ABU DAWD OSMAN
3.49K subscribers
587 photos
31 videos
3 files
347 links
Download Telegram
Gammachu gudda muslima hundaf !

Satellite:- E8WB
Frequency :- 12521 MHz,
Symbol rate 27500
Polarization:- vertical
FEC :- 7/8

በፌስቡክ 🔗https://www.facebook.com/daewatv/

ቴሌግራም 🔗
http://t.me/daewatv2013

ዩትዩብ 🔗
https://www.youtube.com/channel/UCrF8wiLRD4IIE1-5-73zdAg

||ደዕዋ ቲቪ /daewa tv ቢሉ ያገኙናል

#ደዕዋ ቲቪ
ጉዞ ስንቅን ይዞ!
ነሲሓ ቲቪን ለማስቀጠል የ1000ብር የድጋፍ ዘመቻ ይፋ ተደርጓል!አንድ ሺህ ብር ያለው ሁሉ ድጋፍ በማድረግ ዳዕዋውን በማስቀጠል የማይቋረጥ አጅር ያግኙ!
የንግድ ባንክ
1000145615929 ኢብኑ መስዑድ
ኢባዳችንን(መልካም ስራችንን) ለፌስብክ እይታ??

አቡ ዳውድ ኡስማን

መልካም ስራዎች በሙሉ በአላህ ዘንድ ተቀበቀይነት የሚያገኙት የተስተካከለ ኒያ ሲኖረው፣ለአላህ ተብሎ ጥርት ተደርጎ ሲሰራ (በኢኽላስ) እና የምንሰራው ኢባዳ በሱናው በተደነገገው መሰረት ከሆነ ብቻ ነው፡፡ ሰዎች እንዲያዩልን ብለን የምንሰራቸው መልካም ስራዎች ሁሉ በአላህ ዘንድ ተቀባይነት አይኖራቸውም፡፡

ሞኝነታችን በዝቶ የምንሰራቸውን መልካም ስራዎች ሰዎች አይተው እንዲያደንቁን ስንል ስራችንን ሰዎች እንዲያዩልን እንጥራለን፡፡ ሰዎች ሰላት ሲሰግዱ ሰው እያያቸው ከሆነ አሳምረው ይሰግዳሉ፡፡ ሰው ከሌለ ግን በሩጫ ሰግደው ይጨርሳሉ፡፡ የሚሰሩትን መልካም ስራ ሁሉ በአደባባይ እንዲታይላቸው ይፈልጋሉ፡፡

በአሁኑ ወቅት ደግሞ ሰዎች መልካም ስራቸውን ሰው እንዲያውቅላቸው ከሚያደርጉበት መንገዶች ፌስቡክ ቀዳሚውን ስፍራ ወስዷል፡፡ ሌሎች በኸይር ስራ ላይ እንዲበረታቱ ለማድረግ ተብሎ ለማነሳሳት ከሚተላለፉ መልዕክቶች ውጪ የግል መልካም ስራዎች ጎልተው እንዲወጡ ይደረጋሉ፡፡

ዛሬ እዚህ መስጂድ ገብቼ የመጀመሪያ ሰፍ ጀምዓ ሰገድኩኝ፣ዛሬ ሱና ፆም ፆምኩኝ፣ ሃጅ አደረኩኝ፣ኡመራ አደረኩኝ፣ሰደቃ ስሰጥ ዋልኩኝ፣ ዳዕዋ በየቦታው ሳደርግ ነበር፣እንዲህ አይነት ኢባዳ ስሰራ አደርኩኝ፣ ይህን ያህል ጁዝ ቁርዓን ዛሬ ቀራሁኝ፣ ለይል ስሰግድ አደርኩኝ ወዘተ … እየተባለ ፖስት ይደረጋል፡፡ ከዚህ ሲብስም ለምሳሌ ሰዎች ኡመራ ወይም ሃጅ እንዳደረጉ ሰው እንዲያወቅላቸው ወይም ለሰው ለማሳየት ጠዋፍ ሲያደርጉ ካዕባ ጋር ሆነው ፎቶ ተነስተው በፌስቡ ይለቃሉ፡፡አንዳንዱ ደግሞ አረፋ ተራራ ላይ ሆኖ እያለቀሰ አላህን እየለመነ ሌላኛው ጓደኛው ፎቶ እንዲያነሳው አድረጎ በፌስቡክ ላይ ይለቃል፡፡

