Addis Ababa City land Development And Administration Bureau
5.41K subscribers
7.97K photos
76 videos
20 files
328 links
Download Telegram
የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በአሰራር ጥራት ኦዲት 1.7 ቢሊየን ብር የሚገመት የመንግስት ሃብት ከብክነት ማዳኑን ገለፀ።

ነሀሴ 04 ቀን 2018 ዓ.ም
*****
የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በአሰራር ጥራት ኦዲት ድንገተኛ፣ የጥቆማ እና መደበኛ ኦዲቶችን ያካሂዶል።

የአሰራር ጥራት ኦዲት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ በየነ ላምቢሶ እንደገለፁት በ2018 በጀት ዓመት 7 ሺህ 557 የይዞታ ማህደራት ላይ ኦዲት በማድረግ የህግ፣ የአሰራር እና የመመሪያ ጥሰት የተገኘባቸውን 2 ሺህ 041 ማህደራት ተለይተዋል።

የሊዝ ክትትል አገልግሎት ፣ የመብት ፈጠራ አገልግሎት፣ የመሬት ዝግጅት ስራዎች፣ የለማ መሬት ማስተላለፍ እና የካሳና ምትክ ቦታ መስተንግዶ ጥሰት የሚስተዋሉባቸው ዋና ዋና አገልግሎቶች ተብለው መለየታቸውን የጠቆሙት ዳይሬክተሩ በዚህም በ843 ማህደራት ላይ የእርምት እርምጃ ተወስዷል ቀሪዎቹ በሂደት ላይ ናቸው ብለዋል።

በእርምት እርምጃዎችም 193 ይዞታዎች ወደ መሬት ባንክ እንዲመለሱ ከማድረግ በተጨማሪ 1.7 ቢሊየን ብር የሚገመት የመንግስት ሃብት ማዳን መቻሉንም አክለው በቀጣይ የቴክኖሎጂ አጠቃቀምን በማሳደግ በሲስተም የታገዘ ኦዲት ማካሄድ እና ህግ አፍራሾችን ተጠያቂ ማድረግ ላይ ትኩረት ተደርጎ እንደሚሰራ ተናግረዋል።

በውይይቱ ላይ ተሳታፊ የነበሩ የማዕከልና ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አመራርና ሰራተኞች በበኩላቸው፤ ዳይሬክቶሬቱ በዘርፉ የሚታዩ ብልሹ አሰራሮችን ከስር መሰረቱ ለመቅረፍ ትልቅ አቅም መሆኑን ጠቅሰው፣ ስራው ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አጽንኦት ሰጥተዋል።

መድረኩን የመሩት የቢሮው አማካሪ አቶ አዳነ ዘለቀ በበኩላቸው፣ በበጀት ዓመቱ የተመዘገቡት ውጤት የሚበረታታ በመሆኑ የኦዲት መረጃዎችን በአግባቡ ለይቶ በመስጠት የተገኙ የህግና የአሰራር ጥሰቶችን ቶሎ ተፈፃሚ ማድረግ ይገባል ብለዋል ።

ለበለጠ መረጃ ትስስር ገፆቻችንን Like, Follow, subscribe በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ።
👇👇👇👇👇👇
Website: - https://www.aalb.gov.et
https://linktr.ee/addisabababacityland
Email :-addisabababacityland@gmail.com
ለልማት የተላለፈ ቦታን አጥሮ ያስቀመጡ የ50 አልሚዎች ውል ማቋረጡን የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ገለፀ ።

ነሀሴ 05/2018 /መልአ/

******
የአዲስ አበባ ከተማ መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በምደባና በጨረታ መሬት ወስደው ለረጅም ጊዜ ያለ አገልግሎት መሬት አጥሮ የያዙ የ50 አልሚዎችን ውል ማቋረጡን የመሬት ዝግጅትና ማስተላለፍ ዘርፍ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ፌኑስ ገላና ተናግረዋል ።

ኃላፊው ይህን የተናገሩት በተለያየ አግባብ መሬት ወስደው ያለ ልማት ለረጅም ጊዜ አጥሮ የያዙ አልሚዎች ወደ ልማት ያልገቡበትን ምክንያት የጋራ ለማድረግ በተደረገ ውይይት ላይ ነው ።

መንግሥት ላለፉት ዓመታት የከተማውን ኢኮሮሚያዊና ማህበራዊ አገልግሎት ለማቀላጠፍ በዝቅተኛ የሊዝ ክፍያ መሬት በምደባ ማስተላለፉን የገለፁት ምክትል ቢሮው ኃላፊው ፤ ሆኖም በርካታ አልሚዎች በገቡት የሊዝ ውል መሰረት ግንባታ ለመጀመር እና ለማጠናቀቅ ፈቃደኛ አልበሩም ብለዋል ።

