Woldia University Muslim Students
379 subscribers
106 photos
39 videos
117 files
793 links
Wdumuslimstu
Download Telegram
አቡ ለሐብ ከተከበረው ሐሸሚይ ቁረይሽ ጎሳ ነው። ነገር ግን የመንቀልቀል ባለቤት የሆነችን ጀሀነም በእርግጥ ይገባ። ቢላል ኢብኑ ረባህ {ረድየ'ሏሁ ዓንሁ} ጥቁር ባሪያ ሐበሻ ነበር ፣ ረሱል ﷺ የጫማውን (ኮቴ) ሹክሹክታ ጀነት ውስጥ ሰምተዋል ።
......................... ሐሳቡን ለናንተው
Copy

http://t.me/wdumuslimstu
እመነኝ ምክንያቱ የሚታወቅም ሆነ የማይታወቅ  ጭንቀት አንዱ እና ዋነኛው መንስዔ አላህን ከማዉሳት መራቅ ነዉ ።
ለዚህ በሽታም ሁነኛ መፍትሔዉ ፍቱን መድሀኒቱ ልብን ጥዶ ዚክር ማብዛት ነዉ ።
اللهم فرج هم المهمومين ونفس كرب المكروبين واقض الدين عن المدينين
Copy

http://t.me/wdumuslimstu
~ሞት አፋፍ ላይ ስትደርስ ቀልብ ይዛ የኖረችዉን ብቻ ነው የምትተፋው። የዛሬ የዕለት ተዕለት ዉሎአችን የነገ ኻቲማችን ነው። ሰው በኖረበት ነገር ላይ ይሞታል፣ በሞተበት ነገር ላይ ይቀሰቀሳል።

አላህ ኻቲማችንን ያሳምርልን

منقول

http://t.me/wdumuslimstu
★ጌታዬ ያኔ ሲጠይቀኝ እያለ " ምነው ማታፍር አንተ እኔን ስታምፀኝ"★


→ጌታዬ ያኔ ሲጠይቀኝ
→እያለ " ምነው ማታፍር አንተ እኔን ስታምፀኝ"
→"ከፍጡሮቼ ሁሉ ወንጀልህን እየሸሸግክ
→እኔ ጋር ግን መጣህ አመፅክን ተሸክመክ"
→ወይኔ! ምን ይውጠኛል
→ማንስ ይጠብቀኛል
→ጊዜ ሄዶ አልፎ ጊዜ ሲተካ
→ነፍሴ በምኞት ሲረካ
→ዘነጋሁ የወዲያኛውን
→ከሞት ከፈኔ የሚከተለውን
→ዘላለም ለመኖር ቃል እንደተገባልኝ
→ሞት የሚባል ነገር እንደማይመጣብኝ
→ይሄው ጣእረ–ሞት መጣ
→ማን ያተርፈኛል ከዚህ ጣጣ?
→ዙርያየ ያሉን ቃኘሁኝ
→የሚጠቅመኝ ግን አጣሁኝ
→ምን እንዳስቀደምኩ ልጠየቅ ነኝ
→ለዚህ ግዜየ የሚሆነኝ
→ያኔ ምን ይሆን መልሴ
→በእምነቴ ችላ ያልኩትን እራሴ
→ወይኔ! ከቶ ምን ይብቃኝ
→ሰምቼ አልነበርን የጌታዬ ቃል ሲጠራኝ?
→በቃፍም፣በያሲን ያለውን
→ምነው አልሰማሁ ተግሳፁን
→ምነው አልሰማሁ ትንሳኤውን
→የፍርዱን ቀንና መሰብሰቡን?
→መለከል–መውት ሲፈልገኝ
→አልሰማሁም ወይ ሲጠራኝ?
→ጌታ ሆይ! እኔ ባሪያህ ተመለስኩኝ
→ማን አለ ከለላ የሚሰጠኝ
→ከምሕረተ ሰፊው ጌታ ሌላ
→እኔን ወደ ሀቅ የሚመራ
→በንሰሐ መጣሁ ይቅር በለኝ
→መልካም ሚዛኔን አክብድልኝ
→ሒሳቤን አርገው ቀና
→ተስፋዬ አንተው ነህና

منقول

http://t.me/wdumuslimstu
ሰዎችን እርስ በእርስ ለማጣላት ወሬ የሚያዋስድ  ሰዉ ጀነት አይገባም በዚህም ግልጽ ሀዲስ መቶል ።
#እንጠንቀቅ
http://t.me/wdumuslimstu
بيْنَما أيُّوبُ يَغْتَسِلُ عُرْيانًا خَرَّ عليه رِجْلُ
جَرادٍ مِن ذَهَبٍ، فَجَعَلَ يَحْثِي في ثَوْبِهِ، فَنادَى رَبُّهُ: يا أيُّوبُ ألَمْ أكُنْ أغْنَيْتُكَ عَمَّا تَرَى؟ قالَ: بَلَى، يا رَبِّ، ولَكِنْ لا غِنَى بي عن بَرَكَتِكَ.

