የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን Addis Ababa City Administration Environmental protection Authority(official)
805 subscribers
13.3K photos
135 videos
17 files
194 links
Addis Ababa City Administration Environmental protection Authority የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አካባቢ ጥበቃ በለስልጣን
Download Telegram
አራዳ ፓርክ የጉብኝት መርሃ ግብር በደመቀ ሁኔታ እየተካሄደ ይገኛል::

የአዲስ አበባከተማ አስተዳደር ለነዋሪዎች የመዝናኛ አማራጮችን ለማስፋትና የከተማዋን ውበት ለመጨመር የተገነባው የአራዳ ፓርክ ከትላንት ከሚያዝያ 23 ቀን ጀምሮ ለጎብኝዎች ክፍት ተደርጓል።

ከንቲባ አዳነች አቤቤ ትናንት ፓርኩን ለጎብኚዎች በነፃ ክፍት ማድረጋቸውን ተከትሎ በርካታ ነዋሪዎች ወደ ፓርኩ በመሄድ እየጎበኙ ይገኛሉ።

የጉብኝቱ ተሳታፊዎች በሰጡት አስተያየት በፓርኩ የተሠሩት ስራዎች የከተማችንን እድገትና ለውጥ መንገድ የሚያሳይ እንዲሁም ለኛ ነዋሪዎች የማረፊያ ስፍራ ተደርጎ የተሰራ መሆኑን ገልፀዋል።

በተለይም ለአዲስ አበባ ነዋሪዎች ምቹ፣ ፅዱና ማራኪ የመዝናኛ ቦታዎችን በመፍጠር ረገድ የተከናወነው ተግባር የሚደነቅ መሆኑን ተናግረዋል።

አክለዉም ሁሉም የከተማዋ ነዋሪዎቹ የተሠሩ ስራዎችን በአካል ተገኝተዉ መጎብኘትና የሚሠሩ የልማት ስራዎችን በሀሳብ፣በገንዘብ እና በጉልበት መደገፍ እንዳለባቸዉና አካባቢዉን መንከባከብና መጠበቅ እንደሚገባም ገልፀዋል።

የአራዳ ፖርክ ከሚያዚያ 23 ቀን 2018 ዓ ም ጀምሮ ለቀጣይ ወራቶች ለጎብኚዎች ክፍት ሆኖ ይቆያል።