Addis Ababa City land Development And Administration Bureau
5.41K subscribers
8.02K photos
76 videos
20 files
331 links
Download Telegram
ዛሬ በቤኒን ሪፐብሊክ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽንና ኢኖቬሽን እና ፈጠራ ሚኒስትር ማሁና አክፕሎጋን የተመራውን የልዑክ ቡድን ተቀብለን በከተማችን እየተገበርነው ያለውን Smart City (ስሉጥ ከተማ) ግንባታ ልምድ አካፍለናል።

ቤኒን የጀመረችውን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ለማሳካት በከተማችን ተግብረነው ውጤታማ እየሆነ ያለውን Smart City (ስሉጥ ከተማ) ግንባታ በተለይ በዋና ዋና ግቦች ( Smart Economy, Smart Environment, Smart Governance, Smart Living, Smart Mobility, Smart People) እና ለስኬቶቻችን መሰረት የሆኑት የተቋማት ቅንጅት፣ የህጎችና ደንቦች ትግበራ፣ የህዝብ ተሳትፎ፣ የመንግስትና የግል ዘርፍ ቅንጅታዊ ስራዎችን ለልዑክ ቡድኑ አካፍለናል።

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ!

ከንቲባ አዳነች አቤቤ
1
የኦሮሞ ሕዝብ በታሪኩ የተቃወመው የተበላሸ የአስተዳደር ሥርዓትን እንጂ ኢትዮጵያን አይደለም - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ኔትዎርክ ጋር በነበራቸው ቆይታ፤ የኦሮሞ ሕዝብ ነፃነት እና እኩልነት ታሪክ ከኢትዮጵያ ሀገር ግንባታ ጋር ያለውን ጥልቅ ቁርኝት በታሪካዊ ማሳያዎች እየጠቀሱ በስፋት አብራርተዋል።

የኦሮሞ ሕዝብ በታሪኩ የተቃወመው የተበላሸ የአስተዳደር ሥርዓትን እንጂ ሀገርን (ኢትዮጵያን) አይደለም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ሀገርን በመገንባት ሂደትም ደሙን፣ አጥንቱን እና ላቡን ማፍሰሱን ገልጸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስለ ኦሮሞ ሕዝብ የረጅም ዘመን ትግል መነሻ ምክንያቶች እንዲሁም ትግሉ ግቡን ለመምታት ስለዘገየበት እና ስላጋጠሙት ተግዳሮቶች ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በማብራሪያቸውም የኦሮሞ ሕዝብ የትግል ጥያቄዎች በዋናነት በሦስት መሠረታዊ ክፍሎች የሚከፈሉ መሆኑን እና እነዚህም የኢኮኖሚ፣ የማንነት እና የዴሞክራሲ ጥያቄ መሆናቸውን ተናግረዋል።

የኢኮኖሚ ጥያቄን በተመለከተ፦ ሕዝቡ የመሬት እና የሀብት ባለቤት የመሆን፣ በላቡ ሠርቶ የማደግ እና አካባቢውን የመቀየር ፍላጎት እንደነበረው ጠቁመዋል። መሬት ለኦሮሞ ሕይወቱ ቢሆንም፣ ይህ ሀብቱ ሲነጠቅ እና ሲበዘበዝ መቆየቱ እንዲሁም አራሹ አርሶ አምርቶ የመጠቀም መብት ማጣቱ ዋነኛ የትግል መነሻ ሆኗል ነው ያሉት።

የማንነት ጥያቄን በተመለከተ ደግሞ ይህ ጥያቄ አፋን ኦሮሞን ከመናገር ባለፈ ባህልን፣ ማንነትን፣ ሥነ-ምግባርን (ሰፉ)፣ ታላላቆችን፣ ፍጥረታትን እና ፈጣሪን ማክበርን በውስጡ ያካተተ ጥልቅ ጥያቄ እንደሆነ አስገንዝበዋል።

