Forwarded from Addis Ababa Education Bureau (Abebe Chernet)
የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤት የ2017 ዓ.ም የተማሪዎችና የመምህራን የሳይንስ ትምህርት የፈጠራ ስራ አውደ ርዕይ አካሄደ።
(ሚያዝያ 15/2017) የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤት "በፈጠራ ስራ የተካነ ትጉህ ትውልድ ለሀገር ብልጽግና!" በሚል መሪ ሀሳብ ለ10ኛ ጊዜ የሚካሄደውን የተማሪዎችና መምህራን የሳይንስ ፈጠራ ሥራ አውደ ርዕይ የክፍለከተማው ት/ፅ/ቤት ኃላፊ ፣ የትምህርት ባለድርሻ አካላት ፣ የትምህርት ባለሙያዎች ፣ መምህራንና ተማሪዎች በተገኙበት በድምቀት በየካቲት 23 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አከናውኗል፡
የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ትምህርት ፅ/ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ ብሩክ ተ/ማሪያም እንዳሉት ተማሪዎች በክፍል ውስጥ በንድፍ ሃሳብ የተማሩትንና መምህራን ተማሪዎቻቸውን በንድፍ ስያስተምሩ የቆዩትን ትምህርት ተጨባጭነቱ የሚረጋገጠው የተለያዩ የፈጠራ ስራዎች በተማሪዎችና በመምሀራኖች መስራት ሲችሉ ነው ብለዋል፡፡
ይህንን ለማረጋገጥ የፈጠራ ስራዎች ውድድር በትምህርት ቤት፣ በወረዳና በክፍለ ከተማ ደረጃ መቆየቱን የገለፁት አቶ ብሩክ ይህ ውድድርም በተማሪዎችና በመምህራን መካከል የወድድር መንፈስ እንዲዳብር፣ ልምድ የሚለዋወጡበትና የተሻለ ስራ የሰረው ተማሪዎችንና መምህራኖችን እውቅና ለመስጠት ነው ሲሉ ገልፀዋል፡፡
በዚህም መሰረት የተሻለ የፈጠራ ስራ ለሰሩ ተማሪዎች፣ መምህራን፣ወረዳዎችና 2ኟ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ሽልማት በመስጠት ኤግዝብሽኑ ተጠናቋዋል፡፡
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ!
https://linktr.ee/aacaebc