የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን Addis Ababa City Administration Environmental protection Authority(official)
812 subscribers
13.3K photos
135 videos
17 files
194 links
Addis Ababa City Administration Environmental protection Authority የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አካባቢ ጥበቃ በለስልጣን
Download Telegram
ለስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች ምቹ የሆነችው አዲስ አበባ

ከዚህ ቀደም የአዲስ አበባ ጎዳናዎች ምቹ ያልነበሩ ተሽከርካሪ እና እግረኛ እኩል የሚጋፋባቸው ለአደጋ የተጋለጡ በተለይም በየመንደሩ የሚኖሩ ታዳጊዎች አማራጭ ባለማግኘታቸው ኳስ ለመጫወት የተሽከርካሪን መንገድ የሚሻሙ ነበሩ። ዛሬ ይህ ታሪክ ሆኖ አልፏል ።

ችግሩን የተረዳው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በሚሰራቸው ስራዎች ሁሉ ለታዳጊዎች ፣ ለወጣቶች እና ለህፃናት ምቹ ከተማን ለመገንባት በመወሰን የከተማዋ ጎዳናዎች ለሁሉም ተስማሚ እንዲሆኑ ዘመን ተሻጋሪ ስራዎችን አከናውኗል ።

ዛሬ ላይ የአዲስ አበባ ውብ ጎዳናዎች ሁሉን በመልኩ አድርገው በእግረኛና በሳይክል መንገድ ተውበው ፣ በአረንጓዴ አበቦች አጊጠው ለእግር ጎዞዎች እንዲሁም ለተለያዩ ስፖርታዊ እንቅሰቃሴ ምቹ ሆነዋል።
አሁን ላይ በአዲስ ጎዳናዎች ሲጓዙ በተመቻቸላቸው ጎዳናዎች እና ቦታዎች ስፖርታዊ እንቅስቃሴ የሚያደርጉ ወጣቶች ፣ ህፃናት፣ አረጋውያን እና ጎልማሶችን መመልከት የተለመደ ባህል ሆኗል ።
❤1