AAU Portal
1.02K subscribers
1.04K photos
16 videos
136 files
578 links
🎓 Everything about Addis Ababa University in one place
📢 Announcements & academic alerts
📅 Schedules & important dates
🎓 Scholarships & opportunities
🏫 Campus news & student resources
⚠️ Unofficial
📚
DM @My1021122
Download Telegram
የምዝገባ ማሰታወቂያ

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሞዴል ማህበረሰብ ትምህርት ቤት በ 2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ልጆቻችሁን ለማስተማር ያመለከታችሁ እና ተቀባይነት ላገኛችሁ ወላጆች በሙሉ፡-
 
1ኛ. ምዝገባ ከነሐሴ 27-29 2018 ዓ.ም 5 ኪሎ (ማመልከቻ ባስገባችሁበት ቦታ) ይካሄዳል፡፡

2ኛ. ስለምዝገባ ክፍያ መጠን እና አከፋፈል መረጃ ከምዝገባ ቦታ ታገኛላችሁ፡፡

3ኛ. ስለ ተማሪዎች የደንብ ልብስ ናሙና እና መረጃ  ከምዝገባ ቦታ ታገኛላችሁ፡፡
 
የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የሞዴል ማህበረሰብ ትምህርት ቤት
3
ማስታወሻ፡

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ (AAU) ፖርታል የመመዝገቢያ ሂደት

ለአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የ UAT ፈተና ምዝገባ ነሐሴ 19 መጀመሩ ይታወቃል። በመሆኑም እንዴት መመዝገብ እንዳለባችሁ የሚከተለውን ደረጃ በደረጃ የተቀመጠ መመሪያ ተከተሉ፡

ምዝገባ ከመጀመራችሁ በፊት፡
Cost Sharing (በመንግስት ወጪ እንዲሸፈንላችሁ የምትፈልጉ)፡ ከቀበሌ ወይም ወላጆቻችሁ/ቤተሰቦቻችሁ ከሚሠሩበት መሥሪያ ቤት ደብዳቤ አጻፉ (አዘጋጁ)።

ፋይዳ ቁጥር (Fayda Number)፡ ሁላችሁም የግዴታ የፋይዳ ቁጥር ሊኖራችሁ ይገባል።

የመመዝገቢያ ደረጃዎች (Step-by-Step Process)
ደረጃ 1፡ ፖርታሉን ክፈቱ (Open Portal)

ወደ AAU Admission Portal ይግቡ፡ https://admission.aau.edu.et

ደረጃ 2፡ ወደ Application ገጽ ሂዱ

ከላይ በስተግራ በኩል Undergraduate application የሚለውን ተጫኑ።

ከ Undergraduate Student ስር Apply የሚለውን ምረጡ።

Call for Undergraduate Regular Admission የሚለውን ተጫኑ።

የትምህርት ፕሮግራሞቹን ከተመለከታችሁ በኋላ Apply now የሚለውን ይጫኑ።

ደረጃ 3፡ Fayda ቁጥር ማረጋገጥ (FAYDA Validation)

የ FAYDA ቁጥራችሁን አስገቡ።

Validate የሚለውን ተጫኑ።

በስልካችሁ በ SMS የሚላክላችሁን OTP ቁጥር አስገቡ።

ደረጃ 4፡ አካውንት ክፈቱ (Create Account)

የሚሰራ የኢሜይል አድራሻ (Working email) ተጠቀሙ።

ቢያንስ 8 የፊደል/ቁጥር ርዝመት ያለው የይለፍ ቃል (Password) ፍጠሩ።

የመጀመሪያ አካውንት አፈጣጠሩን ከጨረሳችሁ በኋላ ሁልጊዜ በኢሜይላችሁና በፓስወርዳችሁ LOG IN እያደረጋችሁ መጠቀም ትችላላችሁ።

ደረጃ 5፡ የትምህርት መረጃ መሙላት (Academic Profile)

"Your Academic Profile" የሚለውን ፎርም ትክክለኛ መረጃችሁን በመሙላት አጠናቅቁ።

UPDATE የሚለውን ከተጫናችሁ በኋላ NEXT የሚለውን ምረጡ።

ደረጃ 6፡ የመግቢያ ዓይነት መምረጥ (Admission Type)

በ Admission type ስር Regular የሚለውን ምረጡ።

ደረጃ 7፡ የትምህርት ክፍያ ዓይነት (Financing Your Study)

ከሁለቱ አንዱን ምረጡ፡ Cost-sharing sponsorship (በመንግስት) ወይም Self-Sponsorship (በግል)።

ለ Cost-Sharing (በመንግስት ለሚሸፈን)፡

ከተዘረዘሩት ምክንያቶች መካከል ቢያንስ አንዱን ተገቢ ምክንያት ምረጡ።

የተዘጋጀውን ማስረጃ በ PDF format (መጠናቸው ከ 5MB ያልበለጠ) አያይዙ (Attach አድርጉ)።

ደረጃ 8፡ የትምህርት ፕሮግራም ምርጫ (Program Choice)

