የካቲት 12 የሆነው ይህ ነው!
#የታሪክ_ማስታወሻ
2️⃣ ለሶስተኛ ጊዜ የፈነዳው ቦምብ ግን ከፍተኛ የፋሺስት ኢጣሊያ ባለሥልጣናት ከተቀመጡበት መካከል አረፈ፡፡በቀጣዮቹ ደቂቃዎች አራት ተጨማሪ ቦምቦች ተወርውረው ፈነዱ፡፡በፍንዳታው ግራዚያኒ ጀርባውን ቆስሎ ወደቀ፣የኢጣሊያ አየር ኃይል አዛዥ የነበረው ጀነራል አውሬሊዮ ሊዮታ ቀኝ እግሩንና ቀኝ ዐይኑን አጣ፣የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ጉይዶ ኮርቲሲ እና ሌሎች ኢጣሊያውያን እንግዶች በፈንጂው ተጎዱ፡፡ፍንዳታው ጋብ ሲል ከንቲባ ኮርቴሲ ከወደቀበት ተነስቶ የተሰበሰቡት ኢትዮጵያውያን ላይ በማነጣጠር የመጀመሪያውን ጥይት ተኮሰ።የፋሺስት ፖሊሶችም ምሣሌውን በመከተል ለቀጣይ ሶስት ቀናት የቆየውንና ከተማውን ያዳረሰውን አሰቃቂ ጭፍጨፋ ከዚያው ከቤተ መንግሥት ውሥጥ ጀመሩ፡፡
ፋሽስት ኢጣሊያ በወቅቱ ድርጊቱን ለመበቀል በወሰደው አሰቃቂ ጭፍጨፋ እዚያው ግቢ ውስጥ ከሶስት መቶ በላይ የሚሆኑ ኢትዮጵያውያንን ጨፈጨፈ። ቀጥሎም የተማሩ ወጣቶችን ፣ የጦር መኮንኖችንና ካህናትን፣ የደብረ ሊባኖስ መነኮሳትን ጨምሮ በርካታ ኢትዮጵያዊያን በፋሽስት ኢጣሊያ እየተለቀሙ በግፍ ተጨፈጨፉ። በዚህ ብቻ ሳያበቃ የአዲስ አበባ ነዋሪዎችን በቤት ውስጥ እያስገቡ ከውጭ በር ቆልፈውባቸው ቤንዚን እያርከፈከፉ በጠራራ ፀሐይ አቃጠሉአቸው።
የአዲስ1879 ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ፡-
ፌስቡክ↠ https://web.facebook.com/addis1879
ቴሌግራም↠ https://t.me/Addis1879
ዩቲዩብ ↠ https://www.youtube.com/@Addis_1879

3️⃣ ከቃጠሎ ያመለጡትን ደግሞ እያሳደዱ በአካፋ ፣ በዶማና በመጥረቢያ እየቆራረጡ የደም ጎርፍ አወረዱ። ባጠቃላይ በሦስት ቀናት የፋሽስቶች ጭፍጨፋ ቁጥራቸው 30,000 ሺህ በላይ የአዲስ አበባና አካባቢው ነዋሪዎች በጅምላ ተጨፈጨፉ። ቦንቡን የወረወሩት አብርሀ ደቦጭ እና ሞገስ አስገዶም ከራስ አበበ አረጋይ ጦር ጋር ተቀላቀሉ ። በኋላም በሱዳን በኩል ከሀገር ለመውጣት ሲሞክሩ ቀድሞ ፎቶዋቸው ተበትኖ ስለነበር በፋሺስት ወታደሮች ተይዘው በስቅላት ተገደሉ።
በስተመጨረሻም አፄ ኃይለሰላሴ በ ሱዳን በኩል ጣልያንን ከእንግሊዝ ሰራዊት ጋር ሆነው ድል አድርገው ወደሀገራቸው ሲገቡ የ አብርሃም እና የሞገስ አስከሬን ተቆፍሮ ወጥቶ አሁን አዲስ አበባ በሚገኘው የ ቅድስት ስላሴ አርበኞች ሃውልት ስር እንዲያርፍ አድርገዋል።ወደ መንበራቸው ከተመለሱ በኋላ የካቲት 12 ለተጨፈጨፉት 30,000 ኢትዮጵያውያን ሰማዕታት በ1934 ዓ.ም የመታሰቢያ ሐውልት በአዲስ አበባ ስድስት ኪሎ ላይ ቆሞላቸዋል።
ለእራሳቸው የእሳትና የገጀራ እራት ሆኖ እኛን ያልተበረዘ ማንነትና ነፃነቷ የተጠበቀ ታላቅ ሀገር አውርሰው በክብር ያኖሩንን የጀግኖች አያቶቻችንን ነብስ ፈጣሪ በገነት ያኑርልን ።

