Addis Ababa City land Development And Administration Bureau
5.41K subscribers
7.97K photos
76 videos
20 files
328 links
Download Telegram
በዚህ ዘመን የትጥቅ ትግል ማድረግ ፋሽን ያለፈበት ነው - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ኔትወርክ ጋር በነበራቸው ቆይታ፣ በትጥቅ ትግል በኃይል ሥልጣን ለመያዝ ወይም ፍላጎትን ለመጫን የሚደረግ ሙከራ እንደማይሳካ ገልጸው፤ በዚህ ዘመን የትጥቅ ትግል ማድረግ ፋሽን ያለፈበት ነው ብለዋል።

በአሁኑ ወቅት ከኦነግ ሸኔ እና ከሌሎች የታጠቁ ቡድኖች በርካታ ታጣቂዎች የመንግሥትን የሰላም ጥሪ ተቀብለው ወደ ሰላማዊ መንገድ መመለሳቸውን ያነሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ በጫካ የቀሩትም ቢሆኑ በሂደት ነገሩ እየገባቸው ይመጣሉ የሚል እምነት እንዳላቸው ገልጸዋል።

መንግሥት በርካታ የፖለቲካ እስረኞችን ፈትቶ የዴሞክራሲ ምህዳሩን ያሰፋ ቢሆንም፣ የተወሰኑ አካላት ግን ትናንት ካሰሯቸው እና ከገረፏቸው አካላት ጋር ድብቅ ጥምረት ፈጥረው ወደ ጫካ መግባታቸው አሳዝኖናል ብለዋል።

በኦሮሚያ ክልል ሰፊ የዴሞክራሲና የፖለቲካ ተሳትፎ ዕድል በመኖሩ በሰላማዊ መንገድ መታገል ይቻላል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፤ በጫካ የሚገኘው የሸኔ ቡድን ግልጽ ዓላማ እና ግብ የሌለው "ተቀጣሪ ኃይል" ነው ሲሉ ገልጸውታል።

ቡድኑ ሽፍታ ሆኖ ሰዎችን ከመግደልና ከመዝረፍ ውጭ የፖለቲካ ፍላጎቱን ማሳካት እንደማይችልም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል።

የኦነግ መስራች ታጋዮች በአሁኑ ወቅት በሰላማዊ መንገድ በሀገር ውስጥ እና በፓርላማ ተቀምጠው እየታገሉ ባሉበት ሁኔታ፣ በጫካ ያለው ቡድን የማንን አጀንዳ ይዞ እንደሚታገል ሕዝቡ ሊጠይቅ እንደሚገባም አሳስበዋል።

ማንኛውም አካል ፍላጎቱንና ጥያቄውን በሰላማዊ መንገድ እና በምክክር ማሳካት እንደሚችል ያመላከቱት ጠቅላይ ሚነስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፣ አሁንም ቢሆን የመንግሥት የሰላም በር ክፍት እንደሆነ አረጋግጠዋል።
🙈2
ተመራቂዎች እንኳን ደስ አላችሁ!

በተለያየ ማህበራዊ ችግር ውስጥ የነበሩ በየለነገዋ የሴቶች ተሃድሶና ክህሎት ማበልፀጊያ ማዕከል በ5ኛ ዙር የክህሎት እና የስብዕና ግንባታ የሰለጠኑ 858 እህቶቻችንን አስመርቀን ወደ ስራ አሰማርተናል።

በከተማችን ከምንሰራቸው ሰው ተኮር ስራዎች አንዱ ትላንት በጎዳና፣ በችግር እና በተለያዩ ማህበራዊ ቀውሶች ውስጥ የነበሩ ሴቶችን በሙያ ክህሎትና ስብዕና ገንብተን ከነበሩበት አስከፊ ህይወት በማውጣት ወደ ተሻለ ህይወት የምናሰማራበት ቀዳሚው ተግባር ነው።

አዲስ አበባችን ማህበራዊ ፍትህ የሰፈነባት እንዲሁም ለዘመናት የከረሙ ስብራቶቿ የሚጠገኑባት ከተማ የማድረግ የተግባር ውጤት ፍሬ ማሳያዎች ከለነገዋ ተመርቀው አዲስ ህይወት እየመሩ ያሉት ሴቶች እህቶቻችን ናቸው።

የዛሬዎቹ ተመራቂዎችን ጨምሮ በማዕከሉ በድምሩ 3259 ሰልጣኞችን አስመርቀን ወደ ስራው ዓለም እንዲቀላቀሉ በማድረግ ህይወታቸውን በተሻለ መንገድ እንዲመሩና ለሌሎችም አርዓያ እንዲሆኑ አድርገናል።

ውድ ተመራቂዎች፤ አስከፊውን ትላንታችሁን አልፋችሁ፤ በማዕከሉ በነበራችሁ ቆይታ በቀሰማችሁት ክህሎት እና ባገኛችሁት የተሀድሶ ስልጠና ዛሬ ማሸነፍ ችላችኋል፤ ነገም በስራው ዓለም ስኬታማ ለመሆን የሚገጥማችሁን ማንኛውንም ፈተና አሸንፉችሁ ህይወታችሁን ይበልጥ ብሩህ እንደምታደርጉ እናምናለን።

በድጋሚ እንኳን ደስ አላችሁ!

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ሕዝቦቿን ይባርክ!

