የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን Addis Ababa City Administration Environmental protection Authority(official)
804 subscribers
13.3K photos
135 videos
17 files
194 links
Addis Ababa City Administration Environmental protection Authority የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አካባቢ ጥበቃ በለስልጣን
Download Telegram
ሀገር ለጠቢባን የሕያው ሥራዎቻቸው ምስክር ሐውልት ታቆማለች!

ዛሬ በአርበኞች ቀን በተለያዩ መስኮች የጀግንነት ሚና የተወጡ አርበኞቻችንን በማስታወስ እየዘከርናቸው ነው።

ሀገር በልማት ስራዎች፣ ድንበርን በመከላከል፣ በሰንደቅ ዓላማ እና በሕግ ብቻ አትገነባም። ሀገር የምትገነባው በሕዝብ የጋራ ትውስታ፣ በጋራ ስሜት እና በታላላቅ የጥበብ ውጤቶችም ጭምር ነው። ይህ እውነት ዛሬ በቆሙት የሀገር ባለውለታ ታላላቅ ጠቢባን ሐውልቶች በአዲስ አበባ ከተማችን እውን አድርገናል።

ከተማ አስተዳደራችን በኮሪደር ልማት እና በታላላቅ ፕሮጀክቶች ውስጥ፣ ጥበብን ማዕከል አድርጓል።

ዛሬ ሃውልት የቆመላቸው ለሃገራቸው ሰላም፣ ለኢትዮጵያዊነት ግንባታ፣ ለህብረ-ብሔራዊ አንድነት፣ ለወንድማማችነትና እህትማማችነት፣ ለፍትሃዊነት፣ ለነፃነትና እኩልነት ላቀነቀኑት አንጋፋዎቹ የሀገር ባለውለታዎች ሎሬት ጸጋዬ ጸጋዬ ጋብረ መድኅን፣ የክብር ዶ/ር ጥላሁን ገሠሠ፣ ማሕሙድ አሕመድ፣ ዓሊ ቢራ፣ ስብሐት ገብረ እግዚአብሔር እና ሐጫሉ ሑንዴሣ ናቸው። ከእነዚህ በተጨማሪም ልናከብራቸው የሚገባን የሀገር ባለውለታዎች የሆኑ የጥበብ ሰዎች መኖራቸው ስለሚታወቅ ይህ ስራ የመጀመሪያ እንጂ የመጨረሻ አይደለም።

ጥበብ ሀገርን ትስራለች፤ ሀገርም ጠቢብን ታስታውሳለች።


ፍጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
👍1