AHADU NEWS አሀዱ ዜና
100 subscribers
10 photos
3 links
ሰላም ውድ ተመልካቾች ይሄንን ቻናል ጆይን በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ።
Download Telegram
የጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ አሸብሪው የህወሀት ቡድን 9ኛ ዙር ስህተት ከመፈፀም እንዲቆጠብ አሳሰቡ!!

ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ፣ አሸባሪው ቡድን ባለፉት ጊዜያት 8 ጊዜ ስህተት መሳሳቱን አስታውሰው ቡድኑ 9ኛ ዙር ስህተት ላለመፍጠር ቁጥብ ሊሆን እንደሚገባ አሳስበዋል።

ቡድኑ አሁንም የምእራብ ኮሪደርን አስከፍታለሁ ብሎ ማወጁን የገለፁት ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ፣ ይህንን እቅዱን ለመተግበር ከተንቀሳቀሰ አስፈላጊው ርምጃ እንደሚወሰድና ለዚህም ተቋሙ በሙሉ ቁመና ላይ እንደሚገኝ አረጋግጠዋል።

@AHADUtv
@AHADUtv
1👍1
አፍሪካ በፀጥታው ም/ቤት ቋሚ መቀመጫ እንዲኖራት የሚደረገው ጥረት ተጠናክሮ ይቀጥላል-አፍሪካ አገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች

አዲስ አበባ፣ ጥር 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አፍሪካ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት ቋሚ መቀመጫ እንዲኖራት የሚደረገው ጥረት ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን የተለያዩ አፍሪካ አገራት የዓለም አቀፍ ግንኙነትና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ገለጹ።   ለ35ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ አዲስ አበባ የተገኙ ታዳሚዎች እንደገለጹት፥አፍሪካ በጸጥታው ምክር ቤት ቋሚ መቀመጫ እንዲኖራት የሚደረገው ጥረት ተጠናክሮ ይቀጥላል።…

https://t.me/AHADUtvአፍሪካ-በፀጥታው-ም-ቤት-ቋሚ-መቀመጫ-እንዲ/
የጸጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል ባስቀመጠው አቅድ መሰረት የህብረቱ የመሪዎች ጉባኤ ሰላማዊ ሂደቱን ጠብቆ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥር 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የጸጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል ባስቀመጠው አቅድ መሰረት የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ሰላማዊ ሂደቱን ጠብቆ እየተካሄደ መሆኑን የጋራ ግብረ ኃይሉ አስተባባሪ ኮሚቴ አስታወቀ፡፡   የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ለጉባኤው ሰላማዊነት እያደረጉት ያለውን ከፍተኛ አስተዋጽኦ አጠናክረው እንዲቀጥሉ የጋራ ግብረ-ኃይሉ ጥሪ አቅርቧል።   የአፍሪካ ህብረት 40ኛው የስራ አስፈጻሚ…

https://t.me/AHADUtv/የጸጥታና-ደህንነት-የጋራ-ግብረ-ኃይል-ባስ/
👍21
35ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ባለሁለት እግር ሞተር ብስክሌት ማሽከርከር የተከለከለ መሆኑን የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ- ኃይል አስታወቀ‼️

35ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት በአዲስ አበባ ጥር 28 እና 29 ቀን 2014 ዓ.ም ይካሄዳል።

ጉባኤው በሰላም እንዲጠናቀቅ ለማስቻል ልዩ ልዩ ኮሚቴዎች ተዋቅረው ወደ ስራ መግባታቸው ይታወቃል።

ህብረተሰቡም ለጉባኤው ስኬታማነት የድርሻውን እንዲወጣ የቀረበለትን ጥሪ ተቀብሎ አካባቢውን እየጠበቀ ይገኛል።

የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ- ኃይል ከአዲስ አበባ ከተማ መንገድና ትራንስፖርት ቢሮ ጋር በጋራ በተወሰነው መሰረት አሁን ያለውን የፀጥታ ሁኔታ በተገቢው ለመምራትና ለእንግዶቹ አስፈላጊውን አቀባበል ለማድረግ እንዲሁም የትራፊክ ፍሰቱን የተሳለጠ ለማድረግ ከነገ አርብ ጥር 27 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ ለሦስት ቀናት የፀጥታ አካላት ከሚጠቀሙባቸው ውጪ ባለሁለት እግር ሞተር ብስክሌት በአዲስ አበባ ከተማ በሁሉም አከባቢዎች በማንኛውም ሰዓት መንቀሳቀስ ፍፁም የተከለከለ መሆኑን የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ- ኃይል አስታውቋል።

