#MoE : በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የምግብ ሜኑ ተመሳሳይ እንዲሆን መወሰኑን ትምህርት ሚኒስቴር አሳወቀ።
የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የምግብ በጀት ማስተካከያ መደረጉንም ይፋ አድርጓል።
" ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተውጣጡ ባለሙያዎች የዩኒቨርስቲ ተማሪዎችን የምግብ ሜኑ ተቀራራቢ እንዲሆን እየሰሩ ነው " ሲል ትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል።
ወቅታዊውን የምግብ ዋጋ መጨመር መነሻ በማድረግ ትምህርት ሚኒስቴር ጥናት ማድረጉን በጥናቱ ውጤት መነሻነትም የከፍትኛ ትምህርት ተቋማት / የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የምግብ በጀት በቀን ወደ 100 ብር ከፍ እንዲል መደረጉን አሳውቋል።
በተደረገው የበጀት ማሻሻያ መሰረት በተቋማቱ የምግብ ሜኑ ተመሳሳይ እንዲሆን ይሰራል ተብሏል።
በአዲሱ የበጀት ተመን መሰረት ለዩኒቨርስቲዎቹ ባላቸው ተማሪ ቁጥር ልክ ገንዘቡ እንደሚለቀቅላቸው ተጠቁሟል።
#MoE
@ASTU_Network

👍5🤣3👀2🕊1
#News #MoE
የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ከመመረቃቸው በፊት ለአንድ ዓመት እንዲያስተምሩ ሊገደዱ ነው።
ትምህርት ሚኒስቴር የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ከመመረቃቸው በፊት ማኅበረሰቡን ለአንድ ዓመት በቅድሚያ እንዲያስተምሩ ወይም እንዲያገለግሉ የሚያደርግ አሰራር ተግባራዊ ለማድረግ ዕቅድ መያዙን አስታወቀ።
''የኢትዮጵያ ዩኒቨርስቲ ሰርቪስ'' የሚል መጠሪያ የተሰጠው አሠራር ከ2019 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ እንዲደረግ ዕቅድ የተያዘ መሆኑን የገለጹት ሚኒስትሩ፣ " በአራት ዓመት የሚመረቅ ተማሪ፣ የሦስተኛ ዓመት ትምህርቱን እንዳጠናቀቀ ወደ አስተማረው ማኅበረሰበብ ተመልሶ ለአንድ ዓመት የማስተማር አገልግሎት ይሰጥና (ማኅበረሰቡን እንዲያገለግል ይደረግና) እንዲመረቅ ይደረጋል " ሲሉ ተናግረዋል።
ይህም ሲሆን የተማሪዎቹ መሠረታዊ ወጪ የሚሸፈን እንደሚሆንም አክለዋል።
ይህ አሰራር ለተማሪዎች ለራሳቸው የተግባር ትምህርት እንደሚሆንና የበለጠ እንዲበስሉ እንደሚያደርጋቸውም ተናግረዋል።
ተማሪዎች የመምህርነትን ሙያ ተላብሰው በዚያው ወደ ሙያው እንዲያመሩ ዕድል በመፍጠር ለጊዜውም ቢሆን በዘርፉ እየቀነሰ የመጣውን ወደ ሙያው የሚገባ የአስተማሪን ቁጥር ለማሳግ እንደሚረዳም ሚንስትሩ አብራርተዋል።
|| @ASTU_Network

