የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት፡-
ከኔዘርላንድስ ጠቅላይ ሚኒስትር ሮብ ጄተን ጋር ውጤታማ የሥልክ ውይይት አድርገናል።
በውይይታችን የሁለትዮሽ ጉዳዮች ዙሪያ የመከርን ሲሆን፣ በተለያዩ ዘርፎች ያለንን ትብብር ይበልጥ ማጠናከር በሚያስችሉ መንገዶች ላይ ሃሳብ ተለዋውጠዋል።

አፍሪካውያን የማህበራዊ ሚዲያ ይዘት ፈጣሪዎች በአዲስ አበባ
አፍሪካውያን የማህበራዊ ሚዲያ ይዘት ፈጣሪዎች የአህጉሪቷን ትክክለኛ ገጽታ ለዓለም በማስተዋወቅ ረገድ እንደ አምባሳደር እያገለገሉ ይገኛሉ።
የአፍሪካ የማህበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች ጉባኤ በፐልስ ኦፍ አፍሪካ (Pulse of Africa-POA) ከኤ.ጂ.ኤ የቴክኖሎጂ ኢንተርፕራይዝ (AGA-Tech) ትብብር በአዲስ አበባ ዓድዋ ድል መታሰቢያ ነገ እና ከነገ በስቲያ ይካሄዳል።
"ተፅዕኖ ፈጣሪዎች ለተሻለች አፍሪካ" በሚል መሪ ሃሳብ በሚካሄደው ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ የአህጉሪቱ የማህበራዊ ሚዲያ ይዘት ፈጣሪዎች አዲስ አበባ ገብተዋል።
የአህጉሪቷ ማህበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች፣ ፖሊሲ አውጪዎች፣ ዳያስፖራዎችና የግሉ ዘርፍ ተዋናዮች የረጅም ጊዜ ትብብር የሚፈጥሩበት ይህ መድረክ የኢትዮጵያን ብሎም የአፍሪካን ትክክለኛ ትርክት ለዓለም ለማስተዋወቅ ወሳኝ ነው።
ታዋቂው የአፍሪካዊ ዲጂታል ታሪክ ተራኪ ጋናዊው በርትሆልድ ኮቢ ዊንክለር አክኮን (ዎዴ ማያ) ጨምሮ የአህጉሪቷ ማህበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች አዲስ አበባ መግባት ጀምረዋል።
ጋናዊው በርትሆልድ ኮቢ ዊንክለር አክኮን (ዎዴ ማያ) እንዳለው፤ የአፍሪካን የይዘት ፈጠራ ባለሙያዎች በአንድ መድረክ በተለይም በአዲስ አበባ ማግኘት እጅግ የሚያስደስት ነው፡፡
የይዘት ፈጣሪዎቹ በአንድ አዳራሽ ተገኝተው የአፍሪካን አጀንዳ ለቀሪው ዓለም ለማድረስ የሚያደርጉት ምክክር ትልቅ ፋይዳ እንዳለው መግለጹን ፐልስ ኦፍ አፍሪካ ዘግቧል።

የአፍሪካ ማህበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች ጉብኝት በአዲስ አበባ
የመጀመሪያው የአፍሪካ ማህበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች ጉባኤ ተሳታፊዎች በአዲስ አበባ ከተማ የሚያደርጉትን ጉብኝት ጀምረዋል።
የአፍሪካን እውነተኛ ገጽታ ለዓለም ለማስተዋወቅና የዲጂታል ትርክቱን በባለቤትነት ለመምራት ያለመው የመጀመሪያው የአፍሪካ ማህበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች ጉባኤ (ASMIS 2026) በአዲስ አበባ ዓድዋ ድል መታሰቢያ ዛሬ እና ነገ ይካሄዳል።
በጉባኤው ለመታደም ከ30 የአፍሪካ ሀገራት የተውጣጡ 321 ሚሊዮን በላይ የማህበራዊ ሚዲያ ተከታዮች ያሏቸው 61 ተጽዕኖ ፈጣሪዎች በአዲስ አበባ ከትመዋል።
በተጨማሪም 150 ሚሊዮን ተከታዮች ያላቸው 120 ኢትዮጵያውያን የይዘት ፈጣሪዎች በጋራ በመሰባሰብ፣ የዓለም የዲፕሎማሲ ማዕከል በሆነችው አዲስ አበባ አዲስ የዲጂታል ታሪክ ለመጻፍ ተዘጋጅተዋል።
እንደ ኢዜአ ዘገባ የአፍሪካ ማህበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች የጉባኤው አካል የሆነውን ጉብኝት የጀመሩ ሲሆን፤ አዲስ አበባ የአፍሪካ መዲናነቷን የሚያጎሉ ድምቀቶቿን ታስጎበኛለች።