Addis Ababa City land Development And Administration Bureau
5.41K subscribers
8.02K photos
76 videos
20 files
331 links
Download Telegram
"የኦሮሞ ሕዝብ ኢትዮጵያን ኢትዮጵያ አድርጎ በመፍጠርና በመገንባት ረገድ ግንባር ቀደም ሚና አለው"

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
የልደታ ክፍለ ከተማ መሬት ልማትና አስተዳደር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ለሶስት አቅመ ደካማ ወገኖች በአጭር ጊዜ ውስጥ ቤት ገንብቶ ለማስረከብ ወደ ስራ መግባቱን ገለፀ።

ነሀሴ 02/2018 (መልአ)

የልደታ ክፍለ ከተማ መሬት ልማትና አስተዳደር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሦስት የአቅመ ደካማ ወገኖችን ቤት በአዲስ መልክ ገንብቶ ለማስረከብ ኃላፊነት ወስዶ ወደ ስራ ገብቷል።

ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ በ90 ቀን ዕቅዱ ከመደበኛ ተግባራት በተጓዳኝ ሰው ተኮር ስራዎችን አካቶ እየተገበረ መሆኑን የገለፁት የቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ካሳሁን ጥላሁን
ከዚህም አንዱ የአቅመ ደካሞችን ቤት መገንባት ነው ብለዋል።

በዚህም ሜሪት ፕሮፐርቲስ ከተሰኝ ግብረ ሰናይ ድርጅት ጋር በመተባበር ሦስት የአቅመ ደካማ ወገኖችን ቤት በአጭር ጊዜ ውስጥ በአዲስ መልክ ገንብቶ ለማስረከብ ወደ ስራ መገባቱን ተናግረዋል።

ለበለጠ መረጃ ትስስር ገፆቻችንን Like, Follow, subscribe በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ።
👇👇👇👇👇👇
Website: - https://www.aalb.gov.et
https://linktr.ee/addisabababacityland
Email :-addisabababacityland@gmail.com
2
ትናንት አንዱን ከሌላው ጥቃት እንዲታደጋቸው መንግሥትን ሲወተውቱ የነበሩ ኃይሎች ዛሬ ጥምረት መፍጠራቸው እየተዳከሙ መምጣታቸውን ያሳያል - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ኔትወርክ (ኦቢኤን) ጋር ባደረጉት ቆይታ፣ በሀገራችን ብሎም በኦሮሚያ ክልል ለሚታየው የጸጥታ ችግር መሠረታዊ ምክንያቶችን በዝርዝር አብራርተዋል።

ለችግሮቹ ዋና ዋና ምክንያቶች ያሏቸውም የፖለቲካ ሽግግሩ ተፈጥሯዊ ፀባይ፣ የሥልጣን ማዕከል ሽግግር እና የትጥቅ ኃይሎች መዳከምን ተከትሎ የተፈጠረ ያልተጠበቀ ጥምረት መሆናቸውን አስረድተዋል፡፡

የሥልጣን ማዕከል ሽግግሩን እና የፖለቲካውን ተፈጥሯዊ ፀባይ በተመለከተ ሲያብራሩ ቀድሞ ኢትዮጵያን በብቸኝነት ሲመራ የነበረው ቡድን ሥርዓቱ ሁሉንም አሳታፊ ወደሆነ መንገድ መግባቱን ባለመቀበል ሥልጣን በጉልበት ለመመለስ እያደረገ ያለው ጥረት ለግጭቶች መንስኤ መሆኑን አስታውሰዋል፡፡

ኢትዮጵያ የብዙ እምነቶች፣ ቋንቋዎች እና ባህሎች ባለቤት በመሆኗ በአንድ ብሔር ወይም ቡድን የበላይነት ብቻ ልትመራ እንደማትችልም አጽንኦት ሰጥተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ አያይዘውም የትጥቅ ኃይሎች መዳከምን ተከትሎ ስለተፈጠረው ያልተጠበቀ ጥምረት ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በኦሮሚያ፣ በአማራ እና በትግራይ ክልሎች የሚንቀሳቀሱ ታጣቂ ኃይሎች መንግሥትን ማሸነፍ እንደማይችሉ ሲገነዘቡ ያልተቀደሰ ጋብቻ መፍጠራቸውን ጠቁመዋል፡፡

ትናንት አንዱን ከሌላው ጥቃት እንዲታደጓቸው መንግሥትን ሲወተውቱ የነበሩ ኃይሎች፣ ዛሬ ተጣምረው መሰለፋቸው ምን ያህል እንደተዳከሙ እና ተስፋ እንደቆረጡ የሚያሳይ መሆኑን አብራርተዋል፡፡

ከዚህም አልፎ እነዚህ ኃይሎች እንደ ኤርትራ እና ሱዳን ያሉ የውጭ አካላትን ለእርዳታ እየጋበዙ መሆኑን ሕዝቡ ሊገነዘበው እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

ይህንን የተዛባ ትርክት በማረም እንዲሁም አፍራሽ ከሆነ አስተሳሰብ በመውጣት፣ ሁሉንም የሚያስታርቅ እና የተሻለ ሀሳብ የሚያመጣ ውህድ መንገድ መከተል አማራጭ የሌለው ጉዳይ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስገንዝበዋል፡፡
የህወሓት ቡድን ኢትዮጵያን የማዳከም እና የመበተን ፍላጎት ላላቸው የውጭ ጠላቶች መሳሪያ በመሆን እያገለገለ ይገኛል - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ኔትወርክ ጋር ባደረጉት ቆይታ፣ የህወሓት ቡድን የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነትን ስለመጣሱ ተናግረዋል።