🤣17😭5👍4🤬3🤔1💔1
ASTU Network ®️
Photo
#MoE
"ከ2019 ጀምሮ 3ኛ ዓመት የጨረሱ ተማሪዎች 4ኛ አመት ከመግባታቸው በፊት የ1 ዓመት አገልግሎት እንዲሰጡ ይደረጋል " - ብርሃኑ ነጋ (ፕሮፌሰር)
በዩኒቨርሲቲ የሚማሩ 3ኛ ዓመት የጨረሱ ተማሪዎች 4ኛ ዓመት ሳይገቡ በፊት የአንድ ዓመት አገልግሎት እንዲሰጡ ለማድረግ የተጀመረው እንቅስቃሴ ከ2019 ዓ/ም ጀምሮ ተግባር ላይ እንደሚውል የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕሮፌሰር) ጠቁመዋል።
ብርሃኑ ነጋ (ፕሮፌሰር) ፤ " በሚቀጥለው ዓመት ላይደርስልን ይችላል ግን ህጋዊ ስርዓቱን በሙሉ ጨርሰን በ2019 ዩኒቨርሲቲ ውስጥ የሚማሩ 3ኛ ዓመት የጨረሱ ተማሪዎች ከ2019 ጀምሮ 4ኛ አመት ከመግባታቸው በፊት የ1 ዓመት አገልግሎት እንዲሰጡ ይድረጋል " ብለዋል።
"ከዚህ በፊት የነበረ ነው አዲስ አይደለም በጃንሆይ ጊዜ (በአጼ ኃይለስላሴ ጊዜ ማለታቸው ነው) የነበረ ነው" ሲሉ ገልጸዋል።
"ሁለት ጥቅም አለው ብለን ነው ይሄን የምናደርገው አንደኛ ልጆቹ ዝም ብሎ የቀለም ትምህርት ብቻ ተምረው ሳይሆን ተግባራዊ የሆነ ትምህርትም ለአንድ ዓመት ሄደው የሚሰሩበት ከማህበረሰቡ ጋር የሚተዋወቁበት ነው። ሁለተኛ የአስተማሪዎች እጥረትም ስላለ ልጆችን ወደ አስተማሪነት ለአንድ አመት ቢሆንም ለማስገባት ነው " ብለዋል።

🤬6👏3💔3👍2❤1🤨1😭1
#ማስታወቂያ! #MoE
ለቅድመ ምረቃ ፕሮግራሞች የመውጫ ፈተና (Exit Exam) ምዝገባ ከታች ያለውን ሊንክ በመጠቀም መመዝገብ የሚቻል መሆኑን እንገልጻለን።
🔗 Link 🔗
ትምህርት ሚኒስቴር
|| @ASTU_Network
ለቅድመ ምረቃ ፕሮግራሞች የመውጫ ፈተና (Exit Exam) ምዝገባ ከታች ያለውን ሊንክ በመጠቀም መመዝገብ የሚቻል መሆኑን እንገልጻለን።
🔗 Link 🔗
https://exam.ethernet.edu.et
ትምህርት ሚኒስቴር
|| @ASTU_Network
👍3👎1
#News #MoE
በዕጩ ተመራቂ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና ውጤት በተከታታይ ሦስት ጊዜ ከ25 በመቶ በታች በሚያስመዘግቡ ዩኒቨርሲቲዎች ላይ እርምጃ ይወሰዳል። - ትምህርት ሚኒስቴር
የትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች ከቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ አባላት ጋር በተወያዩበት ወቅት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕሮፌሰር) እንዳሉት፥ "ዩኒቨርሲቲዎች የሚያስተምሯቸው ተማሪዎች ብቃት ያላቸውና ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ማድረግን ዋና ተግባራቸው አድርገው" ሊሠሩ ይገባል።
በዚህም በዕጩ ተመራቂ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና ውጤት በተከታታይ ሦስት ጊዜ ከ25 በመቶ በታች ካስመዘገቡ በትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን እርምጃ እንደሚወሰድባቸው ገልፀዋል።
በሌላ በኩል ዩኒቨርሲቲዎች በተፈጥሮ የተሰጡ የአካባቢው ፀጋዎች ላይ ራዕይ ይዘው መሥራት እንደሚገባቸው አንስተዋል።
ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ በማዕድን ላይ ሰፊ ምርምር በማድረግ ሀገርን የሚጠቅም ሥራ መስራት ይጠበቅበታል ብለዋል።