በኦሮሞነት ማንነት አድጎ ቋንቋን መናገር ብቻውን የማንነት ጥያቄን ሙሉ በሙሉ ይመልሳል ማለት አይቻልም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ስለዚህ የቋንቋ፣ የባህል እና የማንነት ጥያቄዎች አሁንም እንዳሉ ጠቁመዋል።

ከዴሞክራሲ ጥያቄ አንጻር ደግሞ የኦሮሞ ሕዝብ የራሱ የሆነ አሳታፊ የገዳ ሥርዓት የነበረው ሕዝብ በመሆኑ፣ ራሱን በራሱ የማስተዳደር፣ የራሱን ሕግ የማውጣት እና በሕጉ የመተዳደር የረጅም ጊዜ ዴሞክራሲያዊ ጥያቄ እንደነበረው ጠቁመዋል።

የመንግሥት አስተዳደር ደግሞ ሕዝቡ ከለመደው ዴሞክራሲያዊ አስተዳደር አንፃር ተቃራኒ ሲሆንም ጥያቄዎችን ሲያነሣ እንደነበር ነው የገለጹት።

ይህ የኦሮሞ ሕዝብ ትግል ከአንድ ክፍለ ዘመን በላይ ቢቆይም፣ በሚፈለገው ፍጥነት ድል ሳያመጣ የዘገየባቸውን ምክንያቶች ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአራት ዋና ዋና ነጥቦች አስቀምጠዋል።

አንደኛው የስትራቴጂያዊ ሐሳብ እጥረት ነው፦ ምርት ለማግኘት ትራክተር ቢኖርም 'ምርጥ ዘር' ከሌለ ዋጋ እንደሌለው ሁሉ፣ የትግል ግብን ለማሳካት የሚያስችል ጥራት ያለው ስትራቴጂያዊ ሐሳብ አለመኖር ትልቁ ክፍተት ነበር ሲሉ በምሳሌ አስረድተዋል።

ሁለተኛው የአንድነት እጥረት ነው፡- ኦሮሞ በሰፊ መሬት ላይ የሚኖር እና የጋራ ማንነት ያለው ቢሆንም፣ በፖለቲካ ሴራዎች፣ በእምነት፣ በወንዝ እና በዞን በመከፋፈል ጠንካራ ውስጣዊ አንድነትን ማስቀጠል አለመቻሉን ጠቅሰዋል።

ሦስተኛ የግንኙነት አያያዝ ችግር፦ ከሌሎች ኃይሎች ጋር የሚደረጉ ግንኙነቶች በጊዜያዊ ፍላጎት ላይ ብቻ የተመሠረቱ መሆናቸው እና የኦሮሞን ሕዝብ ፍላጎት ከማስከበር ይልቅ ለሌሎች ተገዢ ወይም አገልጋይ የሚያደርጉ በመሆናቸው በሂደቱ ላይ ትልቅ ጉዳት አምጥቷል ብለዋል።

አራተኛው የአመራር እጦት እና የአሸናፊነት ሥነ-ልቦና ማጣት ነው፦ ሕዝቡን አደራጅቶ እና አቅጣጫ አስይዞ ሊመራ የሚችል ትልቅ ዕይታ ያለው አመራር ማጣት እንቅፋት እንደነበር ነው አንሥተዋል።

ትግሉን ለማሸነፍ ልክ እንደ አንበሳ "የአሸናፊነት አስተሳሰብ" ይዞ መነሣት ሲገባው፣ ገና ከመጀመሪያው የመሸነፍ ስጋት ውስጥ መግባት የድል እንቅፋት ሆኖ መቆየቱን ነው የገለጹት።
"የኦሮሞ ሕዝብ ኢትዮጵያን ኢትዮጵያ አድርጎ በመፍጠርና በመገንባት ረገድ ግንባር ቀደም ሚና አለው"

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
የልደታ ክፍለ ከተማ መሬት ልማትና አስተዳደር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ለሶስት አቅመ ደካማ ወገኖች በአጭር ጊዜ ውስጥ ቤት ገንብቶ ለማስረከብ ወደ ስራ መግባቱን ገለፀ።