የሞተር ብስክሌት ባለንብረቶች ሆኑ አሽከርካሪዎች ይህንን መልእክት ተግባራዊ እንዲያደርጉ ግብረ ኃይሉ መልእክቱን እያስተለለፈ ይህንን መልእክት በሚተላለፉ አካላት ላይ ጥብቅ እርምጃ እንደሚወስድ አስታውቋል።

@AHADUtv
@AHADUtv
የመሪዎች ጉባኤ ተጠናቆ እስኪመለሱ ድረስ ነዋሪው የተለመደ ትብብሩን እንዲያደርግ ጥሪ ቀረበ

ጥር 28/2014 (ዋልታ) ነዋሪው እስካሁን እያደረገ ያለውን አስተዋጽኦ ጉባኤው እስኪጠናቀቅና እንግዶች ወደየመጡበት አገር እስኪመለሱ ድረስ የተለመደ ትብብሩን እንዲያደርግ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አበቤ ጥሪ አቀርበዋል።

ዛሬ የሚጀመረው 35ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባኤና ከትናንት በስቲያ የተጠናቀቀው 40ኛው የኅብረቱ ሥራ አስፈጻሚ ምክር ቤት በስኬት እንዲካሄድ የከተማዋ ነዋሪዎች እያደረጉ ላለው አስተዋጽኦ ከንቲባዋ ምስጋና አቅርበዋል።

ነዋሪው እስካሁን እያደረገ ያለውን አስተዋጽኦ ጉባኤው እስኪጠናቀቅና እንግዶች ወደየመጡበት አገር እስኪመለሱ ድረስ የተለመደ ትብብሩንና እንግዳ ተቀባይነቱን እንዲያጠናክር ጠይቀዋል።

በኢትዮጵያዊ ጨዋነት በያላችሁበት እንግዳ በማስተናገድ ትልቁ ባህላችን ሁሉንም በየአካባቢው ውብና ድንቅ አድርጋችሁ እንደምታስተናግዱ እምነቴ የፀና ነው ያሉት ከንቲባዋ የከተማችን ነዋሪዎች ይህን የአፍሪካ ኅብረት ጉባኤ ስኬታማ በማድረግ በኩል ያላችሁ ሚና እጅግ በጣም ትልቅ ነው ብለዋል።

በተለያየ መንገድ ከፀጥታ ኃይሎች ጋር በመቀናጀት በከተማዋ የሰላምና ፀጥታ ሥራ በመሳተፍ ስታደርጉ የነበረውን ጥረት አጠናክራችሁ እንድትቀጥሉና ትኩረታችሁን እንደ ወትሮው እንድታደርጉ እያሳሰብኩ፣ ጉባኤው ስኬታማ እንዲሆን የበኩላችሁን እንድትወጡ ከአደራ ጭምር እጠይቃለሁ ሲሉ ለኢዜአ ገልፀዋል።

ዛሬ ለሚጀመረው 35ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባኤ የተለያዩ የአፍሪካ አገራት መሪዎች፣ ሚኒስትሮች፣ ዲፕሎማቶችና ሌሎች የጉባኤው ተሳታፊዎች አዲስ አበባ መግባታቸው ይታወቃል።

ለፈጣን መረጃዎች፦
https://t.me/AHADUtv
2
#Update

የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች በ35ተኛዉ የአፍሪካ ህብረት (AU) የመሪዎች ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ወደ አዲስ አበባ እየገቡ ናቸው።

