐዊ የካሳ ክፍያ እንዲያገኙ ከማስቻል ባለፈ በአተገባበር ወቅት ይስተዋል የነበረውን ብልሹ አሰራር መግታቱን የየካ ክፍለ ከተማ መሬት ልማትና አስተዳደር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ገለፀ።

ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ በተጠናቀቀው 2018 በጀት ዓመት ለ1ሺ 226 የልማት ተነሺዎች 2.5 ቢሊየን ብር የካሳ ክፍያ ስለ መፈፀሙም ተመላክቷል ፡፡

ነሀሴ 06/2018 (መልአ)

************

የአዲስ አበባ ከተማ መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ያለ ፕላን የተሰሩና የተጎሳቆሉ የከተማዋን ክፍል መልሶ በማልማት ፤ ከተማዋን ምቹ የመኖሪያ እና ተመራጭ የኢንቨስትመንት መዳረሻ ለማድረግ የተያዘው ውጥን እንዲሳካ የበኩላን አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል ፡፡

ቢሮው በተለይ ባለፉት የለውጥ ዓመታት በኮሪደር ልማትና በወንዝ ዳርቻ ፕሮጀክቶች ምክንያት ለሚነሱ ህጋዊ የልማት ተነሺዎች ምትክ ቤት ፣ ቦታ እና የካሳ ክፍያ በመፈፀም አካባቢው መልሶ እንዲለማ ክትትልና ድጋፍ እያደረገ ይገኛል፡፡

የየካ ክፍለ ከተማ መሬት ልማትና አስተዳደር ቅርንጫፍ ጽ/ቤትም ጫካ ፕሮጀክትን ጨምሮ በክፍለ ከተማ እየተተገበረ ባለው የኮሪደር ልማትና የወንዝ ዳርቻ ፕሮጀክት ምክንያት ከአከባቢው ለተነሱ 1ሺ 226 የግልና የቀበሌ ቤቶች 2.5 ቢሊየን ብር የካሳ ክፍያ በመፈፀም ፕሮጀክቶቹ በተያዘላቸው የጊዜ ገደብ እንዲጠናቀቁ መደላድል መፈጠሩን የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ኃላፊ አቶ ቢሆነኝ አበጋዝ ተናግረዋል፡፡

ከተከፈለው ካሳ 38.55 ሚሊየኑ ለ581 የቀበሌ ቤቶች ለዕቃ ማጓጓዣ ትራንስፖርት የተፈፀመ መሆኑንም ኃላፊው አብራርተዋል፡፡

በበጀት ዓመቱ የልማት ተነሺዎች መረጃ አሰባሰብና የካሳ ትንተና ስራዎችን ለማዘመን ስራ ላይ የዋለው የካሳ ሞጁል ፤ የልማት ተነሺዎች ፍትሐዊ የካሳ ክፍያ እንዲያገኙ ከማስቻል ባለፈ ብልሹ አሰራርን መሉ ለሙሉ ማክሰም ያስቻለ መሆኑን አቶ ቢሆነኝ ጨምረው ገልፀዋል ፡፡

ለበለጠ መረጃ ትስስር ገፆቻችንን Like, Follow, subscribe በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ።
👇👇👇👇👇👇
Website: - https://www.aalb.gov.et
https://linktr.ee/addisabababacityland
Email :-addisabababacityland@gmail.com
4