"የእርጅና ገፅታን ገፍፎ፥ የውበት ፀዳል ያለበሰ ለውጥ!"
ዛሬ በመስቀል አደባባይ “የእርጅና ገፅታን የገፈፈ፣ የውበት ፀዳል ያላበሰ ለውጥ!” በሚል ርዕስ የአምስት ዓመት የልማት እና ሰው ተኮር ስራዎችን ለማሳየት የተዘጋጀ የፎቶግራፍ ኤግዚቢሽን ከፍተናል።
እንደሚታወቀው አዲስ አበባ ላለፉት አምስት ዓመታት ስሟን የምትመጥን መዲና እንድትሆን ከማድረግ አንፃር ከፍተኛ ስራ መሠራቱና ብዙሃኑን ተጠቃሚ ማድረግ ያስቻሉ አንፀባራቂ ውጤቶች መመዝገባቸው፣ ከአገራችን አልፎ በተለያዩ ዓለም አቀፍ መድረኮች እውቅና የተሰጠበት አኩሪ ተግባር መሆኑ የሚታወቅ ነው።
ፎቶዎቹ የመፈፀም ብቃታችንን የሚያረጋግጡ፤ በታማኝነት ማገልገልን፣ የልማት አርበኝነትንና ተነሳሽነትን የሚመሰክሩ ከመሆንም ባለፈ የእድገት ራዕይ፤ የአላማ-ፅናት፤ የማያቋርጥ ትጋት የተተገበረበት በህዝብና መንግስት ጠንካራ ጥምረት እውን የሆነ የጋራ አሻራ ነው።
በዚህ አውደ-ርዕይ እየተዘዋወራችሁ ፎቶዎችን ስትመለከቱ ለህዝባችን የገባነውን ቃል ጠብቀን ማከናወን የቻልነውን ብቻ ሳይሆን፣ ቀሪ ስራዎችን በቀጣይ ለመስራት የሚያስችለን ምቹ ሁኔታ መፈጠሩንም በማስተዋል የበለጠ ውጤት ለማስመዝገብ በመዘጋጀት ይሁን።
በመጨረሻም ይህንን አውደ-ርዕይ ያዘጋጃችሁ አካላትን በሙሉ ከልብ እያመሠገንኩ ከዛሬ ጀምሮ ለ5 ቀናት ክፍት በመሆኑ እንድትጎበኙት ልጋብዛችሁ እወዳለሁ።
አመሠግናለሁ !!
ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ!!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ ልሳን የቅዳሜ ሚያዚያ 24 ቀን 2018
የአራዳ ፓርክን ይጎብኙ!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ መላው የአዲስ አበባ ነዋሪ አራዳ ፓርክን ለሚቀጥሉት ጥቂት ወራት በነፃ እንዲጎበኝ መግለፃቸው ይታወሳል። በዚህ መሰረት በፓርኩ ለመዝናናትና አገልግሎት ፈልገው የሚመጡ እንግዶች ሊያውቋቸው የሚገቡ እውነቶች እንደሚከተለው ቀርቧል።
👉ፓርኩ አገልግሎት የሚሰጠው ከጧቱ 12:00 - 5:30 እና ከሰዓት 8:00 - ምሽት 4:00 ሰዓት ይሆናል።
👉ወደ ፓርኩ ለመግባትና ከፓርኩ ለመውጣት መጠቀም ያለብን አራት በሮች 1ኛ. በሲኒማ አምፒር በኩል 2ኛ. በጣይቱ መውጫ በኩል 3ኛ. በቀይ ባህር በኩል እና 4ኛ. በራስ መኮንን ድልድይ በኩል ይሆናል፣
👉ተሽከርካሪ ይዘው ለሚመጡ ጎብኚዎችና አገልግሎት ተጠቃሚዎች መኪና ማቆም የሚቻለው በአራዳ ፓርክ እና ችሎት የመኪና ማቆሚያዎችን (ፓርኪንግ) የሚጠቀሙበት ተዘጋጅቶላቿል ::
👉በፓርኩ ውስጥ የለሙ ሳሮችን ስንጠቀም የጋራ ሃብታችን ስለሆነ እየጠበቅን በሃላፊነት እንድንጠብቅም ጥሪ እናቀርባለን።