አላህ ሆይ አንተ በእኔ ተቆጥረው የማያልቁ ኒእማወችን ሰተኸኛል ።

አንተ ጨምርልኝ ።
ከአንተ ፀጋ መብቃቃት አልችልምና
منقول
http://t.me/wdumuslimstu
قال ابنُ تَيميَّةَ: (التَّقليدُ هو قَبولُ القَولِ بغيرِ دليلٍ)
ኢብኑ ተይሚያ እንዲህ አለ ተቅሊድ ብሎ ማለት የሆነን ንግግር ያለ መረጃ መቀበል ነው።

http://t.me/wdumuslimstu
ወንዶች ሰምታችኋል
--------------- -----------
ኢማም አህመድ ኢብን ሀንበል (አላህ
ይዘንላቸው) ልጃቸው ሲያገባ የለገሱት ምክር: " ልጄ ሆይ እነዚህን አስር ነገሮች
ለባለቤትህ መፈጸም ካልቻልክ በትዳር
ህይወትህ ደስተኛ መሆን ስለማትችል
ምክሬን ጠበቅ አድርገህ ለመያዝ ሞክር"

1- ሴት ልጅ ምቾትን ስለምትፈልግ ያለህን
ነገር ሳትሰስት አጋራት

2- ሴት ፍቅርህን እንድትገልጽላት ትሻለች
(ባገኘከው አጋጣሚ) ፍቅርህን ከመግለጽ
ወደኋላ አትበል

3- ሴቶች ግትር ወንዶችን ይጠላሉ ደካማ
ወንዶችን ደግሞ ይንቃሉ አንተ ጥንካሬ
በሚያስፈልግበት ቦታ ጠንካራ ሌላ ጊዜ
ደግሞ ገር ለመሆን ሞክር

4- ሴቶችን መልካም ንግግር ውብ ገጽታ
ንጹህ ልብሶችና ጥሩ መአዛ ስለሚማርካቸው
ሁሌም እነዚህ ነገሮች እንዲኖሩህ ጥረት
አድርግ

5- ለሴት ቤቷ የቤተ መንግስት ያህል ክብር
የምትሰጠው ስፍራ ነው። ቤቷ ስትሆን ዙፋኗ
ላይ በክብር የተቀመጠች ንግስት ያህል ክብር
ይሰማታል። በምንም ተአምር ይህን ቤተ
መንግስቷን የሚያፈርስባትን ነገር
እንዳትፈጽም። ከንግስና ዙፋኗ ላይ
ልታወርዳትም አትሞክር። ይህን ካደረክ
ንግስናዋን እንደመቃወም ይቆጠራል
ለንጉስ ንግስናውን ከመቀናቀን የበለጠ
ትልቅ ወንጀል የለምና ጥንቃቄ አድርግ

6- ሴት የቱን ያህል ብትወድህም ቤተሰቧን
ማጣት አትፈልግም። አንተን ከቤተሰቦቿ
በላይ እንድትወድህ ለማድረግ አትጣር። ይህን
ማድረግ ፍጻሜው የማያምር ጠላትነትን
ሊያመጣብህ ይችላል

7- ሴት ከጎንህ (ጠማማ አጥንት) መፈጠሯን
አትዘንጋ  ይህ አፈጣጠሯ የውበቷ ሚስጥር
መሆኑን እወቅ ትንሽ ስህተት ባየህ ቁጥር
አቃናታለሁ እያልክ እንዳትሰብራት
ተጠንቀቅ ስብራቷ ፍቺ ነው ላቃናት
ከሞከርኩ ትሰበራለች በማለትም የባሰ
እንድትጠም መንገድ አትክፈትላት መካከለኛ
ሰው ሁንላት

8- ሴት አንዳንዴ የዋልክላትን ውለታ
ልትዘነጋ ትችላለች  (ስትናደድ) ያደረክላትን
ነገርም ልትክድ ትችል ይሆናል ነገር ግን
እንዲህ አደረገች በማለት ብቻ እንዳትጠላት
ይህን ባህሪዋን ባትወድላት ሌሎች የሚስቡህ
ብዙ ባህሪዎች እንዳሏት አትዘንጋ