Continue የሚለውን ተጫኑ።

Self-Sponsored (በግል) ከሆናችሁ፡ ከ Program Choice ፎርም ላይ 10 የትምህርት ምርጫዎችን ምረጡ።

ደረጃ 9፡ የFreshman ዘርፍ ምርጫ (ለ Cost-Sharing ብቻ)

ከሁለቱ አንዱን ምረጡ፡ Natural Science Freshman ወይም Social Science Freshman።

ከዚያ Continue የሚለውን ተጫኑ።

ደረጃ 10፡ ሰነዶችን መስቀል (Upload Documents)

የሚከተሉትን ሰነዶች በ PDF format (እያንዳንዳቸው ከ 5MB ያልበለጠ) Upload አድርጉ፡

የ12ኛ ክፍል ውጤት ሰርተፊኬት (12th-grade result certificate)

ከ9ኛ - 12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት (9th-12th transcript)

ደረጃ 11፡ የፈተና ቦታ መምረጥ (Exam Location)

የ UAT ፈተና መፈተን የምትፈልጉበትን ቦታ ከ Drop-down አማራጮች ውስጥ ምረጡ።

ደረጃ 12፡ ስምምነት ማረጋገጥ (Consent)

የስምምነት ጽሑፉን (Consent Statements) አንብቡ።

Accept የሚለውን ምረጡ።

ከዚያ CONTINUE የሚለውን ተጫኑ።

ደረጃ 13፡ መረጃን መከለስ እና ማረጋገጥ (Review Application)

የሞላችሁትን መረጃ ለመከለስ View summary የሚለውን ተጫኑ።

ማስተካከል የምትፈልጉት ነገር ካለ ከላይ የሚገኘውን Academic Profile የሚለውን ቁልፍ በመጫን ማስተካከል ትችላላችሁ።

ደረጃ 14፡ ክፍያ መፈጸም (Payment)

Continue to Payment የሚለውን ተጫኑ።

Proceed to Payment የሚለውን ምረጡ።

Completion of payment የሚለውን ተጫኑ።

750 ብር (ETB 750) በ Telebirr ይክፈሉ ወይም የተሰጠውን QR code Scan በማድረግ ክፍያውን ፈጽሙ።

ደረጃ 15፡ ከክፍያ በኋላ (After Payment)

የፈተና መግቢያ ቲኬት ለማውጣት UAT ADMISSION TICKET የሚለውን ተጫኑ።

የፈተና ፕሮግራም ለማየት EXAM SCHEDULE የሚለውን ተጫኑ።

የክፍያ መረጃ (Payment Information)
የምዝገባና የ UAT ፈተና ክፍያ፡ 750 ETB

የመክፈያ መንገድ፡ Telebirr ወይም QR Code Scan በማድረግ

ተጨማሪ ማስታወሻ፡ መግቢያ ፈተናውን የሚፈተኑት 25ሺ በላይ ተማሪዎች ሲሆኑ አልፈው የሚገቡት 5ሺ ብቻ ናቸው። ጊዜው ሳይሄድ ዛሬውኑ ተመዝግባችሁ ጥናት ጀምሩ።

@AAUPortal
3
My UAT experience via voice
2019Academic Calender 2026_27_FINAL.pdf
456 KB
AAU 2019 E.C Academic Calender

🗄Registrar office
📢 REMINDER – PTR TENNIS COACHING COURSE 🎾
The Commercial Graduates Association (CGA) in collaboration with Addis Ababa Tennis Federation, reminds all registered and interested tennis coaches about the upcoming PTR Tennis Coaching Course.
📅 August 31 – September 3, 2026
📍 CGA Tennis Court, Addis Ababa
👨‍🏫 Coach: Habtu A. Belayneh
🎾 Don’t miss this opportunity to upgrade your coaching skills and strengthen your professional career!
Please be present on time and come prepared for the training.
👉 Register here:
https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLSf2To35Rb1LhYcu8GpGDLJewm87K3wB20HRUOpaKhGarNxkNg/viewform?usp=publish-editor
CGA – Promoting Professionalism, Empowering Youth, and Building Healthy Lives Through Tennis Since 1950.

