የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን Addis Ababa City Administration Environmental protection Authority(official)
808 subscribers
13.3K photos
135 videos
17 files
194 links
Addis Ababa City Administration Environmental protection Authority የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አካባቢ ጥበቃ በለስልጣን
Download Telegram
አዲስ አበባ የዓለም አቀፉን "ሲቲ ማውንቴን ባይክ ኤሊሚኔተር ፕሮ ሊግ" ልታስተናግድ ነው

የዓለም አቀፉ የብስክሌት ሕብረት (UCI) ዕውቅና የሰጠውና በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ተወዳጅነት ያለው "ሲቲ ማውንቴን ባይክ ኤሊሚኔተር ፕሮ ሊግ" በአፍሪካ ለመጀመሪያ ጊዜ በአዲስ አበባ ሊካሄድ ነው።

ይህ ከመላው ዓለም የተውጣጡ ምርጥ ብስክሌተኞች የሚሳተፉበት ታላቅ ውድድር የፊታችን ሚያዝያ 24 እና 25 ቀን 2018 ዓ.ም በፒያሳ አድዋ ድል መታሰቢያ ዙሪያ የሚከናወን ይሆናል።

ውድድሩ በዓለም አቀፍ የቴሌቪዥን ጣቢያዎች በቀጥታ የሚተላለፍ ሲሆን፣ ከ20 ሚሊዮን በላይ ተመልካቾች ይከታተሉታል ተብሎ ይጠበቃል።

አዲስ አበባ እንዲህ ያሉ ዓለም አቀፍ ስፖርታዊ ውድድሮችን ለማስተናገድ ተመራጭ መሆኗ፣ በከተማዋ በስፋት እየተገነቡ ያሉት ዘመናዊ የስፖርት መሠረተ ልማቶች ውጤት መሆኑ ተገልጿል።

የከተማ አስተዳደሩ የስፖርት ዘርፍ ለኢኮኖሚ ግንባታና ለትውልድ ዕድገት ያለውን ሚና ከግምት ውስጥ በማስገባት የጀመራቸው የልማት ሥራዎች፣ ከተማዋን የዓለም አቀፍ ስፖርታዊ ኩነቶች ማዕከል እያደረጓት ይገኛል።
የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ ባለፉት ስምንት የለውጥ ዓመታት በሚኒስትር መስሪያቤታቸው የተመዘገቡ ዐበይት ስኬቶችን አቅርበዋል።

‎በዚህም ዘርፉ ከለውጡ በፊት ሲቸገርበት የነበሩ መጠነ ሰፊ ክፍተቶችን በመለየት ፈጣን መፍትሔ በመስጠት ሰፊ ስኬቶችን አስመዝግቧል።
‎
‎ከተገኙ ስኬቶች መካከል ጥቂቶቹ የሚከተሉት ናቸው፦
‎የፖሊሲና የህግ ማዕቀፎችን በማዘጋጀት የዜጎችን መብት ጥበቃ፣ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ማረጋገጥ። አደረጃጀቶችን በመደገፍና በማጠናከር መብትና ግዴታ በማወቅ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ፣ የአቅመ ደካማ ዜጎችን የመደገፍና የማገዝ ባህል ማሳደግ ጥቂቶቹ ናቸው።
‎
እነዚህ ስኬቶች ቁጥር ብቻ ሳይሆኑ በተጨባጭ 4,330,948 የሚሆኑ ወጣቶች እና 26,845,686 ሴቶች ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ የተቻለበት ትልቅ ስኬትም ጭምር እንጂ! ከዚህ በተጨማሪም የሴቶችንና ወጣቶችን የፖለቲካ ተሳትፎን ከማሳደግ አኳያ ሰፊ ስራ ተሰርቶ ተጨባጭ ስኬቶች ተመዝግበዋል።
‎
በተጨማሪም ዘርፉ ካስመዘገባቸው ስኬቶች መካከል የማህበራዊ አገልግሎት ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ አንዱና ዋነኛው ሲሆን በተፈጥሮ እና ሰው ሰራሽ አደጋ ተጋላጭ ሆነው ድጋፍ የተደረገላቸው ዜጎች፣ ከጎዳና ላይ የተነሱ ዜጎች፣ የተሀድሶ አገልግሎት ያገኙ አካል ጉዳተኞች፣ በማህበረሰብ እንክብካቤ ጥምረቶች የተሰበሰበ ሀብት ዋነኞቹ ስኬቶች ናቸው።