ይህን ኢባዳ ፈፅመን ለሰዎች ለማሳየት መጣርም ጉረኝነትም ነው፡፡ ጉረኛ ሰውን ደግሞ አላህ አይወደውም፡፡

إِنَّ اللَّـهَ لَا يُحِبُّ مَن كَانَ مُخْتَالًا فَخُورً‌ا
አላህ ኩራተኛ ጉረኛ የኾነን ሰው አይወድም፡፡(4:36)

ብዙ መልካም ስራዎች ተሰርተው በፌስቡክ እዩልኝ እና ስሙልኝ በሚል ፎቶዎች እና መልዕክቶችን በመልቀቅ የሰራነው መልካም ስራ አመድ ሆኖ እንዲቀር ይደረጋል፡፡

አላህ በቁርአኑ ለሰዎች ተብሎ ኢባዳን የሚያሳምሩትን፣እዩልኝ ይስሙልኝ ብለው የሚሰሩ ሰዎችን ወዮላቸው ሲል አስጠንቅቋል፡፡

فَوَيْلٌ لِّلْمُصَلِّينَ ﴿٤﴾ الَّذِينَ هُمْ عَن صَلَاتِهِمْ سَاهُونَ ﴿٥﴾ الَّذِينَ هُمْ يُرَ‌اءُونَ ﴿٦﴾

ወዮላቸው ለሰጋጆች፡፡ለእነዚያ እነርሱ ከስግደታቸው ዘንጊዎች ለኾኑት፤ (ሰጋጆች)፡፡ለእነዚያ እነርሱ ይዩልኝ ባዮች ለኾኑት፡፡(107፡3-6)

ነብዩ(ሰ.ዐ.ወ) ከሃሰተኛ ነብይ ይልቅ የምፈራላችሁ ድብቁን ሽርክ ነው ብለዋል፡፡ ድብቁ ሽርክ ምንድነው ተብለው ሲጠየቁ አንድ ሰው ሰላት ለመስገድ ይቆማል፡፡ ሌላ ሰው እየተመለከተው መሆኑ ሲያውቅ ሰላቱን እጅግ አሳምሮ ይፈፅማል ብለዋል፡፡(ኢማሙ አህመድ ዘግበውታል)

ለእዩልኝ እና ይስሙልኝ ብሎ መልካም ስራ መስራት ትንሹ ሽርክ ነው፡፡ ከሽርክ(በአላህ ላይ ከማጋራት) ተግባራት ትንሹ ይሁን እንጂ ከወንጀሎች ሁሉ ግን ትልቁ መሆኑን ኡለሞች ይናገራሉ፡፡

ለሰዎች እዩልኝ እና ይስሙልኝ ብለን መልካም ስራዎችን ከመስራት አላህ ይጠብቀን!!

አሚን!!
አሚን!!

۩○◙◙○◙◙○◙◙○◙◙○۩
ወቅታዊ መረጃዎችን እና ኢስላማዊ ትምህርቶችን ለማግኘት ይህን ገፅ ላይክ ያድርጉ
Click and Like ➤➤ @ https://www.facebook.com/abudawdosman
በቴሌግራም ለመከታተል ከዚህ በታች ያለውን ሊንክ በመጫን መቀላቀል ይችላሉ
Click and Like ➤➤ @ https://telegram.me/abudawdosman
ያበደ ውሻን ይሩቁታል እንጂ አይታገሉትም

አቡ ዳውድ ኡስማን

የአማራ ክልል የእስልምና ጉዳዮች ፅ/ቤት የከተራ በኣልን ለማክበር በወጡ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ጥቃት ተፈፅሞበታል::

ይህን ነውረኛ ድርጊትን ሲፈፅሙም አስነዋሪ ስድብ እየተሳደቡ እንደነበር ተገልፆል::

ይህን አሳፋሪ ድርጊት የፈፀሙ ፅንፈኞች አላማቸው በውስጣቸው ያለውን የእስልምና ጥላቻ ለማንፀባረቅ ቢሆንም ቢሳካላቸው ይህን ትንኮሳ በመፈፀም ሰላማዊ የበዓሉን ታዳሚያን ከሙስሊሙ ማህበረሰብ ጋር ለማጋጨት ነበር::

ይህን ድርጊት በመፈፀማቸው በሃይማኖታቸው ምን አይነት መንፈሳዊ ጥቅም ያገኙበት ይሆን???