👍1🕊1
#MoE
በኃላፊነት ላይ ያለ የመንግስት ሹመኛ ወይም ተመራጭ ለ #ክብር_ዶክትሬት እንዳይታጭ የሚከለክል መመሪያ የትምህርት ሚኒስቴር አወጣ፡፡
መመሪያው 8 ዙር ተማሪዎችን ያላስመረቁ እና ሶስተኛ ዲግሪ ወይም (PhD) የማያስተምሩ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የክብር ዶክትሬት እንዳይሰጡ ይከለክላል፡፡
በትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ሃምሌ 15 ቀን 2017 ዓ.ም ተፈርሞ ለሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት የተመራው ይህ መመሪያ በቅርብ ጊዜ የተመሰረቱ የትምህርት ተቋማት የክብር ዶክትሬት እንዳይሰጡ ይከለክላል፡፡
በመመሪያው ክፍል ሁለት ላይ የክብር ዶክትሬት የሚሰጡ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት መስፈርትን በተመለከተ የተቀመጠው ድንጋጌ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የክብር ዶክትሬት ለመስጠት ቢያንስ ከ8 ጊዜ በላይ ተማሪዎችን ያስመረቁ እና የሶስተኛ ዲግሪ የሚሰጡ መሆን እንዳለባቸው ያስገድዳል፡፡
በዚህም መሰረት ሰላሌ፣ ደምቢ ዶሎ፣ መቅደላ አምባ፣ ራያ፣ ደባርቅ እና መሰል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ስምንት ዙር ተማሪዎችን ስላላስመረቁ በመመሪያው መሰረት የክብር ዶክትሬት መሰጠት አይችሉም፡፡
በዚሁ ክፍል ስር ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የክብር ዶክትሬት ማዕረግ ለመስጠት አገር እና አለም አቀፍ መስፈርቶችን ማሟላት እንዳለባቸው ሰፍሯል፡፡
በሞያ መስኩ የተለየ ስራ ያበረከተ ከሆነ ኢትዮጵያዊም ሆነ ሌላ ዜጋ የክብር ዶክትሬት ማዓረግ ማግኘት እንደሚችል የዘረዘረው መመሪያው መስፍርቱን ካሟሉ ለግለሰብም ይሁን ለቡድን መስጠት እንደሚቻል አመላክቷል፡፡
በሕይወት ላለም ይሁን ለሌለ ሰው ማዕረጉን መስጠት እንደሚቻል የሚፈቅደው ይህ መመሪያው የክብር ዶክትሬት ለማግኘት የማይቻልባቸውን ገደቦችም በክፍል ሁለት አንቀጽ 10 ስር ዘርዝሯል፡፡
በዚህም መሰረት የከፍተኛ ትምህርት ተቋሙ የሙሉ ሰዓት ተቀጣሪ ሰራተኛ፣ የሴኔት አባላት ወይም የአስተዳደር አካላት ከተቋሙ ጋር ያላቸው ቀጥተኛ ግንኙነት እስካላበቃ ድረስ ለክብር ዶክትሬት መታጨት እንደማይችሉ ደንግጓል፡፡
መመሪያው በስራ ላይ ያሉ የመንግስት ሹሞች ወይም ባለስልጣናት ለክብር ዶክትሬት እንዳይታጩም የሚከለክል ነው፡፡
የክብር ዶክትሬት የተሰጠው ግለሰብ ዶክተር፣ የክብር ዶክተር እና መሰል መጠሪያዎችን ከሰጪው ተቋም ውጪ በየትኛውም ድርጅት ውስጥ መጠቀም እንደማይችሉም ደንግጓል፡፡
የትምህርት ሚኒስቴር በለፈው ዓመት በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በሽምያ የሚሰጡ የክብር ዶክትሬት ማዕረጎች መመሪያ እስኪወጣ ድረስ እንዲያቆሙ ማዘዙ ይታወሳል፡፡
መረጃው የሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬድዮ ጣቢያ ነው።
@tikvahethiopia