#PMOEthiopia
የከተማ አስተዳደራችንን የ2018 በጀት ዓመት የ9 ወራት ስራዎች አፈፃፀም ግምገማ ማካሄድ ጀምረናል።

በበጀት ዓመቱ በእቅድ ከያዝናቸው ተግባራት 96 በመቶ መፈፀም ችለናል።

ለሁለት ተከታታይ ቀናት በሚቆየው የግምገማ መድረክ በበጅት ዓመቱ ለመፈፀም ካቀድናቸው ውስጥ በ9 ወራት በጥብቅ ክትትል የተከናወኑትን የምንገመግምበት እና በቀሪ ወራት የትኩረት ማዕከል አድርገን የምንፈፅማቸው በመልካም አስተዳደር ተለይተው ያልተመለሱትን ምላሽ በመስጠት ማጠናቀቅ፣ የኑሮ ውድነትን የሚያባብሱ ችግሮችን በመቀነስ የዋጋ ንረትን መከላከል፣ የገበያ ማዛባት ችግሮችን መከላከል፣ ከአገልግሎት አሰጣጥ ጋር በመሶብ ዲጅታል የአንድ ማዕከል የመንግስት አገልግሎት የጀመርነውን ውጤታማ ስራ በቀሪ ወራት በተሟላ ሁኔታ በማጠናቀቅና ወደ ስራ ማስገባት እንዲሁም ቀሪ አገልግሎቶችን ዲጅታላይዝ አድርጎ ወደ መሶብ ማስገባት፣ ተጀምረው በዚህ ዓመት መጠናቀቅ ያለባቸውን ፕሮጀክቶች በፍጥነትና በጥራት ማጠናቀቅ የአፈፃፀም ግምገማ ማዕከላችን ይሆናሉ።

ባለፋት አምስት ዓመታት የእቅድ አፈፃፀማችን ከ90 በመቶ በላይ እያደገ መጥቶ በ2018 ደግሞ 96 በመቶ የደረሰበት ውጤታማ አፈፃፀም መኖሩን በመገምገም፣ ይህንን እያደገ የመጣ የመፈፀም ልምድ አጠናክረን መቀጠል እንድንችል በትኩረት እንገመግማለን ።

በተጨማሪም 7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ፍትሃዊ፣ ነፃ፣ ተዓማኒና ገለልተኛ ሆኖ እንዲከናወን ሁሉም አመራራችን ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር ትልቅ ሃላፊነት መወጣት እንዲችሉ የግምገማ አቅጣጫን አስቀምጠናል።

የነበሩ ጥንካሬዎችን ማስቀጠል፣ ጉድለቶችን በመሙላት በቀሪዎች ወራት በላቀ መፈፀም የግምግማችን ማዕከል ይሆናል።

ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ!

ከንቲባ አዳነች አቤቤ

ለተጨማሪ መረጃ👇🏻👇🏻👇🏻

https://linktr.ee/Addis_Ababa_Communication
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ2018 ዓ.ም በ9 ወሩ የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት ።

1. የአየር ንብረት ለውጥ ሥራዎች በሴክተሮች ማስተሰረይ እና ማላመድን በተመለከተ
☑️ የአየር ንብረት ለውጥ ሥራዎችን ለሴክተር ተቋማት በዕቅዳቸው ተካቶ አተገባበሩን ክትትልና ድጋፍ ለማድረግ 13 ሴክተሮችን ለመከታተል/ መደገፍ ታቅዶ 13 ማከናወን ተችሏል፡፡

