🇸🇦أبو مُصْعَبُ أنـــــــور [ከጥበባት አወድ]🇸🇦Abu-Musaa'b Anwar
207 subscribers
315 photos
51 videos
2 files
570 links
በ አላህ ፍቃድ ትክክለኛው ኢስላማዊ አስተምህሮ ከ ቁርኣን፣ከሐዲሥ በሰለፎች ግንዛቤ ይቀርብበታል ።በተጨማሪም ከነቢያዊ፣ከሰሐቦች፣ከታቢዒዮችና ከኡለሞች ጥበባዊ ምክሮች ይቀርብበታል።
Download Telegram
ሀሰን አል-በስሪ(ረሒመሁላህ) እንዲህ ብለዋል:"አላህ የወሰነልህን ነገር ውደድ፤ ምክንያቱም እርሱ ላንተ የመረጠልህ ነገር አንተ ለራስህ ከመረጥከው ይበልጣል።"
📚 (አር-ሪዳ አን አላህ ቢ ቀዳኢህ_85)
https://t.me/Abu_MusaabAnwar
ጥበባዊ ምክር ~ ከፍልስጤሙ ሊቅ
🍂🌿🍂🌿🍂🌿🍂🌿🍂🌿🍂

🔹ኢማም ኢብኑ ቁዳማ አል-መቅዲሲ (ረሒመሁላህ) እንዲህ ብለዋል:-
واعلم رحمك الله أن هذه الدنيا سوق متجر الأبرار، وحلَبة السباق بين الكِرام الأخيار، ومزرعُ التقوى ليوم القرار، ومحلُّ تحصيل الزاد للسفر الذي ليس كالأسفار، فبادِر رحمك الله قبل فوات إمكان البِدار، واغتنم أنفاسك العظيمة المقدار، واذرِف من دموعك على ما سلف من تفريطك، فإن القطرة من الدموع من خشية الله تعالى تُطفئ البحور من النار.
•• وتيقَّظ في ساعات الأسحار عند نزول الجبار، وأحضِر بقلبك قول العزيز الغفَّار: «هل من سائل فأُعطيه؟ هل من داعٍ فأستجيب له؟ هل من مُستغفر فأغفِر له؟».

📚[ رسالة بعنوان: وصية الإمام ابن قدامة المقدسي رحمه الله].


"አላህ ይዘንልህና እወቅ፤ ይህች ዓለም የደጋግ ሰዎች የንግድ አውድማ፣
የክቡራንና ምርጥ ሰዎች የውድድር ሜዳ፣
ለዘላለማዊው ዓለም (የቂያማ ቀን) የተቅዋ ዘር የሚዘራባት እርሻ፣
እና እንደማንኛውም ጉዞ ላልሆነው (ለአኺራ) ጉዞ ስንቅ የሚሰበሰብባት ቦታ ናት።
ስለዚህ አላህ ይዘንልህና፤ የመሽቀዳደም ዕድሉ ሳያመልጥህ ፈጥነህ ተንቀሳቀስ፤
እጅግ ውድ የሆኑትን የትንፋሽህን ሰከንዶች በአግባቡ ተጠቀም። ላለፈው ግድየለሽነትህም እምባህን አፍስስ፤
አላህን በመፍራት የምትፈስ አንዲት ጠብታ እምባ የጀሃነምን የእሳት ባህሮች ታጠፋለችና።
ጌታህ (ወደ ቅርቢቱ ሰማይ) በሚወርድበት በሌሊቱ መጨረሻ ሰዓታት (በሰሐር) ንቁ ሁን።
የዚያን አሸናፊና መሀሪ የሆነውን ጌታ ቃል በልብህ አስብ፦ 'የሚጠይቀኝ አለን? እሰጠዋለሁ፤ የሚለምነኝ አለን? እቀበለዋለሁ፤ ምሕረት የሚጠይቀኝስ አለን? እምረዋለሁ' የሚለውን።"

📚(አል-ወሲያ_12-13)
https://t.me/Abu_MusaabAnwar
2
ኢማም አህመድ(ረሒመሁላህ) ለልጃቸው አብዱላህ ከለገሷቸው ምክሮች መካከል

قال عبدُ اللَّه: "أوْصِنِي يا أبَتِ. فقال: يا بُنيَّ انْوِ الخَيْرَ؛ فَإنّكَ لا تَزالُ بِخَيْرٍ ما نَوَيْتَ الخَيرَ"


