ህብረተሰቡ ስለ ስርዓተ-ምግብ በቂ ግንዛቤ እንዲኖረው ቢሮው በትኩረት እየተሰራ ነው፡፡
አ/አ/ጤና ቢሮ የካቲት 2 ቀን 2018 ዓ.ም
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ ህብረተሰቡ ስለ ስርዓተ-ምግብ በቂ ግንዛቤ እንዲኖረው እና በአግባቡ ተግባራዊ በማድረግ ጤንነቱ የተጠበቀ እንዲሆን የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራ እየሰራ ይገኛል፡፡
በተለይም በየቀኑ የምንበላው ምግብ የተመጣጠነ እንዲሆን የጥቃቅን ንጥረ-ነግሮች (Iron and folic acid, Vitamin A, Iodine, and zinc) እጥረት እንዳይከሰት ማድረግ ደግሞ በዋናነት ይጠቀሳል፡፡
ቢሮው በጉለሌ ክፍለ-ከተማ ውስጥ ባሉ ትምህርት ቤቶች እድሜያቸው ከ10-19 ለሆኑ ልጃገረዶች ሳምንታዊ የአይረንና ፎሊክ አሲድ እንክብል (WIFAS) እደላ በሙከራ ደረጃ ለመጀመር ዝግጅት እያደረገ ሲሆን ለፕሮግራሙ ውጤታማነት በክፍለ ከተማና በጤና ጣቢያ ደረጃ ላሉት የእናቶችና ህጻናት ቡድን አስተባባሪዎች ፣ የወጣቶችና አፍላ-ወጣቶች አገልግሎት ተጠሪዎች ፣ የስርዓተ-ምግብ ተጠሪዎች ፣ የትምህርት ጽህፈት ቤት ኃላፊዎች ፣ ለርዕሰ መምህራንና መምህራን ግንዛቤ መስጠት መቻሉን በቢሮው የእናቶችና ህጻናት ዳይሬክቶሬት የስርርዓተ-ምግብ ባለሞያ አቶ አብዮት ጠና ተናግረዋል፡፡
የአይረንና ፎሊክ አሲድ እደላ እስፈላጊነት ፣ እንዴት እንደሚጥ ፣ የክትትልና ድጋፍ አግባብ እንዲሁም አጠቃላይ አተገባበር ላይ ግንዛቤ ማስጨበጥ መቻሉን እና በቀጣይም በሌሎች ክፍለ ከተሞች ለማስፋት በትኩረት እንደሚሰራ ባለሞያው አቶ አብዮት ጠና ገልጸዋል፡፡

❤4👍1
የገላን ሆስፒታል ግንባታ በመጠናቀቅ ላይ ነው፡፡
አ/አ/ጤና ቢሮ የካቲት 3 ቀን 2018 ዓ.ም
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እና ጤና ቢሮ የህብረተሰቡን ፍትሐዊ የጤና ተደራሽነትን ለማረጋገጥ ከምንጊዜውም በላይ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ይገኛል፡፡
በከተማ አስተዳደሩ እየተገነቡ ከሚገኙ አዳዲስ ግዙፍ እና ዘመኑን የዋጁ ሆስፒታሎች መካከል በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የሚገኘው የገላን ሆስፒታል አንዱ ሲሆን ግንባታው በመጠናቀቅ ላይ ይገኛል፡፡
ሆስፒታሉ ባለ 2 ቤዝመንት እና ባለ7 ወለል(G+6) ህንጻ ሲሆን ከ500 በላይ አልጋዎች ያሉት እና በምስራቅ አፍሪካ የመጀመሪያው የድንገተኛ (የትራኦማ ) ማዕክል ሆኖ የተገነባ ነው፡፡
ሆስፒታሉ 8 ስታንዳርዳቸውን የጠበቁ የቀዶ ህክምና ክፍሎች እና የራሱ ኤር አምቡላንስ እና ማረፊያ ይኖረዋል፡፡
በተጨማሪም ሆስፒታሉ 6 ጥራታቸውን የጠበቁ እና እያንዳንዳቸው 10 አልጋዎች ያሉት የጽኑ ህሙማን ክፍሎች ይኖሩታል፡፡
ሆስፒታሉ በእያንዳንዱ ወለል ላይ ፋርማሲ እና ላብራቶሪ ከመኖሩ በተጨማሪ B+1 ላይ ሰፊ ጠቅላላ ላብራቶሪ እንዲሁም B+2 ላይ ሰፊ የመኪና ማቆሚያ ይኖረዋል፡፡
ሆስፒታሉ ግንባታው ተጠናቅቆ አገልግሎት መስጠት ሲጀምር ከአዲስ አበባ ከተማ ባለፈ እንደ ሃገር በሪፈራል ለሚመጡ ታካሚዎች አገልግሎት በመስጠት በጤናው ዘርፍ ከፍተኛ ሚና ከመጫወቱ በተጨማሪ አዲስ አበባ ከተማን የጤና ቱሪዝም ማዕከል ለማድረግ እየተሰራ በሚገኘው ሂደት ከፈተኛ አስተዋጽኦ ያበረክታል ፡፡

👍8❤4👏2🙏1