❤3🤷♀1
#MoE
የመውጫ ፈተና መሰጠት ከተጀመረ ወዲህ ትምህርታቸውን ላጠናቀቁ፥ የዲግሪ ህትመት የሚዘጋጀው የመውጫ ፈተናውን ላለፉ ተማሪዎች ብቻ እንደሆነ ትምህርት ሚኒስቴር አሳወቀ፡፡
ሚኒስቴሩ የዲግሪ ህትመትን የተመለከተና በሚኒስትር ዲኤታ ኮራ ጡሹኔ በቀን ነሐሴ 06/2017 ዓ.ም የተፈረመ ደብዳቤ ለሁሉም የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች እና የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ልኳል፡፡
በዚህም የዲግሪ ማስረጃ ወይም ሰርተፊኬት ህትመት በሀገር አቀፍ ደረጃ በማዕከል የሚታተም መሆኑን መጋቢት 02/2017 ዓ.ም ለሁሉም የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች እና የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በላከው ደብዳቤ ማሳወቁን አስታውሷል፡፡ ከ2017 ዓ.ም ጀምሮ ለተመረቁ እና ከዚህ በፊት ተመርቀው መረጃውን ያልወሰዱ ከተመረቁ ጊዜ ጀምሮ ህትመቱ በማዕከል ተከናውኖ በዩኒቨርሲቲው ወይም በተቋሙ በኩል የሚሠራ ወይም የሚሰጥ መሆኑን ገልጿል፡፡
በመሆኑም ከፍተኛ ትምህርት ተቋሙ ሊሠራለት የሚገባውን የሰርተፍኬት ይዘት (በውስጡ የሚገለፁ ይዘቶችን፣ ሎጎዎች እና ተጨማሪ መብት ያላቸው ጉዳዮች) በማካተት እጅግ ቢዘገይ እስከ ሐሙስ ነሐሴ 08/2017 ዓ.ም ባሉት ቀናት ውስጥ እንዲያሳውቁ አሳስቧል፡፡
የመውጫ ፈተና መሰጠት ከተጀመረ ወዲህ ያለው ህትመት የሚዘጋጀው፣ የመውጫ ፈተናውን ላለፉ ተማሪዎች ብቻ መሆኑን ጠቁሟል፡፡
(ከትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን ያገኘነው ደብዳቤ ከላይ ተያይዟል፡፡)
©️ tikvahuniversity

❤2🗿2
#MoE
ትምህርት ሚኒስቴር ተቀራራቢ ይዘት ባላቸው የከፍተኛ ትምህርት ፕሮግራሞች ስያሜ እና ስርዓተ ትምህርት ላይ ክለሳ በማድረግ ወደ ትግበራ ገብቷል።
ሚኒስቴሩ ከሰኔ 2014 ዓ.ም እስከ ግንቦት 2017 ዓ.ም ድረስ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚሰጡ ተቀራራቢ ይዘት እና ስያሜ የነበራቸው ፕሮግራሞችን በመለየት ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች እና ኢንዱስትሪዎች ከተውጣጡ የዘርፉ ባለሙያዎች ጋር በመሆን በፕሮግራሞቹ ስያሜ እና ስርዓተ ትምህርት ላይ ማስተካከያ አድርጓል፡፡
ተቀራራብ ይዘት ያላቸው ፕሮግራሞችን በማጠፍ/በማዋሃድ አዳዲስ የፕሮግራሞች ስያሜዎች መሰጠቱን በአካዳሚክ ጉዳዮች ዋና ስራ አስፈፃሚ ኤባ ሚጀና (ዶ/ር) ተፈርሞ ለሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች የተላከው ደብዳቤ ያሳያል።
በዚህም 147 ፕሮግራሞችን ወደ 54 በመጠቅለል አዳዲስ የፕሮግራሞች ስያሜ መሠጠቱ ተገልጿል። በተወሰኑ ፕሮግራሞች ላይ ማስተካከያ የተደረጉ ሲሆን የታጠፉ ፕሮግራሞች እንዳሉም ለማወቅ ተችሏል።
ይህም በሁሉም ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተግባራዊ እንዲደረግ ሚኒስቴሩ አሳስቧል። (የፕሮግራሞቹ ዝርዝር ከላይ ተያይዟል።)

