Addis Ababa City land Development And Administration Bureau
5.42K subscribers
8.08K photos
77 videos
20 files
331 links
Download Telegram
ዛሬ የባህር ዳር ደጃዝማች በላይ ዘለቀ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ አዲሱን ተርሚናል መርቀናል። ለኢትዮጵያ ቁልፍ የበረራ በሮች አንዱ ለሆነው ለዚህ አውሮፕላን ማረፊያ ትልቅ ምዕራፍ ነው። ይህ ፕሮጀክት ከዘመናዊ ተርሚናል በላይ ትርጉም አለው። ባህር ዳር በቅርብ ጊዜያት ካስተናገደቻቸው ፈተናዎች ማግስት፤ የዚህ ተርሚናል ግንባታ ተጠናቆ አገልግልት መጀመር የፅናት፣ የማገገም እና ቀጣይነት ያለው ኢንቨስትመንት ማረጋገጫ ነው።

‎አዲሱ ተርሚናል ሰፊ የአውሮፕላን ማቆሚያዎችን፣ የላቁ መሰረተ ልማቶችን፣ የተስተካከሉ መዳረሻ መንገዶችን እና ዘመናዊ መገልገያዎችን ያካተተ ነው። ይህም የአውሮፕላን ማረፊያውን የመቀበል አቅም በማሳደግ የአካባቢውን እያደገ የመጣ ፍላጎት የሚያሟላ ሲሆን፣ ለመንገደኞችም ምቹና ቀልጣፋ አገልግሎት ይሰጣል። ይህ አዲስ ተርሚናል ከተማዋን እያደሰ ካለው የከተማ ትራንስፎርሜሽን ጋር ተዳምሮ፤ ባህር ዳርን ለዓለም አቀፍ እና ለሀገር ውስጥ በረራዎች ሌላኛዋ ቁልፍ መዳረሻና ማዕከል ያደርጋታል። ባህር ዳርን የመሰለች ንቁ ከተማ የምታስገኘውን ኢኮኖሚያዊ ጥቅም ለማረጋገጥ የአካባቢው ማህበረሰብ ሰላሙን መጠበቁን እንደሚቀጥል ተስፋ አደርጋለሁ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
3
ዛሬ በቤኒን ሪፐብሊክ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽንና ኢኖቬሽን እና ፈጠራ ሚኒስትር ማሁና አክፕሎጋን የተመራውን የልዑክ ቡድን ተቀብለን በከተማችን እየተገበርነው ያለውን Smart City (ስሉጥ ከተማ) ግንባታ ልምድ አካፍለናል።

ቤኒን የጀመረችውን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ለማሳካት በከተማችን ተግብረነው ውጤታማ እየሆነ ያለውን Smart City (ስሉጥ ከተማ) ግንባታ በተለይ በዋና ዋና ግቦች ( Smart Economy, Smart Environment, Smart Governance, Smart Living, Smart Mobility, Smart People) እና ለስኬቶቻችን መሰረት የሆኑት የተቋማት ቅንጅት፣ የህጎችና ደንቦች ትግበራ፣ የህዝብ ተሳትፎ፣ የመንግስትና የግል ዘርፍ ቅንጅታዊ ስራዎችን ለልዑክ ቡድኑ አካፍለናል።

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ!

ከንቲባ አዳነች አቤቤ
1