🔹አብዱላህ(ረሒመሁላህ) እንዲህ ይላሉ፦ "አባቴ ሆይ! ምከረኝ አልኳቸው። እሳቸውም፦ 'ልጄ ሆይ! መልካምን ነገር አስብ (ነይይ)፤ መልካምን እስካሰብክ ድረስ ሁልጊዜም በመልካም ላይ ትሆናለህና' አሉት።"

📚 (መናቂብ ኢማም አህመድ ገጽ 274)
https://t.me/Abu_MusaabAnwar
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
🎙ከኢራቅ~በሽይኽ ሰዓድ አል-ናይፍ (ሀፊዘሁሏህ)
"የተውሂድ እና የሱና ጥሪ አድራጊዎችን (ዳዒዎችን) በሐሰት እና በፈጠራ ለሚወነጅሉ ሰዎች የተሰጠ ምላሽ"

https://t.me/Abu_MusaabAnwar
🔹ዑመር ኢብኑ ዐብዱልዐዚዝ (ረሒመሁላህ )እንዲህ ብለዋል፦ "ፍትህ የሀገር ግንብ ነው፤ ሀገር በፍትህ ትጠነክራለች እንጂ በግንብና በምሽጎች ብቻ አትቆምም።"
[📚ሒልየቱል አውሊያዓ 5/253]
https://t.me/Abu_MusaabAnwar
ሸይኽ ሙቅቢል ቢን ሃዲ አል-ዋዲዒ (ረሒመሁላህ) እንዲህ ብለዋል:-

ከቢዳዓ ሰዎች ጋር መተባበር ዳዕዋውን እንዲቀልጥ(እንዲሟሟ) የሚያደርግ ተግባር ነው። ... ስለዚህ ከእያንዳንዱ የቢዳዓ ሰው እንድትርቁ (እንድትለዩ) እንመክራለን።"
📚 (ሪሕላት ደዕዊያህ_121)
https://t.me/Abu_MusaabAnwar
🥰1
ሰዎችን መበደል -ነገ በአኼራ ድሃ ያደርጋል!


📚ሱፍያን አል-ሰውሪ(ረሒመሁላህ) እንዲህ ብለዋል፦

إن لقيت الله تعالى بسبعين ذنباً فيما بينك وبين الله تعالى أهون عليك من أن تلقاه بذنب واحد بينك وبين العباد"

"በአንተና በአላህ መካከል ባለ (አላህን ብቻ በሚመለከት) ሰባ ወንጀል አላህን ብታገኘው፤ በአንተና በባሮቹ (በሰዎች) መካከል ባለ በአንዲት ወንጀል ከመገናኘት ይሻልሃል (ቀላል ይሆንልሃል)።"

📚[ተንቢሁል ጋፊሊን  1/380]
https://t.me/Abu_MusaabAnwar
🔹ሸይኽ ሙቅቢል ቢን ሃዲ አል-ዋዲዒ (ረሒመሁላህ) እንዲህ ብለዋል:-

"السكوت عن أهل البدع يعتبر خيانة للإسلام."
"ስለ ቢዳዓ ሰዎች ዝም ማለት እስልምናን እንደ መክዳት ይቆጠራል።"
📚 ቱሕፈቱል ሙጂብ (ገጽ 155)
https://t.me/Abu_MusaabAnwar
ባገኘነው አጋጣሚ ሁሉ እውቀትን እናሰራጭ!

🌿🍂🌿🍂🌿🍂🌿🍂🌿🍂🌿
✍️قال الشيخ محمد بن صالح العثيمين رحمه الله:

"ولقد أوصاني رجل من عامة الناس فقال لي : يابني احرص على نشر العلم حتى في المجالس كمجالس القهوة، أوالغداء، أوما أشبه ذلك
ولاتترك مجلسا واحدا إلا وأهديت إلى الجالسين ولومسألة واحدة، أوصاني بذلك وأنا أوصيكم بذلك؛ لأنها وصية نافعة”


🔹ሸይኽ ሙሐመድ ቢን ሳሊህ አል-ዑሰይሚን(ረሒመሁላህ) እንዲህ ብለዋል፦
"አንድ ተራ ሰው 'ልጄ ሆይ! በቡና፣ በምሳ ወይም መሰል ፕሮግራሞች ላይ እንኳን ሳይቀር እውቀትን ለማሰራጨት ጣር። በአንድም መጅሊስ (ክፍለ ጊዜ) ላይ እንኳን ቢያንስ አንዲትን ጉዳይ ሳታስተምር እንዳታልፍ' ብሎ መከረኝ። እኔም ይህችን ጠቃሚ ምክር ለእናንተ እመክራለሁ።"

📚[ التعليق على صحيح مسلم/حديث152،1147،1154]
https://t.me/Abu_MusaabAnwar
🔹ታላቁ ሰሃቢ ዐብዱላህ ኢብኑ መስዑድ (رضي ﷲ عنه) እንዲህ ብለዋል፡- “ጀመዓ (ህብረት) ማለት እውነትን (ሐቅን) የገጠመ ነው፤ አንተ ብቻህን ብትሆን እንኳ።”
📚(ሸርህ ኡሱል ኢዕቲቃድ አህሊሱናህ ወልጀመዓ ሊ አል-ላለካኢ-1/121)
https://t.me/Abu_MusaabAnwar
በእውነት ላይ ብቻ መሰባሰብ!