በተያዘው በጀት ዓመት ብቻ መሬት በምደባ እንዲያገኙ ከተላለፉ የካብኔ ውሳኔዎች በተደጋጋሚ ጥሪ ቢቀርብም 100 አልሚዎች የሚጠበቅባቸውን የሊዝ ቅድመ ክፍያ ከፍለው ወደ ስራ ለመግባት ዝግጁ እንዳልሆኑ ለማሳያነት የጠቆሙት ኃላፊው አልሚዎች እርምጃ ከመወሰዱ በፊት መንግሥት ያመቻቸውን ተጨማሪ እድል በመጠቀም ወደ ልማት እንደሚገቡ አሳስበዋል ።

ለበለጠ መረጃ ትስስር ገፆቻችንን Like, Follow, subscribe በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ።
👇👇👇👇👇👇
Website: - https://www.aalb.gov.et
https://linktr.ee/addisabababacityland
Email :-addisabababacityland@gmail.com
2
የሲስተም ልማቱ አገልግሎት አሰጣጥን በማቀላጠፍ ብልሹ አሰራርን መግታት ችሏል፡፡ አቶ ቢሆነኝ አበጋዝ

ነሀሴ 05/2018 /መልአ/
******************
በተጠናቀቀው 2018 በጀት ዓመት ተሻሽሎ ስራ ላይ የዋለው የሲስተም ማሻሻያ አገልግሎት አሰጣጥን በማሳለጥ ብልሹ አሰራርን መግታት መቻሉን የየካ ክፍለ ከተማ መሬት ልማትና አስተዳደር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ቢሆነኝ አበጋዝ ገልፀዋል፡፡

እንደ ጽ/ቤቱ ኃላፊው ማብራሪያ የሲስተም ልማቱ ደንበኞች በጊዜና በቦታ ያልተገደበ ፈጣን እና ፍትሐዊ አገልግሎት እንዲያገኙ ከማስቻሉም ባለፈ ተጠያቂነትን በማስፈን ብልሹ አሰራርን ማክሰም ችሏል፡፡

በ2018 አፈፃፀም በተሸሻለው ሲስተም በመታገዝ 5ሺ 639 ኢ-ካርታ ተዘጋጅቶ መሰራጨቱን ገልፀው ይህም የሲስተም ማሻሻያው ውጤታማነት አንዱ ማሳያ ነው ያሉት ኃላፊው ከዚህ በተጨማሪ በበጀት ዓመቱ ከይዞታና ከሊዝ አገልግሎት 638 ሚሊየን 776 ሺ ብር ለመሰብሰብ እቅድ ተይዞ ከ 674 ሚሊየን ብር በላይ በመሰብሰብ የእቅዱን 105% ማሳካት መቻሉን በማስረጃነት አቅርበዋል ፡፡

በቢሮው ደረጃ የተያዘውን የገቢ እቅድ ለማሳካትም የዘጠና ቀን የማካካሻ እቅድ ተዘጋጅቶ ወደ ስራ ተገብቷል ያሉት ኃላፊው በሐምሌ ወር ከመደበኛ የይዞታ አገልግሎትና ከሊዝ ገቢ 46 ሚሊየን ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ ከ48 ሚሊየን ብር በላይ መሰብሰብ እንደተቻለ ገልፀዋል፡፡

አያይዘውም በተለያየ ጊዜ በውልና ማስረጃ ለተፈፀሙ ግዥዎች ልዩ ስመ ንብረት ዝውውር እየተደረገ መሆኑን ጠቁመው ደንበኞች እስከ ጳጉሜ 5/2018 ዓ.ም በተመቻቸው የኦንላይን አገልግሎት በማመልከት የባለቤትነት ዋስትናቸውን እንዲያረጋግጡ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ከቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተውም በበጀት ዓመቱ ተጠያቂነትን ለማስፈን በተሰራ ስራ የመንግስት የስራ ሰዓት የሸራረፉ እና ደንበኞችን ለእንግልት የዳረጉ 11 ባለሙዎች ላይ ከከባድ እስከ ቀላል የዲስፕሊን እርምጃ ተወስዷል፡፡

ለበለጠ መረጃ ትስስር ገፆቻችንን Like, Follow, subscribe በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ።
👇👇👇👇👇👇
Website: - https://www.aalb.gov.et
https://linktr.ee/addisabababacityland
Email :-addisabababacityland@gmail.com
6