የበጋ መስኖ እርሻ፤ በምግብ ራሳችንን ለመቻል በሚደረገው ጉዞ ውስጥ የጸና መሰረትን የጣልንበት ምዕራፍ ነው።
የውሃ ሀብታችንን በአግባቡ በመጠቀም፣ ባልተቋረጠ ጥረት እና ቁርጠኝነት፣ የመልማት ጉዟችን አስተማማኝና ዘላቂ የሆነ የምግብ ዋስትና ወደምናረጋግጥበት ብሩህ ተስፋ እንደሚያሸጋግረን ጥርጥር የለውም።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ (ዶ/ር)

የአደይ-አበባ የካ አዲሱ ወንዝ ዳርቻ የብክለት ቁጥጥር ስራዎች አፈጻጸም ሪፖርት ቀረበ።
የአዲስ አበባ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ባለፉት ሶስት ወራት በአደይ-አበባ የካ እና ቦሌ ክፍለ ከተማ አዲሱ ወንዝ ዳርቻ ላይ ሲያከናውን የቆየውን የወንዝ ብክለት ክትትልና ቁጥጥር ስራ አፈጻጸም ሪፖርት ከአስራ አንዱም ክፍለ ከተማ የተውጣጡ የአካባቢ ጥበቃ ጽ/ቤት ሃላፊዎች እና ባለሙያዎች በተገኙበት ገመገመ።
ሪፖርቱ በዋናነት በየካ እና በቦሌ ክፍለ ከተሞች ከቦሌ ቪ.አይ.ፒ እስከ ሳውዝጌት ባለው ክልል እየተከናወነ ያለውን የወንዝ ዳርቻ ልማት ከብክለት የመከላከል ስራ ግምገማ ላይ ያተኮረ ነው።
ባለፉት ሶስት ወራትም ብክለትን በሳይንሳዊ መንገድ ለመከላከል ከፍተኛ የብክለት ጫና ያለባቸውን ቦታዎች የመለየት ስራ ተከናውኗል። በዚህም፦ በየካ ክፍለ ከተማ፡ 11 ስልታዊ ቦታዎች ተለይተው የጂ.ፒ.ኤስ (GPS) ኮኦርዲኔትስ በመሰብሰብ የካርታ ስራ ተሰርቷል።
በተመሳሳይ በቦሌ ክፍለ ከተማ፡ 13 ስልታዊ ቦታዎች በተመሳሳይ ሁኔታ ተለይተው ወደ ካርታ እንዲገቡ ተደርጓል እነዚህ መረጃዎች የተሰበሰቡት ከአምራች ኢንዱስትሪዎች፣ ከአገልግሎት ሰጪ ተቋማት፣ ከመንግስታዊና የግል ድርጅቶች፣ ከሀይማኖት ተቋማት እንዲሁም ከመኖሪያ ቤቶችና ከኮንዶሚኒየሞች መሆኑ ተመልክቷል።
የተወሰዱ ተግባራዊ እርምጃዎች
ባለፉት ሶስት ወራት የወንዝ ብክለትን ለመቀነስ የተከናወኑ አበይት ተግባራት የሚከተሉት ናቸው።
ወደ ወንዝ የሚገቡ 78 የፍሳሽ ቱቦዎች እንዲቋረጡ ተደርጓል 5 ሴፒቲክ ታንኮች እና 8 የፍሳሽ ማስረጊያዎች ተገንብተዋል 65 ተቋማትና መኖሪያ ቤቶች በቋሚነት ፍሳሽ ማስመጠጥ እንዲጀምሩ ተደርጓል።
የአመራር አቅጣጫ
የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ዶ/ር እሸቱ ለማ በመድረኩ ባስተላለፉት መልእክት፣ ወንዞችን ከብክለት መከላከል የሁሉም ክፍለ ከተሞች የጋራ ኃላፊነት መሆኑን አሳስበዋል። ዋና ስራ አስኪያጁ ሲያብራሩም፦ "በየክፍለ ከተሞቻችን ያሉትን ወንዞች ፣ የብክለት መንስኤዎቻቸውንና ደረጃቸውን በትክክል አውቆ መስራት ይገባል" ብለዋል።
በተጨማሪም በበካይ አካላት ላይ የሚወሰደው ህጋዊ እርምጃ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ ለተቋማትና ለማህበረሰቡ ስልጠናና የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች በስፋት መሰጠት እንዳለባቸው አሳስበዋል። ጥሩ ተሞክሮ ያላቸው ተቋማትም ልምዳቸውን ለሌሎች እንዲያካፍሉ በማድረግ የወንዝ ብክለትን በዘላቂነት ለመከላከል እንደሚሰራ ገልፀዋል።