ሥርዓተ ቤተክርስቲያን Tube
35.2K subscribers
2.06K photos
43 videos
105 files
1.97K links
https://www.youtube.com/channel/UCyyw8be1uLS-PdwVLd-zyKw

#subscribe ያርጉ ይቀላቀሉ እና ይማሩ👆👆👆
Download Telegram
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ነገ ማርያም ናት እና ይሰገዳል ወይ ብላችሁ ለምትጠይቁ በሙሉ!

አዎ ይሰገዳል!

For all those who ask if tomorrow is Maryam and will be worshiped!

Yes, he worships!
የብዙ ሰው ጥያቄ

ማማተብ ይቻላል?

መልሱላቸው!
Forwarded from ሥርዓተ ቤተክርስቲያን Tube (Ⓕⓔⓚⓡⓔ 🇦 🇧 🇪)
😍ዕለተ ሐሙስ😍
😍ክፍል አስራ አንድ😍
 
አዘጋጅ ዲያቆን ፍቅረ አብ

ከሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ቲዩብ (ቻናል)



ጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህ ዕለት ፍጹም ሰው፤ ፍጹም አምላክ መኾኑን ለመግለጥ እና ለአርአያነት ሲጸልይ በማደሩ ምክንያት ዕለቱ ‹ጸሎተ ሐሙስ› በመባል ይታወቃል፡፡ ትሕትናንና ፍቅርን እንደዚሁም የአገልግሎትን ትርጕም ለማስረዳትና ለማስገንዘብ ጌታችን የደቀ መዛሙርቱን እግር በማጠቡ ዕለቱ ‹ሕጽበተ ሐሙስ› በመባልም ይጠራል፡፡ ጌታችን የደቀ መዛሙርቱን እግር ባጠበ ጊዜም፡- «… ያደረግሁላችሁን ታስተውሉታላችሁን?…
እንግዲህ እኔ ጌታና መምህር ስኾን እግራችሁን ካጠብሁ እናንተ
ደግሞ እርስ በእርሳችሁ ትተጣጠቡ ዘንድ ይገባችኋል፤›› በማለት የእርሱን አርአያነት መከተል እንደሚገባ አስተምሯል (ዮሐ. ፲፫፥፲፪-፳)፡፡


ዕለተ ሐሙስ ጌታችን ‹‹… ይህ ስለ እናንተ በመስቀል ላይ የሚቈረሰው
ሥጋዬ ነው፤ እንካችሁ ብሉ፡፡ ይህ ስለ እናንተ የሚፈስ ደሜ ነው፤
ከእርሱ ጠጡ
፤›› በማለት ምሥጢረ ቍርባንን የመሠረተበት የጀመረበት ቀን በመኾኑ ‹የምሥጢር ቀን› ተብሎም ይጠራል (ማቴ. ፳፮፥፳፮-፳፱)፡፡ ይኸውም ምእመናን ሥጋውንና ደሙን ተቀብለን ከእርሱ ጋር አንድነትና ኅብረት እንዲኖረን፤ ጥንተ ጠላት ዲለብሎስንም ፍጹም ድል ነሥተን ሰማያዊት ርስት መንግሥተ ሰማያትን እንድንወርስ ለማስቻል ነው፡፡ አይሁድ ጌታችንን የያዙበት ቀን ስለ ኾነ በዚህ ዕለት በለኆሣሥ (ብዙ የድምፅ ጩኸት ሳይሰማ) የቅዳሴ ሥርዓት ይፈጸማል፡፡ መላው ሕዝበ ክርስቲያን የሕጽበት፣ የምሥጢር፣ የጸሎት ቀን በተባለው በዚህ ዕለት በንስሐ ታጥበው፣ ሥጋ ወደሙ እንዲቀበሉ ቤተ ክርስቲያን በአፅንዖት ታዛለች!