9- ሴት አካላዊ ድካምና ስነልቦናዊ ጫና
ሊያርፍባት ይችላል በዚህን ወቅት አላህ
(ሱብሀነሁ ወተአላ) የግዴታ አምልኮዎችን
(ሰላትና ጾም) ሳይቀር ውድቅ አድርጎላታል
በዚህን ጊዜ እዘንላት  ትእዛዝ አታብዛባት

10- ሴት አንተ ዘንድ ያለች (የፍቅር)
ምርኮኛህ መሆኗን አትዘንጋ ምርኮኛህን
በጥሩ ሁኔታ ያዛት እዘንላት በድክመቷ
(የምትፈጽመውን ስህተት) እለፋት ምርጥ
የሂዎት አጋርህ ትሆናለች

አላህ ሷሊህ የሆነችሁን  ይወፍቃችሁ 🤲 https://t.me/wdumuslimstu
☞ « ዚና ሲቀል . . .
     ኒካሕ ይከብዳል!! »

• ዚና ጠዕሙ ከ5 ደቂቃ አይዘልም። የህሊና ጠባሳው እና ፀፀቱ ግን በ50 አመት አይሽርም ።

• የደቂቃ ስህተት የዘላለም ፀፀት ነው።
Copy

https://t.me/wdumuslimstu
የድሮ ሴቶች ወንዶች የሚያማልሉ   ሳይሆኑ

      ወንዶች የሚሰሩ ነበሩ‼️

አላህ ይህንን ዲን ይጠበቅ ዘንዳ ሰበብ ካደረጋቸው ሰዎች በግንባር ቀደምትነት ከሚጠቀሱት ውስጥ አንዱ የሆኑት; ታላቁ የአህለል ሱና ወል_ጀምዓ ኢማም
  አቡ ዐብደላህ አሕመድ ቢን ኸንበል
እንዲህ ይላሉ፦

   «የአስር ዓመት ልጅ ሳለሁ እናቴ ቁርኣን አስሃፍዛኛለች። ከፈጅር ሰላት በፊት ቀስቅሳኝ ብርዳማ በነበሩ የበግዳድ ሌሊቶች እንዳልቸገር የውዱእ ውሃ ታሞቅልኛለች። ልብሴን አልብሳኝ እሷም ለባብሳ; መስጂዱ ከቤታችን ራቅ ያለ ቦታ ስለ ነበርና ሌሊቱም ጨለማ ስለ ነበር አብራኝ ወደ መስጂዱ ትወስደኛለች።»

    የዚህ ትውልድ ታሪክ እንዲታደስእኛን የሚያማልሉን ሳይሆንልጆቻችንን የሚሰሩልን እህቶች ያስፈልጉናል
https://t.me/wdumuslimstu
💎....................ሶብር...........    

ትግስት የዚህ አለም ሀብት የመጭው አለም ስኬት ናት። አላህ ለታጋሾች ትልቅ ስጦታን ሰጣቸዋ በገነትም አበሰራቸው።

وَلَنَبْلُوَنَّكُم بِشَيْءٍ مِّنَ الْخَوْفِ وَالْجُوعِ وَنَقْصٍ مِّنَ الْأَمْوَالِ وَالْأَنفُسِ وَالثَّمَرَاتِ ۗ وَبَشِّرِ الصَّابِرِينَ

ከፍርሃትና ከረኃብም በጥቂት ነገር፣ ከገንዘቦችና ከነፍሶችም፣ ከፍራፍሬዎችም በመቀነስ በእርግጥ እንሞክራችኋለን፡፡ ታጋሾችንም (በገነት) አብስር፡፡

''ትግስት ከኢባዳዎች አንዱና ምንዳውም የላቀ ነው። አላህ ትእግስትን ከሶላት ጋር አብሮ በማቆራኘት ጠቅሶታል።

يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا اسْتَعِينُوا بِالصَّبْرِ وَالصَّلَاةِ ۚ إِنَّ اللَّهَ مَعَ الصَّابِرِينَ

እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በመታገስና በሶላት ተረዱ፡፡ አላህ (በእርዳታው) ከታጋሾች ጋር ነውና፡፡

الَّذِينَ إِذَا ذُكِرَ اللَّهُ وَجِلَتْ قُلُوبُهُمْ وَالصَّابِرِينَ عَلَىٰ مَا أَصَابَهُمْ وَالْمُقِيمِي الصَّلَاةِ وَمِمَّا رَزَقْنَاهُمْ يُنفِقُونَ