ጌታችን አላህ ለኛ ያላቸውን ጥላቻ ቀድሞ በቅዱስ ቃሉ ስለነገረን ድርጊታቸው አዲስ አይሆንብንም!

እቺ ሃገር በሙስሊሙ ታጋሽነት እና ቻይነት እስካሁን መዝለቅ ቻለች እንጂ እንደ አክራሪ ደብተራዎች ምኞት ቢሆን እርስ በእርስ በተላለቅን ነበር::

ዛሬም ትንኮሳቸው ግጭት መፍጠር ቢሆንም በአርቆ አስተዋዩ ህዝበ ሙስሊም በትዕግስት እና ንቆ በማለፍ ሴራቸውን እያከሸፈ የሃገሩን ሰላም እያስጠበቀ ይቀጥላል

የክልሉ የፀጥታ ሃይሎች ይህን ትንኮሳ የፈፀሙ ፅንፈኞችን ይዞ ለህግ ማቅረብ ግዴታው ነው:: እንደተለመደው ባልሰማ እና ባላየ ያልፉታል ወይስ ሃላፊነታቸውን ይወጣሉ የሚሉውን አብረን የምናይ ይሆናል!

የክልሉ ሙስሊሞች አብሽሩ:-

ውሻ ተናከሰ ተብሎ እሱን መልሶ ለመንከስ እንደማይሞከረው ሁሉ በጥላቻ በታወሩ ደብተራዎች ድርጊትም ብዙ አትሸበሩ:: ሁሌም በጥበብ እና በትዕግስት ትንኮሳዎችን እንደምታልፉት ሁሉ አሁንም በትዕግስት እለፉት:: ያበደ ውሻን ይሩቁታል እንጂ አይታገሉትም
ሼይኽ ያህያ ኡስማን አል ሙደሪስ ወደ አኼራ ሄደዋል

አቡ ዳውድ ኡስማን

በመስጂደል ሀረም ለ70 አመታት ኢልም ሲያቀሩ ያሳለፉት ታላቅ አሊም እና ሙሀዲስ ሼይኽ ያህያ ኡስማን አል ሙደሪስ ወደ አኼራ ሄደዋል:: ኢና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን

እኚህ አሊም ለ 70አመታት ሳያቋርጡ በሳምንት ሰባቱንም ቀን በቋሚነት በተከበረው መስጂደል ሃረም ኢልም ያቀሩ ነበር::

እውቅ ከሆኑ የሳቸው ተማሪዎች መካከል የመስጂደል ሀረም ኢማም የነበሩት ሼይሕ ኡመር ቢን ሙሐመድ ሱቤይል (ረሂመሁላህ) ተጠቃሽ ናቸው::

ምንኛ መታደል ነው በተከበረው ቤቱ ውስጥ ለ70 አመታት የአላህን እና የመልእክተኛውን ቃል እያስተማሩ ማሳለፍ?

ሞት በሁሉም ነፍስ ላይ የሚወድቅ ግዴታ ነውና እኚህ ታላቅ አሊምም የዱንያ ቆይታቸውን አጠናቀው ወደ አኼራ ሄደዋልል::

አላህ ይዘንላቸው፣ ማረፊያቸውንም በጀነተል ፊርዶስ ያድርግላቸው፣ መልካም ስራቸውን ሁሉ ይቀበላቸው

አሚንንን
The account of the user that owns this channel has been inactive for the last 5 months. If it remains inactive in the next 30 days, that account will self-destruct and this channel may no longer have an owner.
በሳኡዲ የመጅሊሱ አካውንት ተቀምጦ የነበረው የሶማሌ ክልል ሁጃጆጅ ገንዘብ

አቡ ዳውድ ኡስማን

ከ 3 አመት በፊት ሀጅ ሳይሄዱ የቀሩት 423የሶማሌ ክልል ሁጃጆች ገንዘብ በወቅቱ በባንክ በኩል ተልኮ 3.4 ሚሊዮን ሪያል በሳኡዲ የመጅሊሱ አካውንት ገቢ ተደርጎ ነበር!