አዘጋጅ   ዲያቆን ፍቅረ አብ
❤️🙏👍ለሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ቻናል ተከታታዮች የተዘጋጀ
❤️🙏👍


https://www.youtube.com/channel/UCyyw8be1uLS-PdwVLd-zyKw

#subscribe ያርጉ ይቀላቀሉ እና ይማሩ👆👆👆
❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️
💛 @seratebtkrstian    💚
💛 @seratebtkrstian    💚
💛 @seratebtkrstian    💚
💙💙💙💙💙💙💙💙💙

     🙏join👍
Forwarded from ሥርዓተ ቤተክርስቲያን Tube (Ⓕⓔⓚⓡⓔ 🇦 🇧 🇪)
ጸሎተ ሐሙስ
😍ክፍል አስራ ሁለት😍

በሰሙነ ሕማማት (ሀሙስ) በየሰዓቱ የሚደረገው በጸሎተ ሀሙስ የህጽበተ እግር ሥነ ስርዓት

በጸሎተ ሀሙስ በ፱ ሰዓት የሚደረግ የህጽበተ እግር ሥርዓት:- ማስታወሻ! 6_7 ሰአት ድረስ ቅዳሴ ይገባል ይህን የሚያረጉት ሰአቱን በማጠጋጋት እና ለምዕመናኑ በማሰብ ወደ9 ሰአት አካባቢ እስከ 10 ሰአት ለመጨረስ ይሞከራል!!


ምስባክ ዘህጽበተ እግር


ትነዝኃኒ በአዛብ ወእነጽሕ
ተሐጽበኒ እምበረድ ወእጸዓዱ
ታሰምዓኒ ትፍሥሕተ ወሀሴተ

ቄሱ በመጀመሪያ ውኃውን ያቅርብ : ከወንጌል ንባብ በኋላ ቄሱ ውኃውን እንዲህ እያለ ይባርክ:-

ይ.ካ ቡሩክ እግዚአብሔር አብ አሃዜ ኲሉ ዓለም አምላክነ : ወቡሩክ ወልድ ዋህድ እግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ ዘተወልደ እማርያም እምቅድስት ድንግል ለመድኃኒተ ዚአነ : ወቡሩክ መንፈስ ቅዱስ ጰራቅሊጦስ መጽንዒ ወመንጽሒ ለኲልነ : ስብሐት ወክብር ለሥሉስ ቅዱስ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ይእዜኒ ወዘልፈኒ ወለዓለመ ዓለም።

ይ.ሕ አሜን

ከዚህ በኋላ ቄሱ በታላቅ ድምጽ በዜማ የሚከተለውን ይበል:-

ይ.ካ አሐዱ አብ ቅዱስ : አሐዱ ወልድ ቅዱስ : አሐዱ ውእቱ መንፈስ ቅዱስ።

ይ.ሕ በአማን አብ ቅዱስ : በአማን ወልድ ቅዱስ : በአማን ውእቱ መንፈስ ቅዱስ።

ይ.ካ ሰብሕዎ ለእግዚአብሔር ኲልክሙ አሕዛብ።

ይ.ሕ ወይሴብሕዎ ኲሎሙ ሕዝብ።

ይ.ካ እስመ ጸንዓት ምህረቱ ላዕሌነ።

ይ.ሕ ጽድቁሰ ለእግዚአብሔር ይሄሉ ለዓለም።

ይ.ካ ስብሐት ለአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ።

ይ.ሕ ስብሐት ለአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ።

ይ.ካ ይእዜኒ ወዘልፈኒ።

ይ.ሕ ይእዜኒ ወዘልፈኒ።

ይ.ካ ወለዓለመ ዓለም አሜን ሃሌ ሉያ።

ከዚህ በኋላ ቄሱ የካህናቱን እግር ይጠብ  ከዚያም የሕዝቡን ሁሉ እግር ይጠብ በመቀጠልም መዘምራኑ የሚከተለውን ክብር ይእቲ ከመዝሙር ፻፶ ጋር አያይዘው ይበሉ:-

ክብር ይእቲ

ሐዋርያቲሁ ከበበ : እግረ አርዳኢሁ ሐጸበ : ኮኖሙ አበ ወእመ ወመሀሮም ጥበበ : ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ እንዘ ንብል ኢንትኀጎል።

በቁርባን ሰዓት መዘምራኑ የሚከተለውን ይበሉ:-

ዕጣነ ሞገር

ሃሌ ሉያ ሐጸበ እግረ አርዳኢሁ ወይቤሎሙ አነኒ ሐጸብኩ እገሪክሙ አንትሙኒ ከመዝ ግበሩ ለቢጽክሙ።
       
  ምስባኩን እና ንባቡን ቀጥዪ አዘጋጃለሁ....

