የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን Addis Ababa City Administration Environmental protection Authority(official)
806 subscribers
13.3K photos
135 videos
17 files
194 links
Addis Ababa City Administration Environmental protection Authority የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አካባቢ ጥበቃ በለስልጣን
Download Telegram
መዲናችን አዲስ አበባ ለዓለም እና አኅጉር አቀፍ ኩነቶች ተመራጭ ከተማ።

የአለም አቀፍ እጅ ኳስ ፌዴሬሽን ትሮፊ 2026 የዞን 5 የምስራቅ አፍሪካ ውድድር በአዲስ አበባ ይካሄዳል

ኢትዮጵያን ጨምሮ 10 ሀገራት የሚሳተፉበት "የአለም አቀፍ እጅ ኳስ ፌዴሬሽን ትሮፊ 2026 የዞን 5 የምስራቅ አፍሪካ ውድድ ሚያዝያ 26 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ እንደሚካሄዳል።

በዚህ ውድድር ላይ ኢትዮጵያን ጨምሮ 10 ሀገራት በሁለት እድሜ ክልል ከ17 እና ከ19 ዓመት በታች ይሳተፋሉ፡፡

በውድድሩ ኢትዮጵያ፣ ኬንያ፣ ኡጋንዳ፣ ሩዋንዳ፣ ቡሩንዲ፣ ታንዛኒያ፣ ጅቡቲ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ሶማሊያ እና ሱዳን የሚሳተፉ ሲሆን በሁለቱም እድሜ ክልል አንደኛ የሚወጡት ቀጥታ ለአህጉራዊው አፍሪካ ውድድር የሚያልፉ ይሆናል።
#addisababa
#Ethiopia
ምክር ቤቱ የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት የቦርድ አባላትን ሹመት አጸደቀ

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት የቦርድ አባላትን ሹመት በአብላጫ ድምጽ አጽድቋል።

የቦርድ አባላቱን ሹመት አስመልክቶ ማብራሪያ የሰጡት በምክር ቤቱ የመንግስት ተጠሪ ሚኒስትር ዴኤታ ምህረቱ ሻንቆ (ዶ/ር) ተሿሚዎቹ በትምህርት ዝግጅት እንዲሁም ባዳበሩት ክህሎት የድርጅቱን ተልእኮ ማሳካት የሚችሉ መሆናቸውን ገልጸዋል።

ብሔራዊ ጥቅምን መረዳት የሚችሉ እንዲሁም ተቋሙን ለስኬት እንደሚያበቁ የታመነባቸው መሆናቸውን ተናግረዋል።

በዚህም ፦
1፡- ብሌን ማሞ ....... የቦርድ ሰብሳቢ
2፡- ፈዲላ ቢያ ....... አባል
3፡- ተስፋዬ ዘውዴ ....... አባል
4፡- መሐመድ ካሳ ....... አባል
5፡- አፈወርቅ በደዊ ....... አባል
6፡- አስማ ረዲ ....... አባል
7፡- ዮናስ በቀለ ....... አባል
8፡- ሃፍታይ ገብረእግዚአብሔር ....... አባል
9፡- ኢሳያስ ካሳ (ዶ/ር)....... አባል ሆነው እንዲሾሙ የቀረበውን የውሳኔ ሀሳብ ምክር ቤቱ መርምሮ በአንድ ድምጸ ተአቅቦ በአብላጫ ድምጽ አጽድቋል።

ተሿሚዎችም በምክር ቤቱ ቀርበው ቃለ-መሀላ ፈጽመዋል።
❤1
አዲሱ የአራዳ ፓርክ፦ የታሪክ፣ የውበትና የዘመናዊነት መገናኛ !

የአራዳ ፓርክ የጉስቁልና ታሪክን፣ የቆሻሻና የብክለት ስጋትን እንዲሁም የአስከፊ ድህነትን ገጽታ የቀየርንበት ታላቅ ፕሮጀክት ነው። የባዕዳንን አሉታዊ የታሪክ አሻራዎች በመናድ፣ የኢትዮጵያን ውበትና የትውልድን አዲስ ታሪክ በጋራ በማተም አዲሱን ማንነታችንን ገንብተናል።