🔹ሸይኽ አህመድ ቢን ያህያ አል-ነጅሚ (አላህ ይዘንላቸው) እንዲህ ብለዋል:- «የቢድዓ ባለቤቶችን መቃወም ኡማውን (ህዝበ ሙስሊሙን) መከፋፈልና መበተን ነው ብሎ የሚሞግት ሰው እርሱ ራሱ ጠማማ ነው፤ ምክንያቱም እርሱ የኡማውን ስብስብ በባጢል (በሀሰት) ላይ እንዲሆን ይፈልጋልና።»
📚 ኢርሻድ አል-ሳሪ (ገጽ 64)
https://t.me/Abu_MusaabAnwar
📜 የዕፎይታ ተስፋ

ትካዜው ቢጠናም ጭንቁ ቢበረታም፣
መክራው ቢበዛም መቋጫው አይቀርም፣
ጨለማው ቢነግስም ንጋቱ አይቀርም፣
ከመከራው ጀርባ ፋታ አለህና
ነፍስህን አርጋጋት በጎውን አስብና
ከአንዱ ችግር ጋር ሁለት ምቾት አለ
የአላህ ቃል ነው ተስፋን ያበሰረ
መጨረሻው ያምራል ይሆናል ጤና
ተስፋን የሰነቀ መጨረሻው ያምራል
የዕፎይታ ቀን መጥቶ ልብህን ይረካል።

አቡ ሙስዐብ አንዋር
22/4/2026
https://t.me/Abu_MusaabAnwar
👍2
قال العلامة ابن القيم رحمه الله:- ما سُلبت النّعَم إلا بترك تقوى الله والإساءة إلى الناس

🔹ኢማም ኢብኑል ቀዪም (ረሂመሁሏህ) እንዲህ ብለዋል:-“ጸጋዎች አይገፈፉም፤ የአላህን ፍራቻ በመተውና በሰዎች ላይ ክፋትን በመፈጸም እንጂ።”
📚[አህካም አህሊ-ዚማ 1/21]
https://t.me/Abu_MusaabAnwar
ወሳኝ ምክር ~ከመዲናው ቃዲ!


قال أبو حازم سلمة بن دينار رحمه الله:- كل عمل تكره الموت من أجله فاتركه، ثم لا يضرك متى مت .
🔹አቡ ሀዚም ሰለማ ቢን ዲናር(ረሒመሁላህ) እንዲህ ብለዋል፦
"ሞትን በሱ ምክንያት የምትጠላው ማንኛውም ስራ ካለ ተወው፤ ከዚያም በፈለግከው ጊዜ ብትሞት ምንም አይጎዳህም።"
📚(አል-ሙሳናፍ 7/194)
https://t.me/Abu_MusaabAnwar
🔹ሸይኽ ሙቅቢል ቢን ሃዲ አል-ዋዲዒ (ረሒመሁላህ) እንዲህ ብለዋል:-
الهجر بمنزلة الدواء، فإذا زاد على مقداره ربما أفسد، وإذا نقص عن مقداره ربما لم ينفع."
"ሐጅር (ማግለል) እንደ መድኃኒት ነው፤ መጠኑ ካለፈ ሊያበላሽ ይችላል፣ ከመጠኑ ካነሰ ደግሞ ላይጠቅም ይችላል።"
📚 ቱሕፈቱል ሙጂብ (ገጽ 163 )
https://t.me/Abu_MusaabAnwar
قال الله تعالى:-‏{ لِّكَیۡلَا تَأۡسَوۡا۟ عَلَىٰ مَا فَاتَكُمۡ وَلَا تَفۡرَحُوا۟ بِمَاۤ ءَاتَاكُمۡۗ }
{(ይህ ማሳወቃችን) ባመለጣችሁ ጸጋ ላይ እንዳታዝኑ አላህም በሰጣችሁ ነገር (በትዕቢት) እንዳትደሰቱ ነው፡፡ }
ይህ አንቀጽ ሲያብራሩ ታላቁ ታቢዕይ እና ሊቅ ኢክሪማህ መውላ ኢብኑ አባስ(ረሒመሁላህ) እንዲህ ብለዋል፦
( ليس أحد إلا وهو يفرح ويحزن،ولكن اجعلوا الفرح شكراً والحزن صبراً..)