ነሀሴ 02/2018 (መልአ)

የልደታ ክፍለ ከተማ መሬት ልማትና አስተዳደር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሦስት የአቅመ ደካማ ወገኖችን ቤት በአዲስ መልክ ገንብቶ ለማስረከብ ኃላፊነት ወስዶ ወደ ስራ ገብቷል።

ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ በ90 ቀን ዕቅዱ ከመደበኛ ተግባራት በተጓዳኝ ሰው ተኮር ስራዎችን አካቶ እየተገበረ መሆኑን የገለፁት የቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ካሳሁን ጥላሁን
ከዚህም አንዱ የአቅመ ደካሞችን ቤት መገንባት ነው ብለዋል።

በዚህም ሜሪት ፕሮፐርቲስ ከተሰኝ ግብረ ሰናይ ድርጅት ጋር በመተባበር ሦስት የአቅመ ደካማ ወገኖችን ቤት በአጭር ጊዜ ውስጥ በአዲስ መልክ ገንብቶ ለማስረከብ ወደ ስራ መገባቱን ተናግረዋል።

ለበለጠ መረጃ ትስስር ገፆቻችንን Like, Follow, subscribe በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ።
👇👇👇👇👇👇
Website: - https://www.aalb.gov.et
https://linktr.ee/addisabababacityland
Email :-addisabababacityland@gmail.com
2
ትናንት አንዱን ከሌላው ጥቃት እንዲታደጋቸው መንግሥትን ሲወተውቱ የነበሩ ኃይሎች ዛሬ ጥምረት መፍጠራቸው እየተዳከሙ መምጣታቸውን ያሳያል - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ኔትወርክ (ኦቢኤን) ጋር ባደረጉት ቆይታ፣ በሀገራችን ብሎም በኦሮሚያ ክልል ለሚታየው የጸጥታ ችግር መሠረታዊ ምክንያቶችን በዝርዝር አብራርተዋል።

ለችግሮቹ ዋና ዋና ምክንያቶች ያሏቸውም የፖለቲካ ሽግግሩ ተፈጥሯዊ ፀባይ፣ የሥልጣን ማዕከል ሽግግር እና የትጥቅ ኃይሎች መዳከምን ተከትሎ የተፈጠረ ያልተጠበቀ ጥምረት መሆናቸውን አስረድተዋል፡፡

የሥልጣን ማዕከል ሽግግሩን እና የፖለቲካውን ተፈጥሯዊ ፀባይ በተመለከተ ሲያብራሩ ቀድሞ ኢትዮጵያን በብቸኝነት ሲመራ የነበረው ቡድን ሥርዓቱ ሁሉንም አሳታፊ ወደሆነ መንገድ መግባቱን ባለመቀበል ሥልጣን በጉልበት ለመመለስ እያደረገ ያለው ጥረት ለግጭቶች መንስኤ መሆኑን አስታውሰዋል፡፡

ኢትዮጵያ የብዙ እምነቶች፣ ቋንቋዎች እና ባህሎች ባለቤት በመሆኗ በአንድ ብሔር ወይም ቡድን የበላይነት ብቻ ልትመራ እንደማትችልም አጽንኦት ሰጥተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ አያይዘውም የትጥቅ ኃይሎች መዳከምን ተከትሎ ስለተፈጠረው ያልተጠበቀ ጥምረት ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በኦሮሚያ፣ በአማራ እና በትግራይ ክልሎች የሚንቀሳቀሱ ታጣቂ ኃይሎች መንግሥትን ማሸነፍ እንደማይችሉ ሲገነዘቡ ያልተቀደሰ ጋብቻ መፍጠራቸውን ጠቁመዋል፡፡

