የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን Addis Ababa City Administration Environmental protection Authority(official)
806 subscribers
13.3K photos
135 videos
17 files
194 links
Addis Ababa City Administration Environmental protection Authority የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አካባቢ ጥበቃ በለስልጣን
Download Telegram
የአራዳ ፓርክን ይጎብኙ!

ከንቲባ አዳነች አቤቤ መላው የአዲስ አበባ ነዋሪ አራዳ ፓርክን ለሚቀጥሉት ጥቂት ወራት በነፃ እንዲጎበኝ መግለፃቸው ይታወሳል። በዚህ መሰረት በፓርኩ ለመዝናናትና አገልግሎት ፈልገው የሚመጡ እንግዶች ሊያውቋቸው የሚገቡ እውነቶች እንደሚከተለው ቀርቧል።

👉ፓርኩ አገልግሎት የሚሰጠው ከጧቱ 12:00 - 5:30 እና ከሰዓት 8:00 - ምሽት 4:00 ሰዓት ይሆናል።

👉ወደ ፓርኩ ለመግባትና ከፓርኩ ለመውጣት መጠቀም ያለብን አራት በሮች 1ኛ. በሲኒማ አምፒር በኩል 2ኛ. በጣይቱ መውጫ በኩል 3ኛ. በቀይ ባህር በኩል እና 4ኛ. በራስ መኮንን ድልድይ በኩል ይሆናል፣
👉ተሽከርካሪ ይዘው ለሚመጡ ጎብኚዎችና አገልግሎት ተጠቃሚዎች መኪና ማቆም የሚቻለው በአራዳ ፓርክ እና ችሎት የመኪና ማቆሚያዎችን (ፓርኪንግ) የሚጠቀሙበት ተዘጋጅቶላቿል ::

👉በፓርኩ ውስጥ የለሙ ሳሮችን ስንጠቀም የጋራ ሃብታችን ስለሆነ እየጠበቅን በሃላፊነት እንድንጠብቅም ጥሪ እናቀርባለን።
አራዳ ፓርክ የጉብኝት መርሃ ግብር በደመቀ ሁኔታ እየተካሄደ ይገኛል::

የአዲስ አበባከተማ አስተዳደር ለነዋሪዎች የመዝናኛ አማራጮችን ለማስፋትና የከተማዋን ውበት ለመጨመር የተገነባው የአራዳ ፓርክ ከትላንት ከሚያዝያ 23 ቀን ጀምሮ ለጎብኝዎች ክፍት ተደርጓል።

ከንቲባ አዳነች አቤቤ ትናንት ፓርኩን ለጎብኚዎች በነፃ ክፍት ማድረጋቸውን ተከትሎ በርካታ ነዋሪዎች ወደ ፓርኩ በመሄድ እየጎበኙ ይገኛሉ።

የጉብኝቱ ተሳታፊዎች በሰጡት አስተያየት በፓርኩ የተሠሩት ስራዎች የከተማችንን እድገትና ለውጥ መንገድ የሚያሳይ እንዲሁም ለኛ ነዋሪዎች የማረፊያ ስፍራ ተደርጎ የተሰራ መሆኑን ገልፀዋል።

በተለይም ለአዲስ አበባ ነዋሪዎች ምቹ፣ ፅዱና ማራኪ የመዝናኛ ቦታዎችን በመፍጠር ረገድ የተከናወነው ተግባር የሚደነቅ መሆኑን ተናግረዋል።

አክለዉም ሁሉም የከተማዋ ነዋሪዎቹ የተሠሩ ስራዎችን በአካል ተገኝተዉ መጎብኘትና የሚሠሩ የልማት ስራዎችን በሀሳብ፣በገንዘብ እና በጉልበት መደገፍ እንዳለባቸዉና አካባቢዉን መንከባከብና መጠበቅ እንደሚገባም ገልፀዋል።

የአራዳ ፖርክ ከሚያዚያ 23 ቀን 2018 ዓ ም ጀምሮ ለቀጣይ ወራቶች ለጎብኚዎች ክፍት ሆኖ ይቆያል።