ዛሬ ጠዋት የስራ ዘመኑን ሶስተኛ የ100 ቀናት የመንግሥት ሥራ አፈፃፀም ከዘጠኝ ወራት አጠቃላይ አፈፃፀም ጎን ለጎን መገምገም ጀምረናል።
ለእድገት አመቺ ካልነበረው እና በደካማ የተቋማት እና የፖለቲካ ማዕቀፍ ፣ በታጠረ የግል ዘርፍ ተሳትፎ እንዲሁም ውጤታማ ባልነበረ የቁጥጥር ከባቢ ከሚገለጠው የኢኮኖሚ መልክ ወጥተናል። የግሉ ዘርፍ ደካማ ውድድር ውስጥ ነበር፤ በመንግሥት ሥር የነበሩ በርከት ያለ ቁጥር ያላቸው የንግድ ተቋማትም ከፍ ባለ የዕዳ ሸክም ተዘፍቀው ከአቅም በታች ሲንቀሳቀሱ እንደነበር ይታወቃል። ምርታማነት አሽቆልቁሎ ኢኮኖሚውም ለአየር ንብረት ለውጥ በከፍተኛ ደረጃ ተጋላጭ የነበረውን ነባራዊ ሁኔታ ምላሽ በሚሰጥ አዲስ ገቢር ነበብ የፓለቲካ ኢኮኖሚ መንገድ ቀይሰናል።
የቀየስነው አዲሱ የኢኮኖሚ አካሄድ በአጭር ጊዜ ትግበራ ጠንካራ ባለሁለት አሃዝ የእድገት ሂደትን አስመዝግቧል። በአሁኑ ወቅት ኢኮኖሚያችን በ9.2 በመቶ እያደገ ይገኛል። ይኽ እድገት በመጪው ዓመት ወደ10.2 በመቶ እንደሚያድግ እንጠብቃለን። በየዘርፉም የታቀዱ ግቦቻችንን ለማሳካት ከፍ ባለ ትጋት ቀጥለን፤ በግብርና 7.9 በመቶ፣ በኢንደስትሪ 13.2 በመቶ፣ በአገልግሎት 9.3 በመቶ ዕድገቶች ሳይቆራረጡ የሚከናወኑ ይሆናል።
እነዚህ ጥረቶች የበለጠ ጽኑ፣ ተወዳዳሪ እና አካታች ኢኮኖሚ ለመገንባት ያለንን አቋም እና የመተግበር ዐቅም ያሳያሉ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የመራጮች ምዝግባ ሊጠናቀቅ ሁለት ቀናት ብቻ ቀሩት!
እንግዲያውስ ባሉበት ሆነው በ"ምርጫዬ” የሞባይል መተግበሪያ ወይም ስድስት ወር እና ከዚያ በላይ በኖሩበት አካባቢ በሚገኝ የምርጫ ጣቢያ በአካል በመገኘት በቀላሉ መመዝገብ ይችላሉ።
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/addisababacommunication

የስፖርት ቱሪዝም እድገት ማሳያ አዲስ አበባ !
መዲናችን አዲስ አበባ ባከናወነቻቸው አመርቂ የልማት ስራዎች የሁሉ ቀልብ ማረፊያ ሆናለች፡፡
ወንዞቿን አክማ የጎሰቀሉ እና ደሃ ነን የሚል መልዕክት ያስተላልፉ የነበሩ መንደሮቿን አፍርሳ ደረጃቸውን የጠበቁ ቤቶች ፣ መንገዶች ፣ የህፃናት መጫወጫ ስፍራዎችና የስፖርት ማዘውተሪያ ሜዳዎች እንዲሁም ቤተመፅሀፍት ገንብታ እንካችሁ ብላለች፡፡
ከተማዋ በሰራችው ለትውልድ ተሻጋሪ ስራ የሁሉም ቀልብ ማረፊ ፣ የአፍሪካውያን መቀመጫ ፣ ምቹ ፣ ለሁሉ ተስማሚ ከተማ መሆኗን ዓለም በአንድ ድምፅ እየመሰከረ ይገኛል፡፡ ለዚህ ማሳያው አገራችን ኢትዮዽያ በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ ያስተናገደቸው እና በአዲስ አበባ በድምቀት የተካሄደው የዓለም አትሌቲክስ የአንድ ቀን ሩጫ (Addis Ababa Grand Prix) ውድድርን ተጠቃሽ ነው ፡፡
ከተማዋ ያስመዘገበችውሁለንተናዊ የልማት ስራዎች እና አካታች ዘመናዊ የመሰረተ ልማት ግንባታዎች የስፖርት ቱሪዝምን በከፍተኛ ሁኔታ በማሳደግ ረገድ ጠቀሜታቸው የጎላ ነው ፡፡
ኢትዮጵያውያን በአለም አደባባይ አይችሉም የተባለውን ስማችንን የቀይረን ውብ ንፁህና እና ተስማሚ የአየር ፀባይ ያለን ጥንታዊ የሰው ዘር መገኛ ህዝቦች መሆናችንን አለም በአይኑ አይቶ እያረጋገጠ ይገኛል።