ለልማት የተላለፈ ቦታን አጥሮ ያስቀመጡ የ50 አልሚዎች ውል ማቋረጡን የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ገለፀ ።
ነሀሴ 05/2018 /መልአ/
******
የአዲስ አበባ ከተማ መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በምደባና በጨረታ መሬት ወስደው ለረጅም ጊዜ ያለ አገልግሎት መሬት አጥሮ የያዙ የ50 አልሚዎችን ውል ማቋረጡን የመሬት ዝግጅትና ማስተላለፍ ዘርፍ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ፌኑስ ገላና ተናግረዋል ።
ኃላፊው ይህን የተናገሩት በተለያየ አግባብ መሬት ወስደው ያለ ልማት ለረጅም ጊዜ አጥሮ የያዙ አልሚዎች ወደ ልማት ያልገቡበትን ምክንያት የጋራ ለማድረግ በተደረገ ውይይት ላይ ነው ።
መንግሥት ላለፉት ዓመታት የከተማውን ኢኮሮሚያዊና ማህበራዊ አገልግሎት ለማቀላጠፍ በዝቅተኛ የሊዝ ክፍያ መሬት በምደባ ማስተላለፉን የገለፁት ምክትል ቢሮው ኃላፊው ፤ ሆኖም በርካታ አልሚዎች በገቡት የሊዝ ውል መሰረት ግንባታ ለመጀመር እና ለማጠናቀቅ ፈቃደኛ አልበሩም ብለዋል ።
በተያዘው በጀት ዓመት ብቻ መሬት በምደባ እንዲያገኙ ከተላለፉ የካብኔ ውሳኔዎች በተደጋጋሚ ጥሪ ቢቀርብም 100 አልሚዎች የሚጠበቅባቸውን የሊዝ ቅድመ ክፍያ ከፍለው ወደ ስራ ለመግባት ዝግጁ እንዳልሆኑ ለማሳያነት የጠቆሙት ኃላፊው አልሚዎች እርምጃ ከመወሰዱ በፊት መንግሥት ያመቻቸውን ተጨማሪ እድል በመጠቀም ወደ ልማት እንደሚገቡ አሳስበዋል ።
ለበለጠ መረጃ ትስስር ገፆቻችንን Like, Follow, subscribe በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ።
👇👇👇👇👇👇
Website: - https://www.aalb.gov.et
https://linktr.ee/addisabababacityland
Email :-addisabababacityland@gmail.com

❤2
የሲስተም ልማቱ አገልግሎት አሰጣጥን በማቀላጠፍ ብልሹ አሰራርን መግታት ችሏል፡፡ አቶ ቢሆነኝ አበጋዝ
ነሀሴ 05/2018 /መልአ/
******************
በተጠናቀቀው 2018 በጀት ዓመት ተሻሽሎ ስራ ላይ የዋለው የሲስተም ማሻሻያ አገልግሎት አሰጣጥን በማሳለጥ ብልሹ አሰራርን መግታት መቻሉን የየካ ክፍለ ከተማ መሬት ልማትና አስተዳደር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ቢሆነኝ አበጋዝ ገልፀዋል፡፡
እንደ ጽ/ቤቱ ኃላፊው ማብራሪያ የሲስተም ልማቱ ደንበኞች በጊዜና በቦታ ያልተገደበ ፈጣን እና ፍትሐዊ አገልግሎት እንዲያገኙ ከማስቻሉም ባለፈ ተጠያቂነትን በማስፈን ብልሹ አሰራርን ማክሰም ችሏል፡፡
በ2018 አፈፃፀም በተሸሻለው ሲስተም በመታገዝ 5ሺ 639 ኢ-ካርታ ተዘጋጅቶ መሰራጨቱን ገልፀው ይህም የሲስተም ማሻሻያው ውጤታማነት አንዱ ማሳያ ነው ያሉት ኃላፊው ከዚህ በተጨማሪ በበጀት ዓመቱ ከይዞታና ከሊዝ አገልግሎት 638 ሚሊየን 776 ሺ ብር ለመሰብሰብ እቅድ ተይዞ ከ 674 ሚሊየን ብር በላይ በመሰብሰብ የእቅዱን 105% ማሳካት መቻሉን በማስረጃነት አቅርበዋል ፡፡
በቢሮው ደረጃ የተያዘውን የገቢ እቅድ ለማሳካትም የዘጠና ቀን የማካካሻ እቅድ ተዘጋጅቶ ወደ ስራ ተገብቷል ያሉት ኃላፊው በሐምሌ ወር ከመደበኛ የይዞታ አገልግሎትና ከሊዝ ገቢ 46 ሚሊየን ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ ከ48 ሚሊየን ብር በላይ መሰብሰብ እንደተቻለ ገልፀዋል፡፡
አያይዘውም በተለያየ ጊዜ በውልና ማስረጃ ለተፈፀሙ ግዥዎች ልዩ ስመ ንብረት ዝውውር እየተደረገ መሆኑን ጠቁመው ደንበኞች እስከ ጳጉሜ 5/2018 ዓ.ም በተመቻቸው የኦንላይን አገልግሎት በማመልከት የባለቤትነት ዋስትናቸውን እንዲያረጋግጡ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ከቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተውም በበጀት ዓመቱ ተጠያቂነትን ለማስፈን በተሰራ ስራ የመንግስት የስራ ሰዓት የሸራረፉ እና ደንበኞችን ለእንግልት የዳረጉ 11 ባለሙዎች ላይ ከከባድ እስከ ቀላል የዲስፕሊን እርምጃ ተወስዷል፡፡