አዘጋጅ #ዲያቆን ፍቅረ አብ
ከሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ቻናል!!

https://www.youtube.com/channel/UCyyw8be1uLS-PdwVLd-zyKw

#subscribe ያርጉ ይቀላቀሉ እና ይማሩ👆👆👆
❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️
💛 @seratebtkrstian    💚
💛 @seratebtkrstian    💚
💛 @seratebtkrstian    💚
💙💙💙💙💙💙💙💙💙

     🙏join👍
Forwarded from ሥርዓተ ቤተክርስቲያን Tube (Ⓕⓔⓚⓡⓔ 🇦 🇧 🇪)
ጸሎተ ሐሙስ


#አዘጋጅ_ዲያቆን_ፍቅረ_አብ_ለሥርዓተ_ቤተ_ክርስቲያን_ቲዩብ_(ቻናል)_የተዘጋጀ!



#ጉልባን

ከባቄላ ከስንዴ ከገብስ የሚዘጋጅ በጸሎተ ሐሙስ ዕለት የሚበላ ንፍሮ ሲሆን ትውፊቱም የስቅለቱ ሐዘን መግለጫ ነው

ህፅበተ እግር (እግርን መታጠብ)

እግርን ማጠብ እንግዲህ ያስተማረን ያጠበው እርሱ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው!

ሐዋርያትን (ደቀ መዛሙርቱን) እግራቸውን አጠበ! ትህትናን ሲያስለምረን!

ይህን ድንቅ ትህትና የቤተ ክርስቲያን ሥርዓት እንዴት ነው?

እግር ማጠቢያ ይዘጋጃል የሚዘጋጀው ከምንድን ነው ?

መልስ

ካህኑ አልባስ እና መጎናፀፊያ ወገቡ ላይ ይጠመጥማሉ ! ከዛም የፀሎት ስርዓቱ ሲያልቅ እርስ በእርሳቸው መጀመሪያ የሚያጥጡት ይታጠባሉ ከዛም ደሞ እኚህን ያጠባቸው በተራው የታጠቡት ያጥባሉ ከዛም  ጳጳሳት ከዛም ኤጲስ ቆጶሳት ከዛም ቀሳውስት ከዛም ዲያቆናት ከዛም የሚቆርቡ ምህመናን ከዛም ሁሉም ሰው በተራ በተራ ይታጠባል!

አስተጣጠቡ እንዴት መሠላቹ እግራቹህን ሳፋው ውስጥ ታደርጋላቹ ከዛም እግራችሁ ካህኑ ወይም ኤጲስ ቆጶስ ወይም ጳጳሱ እግራችሁን ያጥባሉ ከዛም እጃችሁን አንዴ አጠብ ከዛም ትገለብጡታላችሁ ከዛም አጠብ  (እንደ መጥረግ ነገር)  ከዛ በቃ እቤት ሄዳቹ መታጠብ የለም በእዛው ውላቹ አድራቹ በማግስቱ አርብ ጠዋት መታጠብ ትችላላቹ!

ይህን የፃፍኩት ግራ እንዳይገባቹ ነው!

ዋናው ነገር ደሞ ሥጋ ወደሙ የተሠጠበት ቀን ነው እና ሥጋ ወደሙ ተቀበሉ ግን አስባችሁበት ትናንትና ሻወር የወሰዳችሁ እናም ፆሙን ከመጀመሪያ የፆማችሁ መሆን አለበ!


መልካም ጸሎተ ሐሙስ ይሁንላችሁ!

አዘጋጅ #ዲያቆን ፍቅረ አብ
ከሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ቻናል!!