የህወሓት ቡድን ዳግም ለጦርነት እያደረገው ስላለው ዝግጅት በሰጡት አስተያየት፣ ቡድኑ አሁንም ከግማሽ ክፍለ ዘመን በፊት በነበረው አሮጌ የፖለቲካ አስተሳሰብ፣ እሳቤ እና አመራር ውስጥ ተቀርቅሮ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

ቡድኑ ለ27 ዓመታት ሀገርን አስተዳድሮ ከወረደ በኋላም ራሱን እንደ ነጻ አውጪ ግንባር በመቁጠር የትግራይን ሕዝብ ጥቅም ሳይሆን የራሱን ጠባብ የቡድን ፍላጎት ለማስፈጸም እየተንቀሳቀሰ መሆኑን አስረድተዋል።

ከዚህም ባለፈ በሌሎች የሀገራችን ክፍሎች የሚገኙ ታጣቂዎችን እንደ እኩል አጋር ሳይሆን እንደ መጠቀሚያ መሣሪያ በማድረግ ሀገርን የማፍረስ ዓላማ ይዞ እየሠራ እንደሚገኝ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል።

በአሁኑ ወቅት የትግራይ ክልል ሙሉ በሙሉ ራሱን በራሱ እያስተዳደረ እንደሚገኝ እና ፌደራል መንግሥትም ይሁን ሌላ አካል አንድም ሜትር መሬትም ሆነ ሀብት እንዳልወሰደበት ገልጸዋል።

ይህም የቡድኑ ወቅታዊ እንቅስቃሴ ምንም ዓይነት እውነተኛ የሕዝብ ጥያቄን መሠረት ያደረገ አለመሆኑን እንደሚያሳይ አስምረውበታል።

ቡድኑ በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያን የማዳከም እና የመበተን የረጅም ጊዜ ስትራቴጂያዊ ፍላጎት ላላቸው ታሪካዊ የውጭ ጠላቶች መሳሪያ በመሆን እያገለገለ ይገኛል ብለዋል።

ቡድኑ በ1980ዎቹ መጨረሻ ሌሎች ብሔር ብሔረሰቦችን አግልሎ ሥልጣን እንደያዘበት ዓይነት አካሄድ በአሁኑ ወቅት በፍጹም ሊሠራ እንደማይችልም ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስገንዝበዋል።

ሁሉም የኢትዮጵያ ሕዝቦች አሁን ያሉበት የፖለቲካ ንቃት እና ተሳትፎ ከትናንቱ በእጅጉ የተለየ መሆኑንም ተናግረዋል።
"የኦሮሞ ሕዝብ ትግል የእኩልነት እንጂ የበላይነት አይደለም"

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
በሺዎች የሚቆጠሩ ታጣቂዎች የሰላምን መንገድ መርጠው ወደ ኅብረተሰቡ እየተቀላቀሉ ነው - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ኔትወርክ (ኦቢኤን) ጋር ባደረጉት ቆይታ፣ በኦሮሚያ ክልል ውስጥ የሚንቀሳቀሱ ታጣቂ ኃይሎች የያዙት የትጥቅ ትግል በጫካ ውስጥ ተደብቆ ንፁሃንን ከመግደል እና ከመዝረፍ የዘለለ ምንም ዓይነት የፖለቲካ ግብ የሌለው መሆኑን ገልጸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ አክለውም ጦርነት እና ግጭት አውዳሚ መሆናቸውን በመገንዘብ በየዕለቱ በሺዎች የሚቆጠሩ ታጣቂዎች የሰላምን መንገድ መርጠው ወደ ኅብረተሰቡ እየተቀላቀሉ እንደሚገኙ ተናግረዋል።

መንግሥት ችግሮችን በሰላማዊ ውይይት ለመፍታት ያለው ቁርጠኝነት አሁንም ያልተለወጠ መሆኑን ያረጋገጡት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ማንኛውም አካል በሰላማዊ መንገድ ሀሳቡን ይዞ ለመታገል እስከፈለገ ድረስ የመንግሥት የሰላም በር መቼም ቢሆን እንደማይዘጋ አስገንዝበዋል።

የኦሮሞን ሕዝብ ትግል በዋናነት የጀመሩ እና ያደራጁ አንጋፋ ፖለቲከኞች በአሁኑ ወቅት ሀገር ቤት ገብተው በፓርላማ እና በተለያዩ የንግድ ሥራዎች ላይ በሰላም እየተሳተፉ መሆናቸውን አብራርተዋል።

በአንፃሩም፣ አሁን የትጥቅ ትግሉን ከሚመሩት አካላት ጀርባ ያለውን ተቃርኖ አንስተዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ አሁን ላይ በጫካ ውስጥ የሚገኙት ኃይሎች የማንን አጀንዳ እያስፈፀሙ እንደሆነ ሕዝቡና ወጣቱ ቆም ብሎ ሊጠይቅ እንደሚገባ አሳስበዋል።

ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት በጠመንጃ ኃይል ሊገነባ እንደማይችል ያመላከቱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ብልፅግና ፓርቲ በብቁ ሀሳብ እና በአሸናፊ ፖለቲካ ላይ የተመሠረተ እንጂ በዘር ላይ የተንጠለጠለ አደረጃጀት አለመሆኑን አብራርተዋል።

የትኛውም የፖለቲካ ቡድን ፍላጎቱን ማሳካት የሚችለው ሕዝብን አሳምኖ በምርጫ ሲያሸንፍ ብቻ መሆኑን በአፅንዖት ተናግረዋል።