Abergelle Woreda Prosperity Party/AWPP/
138 subscribers
1.39K photos
2 videos
257 links
Political Party
Download Telegram
የአበርገሌ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ፅ/ቤት የኢንስፔክሽንና ስነ ምግባር ኮሚሺን "የተሻሻለው የመተዳደሪያ ደንብ እና የሌሎች መመሪያዎች አዳዲስ ድንጋጌዎች" ዙሪያ የተዘጋጀ የአቅም ግንባታ ስልጠና ተሰጠ!
°°°
የአበርገሌ ወረዳ ተቀዳሚ ዋና አስተዳዳሪ የሆኑት አቶ ነይኑ በላይ መመሪያዎችን በአግባቡ ተገንዝቦ ወደ ተግባር መግባት ስልጠናው የማይተካ ሚና እንዳለው ገልፀው የስልጠናው ተሳታፊዎች በንቃት እና በጥብቅ ዲሲፕሊን ተከታትለው ወደ ተግባር እንዲተገብሩ የተሻሻለው የመተዳደሪያ ደንብ እና የሌሎች መመሪያዎች አዳዲስ ድንጋጌዎች ዙሪያ የተዘጋጀ የስልጠና ላይ በመገኘት በመክፈቻ ንግግራቸው አሳስበዋል።

በአቅም ግንባታ ስልጠናው የወረዳው ጠቅላላ አመራር፣ የመንግስት ሰራተኛ አባላት፣ የኮሚሺን አመራር፣ የብልፅግና ህብረት እና የብልፅግና ቤተሰብ ተሳትፏል።

ወ/ሪት ትእግስት ተፈሪ ባቀረቡት የስልጠና ሰነድ መሰረት ማሻሻያ የተደረገባቸው መመሪያዎች የብልፅግና ፓርቲ የአደረጃጀት እና አሰራር መመሪያ፣ የፓርቲው የኢንስፔክሽን እና ስነ ምግባር አደረጃጀት አሰራር መመሪያ፣ የብልፅግና ፓርቲ ዲሲፕሊን መመሪያዎች፣ የብልፅግና ፓርቲ የቅሬታ እና አቤቱታ አፈታት መመሪያ፣ የአባላት ምልመላ ግንባታ እና ስንብት መመሪያ፣ እንዲሁም የብልፅግና የአመራሮችና የአባላት ምዘና መመሪያ የሚሉት በስፋት ቀርበው ሰፊ ማብራሪያ እና ትንታኔ የተሰጠ ሲሆን በተጨማሪም የብልፅግና ፓርቲ የአደረጃጀትና የአሰራር መመሪያ ዙሪያ የተዘጋጀ የስልጠና ሰነድ በአበርገሌ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ፅ/ቤት አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ በሆኑት ወ/ሮ አበባ አያሌው ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተደርጓል።

በኢንስፔክሽንና ቁጥጥር መመሪያ፣ የኮሚሽን የአሠራር ሥርዓት፣ የውስጠ ፓርቲ ቁጥጥር ምንነትና እሳቤ፣ የፓርቲው መተዳደሪያ ህግና የተሻሻሉ ደንቦች በስልጠናው በዝርዝር ቀርበው ውይይት ተደርጎበታል።

በአበርገሌ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት የኢንስፔክሽን እና ስነ ምግባር ኮሚሽን ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ሃብቱ ካህሳይ እንደተናገሩት ብልጽግና ፓርቲ በአደረጃጀትና በሰው ኃይል ጠንካራ መሆኑን በማንሳት በሁሉም አሰራሮች ህጋዊነትን መከተል እንደሚገባ አንስተዋል።

በሰው ኃይል፣ በአደረጃጀትና በፋይናንስ አቅሙ ግዙፍ የሆነው ፓርቲ ጠንካራ ይሆን ዘንድ በኢንስፔክሽንና ስነ ምግባር ኮሚሽን ሊታገዝ እንደሚያስፈልግም አቶ ሃብቱ ካህሳይ ጠቁመዋል።

የአበርገሌ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት የኢንስፔክሽንና ስነ-ምግባር ኮሚሽን ኃላፊ የሆኑት አቶ ብርሃኑ ሙሉጌታ እንደገለፁት በአሰራሮች ላይ የሚስተዋሉ ክፍተቶችንና ቸግሮችን ለይቶ በማውጣት የመፍትሄ አቅጣጫ እንዲሰጣቸው ለማድረግ ለፓርቲው የማሳወቅ ስራ የሚሰራ እንደሆነ አስረድተው የፓርቲው መመሪያዎች በአግባቡ መተግበራቸውን በጥብቅ ክትትል የሚድረግ መሆኑን አስረድተዋል።

ስልጠናው መመሪያዎቹን በማስመልከት የጠለቀ ዕውቀት እና ግንዛቤ እንዲኖረን አስችሎናል ያሉት የስልጠናው ተሳታፊ አመራሮችና አባላት ለፓርቲው እና የኢንስፔክሽን እና ስነ ምግባር ኮሚሽን ተልዕኮ መሳካት የበኩላቸውን ኃላፊነት እንደሚወጡ አረጋግጠዋል ።

ጠንካራ ኢንስፔክሽን ለጠንካራ ፓርቲ!