"ሁሉም ሰው ይደሰታል፣ ያዝናልም፤ ነገር ግን ደስታህን ለጌታህ ሹክር፣ ሃዘንህን ደግሞ ለሶብር ተጠቀምበት።"

📚(ተፍሲር ኢብኑ ከሲር 8/27)
https://t.me/Abu_MusaabAnwar
1772048860049.mp4
80.1 MB
ወሳኝ አጭር ምክር ስለ ታላቁ ኢማም የመጨረሻ የዱንያ ስንብት ያወሱበት!

ሸይኽ ሙኒር አሰዕዲ አል-ዓደኒ(ሀፊዘሁሏህ)

عن معاذ رضي الله عنه أن النبي ﷺ أنه قال: "من كان آخر كلامه من الدنيا لا إله إلا الله دخل الجنة"
“ከዚህች ምድራዊ ሒዎት (ሲሰናበት) የመጨረሻ ቃሉ “ላኢላሃ ኢልለሏህ” የሆነለት (ሰው) ጀነት ገባ፡፡”
📚 (አቡ ዳውድ: 3116, አህመድ: 22127)
አላህ ሁላችንም ፍፆሜያችን በ“ላኢላሃ ኢልለሏህ” ያድርግልን!
https://t.me/Abu_MusaabAnwar
ታራኪ በወፍ በረር_በጥቂቱ ስልታላቁ ኢማም

🍂🌿🍂🌿🍂🌿🍂🌿🍂🌿🍂🌿

1⃣አቡ ዙረዓ አል-ራዚ (ረሒመሁላህ) በ3ኛው ክፍለ ዘመን (ሂጅራ) የነበሩ ታላቅ የሐዲስ ምሁር ናቸው።
*ስማቸው ዑበይዱላህ ቢን ዓብዱልከሪም ይባላል። በኢራን ሬይ ከተማ የተወለዱ ሲሆን፣ በሐዲስ ዘገባዎች ትክክለኛነትን በመለየት ረገድ ወደር የማይገኝለቸው ሊቅ ነበሩ።
*  በአንድ ወቅት "700,000 ሐዲሶችን በቃሌ አውቃለሁ" ማለታቸው በታሪክ ይጠቀሳል። ከታዋቂው ሊቅ ኢማም ሙስሊም ጋር የቅርብ ጓደኛ የነበሩ ሲሆን፣ ኢማም ሙስሊም "ሶሂህ ሙስሊም" የተባለውን መጽሐፋቸውን ሲያዘጋጁ ለአቡ ዙረዓ አቅርበውለት እርሱ 'ችግር አለበት' ያላቸውን ሐዲሶች በሙሉ ውድቅ አድርገውታል።

ታላቁ የሐዲስ ሊቅ  አቡ ዙረዓ አል-ራዚ(ረሒመሁላህ)ትውስታቸው (ሒፍዝ)
አዝ-ዘሃቢ የአቡ ዙረዓን ትውስታ ሲገልጹ እንዲህ ብለዋል፦

"አቡ ዙረዓ እንዲህ ብሏል፦ 'አንድም ቀን አንድን ነገር አንብቤ አልረሳሁትም።' ደግሞም 'በቃሌ የያዝኳቸው 700,000 (ሰባት መቶ ሺህ) ሐዲሶች አሉ፤ ከእነዚህም ውስጥ 140,000 የሚሆኑት በተፍሲር (ቁርአን ትርጓሜ) ላይ ያሉ ናቸው' ብሏል።"

2. የሊቃውንት ምስክርነት
በዚሁ ጥራዝ ላይ የታላቁ ኢማም አሕመድ ቢን ሐንበል ንግግር እንዲህ ተጠቅሷል፦

"ኢማም አሕመድ እንዲህ አሉ፦ 'ከአቡ ዙረዓ አል-ራዚ የበለጠ ሐዲስን በቃሉ የያዘ (ሀፊዝ) ከምስራቅ እስከ ምዕራብ አላየሁም።'"