ትናንት አንዱን ከሌላው ጥቃት እንዲታደጓቸው መንግሥትን ሲወተውቱ የነበሩ ኃይሎች፣ ዛሬ ተጣምረው መሰለፋቸው ምን ያህል እንደተዳከሙ እና ተስፋ እንደቆረጡ የሚያሳይ መሆኑን አብራርተዋል፡፡

ከዚህም አልፎ እነዚህ ኃይሎች እንደ ኤርትራ እና ሱዳን ያሉ የውጭ አካላትን ለእርዳታ እየጋበዙ መሆኑን ሕዝቡ ሊገነዘበው እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

ይህንን የተዛባ ትርክት በማረም እንዲሁም አፍራሽ ከሆነ አስተሳሰብ በመውጣት፣ ሁሉንም የሚያስታርቅ እና የተሻለ ሀሳብ የሚያመጣ ውህድ መንገድ መከተል አማራጭ የሌለው ጉዳይ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስገንዝበዋል፡፡
የህወሓት ቡድን ኢትዮጵያን የማዳከም እና የመበተን ፍላጎት ላላቸው የውጭ ጠላቶች መሳሪያ በመሆን እያገለገለ ይገኛል - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ኔትወርክ ጋር ባደረጉት ቆይታ፣ የህወሓት ቡድን የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነትን ስለመጣሱ ተናግረዋል።

የህወሓት ቡድን ዳግም ለጦርነት እያደረገው ስላለው ዝግጅት በሰጡት አስተያየት፣ ቡድኑ አሁንም ከግማሽ ክፍለ ዘመን በፊት በነበረው አሮጌ የፖለቲካ አስተሳሰብ፣ እሳቤ እና አመራር ውስጥ ተቀርቅሮ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

ቡድኑ ለ27 ዓመታት ሀገርን አስተዳድሮ ከወረደ በኋላም ራሱን እንደ ነጻ አውጪ ግንባር በመቁጠር የትግራይን ሕዝብ ጥቅም ሳይሆን የራሱን ጠባብ የቡድን ፍላጎት ለማስፈጸም እየተንቀሳቀሰ መሆኑን አስረድተዋል።

ከዚህም ባለፈ በሌሎች የሀገራችን ክፍሎች የሚገኙ ታጣቂዎችን እንደ እኩል አጋር ሳይሆን እንደ መጠቀሚያ መሣሪያ በማድረግ ሀገርን የማፍረስ ዓላማ ይዞ እየሠራ እንደሚገኝ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል።

በአሁኑ ወቅት የትግራይ ክልል ሙሉ በሙሉ ራሱን በራሱ እያስተዳደረ እንደሚገኝ እና ፌደራል መንግሥትም ይሁን ሌላ አካል አንድም ሜትር መሬትም ሆነ ሀብት እንዳልወሰደበት ገልጸዋል።

ይህም የቡድኑ ወቅታዊ እንቅስቃሴ ምንም ዓይነት እውነተኛ የሕዝብ ጥያቄን መሠረት ያደረገ አለመሆኑን እንደሚያሳይ አስምረውበታል።

ቡድኑ በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያን የማዳከም እና የመበተን የረጅም ጊዜ ስትራቴጂያዊ ፍላጎት ላላቸው ታሪካዊ የውጭ ጠላቶች መሳሪያ በመሆን እያገለገለ ይገኛል ብለዋል።

ቡድኑ በ1980ዎቹ መጨረሻ ሌሎች ብሔር ብሔረሰቦችን አግልሎ ሥልጣን እንደያዘበት ዓይነት አካሄድ በአሁኑ ወቅት በፍጹም ሊሠራ እንደማይችልም ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስገንዝበዋል።

ሁሉም የኢትዮጵያ ሕዝቦች አሁን ያሉበት የፖለቲካ ንቃት እና ተሳትፎ ከትናንቱ በእጅጉ የተለየ መሆኑንም ተናግረዋል።
"የኦሮሞ ሕዝብ ትግል የእኩልነት እንጂ የበላይነት አይደለም"

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)