እነዚያን አላህ በተወሳ ጊዜ ልቦቻቸው የሚጨነቁትን፣ በደረሰባቸውም (መከራ) ላይ ታጋሾችን፣ ሶላትንም አስተካክለው ሰጋጆችን፣ ከሰጠናቸውም ሲሳይ የሚለግሱትን (አብስር)፡፡

''ሳትፈተንና መከራን ሳትቀምስ ጀነትን የምታገኝ መሰለህን? አስታውስ! ጀነት ለነዚያ መከራና ችግር ባጋጠማቸው ጊዜ እንዲህ ለሚሉት ናት፦

الَّذِينَ إِذَا أَصَابَتْهُم مُّصِيبَةٌ قَالُوا إِنَّا لِلَّهِ وَإِنَّا إِلَيْهِ رَاجِعُونَ

እነዚያን መከራ፤ በነካቻቸው ጊዜ «እኛ ለአላህ፤ ነን እኛም ወደርሱ ተመላሾች» ነን የሚሉትን (አብስር)፡፡

''ብልህ ሰው ከችግርና መከራ ትምህርት ይወስዳል፣ ነገሮች ቢከብዱም ጌታውን  ያመሰግናል።

ታላቁ የትዕግስት መምህር ነብያችን ሱለላሁ አለይሂ ወሰለም ከፍ ባለ ድምፅ እዲህ ነበር ያሉት፦ "አዋጅ! የአላህ ሸቀጥ እጅግ ውድ ናት፣ የአላህ ሸቀጥ እርሷ ጀነት ናት። "

እናም ችግርና መከራ ቢደራረብብህ አትዘን ተስፋ አትቁረጥም.... አላህ ምን እዳዘጋጀልህ አታውቅምና ታጋሽና አመስጋኝም ሁን

وَلَسَوْفَ يُعْطِيكَ رَبُّكَ فَتَرْضَىٰ

ጌታህም ወደ ፊት (ብዙን ስጦታ) በእርግጥ ይሰጥሃል፡፡ ትደሰታለህም፡፡

'' አላህ ከታጋሾች ጋር መሆኑን አትርሳ።

إِنَّ اللَّهَ مَعَ الصَّابِرِينَ

አላህ (በእርዳታው) ከታጋሾች ጋር ነውና፡፡

አላህ ከታጋሾች ያድርገን!!
منقول
https://t.me/wdumuslimstu
🔖ወርቃማ የዙል-ሒጃ 10 ቀናትና
መልካም ስራ ላይ መበርታት


بسم الله الرحمن الرحيم
فضل عشر ذي الحجة ووصايا لمن أدركها

ምስጋናና ውዳሴ ለዓለማቱ ጌታ ለአላህ ይሁን ሰላትና ሰላም የሰው ልጆች ሁሉ ምርጥ በሆኑት በነቢዩ ሙሐመድ ላይ ይስፈን አላህ በእዝነቱ ለባሮቹ የተለያዩ ወደርሱ የሚያቃርቡ ልዩ የመልካም ስራ እድሎችን ፈጥሯል በዚህም ተፎካካሪዎች እንዲፎካከሩ፣ ተሽቀዳዳሚዎችም እንዲሽቀዳደሙ ገፋፍቷል የስው ልጅ ነፍስ ሁሌ አንድ አይነት ሁኔታ ላይ ስትሆን ትሰለቻለች አዲስ ነገር ስታገኝም ትነቃቃለች ይህንም ባህሪይ ሽሪዓችን ለነፍሲያ በሚገባ ጠብቆላታል ነቢያችን ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በሐዲሳቸው የሚከተለውን ብለዋል

" ነፍስ፥ አንዳንዴ ለመልካም ስራ ትነቃቃለች አንዳንዴም ትሰለቻለች ንቃትና ከፍተኛ ፍላጎት ባላት ጊዜ ኸይርን ስራ በሚገባ አሰሯት በታከተችና በሰለቸች ጊዜ ግዴታ ለሆኑ ነገሮች እንጂ አትጫኗት" ብለዋል

🔹ይህ በጌታው በሚገባ የሚያምንና ስሜቱንም የማይከተልን ሰው ነፍስ ለማለት እንጂ በመሰረቱ ስሜቱን የሚከተልና የጌታውን ህግ የሚጥስን ሰው ነፍስ አይመለከትም!