🎾 Develop Your Skills. Develop Tennis.
I built a free UAT practice simulator for AAU applicants, full 150-minute, two-section mock exam (Verbal + Quantitative) with real timing, question flagging, and instant score breakdown. No signup, just practice. Check it out

https://free-aau-uat-simulator.vercel.app/
#Reposted
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በ2019 የትምህርት ዘመን በቅድመ-ምረቃ መደበኛ መርሐግብር (በመንግሥት ስኮላርሺፕ እና በግል ክፍያ) እንዲሁም በማታና ተከታታይ መርሐግብር አዲስ ተማሪዎችን ተቀብሎ ማስተማር ይፈልጋል።

መስፈርቶች
➻ በ2015፣ 2016፣ 2017 እና 2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ መልቀቂያ ፈተና ወስደው የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ነጥብ ያመጡ ወይም ደረጃ 4 አጠናቀው (COC) ያለፉ
➻ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሚሰጠውን የመግቢያ ፈተና (UAT) ይወስዳሉ

የምዝገባ ጊዜ 👇
እስከ ነሐሴ 29/2018 ዓ.ም ድረስ

ኦንላይን ይመዝገቡ 👇
https://admission.aau.edu.et

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የመግቢያ ፈተና (UAT) ከጳጉሜን 02-04/2018 ዓ.ም ይሰጣል፡፡
2019Academic Calender@AAUPortal2026_27_FINAL.pdf
456 KB
AAU 2019 E.C Academic Calender

🗄Registrar office

Join & share👇
      @AAUPortal
#AAU

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲው ውስጥ በሚያገኙት አገልግሎት የሚሰማቸው እርካታ ዝቅተኛ መሆኑና ይህም ከሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች በዝቅተኝነት ቀዳሚ እንዳደረገው ጥናት አሳየ፡፡

ጥናቱ የቀረበው የትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ፖሊሲ ምርምር፣ የአመራር ልማት መርሃ ግብር እና የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የ2018 አፈጻጸም ዙሪያ በተዘጋጀው ውይይት ላይ ነው፡፡

ጥናቱን ያደረጉት ከተለያዩ ተቋማት የተውጣጡ አጥኚዎች ሲሆን፣ በ2017 እና በ2018 በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ በሚሰጠው አገልግሎት መምህራን፣ ተማሪዎች፣ የአስተዳደር ሰራተኞች እና ማህበረሰቡ ምን ያህል ደስተኛ ናቸው የሚለውን ለማወቅ ነው፡፡

በዚህ ጥናት መሰረት በ2017 የተሻለ ደረጃ ላይ የነበሩ በ2018 ዝቅ ማለታቸው የተነገረ ሲሆን፣ በተቃራኒው ባለፈው አመት ዝቅተኛ ደረጃ ላይ የነበሩት በዚህ አመት መሻሻል ማሳየታቸውን ጥናቱ ጠቁሟል፡፡

በጥናቱ 47ቱም የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች የተካተቱ ሲሆን፤ ከ16 ሺህ በላይ ተማሪዎች፣ ከ16 ሺህ በላይ መምህራን፣ ከ4 ሺህ በላይ የዩኒቨርሲቲ አስተዳደር ሰራተኞች እና 4 ሺህ የሚሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎች (በአጠቃላይ 61 ሺህ 431 ሰዎች) በጥናቱ ውስጥ ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

ከ47ቱ ዩኒቨርሲቲዎች በተማሪዎች የአገልግሎት እርካታ እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ቀዳሚውን ስፍራ ሲይዝ፣ ኦዳ ቡልቱ እና ወልድያ ዩኒቨርሲቲዎች ተከታዮቹን ደረጃዎች ይዘዋል፡፡

በተቃራኒው ደግሞ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በተማሪዎች አገልግሎት ደስተኛ አለመሆን ቀዳሚው ሲሆን ፣ መቀሌ እና ዋቻሞ ዩኒቨርሲቲዎች ተከታዮቹን ደረጃዎች ይዘዋል፡፡

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ ለፕሬዚዳንቱ "ምን ትላላችሁ?" ብለን ላቀረብንላቸው ጥያቄ ለጊዜው መልስ መስጠት እንደማይችሉ ነግረውናል፡፡

ከ47ቱ ዩኒቨርሲቲዎች መካከል በመምህራን "የተሻለ አገልግሎት ይሰጣል፤ ጥሩ ነው" በማለት የተመረጠው ኦዳ ቡልቱ ዩኒቨርሲቲ ቀዳሚው ሲሆን፣ ቀብሪደሃር እና ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲዎች ተከታዮቹን ደረጃዎች ይዘዋል፡፡

በእነዚህ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ የሚያስተምሩ መምህራን ለመምህራን በሚሰጠው አገልግሎት ጥሩ እርካታ እንዳላቸው ጥናቱ ጠቅሷል፡፡

መቀሌ ዩኒቨርሲቲ ዝቅተኛ የመምህራን እርካታ ያለበት ዩኒቨርሲቲ መሆኑን ጥናቱ ያሳየ ሲሆን፣ ዋቻሞ እና ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲዎች ተከታዮቹን ደረጃዎች ይይዛሉ፡፡

