የአፍሪካ ማህበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች ጉብኝት በአዲስ አበባ
የመጀመሪያው የአፍሪካ ማህበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች ጉባኤ ተሳታፊዎች በአዲስ አበባ ከተማ የሚያደርጉትን ጉብኝት ጀምረዋል።
የአፍሪካን እውነተኛ ገጽታ ለዓለም ለማስተዋወቅና የዲጂታል ትርክቱን በባለቤትነት ለመምራት ያለመው የመጀመሪያው የአፍሪካ ማህበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች ጉባኤ (ASMIS 2026) በአዲስ አበባ ዓድዋ ድል መታሰቢያ ዛሬ እና ነገ ይካሄዳል።
በጉባኤው ለመታደም ከ30 የአፍሪካ ሀገራት የተውጣጡ 321 ሚሊዮን በላይ የማህበራዊ ሚዲያ ተከታዮች ያሏቸው 61 ተጽዕኖ ፈጣሪዎች በአዲስ አበባ ከትመዋል።
በተጨማሪም 150 ሚሊዮን ተከታዮች ያላቸው 120 ኢትዮጵያውያን የይዘት ፈጣሪዎች በጋራ በመሰባሰብ፣ የዓለም የዲፕሎማሲ ማዕከል በሆነችው አዲስ አበባ አዲስ የዲጂታል ታሪክ ለመጻፍ ተዘጋጅተዋል።
እንደ ኢዜአ ዘገባ የአፍሪካ ማህበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች የጉባኤው አካል የሆነውን ጉብኝት የጀመሩ ሲሆን፤ አዲስ አበባ የአፍሪካ መዲናነቷን የሚያጎሉ ድምቀቶቿን ታስጎበኛለች።

አሁን በመካሄድ ላይ!
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በተገኙበት "የሚዲያ እመርታ ለትርክት ግንባታ" በሚል መሪ ቃል ሀገራዊ የምክክር መድረክ መካሄድ ጀምሯል።
ኢትዮጵያ ካስመዘገበቻቸው የለውጥ ድሎች አንዱ ተቋማት ጠንካራና ትክክለኛ የዴሞክራሲ ስርዓት መገለጫ እንዲሆኑ ማድረግ ሲሆን፣ ከነዚህም መካከል የመገናኛ ብዙሃን ግንባር ቀደም ተጠቃሽ ናቸው።
#PMOEthiopia

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ዋና ስራ አስኪያጅ ሰይፈ ደርቤ ''የሚዲያ እመርታ ለትርክት ግንባታ'' በተሰኘው ሀገራዊ የምክክር መድረክ ላይ እንዳቀረቡት የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ከምስረታው ባልተናነሰ የለውጡ መንግሥት በዘረፉና በተቋሙ ባደረገው ሪፎርም ምክንያት ዳግም ተወልዷል ማለት እንደሚቻል ገልጸዋል።
የተከናወነው የእሳቤ፣ የህግና አደረጃጀት እንዲሁም የአሰራር ሪፎርም፤ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎትን በአፍሪካ አስተማማኝና ተጽዕኖ ፈጣሪ የዜና ምንጭ በመሆን ብሄራዊ ጥቅምን ማስጠበቅና ብሄራዊ መግባባት መፍጠር የሚያስችል አቅም እንዲላበስ አስችሎታል። ተቋሙ ተደራሽነቱን በማስፋት፣ በቴክኖሎጂ ተደራጅቶ፣ ከኢትዮጵያ ተሻግሮ የአፍሪካ ድምጽ በመሆን የወል ትርክትን እየገነባ ይገኛል።