🔸መንፈስን ለማደስና ነፍስንም መልካም ነገር ላይ ለማነቃቃት አላህ በየጊዜው በመጠነኛ ልፋትና ጥረት ከፍተኛ ምንዳ የሚያስገኙ እድሎችን አስገኝቷል ይህንንም እድል ፈጥነን እንድንጠቀም ትሩፋቱን ገልጿል

ከነዚህም እድሎች መካከል አንዱ የዙል-ሒጃ የመጀመሪያ 10 ቀናቶች ናቸው ቡኻሪይና ሌሎችም ባስተላለፉት ሐዲስ ነቢዩ ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም የሚከተለውን ብለዋል

[ما من أيام العمل الصالح فيها أحب إلى الله من هذه الأيام يعني أيام العشر .... الحديث]

"ከዙል ሒጃ 10 ቀናት የበለጠ መልካም ስራ ከመቼውም በላይ አሏህ ዘንድ ውድ የሚሆንበት ቀን የለም"

🔸እነሆ አዱኒያ አጭር ናት እድሜያችንም አጭር ነው ከአጭሯ ዱኒያ የቀረውም በጣም አጭር ከአጭሯ ዱኒያ የአንተ ድርሻ ደግሞ እጅግ በጣም አጭር ነው ይህም እውነታ ቀደም ሲል በቁርኣን ተነግኖራል

[قُل متاعُ الحياةِ الدنيا قَليل والآخِرةُ خَيرٌ لِمَن اتَقى....] النساء 77

" ነቢዩ ሙሐመድ ሆይ ንገራቸው፥ የዱኒያ ህይወትና መጠቃቀሚያዋ አጭርና ጥቂት ነው የአኼራ ህይወትም (አሏህን ለሚፈሩ) ከዱኒያ የተሻለ ነው" "ሱረቱንኒሳእ 77"

አጭርና ጥቂት ከሆነችዋ የዱኒያ ህይወት የቀረው ጥቂቱ መሆኑንም ሲነግረንም አሏህ እንዲህ ብሏል

(اقتَرَبَت الساعةُ وانشَقَّ القَمَر)

" ቂያማ ተቃረበች ጨረቃም ለሁለት ተከፈለች “ ሱረቱልቀመር 1

(اقتَرَبَ للنَّاسِ حِسابُهم)

“ የሰው ልጆች መተሳሰቢያና መመርመሪያ ጊዜያቸው ተቃረበ እነሱ ግን ቸልታና መዘናጋት ላይ ናቸው
” ሱረቱል አንቢያ 1

▪️አጭሩ እድሜያችን መች እንደሚቋጭ አናውቅምና ሁሌም ራስን ለሞት ማዘጋጀት ብልህነት ነው
ለሞት መዘጋጃትም፥ መልካምን ስራ ተሽቀዳድሞ በመስራት ከወንጀል በመራቅ አኼራን በመናፈቅ ነው

▪️ጊዜያችንን በአግባቡ እንጠቀም የውርደትም ይሁን የስኬት ሰበቡ የጊዜ አጠቃቀም ነው፣በዱኒያም በአኼራ በማይጠቅም ነገር ጊዜና ገንዘባችንን የምናባክን ሰዎች:-

ቀጣይ ምርጥ 10 የዙልሒጃ ቀናትን በአግባቡና ወደ አላህ በሚያቃርብ ስራ ለማሳለፍ ከወዲሁ ነፍሲያችሁን አሸንፉ!
ሌት-ከቀን በኔት ጊዜ፣ ገንዘብና አይናችሁን የምታቃጥሉ፥ አሏህን ፍሩ እራሳችሁንም ፈትሹ ከማይጠቅም ወሬና ተግባርም ራቁ መለከል_መውት ከመምጣቱ በፊትም ከእንቅልፋችሁ ንቁ! የአኼራው ድልድይ/ ሲራጥ ላይ እንዳትወድቁ አላህ ከሚጠላው ስራ በሙሉ በመራቅ ቁርኣን ቅሩ ዘክሩ የኔትና የወሬን ፍቅር በአላህ ውዴታ ቀይሩ!

💥 ውድ የአሏህ ባሮች

አላህ ዘንድ ውድ የሆኑ 10 ቀናትን:-

▪️አምስት ወቅት ሰላቶችን በወቅታቸው፣ ከፊትና ከኋላ የሚሰገዱ ሱናችን ከመጠበቅ ጋር፣ ወንዶች በጀማዓ በመስገድ፣

▪️ቁርኣን በመቅራት፣ ዚክር፣ ዱዓ እንዲሁም ተክቢራ በማብዛት፣

▪️የተቸገሩ ሰዎችን በመርዳትና የታመሙን በመጠየቅ፣

▪️ከዙልሂጃ 1 ጀምሮ እስከ 9ኛው ቀን በመጾምና የጾሙ ሰዎችንም በማስፈጠር ወዘተ አሏህ የሚወዳቸው መልካም ስራዎችን በመስራት እናሳልፋቸው