ሁጃጆቹ መሄድ ሳይችሉ ሲቀር ገንዘባቸው ከሳኡዲ የሐጅ ሚኒስተር የመጅሊሱ አካውንት ወጪ ሆኖ እንዲመለስ ደብዳቤ እንዲፅፉ የተጠየቁት ሐጂ ኡመር ኢድሪስ ዘለቀ ተመላሽ እንዲሆን ደብዳቤ አልፅፍም አሻፈረኝ በማለታቸው ላለፉት ሶስት አመታት ገንዘባቸው በሳዑዲ የሐጅ ሚኒስተር የመጅሊሱ አካውንት ውስጥ በዝግ ሂሳብ ተቀምጦ ቆይቷል::

አሁን የሀጅ ዉቅት በመድረሱ አካውንቱ ወደ ተንቀሳቃሽ ሂሳብ በመዞሩ ገንዘባቸው ተበልቷል እያሉ ሲቀጥፉ የነበሩት ቀጣፊዎች አይናቸውን በጨው አጥበው ብራችሁ ቢበላም አሁን ከራሳችን አውጥተን የሱማሌ ክልል ሀጃጆች ሀጅ እንዲያደርጉ ወስነናል ብለው በራሳቸው ምላስ ያጡትን ገፅታ ህፃን ልጆችን እንኳን ማሳመን የማይችል አመክንዬ በማቅረብ ገፅታቸውን ለመገንባት ውድቅ ሙከራ ለማድረግ ሞክረዋል!
አስቡት የሰራተኛ ደሞዝ እንኳን መክፈል አቅቶት የነበረ ተቋም፣ ላስገነባው ህንፃ ከመቶ ሚሊዮን ብር በላይ እዳ ያለበት ተቋም፣ ከሚስኪኑ ህዝብ የአገልግሎት እያለ ከ8እስከ 12ሽህ ብር እየያስከፈለ ያለ ተቋም፣ በዘንድሮ አመት እንኳን ሀጅ መሄድ ሳይችሉ ቀርተው ገንዘባችንን መልሱልን እያሉ ቀን እና ማታ አፈር ላይ እየተኙ ሲንገላቱ ለከረሙ ሚስኪን አዛውንት እናት እና አባቶች የተቋሙን መስታወት በድንጋይ እየመቱ ኑው በማለት ለፖሊስ በሀሰት በመወንጀል ከግቢው አስደብድበው ለማባረር የሚጥሩ ክብር የማያውቁ ክብር ቢስ ሰዎች፣ ሶስት አመታት ሲያንገላታቸው ለነበሩ ሁጃጆች አዝኖ ከኪሱ አውጥቶ ሐጅ ሲያስደርግ አስቡት ?

የሱማሌ ክልል ሁጃጆች ገንዘባቸውበወቅቱ ከሳኡዲ እንዳይመለስ ማን እንዳደረገው ጠንቅቀው ያውቃሉ::/በክልሉ መንግስት በኩል ሳይቀር በኡለሞች እና በሽማግሌዎች በኩል ገንዘቡ ከሳኡዲ እንዲመለስ መጅሊሱ እንዲያደርግ ተጠይቋል:: አሻፈረኝ ተብሎ እስካሁን ቢቆይም::ይህን እውነታ የሶማሌ ክልል ኡለሞች በይፋ ለህዝባቸው አሳውቀዋል::

የሶማሌ ክልል ሁጃጆች የሰጡትን ምስክርነት በሀሩን ሚዲያ መመልከት ትችላላችሁ

https://youtu.be/vFvlVFZBNzo

አሁን ላይ የሶማሌ ክልል ሁጃጆች ሀጅ ከሄዱም ለሶስት አመታት ገንዘባቹ ተበልቷል እየተባሉ ሲዋሹት በነበረው በራሳቸው ገንዘብ ነው:: በዘንድሮ አመት ሐጅ መሄድ ያልቻሉ ካሉም ገንዘባቸውን የሚቀበሉት የማንም ቀጣፊ በግል ችሮታው የሚመልስላቸው ሳይሆን ሶስት አመታት በሳኡዲ በመጅሊሱ አካውንት ተቀምጦ ከነበረው የራሳቸው ገንዘብ ነው::

