የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን Addis Ababa City Administration Environmental protection Authority(official)
812 subscribers
13.3K photos
135 videos
17 files
194 links
Addis Ababa City Administration Environmental protection Authority የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አካባቢ ጥበቃ በለስልጣን
Download Telegram
የዓለም ድንቅ ከዋክብት አትሌቶች በአዲስ አበባ ልማት መደነቃቸውን ገለፁ

በአዳስ አበባ 2026 የግራን ፕሪ ውድድር ተሳታፊ የነበሩ ስመ ጥር የትራክ ኮኮቦች የአዲስ ስፖርት ፓርክ፥ አድዋ ድል መታሰቢያንና የወንዝ ዳርቻ ልማትን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።

አትሌቶቹ በጉብኝታቸው ታሪክንና፤ የከተማ ውበትን መመልከት መቻላቸውን ተናግረዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ ልማትና በተለይም ደግሞ ለስፖርቱ ዘርፍ የተሰጠውን ትኩረት ለሌሎች ሀገራትም ልምድና ተሞክሮ የሚቀመርባቸዉ ስለመሆኑ ገልፀዋል፡፡

በአለም አደባባይ ሰንደቅ ዓላማን ከፍ ያደረጉ ብርቅየ አትሌቶች መገኛዋ ኢትዮጵያ አሁን ላይ ታሪክን በመዘከር እና አዳዲስ ታሪኮችን በመፃፍ ላይ ትገኛለች፡፡

አዲስ አበባ ከተማ የስፖርት ቱሪዝም ማዕከል ለመሆን በሰራችዉ ስራ እና ባስመገበችዉ ድል የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የአንድ ቀን ሩጫ የአዲስ አበባ ግራን ፕሪ ዉድድርን ማሰተናገድ ችላለች፡
#addisababa #Ethiopia