ከፒያሳ አካባቢ የተነሱ ነዋሪዎቻችንን ለሰው ልጅ ክብር ከማይመጥኑና ከተጎሳቆሉ መኖሪያዎች አውጥተን፤ እጅግ ጤናማ፣ ነፋሻማና ሰብአዊ ክብርን የሚመጥን መሰረተ ልማት የተሟላለት መኖሪያ “ቤት ለእምቦሳ” ብለን አስረክበናል። ማህበራዊ መስተጋብራቸው ሳይቋረጥ እድርና እቁባቸውን ጠብቀው በጋራ እንዲኖሩም አድርገናል። ፒያሳን መልሰን ስንገነባ እውነተኛ ስልጣኔንና አራድነትን በሚያሳይ መልኩ ነው። ወንዞቻችን ከቆሻሻና ከበሽታ አምጪነት ተላቀው ዛሬ የቱሪስት መዳረሻ፣ የተፈጥሮ ውበት መገለጫና የሥራ ዕድል መፍጠሪያ ሆነዋል።

የአራዳ ፓርክ በ40 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈ የተቀናጀ የመሰረተ ልማትና የአገልግሎት ማዕከል ሲሆን፣ በውስጡ የሚከተሉትን ዋና ዋና አገልግሎቶች ይዟል፦
1. የትራንስፖርትና የመንገድ መሰረተ ልማቶች
• የአስፓልት መንገድ፦ 5 ኪ.ሜ. የሚረዝም የውስጥ ለውስጥ መንገድ።
• የእግረኛ መንገድ፦ 6 ኪ.ሜ. ርዝመት ያለው ምቹ የእግር ጉዞ መስመር።
• የብስክሌት መስመር፦ 5 ኪ.ሜ. ርዝመት ያለው የሳይክል ሌን።
• የመሮጫ ትራክ፦ 5 ኪ.ሜ. የሚረዝም ለስፖርተኞች የተዘጋጀ መስመር።
2. የንግድና የፋይናንስ አገልግሎቶች
• የንግድ ሱቆች፦ ከፒያሳ ለተነሱ ነጋዴዎች ቅድሚያ የተሰጠባቸው 131 ዘመናዊ ሱቆች።
• ምግብና መጠጥ፦ 7 ካፌዎችና ሬስቶራንቶች።
• ግብይትና ባንክ፦ 1 ትልቅ ሱፐርማርኬት እና 1 የባንክ ቅርንጫፍ።
3. የስፖርት፣ የኪነ-ጥበብና የመዝናኛ መገልገያዎች
• ዘመናዊ የስፖርት አሬና፦ አንድ (1) ዘመናዊ የአካል ብቃት ማዕከል (Gym) እና 7 አዳራሾች።
• መድረኮች፦ 8 ፕላዛዎችና 3 አንፊ-ቴአትሮች (ለተለያዩ ኩነቶች ማዘጋጃ የሚውሉ)።
• ልዩ ውበት፦ በአይነቱ ልዩ የሆነ “ዳንሲንግ ፋውንቴን” (ተንቀሳቃሽ ፏፏቴ)።
• ብሔራዊ ምልክት፦ በሀገራችን ረጅሙ የሆነው ባለ 100 ሜትር የብሔራዊ ሰንደቅ ዓላማ መስቀያ።
4. ለሕፃናትና ለቤተሰብ
• የሕፃናት መጫወቻ፦ 4 በሚገባ የተሟሉ ዘመናዊ የመጫወቻ ስፍራዎች።
• ትንሿ ከተማ፦ ሕፃናት ስለ ሀገራቸው እውቀት የሚቀስሙበትና የሚዝናኑበት ልዩ ስፍራ።
5. የተፈጥሮ ልማትና የንፅህና አገልግሎቶች
• አረንጓዴ ልማት፦ 15 ሄክታር መሬት በሳርና በተክሎች የተሸፈነ፣ በፓርኩ ውስጥ በተለያዩ ቦታዎች የሚገኙ 22 የሕዝብ መጸዳጃ ቤቶች።
• ፓርኪንግ፦ በአንድ ጊዜ 280 መኪናዎችን መያዝ የሚችል ሰፊ ማቆሚያ ወዘተ አገልግሎቶችን አካትቷል።
የአራዳ ፓርክ የመሬት አጠቃቀምን በላቀ ደረጃ ጥቅም ላይ ያዋለ ፕሮጀክት ነው። መሬትን ከስር ለሱቅና ለአዳራሽ፣ ከላይ ደግሞ ለፕላዛ በመጠቀም ውስን የሆነውን የከተማ መሬት በብቃት ተጠቅመናል።

በተጨማሪም በአካባቢው የነበሩ ከ700 በላይ ቤቶችና ሕንፃዎች ታሪካዊ ይዘታቸውን ጠብቀው እንዲታደሱ ተደርጓል።
ይህ ፓርክ ከንግድ እስከ ስፖርት፣ ከቤተሰብ መዝናኛ እስከ ዓለም አቀፍ የኪነ-ጥበብ መድረኮችን አጣምሮ የያዘ የከተማዋ አዲስ የቱሪስት መዳረሻ ነው።
እንኳን ደስ አለን!

ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
❤1