☑️ ከሴክተሮች ጋር የሚደረግ የዕቅድ ላይ ውይይት ለማድረግ 2 ታቅዶ 2 የተከናወነ ሲሆን
☑️ በአየር ንብረት ለዉጥ አያያዝ ዙሪያ ስልጠና ለመስጠት በማዕከልና በክ/ከተማ መድረኮች ለ2660 ሰው ስልጠና ለመስጠት ታቅዶ ለ3103 ሰዎች ስልጠና ተሰጥቷል፡፡

☑️ ከመቆጣጠሪያ ጣቢያው የሚገኙትን የከተማውን የአየር ብክለት ደረጃ መረጃዎች በማደራጀት፤ በመተንተን በየወሩ ሪፖርት ለማዘጋጀት በ9 ወር 9 ጊዜ ከ 7 አየር ጥራት መሳሪዎች በመሰብሰብ በመተንትን ሪፖርት ማቅረብ ተችሏል፡፡

☑️ የአየር ብክለት መለኪያ መሳሪያዎችን ድህንነት መከታተል በየሩብ ዓመቱ የታቀደ በመሆኑ 3 ጊዜ ማከናወን ተችሏል፡፡

☑️ ከመቆጣጠሪያ ጣቢያው የሚገኙትን የአየር ብክለት ዉጤቶችን ለከተማው ነዋሪዎች መረጃ የሚያገኙበት ስርአት በመዘርጋት በየወሩ ተደራሽ እንዲሆን ተደርጓል፡፡ የአየር ጥራት ደረጃው (PM2.5) በፌስቡክ እንዲተላለፍ ተደርጓል፡፡
1.1. የአማራጭ ኢነርጅ ቴክኖሎጂ አጠቃቀም ማስፋፋትን በተመለከተ

☑️ በ9 ወር ለ1,350 ሰዎች ትምህርት ለመስጠት ታቅዶ ለ1,459 ሰዎች ስልጠናውን ተሰጥቷል፡፡

☑️ በ9 ወር የባዩ ኢነርጂ ቴክኖሎጂና ምንጮች ላይ ለ375 ሰዎች የተግባር ስልጠና ለመስጠት ታቅዶ ለ392 ሰዎች የተግባር ስልጠናውን መስጠት በመቻሉ ተችሏል፡፡

☑️ የተግባር ስልጠናው የተሰጠው በአቃቂ፤ቂርቆስ፣ የካ፣ጉለሌ፣አራዳ፣ቦሌ፣ንፋስ ስልክ፣ለሚ ኩራ እና ልደታ ክ/ከተሞች ናቸዉ፡፡

1.2. የኢነርጂ ኦዲት ላይ ግንዛቤ በመስጠት የኃይል ብክነት ማሻሻልን በተመለከተ፡-

☑️ የኢነርጂ ኦዲት ስልጠና ለመስጠት በሰው 100 ታቅዶ ለ152 ሰው ስልጠናው ተሰጥቷል፡፡
☑️ በአገልግሎት ሰጪ ተቋማት ላይ የኢነርጂ ኦዲት በማካሄድ የኃይል ብክነትን ግብረ መልስ በመስጠት ማሻሻል 22 ተቋማት ላይ ለማድረግ ታቅዶ በ23 ተቋማት ግብረ መልስ ሆኗል፡፡

2. የአካባቢ ብክለት ቁጥጥር ስርዓትን በማጠናከር የህግ ተከባሪነትና ተፈፃሚነትን ከማሳደግ አኳያ የተሰሩ ስራዎች
☑️ ብክለት በሚያደርሱ ተቋማት ላይ ክትትልና ቁጥጥር ለማድረግ 12862 ታቅዶ 13080 የተሰራ ሲሆን ይህም በአየር ፣ በውሃ፣ በድምጽ፣ በውሃ ናሙና እና አፈር ናሙና ላይ ተሰርቷል፡፡ በ አየር 2279፣ ውኃ ላይ 1182፣ ድምፅ 9597 ክትትልና ቁጥጥር ተደርጓል፡፡