በ3.5 ሚሊዮን ብር የተሰራው
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር የተመሰረተበትን 70ኛ ዓመት በደማቁ እያከበረ ይገኛል፡፡ተወዳጅ ቴያትሮቹንም 70ኛ ዓመቱን በማስመልከት በነጻ ቴያትሮቹን ለተመልካች እያደረሰም ነው፡፡በትክክልም 70ኛ ዓመቱን በደማቁ እያከበሩ ስለሆነ አዘጋጆቹ ከልብ ሊመሰገኑ ይገባል፡፡እንኳንም አደረሳችሁ!
የዛሬው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር በቀደመው አጠራሩ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ቴአትር ቤት ህዳር 03 ቀን 1948 ዓ.ም ተመሰረተ::
የቴያትር ቤቱ ህንፃ ግንባታ ሥራ ለንጉሠ ነገሥቱ 25ኛ ዓመት የዘውድ ኢዩቤልዩ በዓል እንዲደርስ ትእዛዝ በመሰጠቱም በቀሪው አራት ወር ጊዜ ውስጥ ሥራውን ለማጠናቀቅ ከፍተኛ ጥረት ተደርጎበት በ3.5 ሚሊዮን ብር ወጪ ግንባታው ተጠናቀቀ፡፡
ቴያትር ቤቱ ህዳር 3 ቀን 1948 ዓ.ም ሲከፈት ከምሽቱ 2:00 ሰዓት ሲሆን ከፈረንሳይ ሀገር የመጡ አርቲስቶች ትርኢትና ከማዘጋጃ ቤት ወደ አዲሱ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ቴአትር ቤት በተዘዋወሩ አርቲስቶችና ሙዚቀኞች በተሰራውና በቢትወደድ መኮንን እንዳልካቸው በተጻፈው ‹‹ዳዊትና ኦርዮን›› በተሰኘው ተውኔት የመጀመርያው የትርዒት ምዕራፍ ተከፈተ፡፡
በዕለቱ 1264 ተመልካቾች የመክፈቻ ትርኢቱን የተመለከቱ ሲሆን ዕለቱም ለሃገራችን የቴያትር ታሪክ ትልቅ ምዕራፍ የተከፈተበት በመሆኑ ታሪኩ በቀደማቁ ተመዝግቦ እነሆ 70ኛ ዓመቱ እየተከበረ ይገኛል፡፡

Facebook
Log in or sign up to view
See posts, photos and more on Facebook.
#ልደት_ገና_አዲስ_1879
የልደት በዓል የሚከበረው በየዓመቱ ታኅሣሥ 29 ቀን ሲሆን በዘመነ ዮሐንስ ግን (ዘመነ ጰጉሜን ስድስት ስለሆነች) በዓሉ ታኅሣሥ 28 ቀን ይከበራል።የዘንድሮው የልደት በዓል (ገና) ረቡዕ ታኅሣሥ 29 ቀን 2018 ዓ.ም ይከበራል፡፡
በክርስቶስ መወለድ የሚደሰቱ እና የሚያምኑ ሁሉ እንኳን ለብርሃነ ልደቱ አደረሳችሁ፡፡ እንሆ ጨለማው ተገፏል፡፡ ብርሃንም ሆኗል፡፡ ሰው እና መላዕክት በአንድ ላይ አመስገኑ፡፡ የእዳ ደብዳቤም ተቀደደ፡፡ ይህን ያደረገ አምላክ ኢትዮጵያን ይባርክ። ህዝቦቿን ይጠብቅ፡፡
#አዲስ_1879