ሶስት አመታት ሙሉ ኦዲት አንደርግም እየተባለ ሲሸሽ የነበረው የሱማሌ ክልል ሀጃጆች ገንዘብ በቦርዱ ተበልቷል እያሉ ሲሰብኩ የነበሩት ቅጥፈት ስለሚጋለጥባቸው ነበር::

ዞሮ ዞሮ ሶስት አመት ሲቀጥፉ ቢሰነብቱም የሱማሌ ክልል ሁጃጆች ገንዘብ ተበልቷል እያሉ መቆየት በኦዲት የሚረጋገጥ መሆኑ አይቀሬ በመሆኑ አሁን ላይ ገንዘባቸው ከተቀመጠበት ወጥቶ አገልግሎት ላይ ውሏል::

የሚገርመው ግን ከ 40ሚሊዬን ብር በላይ የሀጃጆቹ ገንዘብ ተበልቷል እያሉ ሶስት አመታት ሙሉ እየሰበኩ ሲቆዩ ይህን ሁላ ሶስት አመት በኦዲት ገንዘቡ መበላቱን አረጋግጦ ለህዝብ ማሳወቅ እና በህግ እንዲጠየቁ አለማድረጋቸው እራሳቸውን በወንጀል የሚያስጠይቅ መሆኑን አለማወቃቸው/ነው::የህዝብ ገንዘብ ተዘርፎ ዘራፊውን በህግ ሳይጠይቁ ሶስት አመት ዝም ማለት ዘርፈዋል ከተባሉት ጋር እኩል የወንጀሉ ተባባሪነት መሆኑን ዘንግተውታል:: ሌባ ሲዘርፍ እያዩ ዝም ማለት በህግ ያስጠይቃል:: እነሱስ ገንዘቡ ሲዘረፍ የማንን ጎፈሬ ሲያበጥሩ ነበር መባላቸው አይቀርም::

እውነታው ግን ገንዘቡ ተበልቶ ሳይሆን በሳኡዲ የመጅሊሱ አካውንት በዝግ አካውንት እስካሁን ተቀምጦ ስለነበር እና አሁን ሲከፈት ገንዘቡን አውጥተው ለሁጃጆቹ አገልግሎት ላይ እንዲውል ማድረጋቸው ነው::

መጅሊሱ በህጋዊ የውጪ ኦዲተር ይመርመር እና እውነታው ይውጣ በተባለ ቁጥር መጅሊሱ ለሁለት ይከፈል እያሉ ሲሸሹ የነበሩት እነማን እንደሆኑ ሁሉም ያውቀዋል!

የኦዲት ሽሽት በዱኒያ ቢያመልጡት በአኼራ ግን ማምለጫ የለውም!

ነገም አላህ ውሸታሞችን እና ቀጣፊዎችን እንዲህ ያዋርዳቸዋል!

የነገር የአረፋ ቀን የዙልሒጃ 9 ፆም እንዳያልፈን

ነብዩ ሙሀመድ ሶለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ፐአረፋን ፆም አስመልክተው እንዲህ ብለዋል:-

የአረፋ ቀን ፆም ያለፈን የአንድ አመት ሀጥያት እና ወደፊት የሚመጣን የአንድ አመት ሀጥያት ያስምራል"ብለዋል

ይህ ቀን ነገ ጁምዓ ነው እንዳያልፈን
በዛሬው የአረፋ ቀን በብዛት ማለት የሚወስድ ዚክር

لاَ إِلَـهَ إِلاَّ اللهُ وَحْدَهُ لاَ شَرِيْكَ لَهُ، لَهُ الْمُلْكُ وَلَهُ الْحَمْدُ، وَهُوَ عَلَى كُلِّ شَيْءٍ قَدِيْرٌ

‹ላኢላሀ ኢልለሏሁ ዋህደሁ ላሸሪከለህ፣ ለሁል ሙልኩ፣ ወለሁል ሐምድ ወሁወ ዐላ ኩልሊ ሸይኢን ቀዲር።

› «ከአላህ ውጭ በእዉነት የሚገዙት አምላክ የለም፡፡ አንድ ነው፡፡ አጋር የለውም፡፡ ንግሥና የርሱ ብቻ ነው፡፡ ምስጋናም ተገቢነቱ ለረርሱ ነው፡፡ እርሱ በሁሉም ነገር ላይ ቻይ ነው››
አስቸኳይ የድጋፍ ጥሪ