ከላይ እንደተጠቀሰው የሰው ልጅ እድሜ በጣም አጭር ነው አሏህ ኸይርን የሻለት ሰው ግን በአጭር ጊዜ ብዙ ቁም ነገር መስራት ይችላል::
በነዚህ ውድ ቀናት ለአኼራችን ስንቅ እንሸምት በጣም ድንቅና የተከበሩ ቀናት ናቸው አሏህ በተከበረው ቁርኣኑ በነዚህ ቀናት ምሏል አሏህ ትልቅ ነው በትልቅና ጠቃሚ ነገር እንጂ አይምልም! ነቢያችንም ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በነዚህ ቀናት መልካም ስራ ላይ እንደንበረታ ገፋፍተውናል
እራሳቸውም ቀናቱን በመልካም ስራዎች ያሳልፏቸው እንደነበረ ተዘግቧል

እነሆ ኢማሙ አሕመድና ሌሎችም ዘግበውት አልባኒይ ሰሒህ ባሉት ሐዲስ የምእምናን እናት ሐፍሳ ረዲየላሁ ዐንሃ እንዲህ ብለዋል "ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም የዓሹራ፣ የዙልሒጃ 10 ቀናትና በየወሩ 3ቀን መጾምን አይተውም ነበር" ብላለች

▪️እዚህ ላይ ልብ መባል ያለበት ነጥብ ቢኖር እናታችን ዓኢሻ ረዲየላሁ ዐንሃ " ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም የዙልሒጃ10 ቀናትን ጾመው አያውቁም" ብላ የተናገረችበት አጋጣሚ አለ ይህ ማለት እሷ እስከ ምታውቀው ድረስ ለማለት ነው ምክንያቱም ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ዘጠኝ ሚስቶች ነበር ያሏቸው እሷ ቤት በሚያድሩበት እለት ጾመው አለማየቷን ነው የሚያሳየው እንጂ በጭራሽ አይጾሙም ነበረ ማለት አይደለም።ኡመታቸውን ወደ መልካም ነገር አመላክተው እራሳቸው ወደ ኋላ አይቀሩም!

ይህ በእንዲህ እንዳለ የኡሱል ትምህርት ዘርፍ ዑለሞች እንደጠቀሱት አንድን ጉዳይ በተመለከተ ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም አድርገዉታል ወይስ አላደረጉትም የሚል ውዝግብ ከተነሳ ማድረጋቸው የተጠቀሰው በትክክለኛ ሰነድ መሆኑ ከተረጋገጠ ቅድሚያ የሚሰጠውና ተቀባይነት የሚያገኘው እሱ ነው ምክንያቱም አላደረጉም ያለው አካል የማያውቀውን ነገር እርሱ በማወቁ ጉዳዩ ላይ ይበልጥ አዋቂው ቅድሚያ ይሰጠዋል:: በመሆኑም ከነቢዩ ባለቤቶች መሀል አንደኛዋ ጾመዋል ስትል ሌላኛዋ ደግሞ አልጾሙም ካለች ተቀባይነትና ቅድሚያ የሚያገኘው ጾመዋል ያለችዋ ሃሳብ ይሆናል ማለት ነው።
ሰሓቦችና ተከታዮቻቸው እንዲሁም ፈለጋቸውን ይከተሉ የነበሩ ደጋግ ቀደምቶች ትልቁ ጭንቃቸውና የህይወት ዓላማቸው "ዒባዳ" ወይም መልካም ስራ ላይ መሽቀዳደም ነበር ለዚህም ነው ከነሱ መካከል አንዱ እንዲህ ያሉት

" በዱኒያ ጉዳይ አንድ ሰው ሊቀድምህ ቢፈልግ መንገዱን አስፋለት በአኼራ ጉዳይ ግን ማንም እንዳይቀድምህ! "
አሁን አሁን እየዘነጋን ኖሮ እንጂ አላህም በተከበረው ቃሉ እንዲህ ሲል መክሮን ነበር

(سابقوا إلى مغفرة من ربكم وجنة)

" ተሽቀዳደሙ……..ወደ ጌታህቹ ምህረትና ወደ ጀነት" ሱረቱልሀዲድ 21 አላህ መልካሙን ሁሉ ካገራላቸው እርሱ ከሚጠላው ነገር በሙሉ ከጠበቃቸው ባሮቹ ያድርገን!