#ላሊበላ_ዳግማዊት_እየሩሳሌም
በየዓመቱ ታኅሣሥ 29 የልደት (ገና) በዓል በላሊበላ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አማኒያን ዘንድ በድምቀት ይከበራል፡፡ታኅሣሥ 29 ከጌታችን መድኃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ ልደት በተጨማሪ ቅዱስ ላሊበላም የተወለደበት ቀን ነው፡፡ቅዱስ ላሊበላ ታኅሣሥ 29 ቀን 1101 ዓ.ም ተወልዶ፥ ለ40 ዓመታት በንግሥና ቆይቷል፡፡ቅዱስ ላሊበላ በከተማዋ ውስጥ የሚገኙትን ቤተ መቅደሶች ለማነጽ 23 ዓመታትን ፈጅቶበታል።

Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
#ላሊበላ_ዳግማዊት_እየሩሳሌም
የላሊበላ ኪነ ሕንጻ በምድራዊት ኢየሩሳሌም፣ በሰማያዊት ኢየሩሳሌም እና በኖኅ መርከብ ምሳሌ ተደርጎ የተገነባ ነው፡፡ በአስተናነጽ ቅደም ተከተላቸው መሰረትም በምድብ አንድ በምድራዊት ኢየሩሳሌም የሚመሰሉት፥ ቤተ ማርያም፣ ቤተ መድኃኒዓለም፣ ቤተ ጎልጎታ (ቤተ ሚካኤል)፣ ቤተ መስቀል እና ቤተ ደናግል ናቸው፡፡
በምድብ ሁለት የሚገኙት እና በሰማያዊት እየሩሳሌም የሚመሰሉት ደግሞ ቤተ ገብርዔል፣ ቤተ አማኑኤል፣ ቤተ መርቆርዮስ፣ ቤተ አባ ሊባኖስ ሲሆኑ፥ አራቱም በአንድ አቅጣጫ ይገኛሉ።
እንዲሁም በምድብ ሦስት ለብቻው የሚገኘው እና በኖኅ መርከብ ምሳሌ ተደርጎ የታነጸው የቅዱስ ላሊበላ የመጨረሻ ሥራ ቤተ ጊዮርጊስ ነው፡፡ቤተ ጊዮርጊስ የአራቱ አቅጣጫዎች አመላካች ኖሮት በመስቀለኛ ቅርጽ የታነጸ ቤተ መቅደስ ነው፡፡

የጌታችንና ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ በዋዜማው እንዲህ ባማረ መልኩ ተከብሯል፡፡ይህን ዝግጅት ያማረ፤የተዋበ ያደረጉትን በሙሉ ከልብ እናመሰግናለን፡፡
#የኢትየጵያ_ኦርቶዶክስ_ተዋሕዶ_ቤተክርስቲያን
#የአእላፋት_ዝማሬ
#አዲስ_1879
#የኢትየጵያ_ኦርቶዶክስ_ተዋሕዶ_ቤተክርስቲያን
#የአእላፋት_ዝማሬ
#አዲስ_1879
#የገና_ ጨዋታ
የገና ጨዋታ መቼ እንደተጀመረ የሚገልፅ ትክክለኛ መረጃ ባይኖርም ከክርስቶስ ልደት በፊት እረኞች በተለይ በበጋው ወቅት ከብት እየጠበቁ መስክ ላይ ይጫወቱት እንደነበር ይነገራል፡፡
ታድያ ይህ ጨዋታ አዝናኝና ተወዳጅ በመሆኑ ዘር፤ የሀብት ደረጃን፤ የሥራ ኃላፊነትና ሌሎች ልዩነቶች ሳይኖሩት ሁሉንም ሰው ያሳትፋል፡፡ በዚህም “በገና ጨዋታ የለም ሎሌ ጌታ” እየተባለ ይገጠምለታል፡፡ የእየሱስ ክርስቶስ ልደት በዓል የሚከበረው የገና ጨዋታ በሚዘወተርበት ወቅት በመሆኑም በዓሉ ሲከበር የገና ጨዋታም በስፋት ይካሄዳል፡፡