በሰጋጆች ድርቅ የተመታውን የዱራሜውን ቢላል መስጂድ ሁላችንም ለመታደግ እንረባረብ

አቡ ዳውድ ኡስማን

መዕክቱን አንብበው ሲጨርሱ ለሌሎችም ሼር ያድርጉት

በደቡብ ክልል በከምባታ ጠምባሮ ዞን በዱራሜ ከተማ በካሻ ቀበሌ አሮጌ ሰፈር የሚገኘው ቢላል መስጂድ አካባቢው የነበሩ ሙስሊሞች እንዲሁም የመስጂዱ ኢማም ሚስታቸው እና ልጃቸው ሳይቀር ከፍረው የመስጁዱ ሙዓዚን እና ኢማም የሆኑት ሼይኽ መሐመድ ኑር ብቻቸውን በመስጂዱ እየሰገዱ እንደሚገኙ መገለፁ ይታወሳል::

በዚህ ትልቅ መስጂድ ውስጥ ብቻቸውን አዛን እያወጡ ብቻቸውን ኢቃም ብለው እንደሚሰግዱ መገለፁን ተከትሎ ከፍተኛ ቁጭት እና ሀዘን በሁላችንም ላይ ተፈጥሯል::

መስጁዱ በእድሳት እጥረት በመጎዳቱ ዝናብም እያፈሰሰ እንደሚገኝ እንዲሁም ሌሎች እድሳቶችም እንደሚያስፈልገው ተገልፆ ነበር::

የአካባቢውን ሙስሊሙ ማህበረሰብ ወደ ዲናቸው እንዲመለሱ፣ ባዶ የሆነው መስጂድም በጀምዓ እንዲሞላ፣ የከፈሩትንም ለመመለስ ህዝበ ሙስሊሙ በአንድነት ትብብር እንዲያደርግ ጥሪ ቀርቦ ነበር::

ይህን አሳሳቢ ጉዳይ ቀድሞ መረጃው የደረሳቸው በደቡብ ክልል የአክፍሮት ሃይላትን የኩፍር ዘመቻ ለመመከት መሬት ላይ የወረዱ በርካታ ፕሬጀክቶችን፣ መስጂዶችን እና መድረሳዎችን እያሰሩ የሚገኙት ተወዳጁ ኡስታዛችን ኡስታዝ ሷዲቅ መሐመድ(አቡ ሐይደር) ይህንንም የዱራሜ መስጂድ ጉዳይ መፍትሄ እንዲያገኝ እየለፉ ይገኛሉ::

በዚህም መሰረት ይህን መስጂድ ለመታደግ እና የአክፍሮት ሃይላትን እንቅስቃሴ በመመከት የአካባቢውን ህዝበ ሙስሊም ወደ ዲኑ ለመመለስ ይቻል ዘንድ ሁሉም ህዝበ ሙስሊም ያቅሙን ያህል ድጋፍ የሚያደርግበት ሁኔታ ተመቻችቷል::

በኡስታዝ ሷዲቅ መሐመድ (አቡ ሃይደር ) አስተባባሪነት
በዱራሜ ከተማ በካሻ ቀበሌ አሮጌ ሰፈር የሚገኘው በዚሁ የቢላል መስጂድን ማዕከል የሚያደርግ እንቅስቃሴ ተጀምሯል::

በቀዳሚነት ለመስጂዱ ቋሚ ኡስታዝ መቅጠር እንዲሁም መስጂዱ በሚገኝበት በዱራሜ ከተማ በዱራሜ ዩኒቨርሲቲ ለሚገኙ የዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች በዚህ መስጁድ ላይ ታላቅ የዳዕዋ ኮንፍረንስ ለማካሄድ ዝግጅት እየተደረገ ይገኛል::

ይህ ኮንፍረንስ ከነሐሴ 13-15/2014 ለሶስት ቀናት ኢማሙ ብቻቸውን ሲሰግዱበት በነበረው ቢላል መስጂድ የሚሰጥ ይሆናል::