Copy
https://t.me/wdumuslimstu
Morning Dua in Full أذكار الصباح كاملة بدقة عالية بصوت عمر هشام…
Omar Hisham Al Arabi
🌸የጧት ዚክር🔊
        ↷ ⇣🌹⇣↷
ቀንህን በዚክር ጀምረው

أَصْبَحْنَا وَأَصْبَحَ الْمُلْكُ لِلَّهِ وَالْحَمْدُ لِلَّهِ، لَا إِلَهَ إِلَّّا اللَّهُ وَحْدَهُ لَا شَرِيكَ لَهُ، لَهُ الْمُلْكُ وَلَهُ الْحَمْدُ وَهُوَ عَلَى كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرٌ، رَبِّ أَسْأَلُكَ خَيْرَ مَا فِيْ هَذَا الْيَوْمِ وَخَيْرَ مَا بَعْدَهُ، وَأَعُوْذُ بِكَ مِنْ شَرِّ مَا فِي هَذَا الْيَوْمِ وَشَرِّ مَا بَعْدَهُ، رَبِّ أَعُوْذُ بِكَ مِنَ الْكَسَلِ، وَسُوءِ الْكِبَرِ، رَبِّ أَعُوْذُ بِكَ مِنْ عَذَابٍ فِيْ النَّارِ وَعَذَابٍ فِيْ الْقَبْرِ.

اللَّهُمَّ بِكَ أَصْبَحْنَا، وَبِكَ أَمْسَيْنَا، وَبِكَ نَحْيَا، وَبِكَ نَمُوتُ، وَإِلَيْكَ النُّشُورُ.

اللَّهُمَّ أَنْتَ رَبِّي لَّا إِلَهَ إِلَّا أَنْتَ، خَلَقْتَنِي وَأَنَا عَبْدُكَ، وَأَنَا عَلَى عَهْدِكَ وَوَعْدِكَ مَا اسْتَطَعْتُ، أَعُوذُ بِكَ مِنْ شَرِّ مَا صَنَعْتُ، أَبُوءُ لَكَ بِنِعْمَتِكَ عَلَيَّ، وَأَبُوءُ بِذَنْبِي فَاغْفِر لِي فَإِنَّهُ لَا يَغْفِرُ الذُّنُوبَ إِلَّا أَنْتَ

https://t.me/wdumuslimstu
001 🕋 تكبيرات العيد مكررة🕋
▪️بصوت الأخ : أبي حمزة عبدالحميد بن محمد حفظه الله
ተክቢራ እያላቹ

الله أكبر الله أكبر الله أكبر
لا إله إلاّ الله
الله أكبر الله أكبر
ولله الحمد.

كبروا ليبلغ تكبيركم عنان السماء
https://t.me/wdumuslimstu
غربة أهل السنة
:
قال الشيخ الألباني رحمه الله تعالى :

إن تكلمت عن التوحيد نبذك أهل الشرك

وإن تكلمت عن السنة نبذك أهل البدعة

وإن تكلمت عن الدليل والحجة نبذك أهل التعصب المذهبي و المتصوفة والجهلة


وإن تكلمت عن طاعة ولاة الأمر بالمعروف والدعاء والنصح لهم وعقيدة أهل السنة نبذك الخوارج والمتحزبة

وإن تكلمت عن الإسلام وربطته بالحياة نبذك العلمانيون والليبراليون و أشباههم ممن يريدون فصل الدين عن الحياة

غربة شديدة على أهل السنة
حاربونا بجميع الوسائل حاربونا بالإعلام المسموع والمرئي والمكتوب


حتى أصبح الأهل والأصحاب يحاربون هذا الغريب المتمسك بكتاب الله وسنة رسول الله ،
ورغم هذا ،

نحن سعداء بهذه الغربة ونفتخر بها ،
ﻷن رسول الله ﷺ أثنى على هؤلاء الغرباء


فقال عليه السلام:

إن الإسلام بدأ غريبًا ،
وسيعودُ غريبًا كما بدأَ
فطُوبَى للغُرباءِ قيل :
من هم يا رسولَ اللهِ


قال : الذينَ يصلحونَ إذا فسدَ الناسُ

السلسلة الصحيحة رقم : (1273)

Copy

https://t.me/wdumuslimstu
Facebook wordmark - 2765088103655950
በቅርቡ የሰለመዉ ወንድማችን ጃ ምን እንደሚል እንስማዉ
ከክርስትና ሃይማኖት ወደ እስልምና የመጣ ወንድም ለምን እንደስለመ እንዲህ በማለት ይመስከራል
::