ለወቅታዊ ፣ ትክክለኛና አዳዲስ መረጃዎች የፓርቲያችንን የማህበራዊ ገፆች ይወዳጁ።
°°°
Twitter;https://twitter.com/AbergelleW_PP
Telegram;https://t.me/AWPP_DSM
Youtube;https://www.youtube.com/@abergelleworedaprosperityparty
Facebook;https://www.facebook.com/100055961503780/posts/pfbid0Vhb9YhQon7642KPnL9bu76gWGUCRQWqXr8Sh33NsPnN8cQf97myvkikFnicxfdHMl/?app=fb
"የጥፋት እጆችና መዘዞች" በሚል መሪ ቃል በዋግ ኽምራ ብ/ሰብ አስ/ር በአበርገሌ ወረዳ ከመንግሥት ሰራተኞች ጋር የሰላም ውይይት እየተካሄደ ነው።
   *   *   *
"የጥፋት እጆችና መዘዞች" በሚል መሪ ቃል በፅንፈኛ ኃይል ያደረሰውን ዘግናኝ ግፍ በተመለከተ ዘጋቢ ፊልም የቀረበ ሲሆን ፅንፈኛው የሚያደረሰው ግድያ፣ ዘረፋ፣ እገታ፣ ሰቆቃ፣ በሕዝቡ ላይ ታሪክ ይቅር የማይለውና ተፈፅሞ የማይታወቅ ዘግናኝ ግፍ መፈፀሙን ማህበረሰቡ ተረድቶ ፅንፈኛውን አምርሮ መታገል እንደሚገባ በመድረኩ ተገልፀዋል።

በክልላችን በተፈጠረው ግጭት በልማትና በመልካም አስተዳደር ዘርፍ እየደረሰ ያለውን የጉዳት ደረጃ በመገንዘብ መንግስት የሚወስደውን የህግ ማስከበር ስራ እንዲያግዝ ያስችላል ብለዋል፡፡

መንግስት በግጭት ውስጥ ለሚገኙ ወገኖች የሰላም ጥሪ እድል እየሰጠ መሆኑን የገለፁት የአበርገሌ ወረዳ ተቀዳሚ ዋና አስተዳዳሪ የሆኑት አቶ ነይኑ በላይ ህብረተሰቡ ለሰላም ጥሪው የበኩሉን ድርሻ በመወጣት ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በክልላችን የተፈጠረውን የሰላም ችግር ለመፍታት መስራት ይገባዋል ያሉት አስተዳዳሪው ህብረተሰቡ በባለቤትነት ሰላምን ለማረጋገጥ በቅድሚያ ግጭትና ጦርነትን ማውገዝ ይገባዋል ብለዋል፡፡

የአበርገሌ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ብርሃኑ ሙሉጌታ ደግሞ በክልላችን ከአንድ ዓመት በላይ በፅንፈኛው ሃይል  ግጭት በመበራከቱ የተነሳ ከፍተኛ ተጎጅው የክልሉ ህዝብ ሲሆን ይህም በሁሉም የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎች ላይም ጉዳት መድረሱን ተናግረዋል፡፡ 

መንግስት ለዘላቂ ሰላም ያለውን ቁርጠኝነት ህብረተሰቡም እንዲደግፈው የውይይት መድረኮቹ አስፈላጊ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

በየደረጃው ከሚገኙ የህብረተሰብ  ክፍሎች ጋር በሁሉም የአስተዳደር እርከኖች ውይይቱ በተመሳሳይ ርዕሰ ጉዳይ እንደሚካሄድ ተናግረዋል፡፡

የውይይት መድረኩ ለሰላም ይበልጥ እንድንተጋና ለሰላም ልዩ ትኩረት ሰጥተን እንድንስራ አነሳሰቶናል ሲሉ የመድረኩ ተሳታፊዎች አስተያታቸውን ሰጥተዋል፡፡ 

ለወቅታዊ ፣ ትክክለኛና አዳዲስ መረጃዎች የፓርቲያችንን የማህበራዊ ገፆች ይወዳጁ።
°°°
Twitter;https://twitter.com/AbergelleW_PP
Telegram;https://t.me/AWPP_DSM
Youtube;https://www.youtube.com/@abergelleworedaprosperityparty
Facebook;https://www.facebook.com/100055961503780/posts/931701855371856/?app=fb
በንየረ-አቚ ከተማ የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍል በተገኙበት የውይይት መድረክ ጀመረ

በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር አበርገሌ ወረዳ በንየረ-አቚ ከተማ የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍል በተገኙበት የውይይት መድረክ መካሄድ ጀመረ።

