የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን Addis Ababa City Administration Environmental protection Authority(official)
812 subscribers
13.3K photos
135 videos
17 files
194 links
Addis Ababa City Administration Environmental protection Authority የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አካባቢ ጥበቃ በለስልጣን
Download Telegram
ከብዙ ወደ አንድ ፣ አንዱም ፣ ወደ-እያንዳንዱ ቤት!

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር “በአዲስ መሶብ ዲጅታል የአንድ ማዕከል በተንቀሳቃሽ አውቶቢስ የሚሰጡ 8ቱ አገልግሎቶች “

- የገቢ አገልግሎት (አዲስ ቲን ማውጣት)
- የንግድ አገልግሎት (ንግድ ፈቃድ ማውጣት፣ ማደስ)
- የጤና (ለመንጃ ፈቃድ አካላዊ የጤና ምርመራ)
- የሲቪል ምዝገባ (መታወቂያ፣ ልደት እና ሌሎች)
- የአሸከረካሪ ተሽከርካሪ (የመንጃ ፈቃድ እና የቦሎ ዕድሳት)
- የኢትዮ ፖስታ (የመንገድ ፈንድ ክፍያ)
- የብሔራዊ መታወቂያ (አዲስ ምዝገባና የመረጃ እርማት)
- የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት (ቅድመ ክፍያ)
❤2
ለባለስልጣንኑ ሰራተኞች የጣት አሻራ አጠቃቀም ኦረንቴሽን ተሰጠ።
“በሳይንስና ፈጠራ የተካነ ትውልድ ለተምሳሌታዊ ሀገር” በሚል መሪ ሀሳብ ዛሬን ጨምሮ ለተከታታይ 2 ቀናት የሚካሄደውን 11ኛው ከተማ አቀፍ የሳይንስ ፈጠራ ስራ አውደ ርዕይ አስጀምረናል።

የዛሬው የሳይንስ ፈጠራ ስራ አውደ ርዕይ ዋነኛ ዓላማ ተማሪዎች በንድፈ ሀሳብ የተማሩትን በተግባር የሚያሳዩበት፣ የውስጥ ተሰጥዖዋቸውን የሚገልጹበት፣ ለሰሯቸው የፈጠራ ስራዎች የሚበረታቱበት፣ በትብብር የመስራት ልምድ የሚለዋወጡበት ትልቅ መድረክ መፍጠር ነው።

እውቀት ችግሮችን ደጋግሞ ማውራት ሳይሆን ለችግሮች መፍትሄ ማፍለቅ እና ችግርን ወደ ድል መቀየር ስለሆነ፣ ከተማችንን የሳይንስና ፈጠራ ማዕከል ለማድረግ ሰፋፊ ስራዎች በመስራት ውጤቱንም በተጨባጭ ማየት የተጀመረበት ወቅት ላይ ደርሰናል። ይህ ውጤታማ ጅምሮ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ሁሉም ባለድርሻ አካላት ሀላፊነትታውን በአግባቡ መወጣት ይኖርባቸዋል።

ዛሬ የፈጠራ ስራችሁን ያቀረባችሁ ተማሪዎችና መምህራን፣ የፈጠራ ስራችሁ አድጎና በልጽጎ ለከተማችን፣ ለሀገራችን ብሎም ለዓለም የሚተርፍ በረከት ሊሆን እንደሚችል ትልቅ ተስፋ ሰንቀናል፡፡

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ!

ከንቲባ አዳነች አቤቤ