አላህ እኛንም እሱም በኢስላምና በሱና ላይ አኑሮ በኢስላምና በሱና ላይ ይግደለን

https://t.me/wdumuslimstu
فضائل ١٠ ذي الحجة في دقيقة
شيخ صالح المنجد
የዙልሂጃ አስርቱ ቀናት
ትሩፋት በ 1 ደቂቃ

በአማርኛ ትርጉም

አስርቱ የመጀመሪያ የዙልሂጃ ቀናት ከአመት ውስጥ ካሉት ቀኖች በላጭ ናቸው
በነዚህም ቀናት የሚፈፀም መልካም ስራ ከሌሎች ቀናት በበለጠ መልኩ አላህ ዘንድ የተወደደ ነው
አላህም በዚህችም ቀናት ምሏል በአስርቱ ሌሊቶች እምላለሁ
ይህችንም ቀን አላህም
" በታወቁ ቀኖች ውስጥ የአላህን ስም ያወሱ ዘንድ" ያለው በእነዚህ ቀኖች ውስጥ ነው

በእነዚህም ቀናት ዲኑን አሟላው
እነዚህም ቀናት በ አምልኮ ላይ በመጠንከር መጠቀም አለብን

ሰላትን በመጠባበቅ፣ ፆም በመፆም፣ ቁርዐን በማንበብ📖፣ በዚክር📿፣ በዱዓ🤲፣ ለወላጆች በጎ በመዋል፣ዝምድናን በመቀጠል፣ የሙስሊሞችን ጉዳይ በማስፈፀም፣ ህመምተኛን በመጠየቅ፣ ጀናዛን በመሸኘት፣ ምግብን በማብላትና በሌሎችም መልካም ስራዎች በመብርታት እንዲሁም አላሁ አክበር ላኢላሃ ኢለሏህ  አላሁአክበር ወሊላሂል ሀምድ የሚለውን ዚክር በሁሉም ጊዚያትና ማንኛውም ሁኔታ ውስጥ ሆነን ማብዛት ይኖርብናል

ልክ እንደዚሁ  የተገደበው የተክቢራ አባባልን በአረፋ ዕለት ከፈጅር ወቅት ጀምረን ማለትን ማብዛት
በሌሊትም የአላህን ምህረት መለመን
ጊዜያችንን ከማባከን መጠንቀቅ መቻል ይኖርብናል

የሚፈለገውን የሚያውቅ አካል ያንን ለማከናውን የሚከብደው ነገር አይኖርም የአላህ ሸቀጥ ውድ ናት! እሷም ጀነት ናት
እንበርታ! እንጠንክር!
Copy
https://t.me/wdumuslimstu
ለነገህ ምን አዘጋጅተሃል?

አዎ ለቀብር ጨለማ !!
ለቂያማ ጭንቀት !!
በሲራጥ ለማለፍ !!
አላህ ፊት ቁመን ስንጠየቅ ላለው ጭንቀት !!
በጥቅሉ ከሞት በሗላ ላለው ሂወታችን  ምን አዘጋጅተናል?

አላህ (ሱብሓነሁ ወተዐላ) እንድህ ይላል:-

{ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا اتَّقُوا اللَّهَ وَلْتَنظُرْ نَفْسٌ مَّا قَدَّمَتْ لِغَدٍ ۖ وَاتَّقُوا اللَّهَ ۚ إِنَّ اللَّهَ خَبِيرٌ بِمَا تَعْمَلُونَ }

« እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን ፍሩ፡፡ ማንኛይቱም ነፍስ ለነገ ያስቀደመችውን ትመልከት፡፡ አላህንም ፍሩ፡፡ አላህ በምትሠሩት ሁሉ ውስጠ ዐዋቂ ነው፡፡ » [ሐሽር (18)
Copy


https://t.me/wdumuslimstu
#እንዳትዘናጋ

ከስኬት ለመድረስ ስትነሳ ማልደህ
ልብህን በተስፋ በጀግንነት ሞልተህ
ጉዞህን ከጀመርክ ነገህን አልመህ
ጋራ ሸንተረሩን በፅናትህ አልፈህ
ለመድረስ ስታስብ ከስኬትህ ፈጥነህ
እራስህን ቅደም ከራስህ ጋር ሮጠህ
ለአላማህ ስትሮጥ
#እንዳትዘናጋ
እንዳታወዳድር አንተን ከሌሎችጋ
ደረሱ አልደረሱ ብለህ አትያቸው
ወደፊት ብቻ ሩጥ ገስግስ ከፊታቸው
ከዚያም ከስኬትህ ደርሰህ ጠብቃቸው



https://t.me/wdumuslimstu