☑️ የብክለት ይወገድልኝ አቤቱታዎች ተቀብሎ ምላሽ ለመስጠት 217 አቤቱታዎችን በመቀበል ለሁሉም ምላሽ ተሰጥቷል፡፡

☑️ እነዚህም የቀረቡ አቤቱታዎች ከአየር፣ ከድምጽ እና ከሽታ ጋር በተያያዘ ከሁሉም ክፍለ ከተሞች የቀረቡ ሲሆን ምላሹም በአግባቡ ታይቶ የተፈታ ነው፡፡ የአካባቢ ብክለት በሚያደርሱ ክትትል ከተደረገባቸው ተቋማት 2671 እርምጃ ለመውሰድ ታቅዶ በ2661 ተቋማት ላይ እርምጃ ተወስዷል፡፡

ብክለት በሚያደርሱ ተቋማት ላይ የተወሰዱ እርምጃዎች።

የፅሑፍ ማስጠንቀቂያ
☑️ በ133 አምራች ተቋማት እና በ2489 አገልግሎት ሰጪ ተቋማት በድምሩ ለ2622 የፅሑፍ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷል፡፡
የማሸግ እርምጃ
☑️ በ11 አምራች ተቋማትና በ28 አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ላይ የማሸግ እርምጃ ተወስዷል፡፡
☑️ የልማት ፕሮጀክቶችን 749 በአካባቢ ተፅዕኖ ግምገማ ይሁንታ እንዲያልፉ ታቅዶ 808 ተከነዉኗል፡፡

ፈቃድ የተሰጣባቸዉም ዘርፎች
☑️ የፕላስቲክ መልሶ መጠቀም ፡ የምግብ ማቀነባበሪያ ፤ የኮንስትራክሽን ማዕድን፤ሆስፒታል፤ባቺንግ ፡ በፋሪማትካል ግብአት፤ ቡና ማቀናባበሪያ፤ ነደጅ ማደያ፤ ህንፃ ግንባታና ሴፍትኔት ናቸዉ፡፡
የተሰራ የአካባቢ ክዋኔ ኦዲት
☑️የአካባቢ ክዋኔ ኦዲትን በተመለከተ 465 ታቅዶ 448 ተሰርቷል፡፡

☑️ የአካባቢ ተጽእኖ ስራ የጀመሩ ተቋማት ላይ ክትትልና ቁጥጥር ማድረግ 668 ታቅዶ 707 ተከናዉኗል፡፡

የአመራር አቅጣጫ

የአዲስ አበባ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ ዶክተር እሸቱ ለማ ባለፉት ዘጠኝ ወራት የተከናወኑ ጠንካራ ስራዎችን በመጥቀስ በቀጣይ ትኩረት ሊሰጣቸው በሚገቡ ጉዳዮች ላይ የሚከተሉትን የአቅጣጫ መመሪያዎች አስተላልፈዋል፡-

የግብረ-መልስ አፈጻጸም፦** ክፍለ ከተሞች የሚሰጣቸውን ግብረ-መልስ መሰረት በማድረግ ስራዎቻቸውን እንዲያስተካክሉ፤

የወንዞች ልማት ቁጥጥር፦ በከተማ ደረጃ እየተከናወነ ያለውን የወንዝ ዳርቻዎች ልማት የቁጥጥር ስራ አጠናክሮ መቀጠል፤

የመረጃ አያያዝ፦ የቁጥጥርና የክትትል ስራዎችን ውጤታማ ለማድረግ ዘመናዊ የመረጃ አያያዝ ስርአትን ማስተካከል፤

ድምጽና መልሶ ማልማት፦በድምጽ ብክለት መከላከልና በመልሶ ማልማት ተግባራት ላይ ጥብቅ የክትትልና የቁጥጥር ስራዎችን ማከናወን፤

መመሪያዎችን ማጠናቀቅ፦ በአሁኑ ወቅት እየተዘጋጀ ያለው የመልሶ ማልማት መመሪያ በአስቸኳይ ተጠናቆ ወደ ስራ እንዲገባ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።