❤6
በጤናው ዘርፍ በ5 ዓመታት ውስጥ ባለፉት 100 ዓመታት ከተመዘገበው በእጥፍ የሚበልጥ እድገት ማስመዝገብ ተችሏል ።
አዲስ አበባን የጤና ቱሪዝም ማዕከል የማድረግ ጉዞ ተጨባጭ ለውጦችን አስመዝግቧል።
ከተማችን በሁለንተናዊ መልኩ እንድትለወጥ ከተሰሩ ስራዎች አንዱ በጤናው ዘርፍ የታየው የጤና መሰረተ ልማት የማስፋፋት ስራ ዋነኛው ነው፡፡
ባለፉት 5 ዓመታት ውስጥ የጤና መሰረተ ልማትን ለማስፋፋት ከተሰሩ ስራዎች ውስጥ በዳግማዊ ሚኒሊክ ሆስፒታል ውስጥ የተገነቡት ዘመናዊ የአይን ሕክምና፣ የኩላሊት እጥበት እንዲሁም የፎረንሲክ እና ስነምረዛ ምርምር አገልግሎት መስጫ ማዕከላት ይጠቀሳሉ፡፡
በዘውዲቱ ሆስፒታል እጅግ ዘመናዊ ተደርጎ የተገነባው የህክምና ልህቀት ማዕከል እና በራስ ደስታ ዳምጠው ሆስፒታል ውስጥ ለታካሚዎች ዘመኑን የዋጀ የህክምና አገልግሎት የሚሰጥ “አዲስ የላቀ የህክምና ማዕከል” ተገንብተው አገልግሎት እየሰጡ ይገኛሉ፡፡ በማዕከላቱ በነባሮቹ ሆስፒታሎች በኋላቀር የህክምና መሳሪዎች እና ለታካሚዎች በማይመችና በተጨናነቀ ሁኔታ ይሰጡ የነበሩ አገልግሎቶችን በመቀየር የዘመኑ ቴክኖሎጂ ተሟልተውላቸው አገልግሎት እየሰጡ ይገኛሉ፡፡
በተጨማሪም የአበበች ጎበና እናቶችና ህጻናት ሆስፒታል፣ ላፍቶ እስፔሻላይዝድ ሆስፒታል፣ ኮልፌ እስፔሻላይዝድ ሆስፒታል እና የገላን ድንገተኛ ህክምና ሆስፒታል በጥቂት ዓመታት ውስጥ በአዲስ አበባ የተገነቡ የህክምና ማዕከላቶች ናቸው።
ለ4ዐ ጤና ጣቢያዎች መሰረታዊ ማስፋፊያ እና 9 አዳዲስ የጤና ጣቢያዎች ተገንብተው ወደ አገልግሎት ገብተዋል፡፡
አዲሰ አበባን የጤና ቱሪዝም ማዕከል ማድረግ እና በጤናው ዘርፍ ያለው ፍላጎት በመንግስት ብቻ የማይሟላ በመሆኑ የግሉን ዘርፍ በመደገፍም እጅግ ዘመናዊ የህክምና አገልግሎት የሚሰጡ ሆስፒታሎች እንዲገነቡ ተደጓል።
በአጠቃላይ በጤናው ዘርፍ በተከናወኑ ስራዎች ከ 5 ዓመት በፊት የነበሩትን አልጋዎች ቁጥር ከ 2 እጥፍ በላይ ማሳደግ ተችሏ፡፡ በዚህም በ 5 ዓመታት ውስጥ የታየው እድገት ባለፉት 100 ዓመታት ከተመዘገበው እድገት በእጥፍ እንዲበልጥ አድርጎታል፡፡
ጤናችንን የምንጠብቀው በሕክምና ብቻ ሳይሆን በመከላከል ጭምር በመሆኑ አዲስ አበባን ከብክለት በመከላከል፣ ፅዱ አረንጓዴ እና ለኑሮ ተስማሚ ከተማ በማድረግ ጤናማ አካባቢን የመፍጠር የጤና ፖሊሲያችን በከተማችን በተሟላ ሁኔታ እየተተገበረ ይገኛል፡፡

❤1
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ስለ ወዳጅነት ፓርክ ካስተላለፉ መልዐክት፦
“በአዲስ አበባ መሐል የሚገኘው የወዳጅነት ፓርክ ባለፉት ስምንት ዓመታት በመደመር መንግሥት ከተገነቡት የመጀመሪያዎቹ ዘርፈ-ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው የሕዝብ መገልገያ ቦታዎች አንዱ ነው። ይህ ፓርክ ባለፉት አራት ዓመታት ብቻ ወደ አንድ ቢሊዮን ብር ገደማ ገቢ ያስገኘ ሲሆን፣ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የሥራ ዕድሎችንና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትን ፈጥሯል።”
Prime Minister Abiy Ahmed’s message about Friendship Park:
“Friendship Park, located in the heart of Addis Ababa, is one of the first multifunctional public spaces built by the Medemer Government over the past eight years. In the past four years alone, the park has generated close to one billion birr in revenue, while creating employment opportunities and economic benefits both directly and indirectly.”
#PMOEthiopia
#EthiopiaDelivers