#የገና_ጨዋታ
ፍጥነትን፤ አካላዊ ጥንካሬንና ትንፋሽን የሚጠይቀው የገና ጨዋታ ሳቢና ተወዳጅ እንዲሆን ልክ እንደ እግር ኳስ ጨዋታ ደንቦቹ ይመሳሰላሉ፡፡በመጀመሪያ ለገና ጨዋታ ሁለት ተጋጣሚ ቡድኖች ያስፈልጋሉ፤ ለጨዋታ የሚስፈልገው ሜዳም በደንብ ለጨዋታ ዝግጁ ይሆናል፡፡
ልክ እንደ እግር ኳስ ሜዳ የጎል ጠባቂ፣ የተከላካይ፣ የአጥቂ፣ የማዕዘን መምቻ በኖራ ይሰመራል፡፡ የሜዳ ስፋቱ ደግሞ ርዝመቱ 90 ሜትር ፤ ጎኑ 50 ሜትር የሆነ ሜዳ ያስፈልጋል፡፡
በዚህ ሜዳ ውስጥ ለመጫወት ሁለቱ ተጋጣሚ ቡድኖች 15 ተጫዋቾችን ያቀርባሉ፤ አስሩ ሜዳ ውስጥ ገብተው የሚጫወቱ ሲሆን አምስቱ በተቀያሪ ወንበር ይቀመጣሉ፡፡ ጨዋታውን የሚመራ የመሀል ዳኛ፣ ዳኛውን የሚያግዙ መስመር ዳኞች እንዲሁም ተቀያሪ ተጫዋቾችን የሚቀይሩ ዳኞችም የገና ጨዋታ ተሳታፊዎች ናቸው፡፡

የገና ጨዋታን ለመጫወት ሩር እየተባለች የምትጠራ ድቡልቡል መጫወቻ ያስፈልጋል፡፡ ክብደቷ እስከ 5 መቶ ግራም የሚመዝን ከእንጨት፤ ከጠፍር አሁን አሁን ደግሞ ከፕላስቲክ ይዘጋጃል፡፡ ድቡልቡል መጫወቻ ወይም ሩሩን ለመምታትና ወደ ተቃራኒ ቡድን ግብ ለማስገባት ልክ እንደ ማንኪያ ቅርፅ ያለው ከ1ሜትር የማይበልጥ ቁመት ያለው የገና ዱላ ያስፈልጋል፡፡ የገና ዱላው ለሁሉም ተጨዋቾች በእኩል ቁመት የተዘጋጀ ሆኖ ይታደላል፡፡
ልዩነት አለመኖሩን ዳኛው የማረጋገጥ ኃላፊነት አለበት፡፡ ጨዋታው ሲጀመር ሁሉም ተጫዋቾች ተነፋነፍ የሚባለውን ባህላዊ ልብሳቸውን ለብሰው ቦታ ቦታቸውን ይይዛሉ አጥቂው ከአጥቂ፤ ተከላካይ እንዲሁ በቦታው፣ በረኛውም በተጠንቀቅ በቦታው ይሰየማል፡፡
ጨዋታውን የሚያስጀምሩት ዳኛ ሶስት ጊዜ “እዚህ እሩር፤ እዛ ገና ” ካለ በኋላ ጨዋታው ይጀመራል፡፡ በጨዋታው ሕግ መሰረት ሩሯን በእግርና በእጅ መንካት ነጥብ ያስቀንሳል፡፡ ለ30 ደቂቃ በመጀመሪያው ምዕራፍ ይጫወታሉ፡፡ ለ10 ደቂቃ ረፍት ከወሰዱ በኋላ የጨዋታ ሜዳ ተቀያይረው ሁለተኛ አጋማሽ ጨዋታቸውን ያካሂዳሉ፡፡
ጨዋታው ለዋንጫ ወይም ለደረጃ ከሆነ ቡድኖቹ ካልተሸናነፉ ተጨማሪ ደቂቃ እንዲጫወቱ ይደረጋል፡፡ በዚህም ካልተሸናነፉ የቅጣት ምት እየተሰጣቸው እስኪሸናነፉ ድረስ ይጫወታሉ፡፡
በገና ጨዋታ፤ አይቆጡም ጌታ

‹‹የ1954 ዓ.ም ወይዘሪት ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ››
በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ኃይለ ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ቅጥር ግቢ ውስጥ በተከበረው የኮሌጅ ቀን በዓል ወይዘሪት አስቴር ግብረ ማርያም የ1954 ዓ.ም ‹‹ወይዘሪት ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ›› ተብላ ተሰየማለች፡፡በኮሌጅ ውስጥ የኢኮኖሚክስ ሁለተኛ ዓመት ተማሪ የሆነችው ወይዘሪት አስቴር ኒው ዮርክ ትምህርቷን እንደምትቀጥል አስታውቃለች፡፡ ወይዘሪት አስቴር የአስመራ ተወላጅ ነች፡፡