የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን Addis Ababa City Administration Environmental protection Authority(official)
809 subscribers
13.3K photos
135 videos
17 files
194 links
Addis Ababa City Administration Environmental protection Authority የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አካባቢ ጥበቃ በለስልጣን
Download Telegram
አዲስ አበባ የዓለም አቀፉን "ሲቲ ማውንቴን ባይክ ኤሊሚኔተር ፕሮ ሊግ" ልታስተናግድ ነው

የዓለም አቀፉ የብስክሌት ሕብረት (UCI) ዕውቅና የሰጠውና በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ተወዳጅነት ያለው "ሲቲ ማውንቴን ባይክ ኤሊሚኔተር ፕሮ ሊግ" በአፍሪካ ለመጀመሪያ ጊዜ በአዲስ አበባ ሊካሄድ ነው።

ይህ ከመላው ዓለም የተውጣጡ ምርጥ ብስክሌተኞች የሚሳተፉበት ታላቅ ውድድር የፊታችን ሚያዝያ 24 እና 25 ቀን 2018 ዓ.ም በፒያሳ አድዋ ድል መታሰቢያ ዙሪያ የሚከናወን ይሆናል።

ውድድሩ በዓለም አቀፍ የቴሌቪዥን ጣቢያዎች በቀጥታ የሚተላለፍ ሲሆን፣ ከ20 ሚሊዮን በላይ ተመልካቾች ይከታተሉታል ተብሎ ይጠበቃል።

አዲስ አበባ እንዲህ ያሉ ዓለም አቀፍ ስፖርታዊ ውድድሮችን ለማስተናገድ ተመራጭ መሆኗ፣ በከተማዋ በስፋት እየተገነቡ ያሉት ዘመናዊ የስፖርት መሠረተ ልማቶች ውጤት መሆኑ ተገልጿል።

የከተማ አስተዳደሩ የስፖርት ዘርፍ ለኢኮኖሚ ግንባታና ለትውልድ ዕድገት ያለውን ሚና ከግምት ውስጥ በማስገባት የጀመራቸው የልማት ሥራዎች፣ ከተማዋን የዓለም አቀፍ ስፖርታዊ ኩነቶች ማዕከል እያደረጓት ይገኛል።
የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ ባለፉት ስምንት የለውጥ ዓመታት በሚኒስትር መስሪያቤታቸው የተመዘገቡ ዐበይት ስኬቶችን አቅርበዋል።

‎በዚህም ዘርፉ ከለውጡ በፊት ሲቸገርበት የነበሩ መጠነ ሰፊ ክፍተቶችን በመለየት ፈጣን መፍትሔ በመስጠት ሰፊ ስኬቶችን አስመዝግቧል።
‎
‎ከተገኙ ስኬቶች መካከል ጥቂቶቹ የሚከተሉት ናቸው፦
‎የፖሊሲና የህግ ማዕቀፎችን በማዘጋጀት የዜጎችን መብት ጥበቃ፣ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ማረጋገጥ። አደረጃጀቶችን በመደገፍና በማጠናከር መብትና ግዴታ በማወቅ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ፣ የአቅመ ደካማ ዜጎችን የመደገፍና የማገዝ ባህል ማሳደግ ጥቂቶቹ ናቸው።
‎
እነዚህ ስኬቶች ቁጥር ብቻ ሳይሆኑ በተጨባጭ 4,330,948 የሚሆኑ ወጣቶች እና 26,845,686 ሴቶች ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ የተቻለበት ትልቅ ስኬትም ጭምር እንጂ! ከዚህ በተጨማሪም የሴቶችንና ወጣቶችን የፖለቲካ ተሳትፎን ከማሳደግ አኳያ ሰፊ ስራ ተሰርቶ ተጨባጭ ስኬቶች ተመዝግበዋል።
‎
በተጨማሪም ዘርፉ ካስመዘገባቸው ስኬቶች መካከል የማህበራዊ አገልግሎት ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ አንዱና ዋነኛው ሲሆን በተፈጥሮ እና ሰው ሰራሽ አደጋ ተጋላጭ ሆነው ድጋፍ የተደረገላቸው ዜጎች፣ ከጎዳና ላይ የተነሱ ዜጎች፣ የተሀድሶ አገልግሎት ያገኙ አካል ጉዳተኞች፣ በማህበረሰብ እንክብካቤ ጥምረቶች የተሰበሰበ ሀብት ዋነኞቹ ስኬቶች ናቸው።

#PMOEthiopia
የከተማ አስተዳደራችንን የ2018 በጀት ዓመት የ9 ወራት ስራዎች አፈፃፀም ግምገማ ማካሄድ ጀምረናል።

በበጀት ዓመቱ በእቅድ ከያዝናቸው ተግባራት 96 በመቶ መፈፀም ችለናል።

ለሁለት ተከታታይ ቀናት በሚቆየው የግምገማ መድረክ በበጅት ዓመቱ ለመፈፀም ካቀድናቸው ውስጥ በ9 ወራት በጥብቅ ክትትል የተከናወኑትን የምንገመግምበት እና በቀሪ ወራት የትኩረት ማዕከል አድርገን የምንፈፅማቸው በመልካም አስተዳደር ተለይተው ያልተመለሱትን ምላሽ በመስጠት ማጠናቀቅ፣ የኑሮ ውድነትን የሚያባብሱ ችግሮችን በመቀነስ የዋጋ ንረትን መከላከል፣ የገበያ ማዛባት ችግሮችን መከላከል፣ ከአገልግሎት አሰጣጥ ጋር በመሶብ ዲጅታል የአንድ ማዕከል የመንግስት አገልግሎት የጀመርነውን ውጤታማ ስራ በቀሪ ወራት በተሟላ ሁኔታ በማጠናቀቅና ወደ ስራ ማስገባት እንዲሁም ቀሪ አገልግሎቶችን ዲጅታላይዝ አድርጎ ወደ መሶብ ማስገባት፣ ተጀምረው በዚህ ዓመት መጠናቀቅ ያለባቸውን ፕሮጀክቶች በፍጥነትና በጥራት ማጠናቀቅ የአፈፃፀም ግምገማ ማዕከላችን ይሆናሉ።

ባለፋት አምስት ዓመታት የእቅድ አፈፃፀማችን ከ90 በመቶ በላይ እያደገ መጥቶ በ2018 ደግሞ 96 በመቶ የደረሰበት ውጤታማ አፈፃፀም መኖሩን በመገምገም፣ ይህንን እያደገ የመጣ የመፈፀም ልምድ አጠናክረን መቀጠል እንድንችል በትኩረት እንገመግማለን ።

በተጨማሪም 7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ፍትሃዊ፣ ነፃ፣ ተዓማኒና ገለልተኛ ሆኖ እንዲከናወን ሁሉም አመራራችን ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር ትልቅ ሃላፊነት መወጣት እንዲችሉ የግምገማ አቅጣጫን አስቀምጠናል።

የነበሩ ጥንካሬዎችን ማስቀጠል፣ ጉድለቶችን በመሙላት በቀሪዎች ወራት በላቀ መፈፀም የግምግማችን ማዕከል ይሆናል።

ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ!

ከንቲባ አዳነች አቤቤ

ለተጨማሪ መረጃ👇🏻👇🏻👇🏻

https://linktr.ee/Addis_Ababa_Communication