እስካሁን የገቡ ፦

🇲🇼 ዶ/ር ላዛሩስ ማካርቲ ቻክዌራ (ማላዊ - ፕሬዝዳንት)
🇬🇲 ዶ/ር ኢሳቱ ቶራይ (ጋምቢያ - ምክትል ፕሬዚዳንት)
🇳🇬 ሙሀሙዱ ቡሃሪ (ናይጄሪያ - ፕሬዝዳንት)
🇨🇮 ኦላሳን ኦታራ (ኮትዲቯር - ፕሬዝዳንት)
🇸🇳 ማኪ ሳል (ሴኔጋል - ፕሬዝዳንት)
🇲🇷 ሞሐመድ ኡልድ ኤል-ጋዝዋኒ (ሞሪታንያ - ፕሬዝዳንት)
🇹🇿 ዶ/ር ፊሊፕ እስዶር መፓንጎ (ታንዛንያ- ምክትል ፕሬዝዳንት)
🇹🇩 አልበርት ፓሂሚ ፓዳክ (ቻድ - ጠቅላይ ሚኒስትር)
🇿🇼 ኤመርሰን ማናንጋግዋ (ዚምባቡዌ - ፕሬዝዳንት)
🇬🇦 ሮዝ ክርስቲያን ኦሳካ (ጋቦን - ጠቅላይ ሚኒስትር)
🇿🇲 ሃካይንዴ ሂቺሌማ (ዛምቢያ - ፕሬዜዳንት)
🇨🇫 ፕሮፌሰር ፎስቲን አካንግ ቶንዳራ (ማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ - ፕሬዜዳንት)
🇳🇪 መሀመድ ባዙም (ኒጀር - ፕሬዜዳንት)
🇺🇬 ጄሲካ አሉፖ (ዩጋንዳ - ምክትል ፕሬዝዳንት)
🇸🇿 ክሊዮፓስ ዲላሚኒ (ስዋቲኒ - ጠቅላይ ሚኒስትር )
🇨🇻 ጆዜ ማሪያ (ኬፕ ቨርዲ - ፕሬዝዳንት)
🇨🇩 ፊሊክስ ሺሴኬዲ (ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ - ፕሬዚዳንት እና የወቅቱ የአፍሪካ ህብረት ሊቀ-መንበር)
🇧🇮 ኤቫሬስት ንዳያሽሜ (ብሩንዲ - ፕሬዚዳንት)
🇰🇲 አዛሊ አሱማኒ (ኮሞሮስ - ፕሬዝዳንት)
🇪🇭 ብራህሚ ጋሊ (ሳህራዊ አረብ ሪፐብሊክ - ፕሬዝዳንት)
🇬🇭 ናና አኩፎ አዶ (ጋና - ፕሬዚዳንት)
🇸🇱 ጁሌስ ማዳ ቢዮ (ሴራሊዮን - ፕሬዚዳንት)
🇨🇬 ዴኒስ ሳሱ ንግኤሶ (ኮንጎ ሪፐብሊክ - ፕሬዝዳንት )
🇱🇾 መሀመድ ዩኑስ አል መንፊ (ሊቢያ - የፕሬዝዳንታዊ ም/ቤት ፕሬዝዳንት)
🇲🇿 ፊሊፕ ኒየሲ (ሞዛምቢክ - ፕሬዜዳንት)
🇩🇯 ኢስማኤል ኦማር ጌሌ (ጅቡቲ - ፕሬዜዳንት)
🇸🇴 መሀመድ አብዱላሂ ፈርማጆ (ሶማሊያ - ፕሬዜዳንት)
🇰🇪 ኡሁሩ ኬንያታ (ኬንያ - ፕሬዜዳንት)

በተጨማሪም ለዚሁ ጉባኤ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ምክትል ፃሀፊ ኦሚና መሀመድ እንዲሁም የፍልስጤም ጠቅላይ ሚኒስትር ሞሃመድ ሽታይ አዲስ አበባ ይገኛሉ።

የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ዛሬ ይጀምራል።
👍112