ይህ ታላቅ ኮንፍረስ ሙስሊም የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን ማዕከል በማድረግ በአካባቢው ያለውን የኩፍር ዘመቻ ለመመከት እና ሰዎች ወደ ዲናቸው እንዲመለሱ እንዲሁም የመስጁዱን ጀምዓ በማጠናከር ሰፊ ስራዎችን ለመስራት የሚያግዝ ነው::

አሁን ላይ የሁላችንንም ርብርብ እና ድጋፍ የሚሹ ወጪዎች ያሉ ሲሆን እነዚህም:-

1/ ቋሚ የኢማም ደሞዝ ክፍያ
2/ የመሰጂዱ አጥርን ማሳጠር
3/ መስጁዱ የጎደለውን ነገር ሁሉ ማሟላት እና
4/ ለታሰበው ታላቅ የዳዕዋ ኮንፍራንስ ወጪውን መሸፈን ይገኝበታል:

በአሁኑ ሰዓት ብቸኛ የነበሩትን ሼይኽ መሐመድኑርን የሚያግዝ በመስጁዱ በቋሚነት ሊያገልግል የሚችል ብቁ ኡስታዝ የተገኘ ሲሆን በዋናነት ኡስታዙም የመስጁዱ ኢማም በቋሚነት በመሆን እንዲያገለግል፣ ከዐሱር በኋላ ልጆችን እንዲያቀራ እንዲሁም ለካምፓሱ ተማሪዎች ኪታብ እንዲያቀራ ታስቧል::

እነዚህን አስቸኳይ ስራዎች በመስጂዱ ለመስራት በሀገር ውስጥም ሆነ ከሃገር ውጪ ያላችሁ የበኩላችሁም ድጋፍ ታደርጉ ዘንድ በአላህ ስም እንጠይቃለን::

በተከሰተው ነገር ከንፈር መምጠት እና ማዘን ብቻ ሳይሆን የመፍትሄ ሃሳብ ሲቀርብም ሁላችንም በቻልነው ያህል ማገዝ ይጠበቅብናል:: መፍትሄው በአንድነት መሬት ላይ ሊወርድ የሚችል ስራ መስራት ስንችል ብቻ ነው::

ለተዘረዘሩት ወጪዎች ድጋፍ ማድረግ ለምትፈልጉ ሁሉ በኡስታዝ ሷዲቅ መሐመድ ስም በተከፈተው አካውንት ድጋፍ ማድረግ ትችላላችሁ

1. COMMERCIAL BANK OF ETHIOPIA
1000317507589
SADIK MOHAMMED AHMED

2. ABYSSINIA BANK
83047178
SADIK MOHAMMED AHMED

3. ኦሮሚያ ህብረት ሥራ ባንክ
1011300008645
SADIK MOHAMMED AHMED

ለበለጠ መረጃ በዚህ ስልክ መደወል ትችላላችሁ
0911103231

ይህን መልዕክት ሁላችንም ሼር በማድረግ እናዳርስ!
ተመሳሳይ ሰብዓዊ ተግባር በተመሳሳይ ቦታ ተፈፅሞ እውቅናው ግን እምነት እየለዩ ብቻ የሚሰጥባት ሀገር

በሀገራችን ያለመድሎ በእኩልነት መልካም የሰሩ ሰዎችን እኩል የምናመሰግንበት፣ ያጠፉትንም እኩል የምንኮንንበት ሚዛን መቼ ይሆን የምናገኘው??

ሁሌም እምነት እና ብሄር እየለዩ ማሞገስ እና
እውቅና. መቸር የት ያደርሰን ይሆን??

በድሮ አስተሳሰብ ተቸንክሮ ለቀረ አካል መች ይሄ ይገባቸዋል?

©አቡ ዳውድ ኡስማን
ይህን አዲሱን የቴሌግራም ቻናሌን ጆይን ማድረግ ትችላላችሁ
https://t.me/abudawdosman1
ይህን አዲሱን የቴሌግራም ቻናሌን ጆይን ማድረግ ትችላላችሁ
https://t.me/abudawdosman1
ይህን አዲሱን የቴሌግራም ቻናሌን ጆይን ማድረግ ትችላላችሁ
https://t.me/abudawdosman1