👀5👎2👏2😁2😨2❤1😢1
#MoE
ትምህርት ሚኒስቴር የ2018 ትምህርት ዘመን የከፍተኛ ትምህርት አካዳሚክ ካላንደርን ይፋ አድርጓል፡፡
በትምህርት ሚኒስትር ዲኤታ ኮራ ጡሹኔ በቀን ነሐሴ 12/2017 ዓ.ም የተፈረመ የ2018 ትምህርት ዘመን የከፍተኛ ትምህርት አካዳሚክ ካላንደር ዝርዝር ለሁሉም ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተልኳል፡፡
መስከረም 05-06/2018 ዓ.ም
➫ የመጀመሪያ ዓመት የቅድመ ምረቃ ተማሪዎች (ሪሚዲያል ተማሪዎችን ጨምሮ) በየተመደቡበት ዩኒቨርሲቲ ሪፖርት ያደርጋሉ፡፡
መስከረም 08-09/2018 ዓ.ም
➫ የሁሉም የቅድመ እና የድኅረ ምረቃ መደበኛ እና ኢ-መደበኛ ተማሪዎች (ሪሚዲያል ተማሪዎችን ጨምሮ) ምዝገባ ያደርጋሉ፡፡
መስከረም 12/2018 ዓ.ም
➫ የሁሉም የቅድመ እና የድኅረ ምረቃ መደበኛ እና ኢ-መደበኛ ተማሪዎች በቅጣት ምዝገባ፣
➫ የ2018 ዓ.ም የመጀመሪያ ሴሚስተር ትምህርት ይጀመራል፡፡
(ሙሉ የ2018 ትምህርት ዘመን የከፍተኛ ትምህርት አካዳሚክ ካላንደር ከላይ ተያይዟል፡፡)

🤷♀3🤣3❤2🥰1
ASTU Network ®️
"ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት ስልክ ይዘው እንዳይሄዱ ለማድረግ እንቅስቃሴ ተጀምሯል" - ብርሃኑ ነጋ (ፕሮፌሰር) || @ASTU_Network
#MoE
ትምህርት ሚኒስቴር ከ2018 የትምህርት ዘመን ጀምሮ ተማሪዎች ሞባይል ስልክ፣ ታብሌት እና መሰል ኤሌክትሮኒክስ ቁሶችን ይዘው ወደ ትምህርት ቤት እንዳይሔዱ ከልክሏል፡፡
ትምህርት ሚኒስቴር በ2018 የትምህርት ዘመን አጀማመር ላይ ከክልል እና ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊዎች ጋር የበይነ-መረብ ምክክር አድርጓል።
የ2018 ትምህርት ዘመን የመማር ማስተማር ሥራ ሰኞ መስከረም 05/2018 ዓ.ም እንደሚጀመር ተገልጿል።
ተማሪዎች ተንቀሳቃሽ ስልክ፣ ታብሌት እና መሰል ኤሌክትሮኒክስ ቁሶችን ይዘው በትምህርት ቤት መገኘት ክልክል መሆኑን ሚኒስቴሩ አሳስቧል።
በሌላ በኩል፤ ባለፈው ዓመት ከትምህርት ገበታ ውጪ የሆኑ ተማሪዎችን ጨምሮ ሁሉም ዕድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ ህጻናት እና ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት እንዲመጡ ወላጆች፣ መምህራን እና የዘርፉ ባለድርሻዎች የሚጠበቅባቸውን እንዲወጡ ተጠይቋል።

🙉6👌5❤3
#Update
የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ነገ ይፋ ይደረጋል።
የትምህርት ሚኒስቴር የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ነገ ይፋ እንደሚደረግ አሳውቋል።
የፈተና ውጤቱን አስመልክቶ ነገ ከቀኑ 10 ሰዓት ጀምሮ መግለጫ ይሰጣል።
#MoE
©️ tikvahethiopia