3. የመጨረሻው አሟሟታቸው:-
አዝ-ዘሃቢ የአቡ ዙረዓን ሞት በሚመለከት አቡ ጃዕፈር የተባለውን ዘጋቢ ጠቅሰው እንዲህ ጽፈዋል፦

"አቡ ዙረዓ በሞት ጣር (ሰከራት) ላይ እያለ አቡ ሐቲም፣ መሐመድ ቢን ሙስሊም እና ሌሎችም እርሱ ዘንድ መጡ። እነዚህ ታላላቅ ሰዎች ግን ከፊታቸው ላለው ታላቅ ሊቅ ተልቂን (ላ ኢላሃ ኢልለላህን ማስባል) ፈለጉና 'በል' ለማለት አፈሩ።  ስለዚህ በሀዲስ ሰንሰለት  ማስታወስ ጀመሩ።መሐመድ ቢን ሙስሊም ሀዲሱን መዘርዘር ጀመረ፡ አቡ ዓሲም ነቢል፣ እሱም ከአብዱልሐሚድ ቢን ጃዕፈር፣ እሱም ከሷሊህ...' እያለ ሲቀጥሉ ክብራቸውን አስታወሱና ድንገት ተንተባተቡ፣ ሀዲሱን መጨረስ አቃተቸው።
ከዚያም አቡ ሐቲም አል-ራዚ ቀጠሉና የሀዲሱን ሰንስለት እንዲህ እያሉ ጀመሩ
ሙሐመድ ኢብን በሻር  ከአቡ ዓሲም ነቢል፣ እሱም ከአብዱልሐሚድ ቢን ጃዕፈር፣ እሱም ከሷሊህ...' መጨረስ አቃተቸው ዝም አሉ
በዚህ ጊዜ አቡ ዙረዓ በዚያ በሞት ጣር ላይ ሆነው አይናቸውን ገለጡና ሰነዱን እንዲህ ብለው ጀመሩ፡-
ሙሐመድ ኢብን በሻር ከአቡ ዓሲም ነቢል፣ እሱም ከአብዱልሐሚድ ቢን ጃዕፈር፣ እሱም ከሷሊህ ቢን አቢ አሪባህ፣ እሱም ከከሲር ቢን ሙራ፣ እሱም ከሙዓዝ ቢን ጀበል (ረዲየአላሁ አንሁ) እንደተረከው፡ የአላህ መልዕክተኛ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦ የመጨረሻ ንግግሩ 'ላ ኢላሃ ኢልለላህ'(لا إله إلا الله) የሆነ ሰው...' እዚህ ጋር ሲደርስ ነፍሱ ወጣች (ንግግሩን ሳይጨርሱት ሞቱ)።


ሙሉውን ይህ ነው ሐዲሱ:-"{عن معاذ رضي الله عنه أن النبي ﷺ أنه قال: "من كان آخر كلامه من الدنيا لا إله إلا الله دخل الجنة"
“ከዚህች ምድራዊ ሒዎት (ሲሰናበት) የመጨረሻ ቃሉ “ላኢላሃ ኢልለሏህ” የሆነለት (ሰው) ጀነት ገባ፡፡”
📚 (አቡ ዳውድ: 3116, አህመድ: 22127)}

አዝ-ዘሃቢ ይህን ታሪክ ካወሱ በኋላ "ይህ ታላቅ ክብርና የአላህ ስጦታ ነው" በማለት ያደንቃሉ።
📚ኢማም አዝ-ዝሃቢ "ሲየር አዕላም አን-ኑበላእ" በተሰኘው መጽሐፋቸው (ጥራዝ 13፣ ከገጽ 65-85 ባለው ክፍል)
ሱብሃን አላህ! ይህ ታሪክ የአላህን ቃል በተግባር የታየበት ማሳያ ነው፡ '
(  يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا اتَّقُوا اللَّهَ حَقَّ تُقَاتِهِ وَلَا تَمُوتُنَّ إِلَّا وَأَنتُم مُّسْلِمُونَ) እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን ተገቢውን መጠንቀቅ ተጠንቀቁት፡፡ እናንተም ሙስሊሞች ኾናችሁ እንጅ አትሙቱ፡፡ (አል-ዒምራን 102)።
ኡለሞች እንደሚሉት፦ 'አንድ ሰው እንዴት ሙስሊም ሆኖ ይሞታል? ቢባል፣ በእስልምና ላይ በመኖር ነው' ይላሉ። በሕይወትህ 'ላ ኢላሃ ኢለላህ' የሚለውን ቃል ስታስተምር፣ ስትተገብርና ስትኖርበት ከቆየህ፣ የሞት ሰዓት ሲደርስ ቃሉ በአንደበትህ ላይ በቀላሉ ይመላለሳል። አላህ በአቡ ዙርአ እና በጓደኞቻቸው ላይ እዝነቱን ያውርድላቸው፤ እኛንም በዚህ ቃል(لا إله إلا الله) ላይ ጽኑዎች ያድርገን።"
https://t.me/Abu_MusaabAnwar