በወረዳው ብሎም በአከባቢው ያለውን የሰላም፣የልማትና እና ሁለንተናዊ ተግባራት ዙርያ ለመምከር የክልልና የብሄረሰብ አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።

በውይይት መድረኩ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉት የአበርገሌ ወረዳ ተቀዳሚ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ነይኑ በላይ የወረዳው ህዝብ ሰላምና ልማት ፈላጊ በመሆኑ መንግስት ለዚህ ተግባር የተለያዩ መድረኮችን እየፈጠረ ከህዝቡ ጋር በቅንጅት እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

ወረዳው በሰሜኑ ጦርነት ምክንያት የመሰረተ ልማት ውድመት የደረሰበት ነው ያሉት የብሔረሰቡ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሀይሉ ግርማይ በወረዳው የሰላምና ፀጥታ፣የመሰረተ ልማት ዝርጋታና የህዝብ ግንኙነት ስራዎቻችን ላይ ውይይት ይደረጋል ብለዋል።

ለወቅታዊ ፣ ትክክለኛና አዳዲስ መረጃዎች የፓርቲያችንን የማህበራዊ ገፆች ይወዳጁ።
°°°
Twitter;https://twitter.com/AbergelleW_PP
Telegram;https://t.me/AWPP_DSM
Youtube;https://www.youtube.com/@abergelleworedaprosperityparty
Facebook;https://www.facebook.com/100055961503780/posts/pfbid0Vhb9YhQon7642KPnL9bu76gWGUCRQWqXr8Sh33NsPnN8cQf97myvkikFnicxfdHMl/?app=fb
የመሰረተ ልማት ችግሮችን ለመፍታትና የሕዝቡን ጥያቄ ለመመለስ መስራት ይገባል – አቶ ሃይሉ ግርማይ

የመሰረተ ልማት ችግሮችን ደረጃ በደረጃ ለመፍታት እና የሕዝቡን ጥያቄ ለመመለስ በትኩረት መስራት ይገባል ሲሉ የዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር አስተዳዳሪ አቶ ሀይሉ ግርማይ ገለጹ፡፡

አቶ ሀይሉ ግርማይ እንደገለፁት በህዝቡ የተነሱ የአንቡላንስ አገልግሎት ነፃ ባልወጡ ቀበሌዎች አገልግሎት እንዲሰጥ እና ተጀምሮ የነበረው ከንየረ-አቚ-ሴሪያ እና ከንየረ-አቚ-ሲቃላ መንገድ የስትራክቸር ስራ መጀመሩን ገልፀው በሰቆጣ የመጣው የመብረት መስመር ከ15 ሺህ ኪ/ዋ ወደ 33 ሺህ ኪ/ዋ እንዲቀየር ፈዴራል ጠይቀናል ሌሎች መስኖ እና የተከዜ ዓሳ ሃብት ስራዎች ላይ በትኩረት ይሰራል ብለዋል።

የማህበራዊ ሚድያ አጠቃቀማችን ህዝቡን ከሚለያዩን ጉዳዮች ይልቅ ሊያስማሙንና ሊያቀራርቡን በሚችሉ መልካም ተግባር ማዋል አለብንም ብለዋል።

ወረዳው በውጥረት ላይ ሁኖ የሰራቸው ልማቶች በማህበረሰቡ የተሰጠው እውቅና የሚበረታታ ነው ያሉት አቶ ሀይሉ ግርማይ አመራሩ ከጸጥታ ሃይሉ ጋር በመቀናጀት ባደረገው ጥረት የመጣውን ሰላም ዘላቂነቱን ለማረጋገጥ በሚደረገው ጥረትም አጠናክሮ መቀጠል አለበት ብለዋል።

የመድረኩ ተሳታፊዎች በበኩላቸው የተነሱ ጥያቄዎች በተለይም የአዴን ስምምነቱ እልባት እንዲሰጠው እና የመብራት አገልግሎቱ እንዲስተካከልላቸው ጠይቀው አካባቢያቸውን ከመጠበቅ ባለፈ በየተሰማሩበት መስክ ጠንክሮ በመስራት በመንግስትና በህዝብ የተጀመሩ የልማት ስራዎችን ለማገዝ ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል።

በውይይት መድረኩ የክልልና የብሄረሰብ አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮች፣ የወረዳ አመራሮች፣መንግስት ሰራተኞች እና የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች ተሳትፈዋል።

ለወቅታዊ ፣ ትክክለኛና አዳዲስ መረጃዎች የፓርቲያችንን የማህበራዊ ገፆች ይወዳጁ።
°°°
Twitter;https://twitter.com/AbergelleW_PP
Telegram;https://t.me/AWPP_DSM
Youtube;https://www.youtube.com/@abergelleworedaprosperityparty
Facebook;https://www.facebook.com/100055961503780/posts/pfbid0Vhb9YhQon7642KPnL9bu76gWGUCRQWqXr8Sh33NsPnN8cQf97myvkikFnicxfdHMl/?app=fb