👀4❤2
ASTU Network ®️
Photo
#MoE : 1,249 ትምህርት ቤቶች ምንም ተማሪ ሳያሳልፉ ቀርተዋል። ከአምናው ጋር ሲነጻጸር 114 ትምህርት ቤቶች ተማሪዎች በማሳለፍ መሻሻል ታይቷል።
መቶ በመቶ ተማሪዎቻቸውን ያሳለፉት 50 ትምህርት ቤቶች ናቸው።
|| @ASTU_Network
መቶ በመቶ ተማሪዎቻቸውን ያሳለፉት 50 ትምህርት ቤቶች ናቸው።
|| @ASTU_Network
❤1💔1🙉1
#MoE : የ2017 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተና ውጤትን አስመልክቶ የተዘጋጀው ጋዜጣዊ መግለጫ ሙሉ ይዘት ከላይ ተያይዟል።
|| @ASTU_Network
|| @ASTU_Network
❤1🕊1
#MoE
በሁሉም የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች በየትኛውም የትምህርት ከፍል የሚገኙ መምህራን እና ተማሪዎች በ2018 ዓ.ም የ 5 ሚሊዮን ኮደርስ ፕሮግራም ስልጠና እንዲወስዱ ትምህርት ሚኒስቴር አሳሰበ፡፡
የፕሮግራሙ አፈጻጸምና ስልጠናውን የወሰዱ መምህራን እና ተማሪዎች በጾታ ተለይተው ሳምንታዊ ሪፖርት እንዲላክለትም ሚኒስቴሩ ጠይቋል፡፡
(በትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ተፈርሞ ለሁሉም የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የተላከ ደብዳቤ ከላይ ተያይዟል፡፡)

🥱7🤣3👀3❤1🤬1🤨1
#MoE
ትምህርት ሚኒስቴር በተለያዩ የሙያ ዘርፎች በመጀመሪያ ዲግሪ ተመርቀው የመምህርነት ሙያን መቀላቀል ለሚፈልጉ የአንድ ዓመት ስልጠና ሊሰጥ ነው፡፡
ስልጠናው አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲን ጨምሮ በተመረጡ አምስት ዩኒቨርሲቲዎች ይሰጣል፡፡
የምዝገባ መስፈርት፦
በተለያዩ የሙያ ዘርፎች በመጀመሪያ ዲግሪ የተመረቁና በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በሚሰጡ የትምህርት ዓይነቶች እና ተዛማጅነት ባላቸው የትምህርት መስኮች በመምህርነት ሙያ መሰልጠን የሚፈልጉ
የምዝገባ ጊዜ
ከዛሬ ህዳር 16/2018 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 ቀናት
የምዝገባ ቦታ
ከስር በተገለፁ በተመረጡ አምስት ዩኒቨርሲቲዎች በኦንላይን
በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የሚሰጡ የትምህርት አይነቶችና ተዛማጅ የትምህርት መስኮችን ዝርዝር ለማግኘት https://shorturl.at/N8e0s ላይ በመግባት “አማራጭ የመምህራን ስልጠና ትምህርት አይነቶች” የሚለውን በማውረድ ማግኘት ይችላሉ፡፡
የዩኒቨርሲቲ መመዝገቢያ ሊንኮች፦
➫ ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ፦ https://forms.gle/JZG12devyUvDe3v6
➫ ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ፦ https://docs.google.com/.../1FAIpQLSfQcnu1ThO.../viewform...
➫ ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ፦ https://portal.hu.edu.et/Home/AvailablePrograms
➫ ጅማ ዩኒቨርሲቲ፦ https://portal.ju.edu.et
➫ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፦ https://forms.gle/6t1BNV9S67oXwzBv9
የስልጠና ፕሮግራሙ በአንድ ዓመት የሚጠናቀቅ ሲሆን፤ በቀን መርሐግብር የሚማሩ ተማሪዎች የትምህርት ወጪያቸው ሙሉ ለሙሉ በመንግሥት እንደሚሸፈን ተገልጿል።

❤4👍4