የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን Addis Ababa City Administration Environmental protection Authority(official)
804 subscribers
13.3K photos
135 videos
17 files
194 links
Addis Ababa City Administration Environmental protection Authority የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አካባቢ ጥበቃ በለስልጣን
Download Telegram
አዲስ አበባ ለሕፃናት ተመራጭ መዲና ለመሆን የጀመረችው ጉዞ ስኬት እያሳየ መምጣቱ ተገለፀ።
********************************
አዲስ አበባን ለሕፃናት እድገትና አስተዳደግ ምቹና ተመራጭ የአፍሪካ ከተማ ለማድረግ የተወጠነው “የቀዳማይ ልጅነት ዕድገት ፕሮግራም” አስገራሚ ውጤቶችን እያስመዘገበ መሆኑ ተገለጸ።

ከተማዋ የነገ አገር ተረካቢ ትውልድን ለመቅረጽ የጀመረችው ይህ ታላቅ ፕሮጀክት፣ ባለፉት አምስት ዓመታት በተለይም ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን የህብረተሰብ ክፍሎችን ማዕከል በማድረግ 1.3 ሚሊዮን ሕፃናትን እና 330 ሺህ አነስተኛ ገቢ ያላቸውን ወላጆችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ አምስት ዋና ዋና የንቅናቄ ዘርፎችን (Initiatives) ተግባራዊ እያደረገች ትገኛለች።

በፕሮግራሙ መጀመሪያ ላይ በከተማዋ የነበሩት የሕፃናት መጫወቻ ስፍራዎች 11 ብቻ የነበሩ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት ሰፊ የንቅናቄ ስራ ተሰርቶ ቁጥራቸው ወደ 4,429 ከፍ እንዲል ተደርጓል ተብሏል። ይህም ሕፃናት በየሰፈራቸው በቂ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ የሚያደርጉባቸውና የሚጫወቱባቸው ስፍራዎች እንዲኖሩ በማድረግ ረገድ ትልቅ ለውጥ ያመጣ መሆኑ ተመልክቷል።

ፕሮግራሙን በሳይንሳዊ ጥናትና ምርምር ላይ የተመሰረተ እንዲሆን ከማድረግ በተጨማሪ ዓለም አቀፍ ምርጥ ተሞክሮዎችን በመቀመር የሕፃናትን የአእምሮና የአካል ዕድገት በሚያፋጥን መልኩ ደረጃቸውን የጠበቁ ማዕከላት እንዲስፋፉ እየተደረገ ነዉ።

ይህ ስራ የከተማዋን ገጽታ ከመቀየር ባለፈ፣ የነገ አገር ተረካቢ ዜጎችን በአእምሮና በአካል ብቁ አድርጎ ለማሳደግ የሚደረግ ትልቅ የትውልድ ግንባታ ኢንቨስትመንት መሆኑን የከተማዋ አስተዳደሩ በተደጋጋሚ ሲገልፅ ይስተዋላል፡፡

በአጠቃላይ አዲስ አበባ ለሕፃናት ያላትን ቁርጠኝነት በተግባር እያሳየች ሲሆን፣ ፕሮግራሙ በተያዘለት ፍጥነት ከተቀጠለ መዲናዋ በቅርቡ በአፍሪካ ለሕፃናት ምቹ የሆኑ ከተሞች ተርታ ቀዳሚዋ እንደምትሆን የሚደረጉ ጥረቶች ያሳያሉ።
"ጥበብ ሀገርን ትሰራለች፤ሀገርም ጠቢብን ታስታውሳለች"
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት፡-

ከኔዘርላንድስ ጠቅላይ ሚኒስትር ሮብ ጄተን ጋር ውጤታማ የሥልክ ውይይት አድርገናል።
‎
በውይይታችን የሁለትዮሽ ጉዳዮች ዙሪያ የመከርን ሲሆን፣ በተለያዩ ዘርፎች ያለንን ትብብር ይበልጥ ማጠናከር በሚያስችሉ መንገዶች ላይ ሃሳብ ተለዋውጠዋል።