ከንቲባ አዳነች አቤቤ
3👏1
የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በአሰራር ጥራት ኦዲት 1.7 ቢሊየን ብር የሚገመት የመንግስት ሃብት ከብክነት ማዳኑን ገለፀ።

ነሀሴ 04 ቀን 2018 ዓ.ም
*****
የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በአሰራር ጥራት ኦዲት ድንገተኛ፣ የጥቆማ እና መደበኛ ኦዲቶችን ያካሂዶል።

የአሰራር ጥራት ኦዲት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ በየነ ላምቢሶ እንደገለፁት በ2018 በጀት ዓመት 7 ሺህ 557 የይዞታ ማህደራት ላይ ኦዲት በማድረግ የህግ፣ የአሰራር እና የመመሪያ ጥሰት የተገኘባቸውን 2 ሺህ 041 ማህደራት ተለይተዋል።

የሊዝ ክትትል አገልግሎት ፣ የመብት ፈጠራ አገልግሎት፣ የመሬት ዝግጅት ስራዎች፣ የለማ መሬት ማስተላለፍ እና የካሳና ምትክ ቦታ መስተንግዶ ጥሰት የሚስተዋሉባቸው ዋና ዋና አገልግሎቶች ተብለው መለየታቸውን የጠቆሙት ዳይሬክተሩ በዚህም በ843 ማህደራት ላይ የእርምት እርምጃ ተወስዷል ቀሪዎቹ በሂደት ላይ ናቸው ብለዋል።

በእርምት እርምጃዎችም 193 ይዞታዎች ወደ መሬት ባንክ እንዲመለሱ ከማድረግ በተጨማሪ 1.7 ቢሊየን ብር የሚገመት የመንግስት ሃብት ማዳን መቻሉንም አክለው በቀጣይ የቴክኖሎጂ አጠቃቀምን በማሳደግ በሲስተም የታገዘ ኦዲት ማካሄድ እና ህግ አፍራሾችን ተጠያቂ ማድረግ ላይ ትኩረት ተደርጎ እንደሚሰራ ተናግረዋል።

በውይይቱ ላይ ተሳታፊ የነበሩ የማዕከልና ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አመራርና ሰራተኞች በበኩላቸው፤ ዳይሬክቶሬቱ በዘርፉ የሚታዩ ብልሹ አሰራሮችን ከስር መሰረቱ ለመቅረፍ ትልቅ አቅም መሆኑን ጠቅሰው፣ ስራው ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አጽንኦት ሰጥተዋል።

መድረኩን የመሩት የቢሮው አማካሪ አቶ አዳነ ዘለቀ በበኩላቸው፣ በበጀት ዓመቱ የተመዘገቡት ውጤት የሚበረታታ በመሆኑ የኦዲት መረጃዎችን በአግባቡ ለይቶ በመስጠት የተገኙ የህግና የአሰራር ጥሰቶችን ቶሎ ተፈፃሚ ማድረግ ይገባል ብለዋል ።

ለበለጠ መረጃ ትስስር ገፆቻችንን Like, Follow, subscribe በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ።
👇👇👇👇👇👇
Website: - https://www.aalb.gov.et
https://linktr.ee/addisabababacityland
Email :-addisabababacityland@gmail.com
ለልማት የተላለፈ ቦታን አጥሮ ያስቀመጡ የ50 አልሚዎች ውል ማቋረጡን የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ገለፀ ።

ነሀሴ 05/2018 /መልአ/

******
የአዲስ አበባ ከተማ መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በምደባና በጨረታ መሬት ወስደው ለረጅም ጊዜ ያለ አገልግሎት መሬት አጥሮ የያዙ የ50 አልሚዎችን ውል ማቋረጡን የመሬት ዝግጅትና ማስተላለፍ ዘርፍ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ፌኑስ ገላና ተናግረዋል ።

ኃላፊው ይህን የተናገሩት በተለያየ አግባብ መሬት ወስደው ያለ ልማት ለረጅም ጊዜ አጥሮ የያዙ አልሚዎች ወደ ልማት ያልገቡበትን ምክንያት የጋራ ለማድረግ በተደረገ ውይይት ላይ ነው ።

መንግሥት ላለፉት ዓመታት የከተማውን ኢኮሮሚያዊና ማህበራዊ አገልግሎት ለማቀላጠፍ በዝቅተኛ የሊዝ ክፍያ መሬት በምደባ ማስተላለፉን የገለፁት ምክትል ቢሮው ኃላፊው ፤ ሆኖም በርካታ አልሚዎች በገቡት የሊዝ ውል መሰረት ግንባታ ለመጀመር እና ለማጠናቀቅ ፈቃደኛ አልበሩም ብለዋል ።

በተያዘው በጀት ዓመት ብቻ መሬት በምደባ እንዲያገኙ ከተላለፉ የካብኔ ውሳኔዎች በተደጋጋሚ ጥሪ ቢቀርብም 100 አልሚዎች የሚጠበቅባቸውን የሊዝ ቅድመ ክፍያ ከፍለው ወደ ስራ ለመግባት ዝግጁ እንዳልሆኑ ለማሳያነት የጠቆሙት ኃላፊው አልሚዎች እርምጃ ከመወሰዱ በፊት መንግሥት ያመቻቸውን ተጨማሪ እድል በመጠቀም ወደ ልማት እንደሚገቡ አሳስበዋል ።

ለበለጠ መረጃ ትስስር ገፆቻችንን Like, Follow, subscribe በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ።
👇👇👇👇👇👇
Website: - https://www.aalb.gov.et
https://linktr.ee/addisabababacityland
Email :-addisabababacityland@gmail.com
2