በዩኒቨርሲቲ አስተዳደር ሰራተኞች እርካታ ኦዳ ቡልቱ፣ ቀብሪደሃር እና ሰላሌ ዩኒቨርሲቲዎች ከፍተኛ እርካታ የተመዘገበባቸው ሲሆኑ፤ መቀሌ፣ ደብረ ማርቆስ እና መቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲዎች ደግሞ ዝቅተኛ ከተመዘገበባቸው መካከል ቀዳሚዎቹ ናቸው፡፡

ሀራማያ፣ አዲግራት እና ወልድያ ዩኒቨርሲቲዎች በአካባቢው ማህበረሰብ ዘንድ በሚሰጡት አገልግሎት ከፍተኛ እርካታ ከተመዘገበባቸው መካከል ሲሆኑ፤ ዲላ፣ ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ እና ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ደግሞ ዝቅተኛ የእርካታ ደረጃ ከተመዘገበባቸው መካከል ቀዳሚዎቹ መሆናቸውን ጥናቱ ጠቅሷል፡፡

ተማሪዎች በማደሪያና በመመገቢያ ስፍራዎች ላይ ከፍተኛ ቅሬታ እንዳላቸው የሚገልጸው ጥናቱ፤ የዩኒቨርሲቲ መምህራንም በደሞዝና ጥቅማ ጥቅም ደስተኛ ስላልሆኑ ይህም ሊታይ እንደሚገባ መክሯል::

#ሸገር ኤፍ ኤም

@AAUPortal
4
Test Day Guide.pdf
513.3 KB
Dear UAT Test Takers,
Please find attached the UAT Test Day Guide for your review and reference.
We wish you the best of luck on your examination!
Best regards,
AAU Testing Center
NOTICE Dear UAT Applicants,

Please find attached the examination venue schedule for the Undergraduate Admission Test (UAT), which will be administered on September 7–8, 2026, in three sessions each day:

Session I: 8:30 a.m. – 11:00 a.m.

Session II: 11:30 a.m. – 2:00 p.m.

Session III: 2:30 p.m. – 5:00 p.m.

https://aau.edu.et/announcements/detail?title=AAU~Undergraduate~Admission~Test~(UAT)~Schedule

Please carefully review the attached schedules provided in separate sheets within the same file. Check the sheet corresponding to your assigned examination venue and confirm your venue and examination time.

Please note that applicants who selected St. Paul’s MMC, Ethiopian Public Service University, or Kotebe University of Education, and were subsequently relocated to Addis Ababa Science and Technology University (AASTU)

Visually impaired candidates who selected AAU as their examination site are required to take the UAT at the Disability Centre, Lab 1 (Main Campus) on September 8, 2026, during Session III.

We wish you every success in your examination.

Sincerely,

AAU Testing Centre

@AAUPortal
Attention AAU UAT Applicants! 🚨
There has been confusion regarding the test center location listed as CHS (College of Health Sciences) for the upcoming Undergraduate Admission Test (UAT).
Please note that CHS is located at Tikur Anbessa Specialized Hospital Campus (around Lideta / Black Lion Hospital).
📍 Official Exam Location: Tikur Anbessa Campus (College of Health Sciences)
Please verify your exact venue, plan your route in advance, and make sure to arrive at the Tikur Anbessa site on time. Good luck with your exam!
Dear UAT Test Takers,
Please note that test takers who selected Ambo University as their examination venue will take the test at Hachalu Hundessa Campus, while those who selected Bahir Dar University will take the test at Poly Campus.
Sincerely,
Dear UAT Test Takers,
Please note that test takers who selected examination sites outside AAU will take the UAT on Monday, September 7, 2026, during Session II (11:30 a.m. – 2:00 p.m.).
The examination venues for the following sites are:
a)      Ambo University: Hachalu Hundessa Campus
b)      Bahir Dar University: Peda Campus
c)       Jimma University: Main Campus – CISCO Building and CISCO Lab
d)      Debre Markos University: Main Campus – Building 621 and Building 22
e)      Jijiga University: CB20, Computer Lab 1 (CB20-R1)
The examination venues for the remaining sites will be announced shortly. Please follow the updates or consult the UAT coordinator at your respective site for further information.
AAU_SoL-PG-applicants list.pdf
4.2 MB
👉🏾 Notice❗️
#AAU_School_of_Law
Postgraduate program applicants for school of law approved list for entrance exam (2026/2027 A.Y.) (Attached Here!)
Important Notice:
·  Entrance exam date: September 14, 2026 @ 2:00 PM
·  Exam place: AAU Digital Library
·  Applicants should come with their ID and GAT result or student copy
@AAUPortal