እኔ እኮ ግርም የምትሉኝ አንባችሁ የምትወጡት ነገር ምን አለበት ሼር ብታደርጉ ለጓደኞቻችሁ ብታሳውቁ ብትረግሩ ? መልሱን ለእናንተ እተዋለሁ!

https://www.youtube.com/channel/UCyyw8be1uLS-PdwVLd-zyKw

#subscribe ያርጉ ይቀላቀሉ እና ይማሩ👆👆👆
❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️
💛 @seratebtkrstian    💚
💛 @seratebtkrstian    💚
💛 @seratebtkrstian    💚
💙💙💙💙💙💙💙💙💙

     🙏join👍
Forwarded from ሥርዓተ ቤተክርስቲያን Tube (Ⓕⓔⓚⓡⓔ 🇦 🇧 🇪)
#ጸሎተ ሐሙስ


አዘጋጅ ዲያቆን ፍቅረ አብ
ከሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ቲዩብ ወቻናል


ምስባክ ዘህጽበተ እግር


ትነዝኃኒ በአዛብ ወእነጽሕ
ተሐጽበኒ እምበረድ ወእጸዓዱ
ታሰምዓኒ ትፍሥሕተ ወሀሴተ

#በዕለቱ_ቅዳሴ_ሰዓት_የሚነበ_መልዕክታት_ወንጌልና_ምስባክ፡፡

ዲ/ን ዕብ 12÷2-18
ን/ዲ 1ጴጥ 3÷15-20
ን/ካ ግብ፡ሐዋ 10÷30-40

#የዕለቱ_ምስባክ

መዝ 20÷5

ወሠራዕከ ማዕደ በቅድሜየ
በአንፃሪሆሙ ለእለ ይሣቅዩኒ
ወአጽሐድከ በቅብዕ ርእስየ



#የዕለቱ_ወንጌል

ማቴ 26፥20 -30

ቅዳሴ፦ ኤጲፋንዮስ



አዘጋጅ #ዲያቆን ፍቅረ አብ
ከሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ቻናል!!


https://www.youtube.com/channel/UCyyw8be1uLS-PdwVLd-zyKw

#subscribe ያርጉ ይቀላቀሉ እና ይማሩ👆👆👆
❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️
💛 @seratebtkrstian 💚
💛 @seratebtkrstian 💚
💛 @seratebtkrstian 💚
💙💙💙💙💙💙💙💙💙

🙏join👍
Forwarded from ሥርዓተ ቤተክርስቲያን Tube (Ⓕⓔⓚⓡⓔ 🇦 🇧 🇪)
🌹🌹ምስብክ 🌹🌹

#ድምፅ📢🔊🔉_ዲያቆን_ፍቅረ_አብ
ከሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ቻናል!!

https://www.youtube.com/channel/UCyyw8be1uLS-PdwVLd-zyKw

#subscribe ያርጉ ይቀላቀሉ እና ይማሩ👆👆👆
❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️
💛 @seratebtkrstian 💚
💛 @seratebtkrstian 💚
💛 @seratebtkrstian 💚
💙💙💙💙💙💙💙💙💙

🙏join👍
Forwarded from ሥርዓተ ቤተክርስቲያን Tube (Ⓕⓔⓚⓡⓔ 🇦 🇧 🇪)
🌹🌹ምስብክ 🌹🌹

#ድምፅ📢🔊🔉_ዲያቆን_ፍቅረ_አብ
ከሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ቻናል!!

https://www.youtube.com/channel/UCyyw8be1uLS-PdwVLd-zyKw

#subscribe ያርጉ ይቀላቀሉ እና ይማሩ👆👆👆
❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️
💛 @seratebtkrstian 💚
💛 @seratebtkrstian 💚
💛 @seratebtkrstian 💚
💙💙💙💙💙💙💙💙💙

🙏join👍
🔔 ከመምህራን የማንን ትምህርት ማግኘት ይፈልጋሉ?👇

┏━━━━━━━━━━━━━━┓
🔔 መምህር ምሕረተአብ አሰፋ
┗━━━━━━━━━━━━━━┛
┏━━━━━━━━━━━━━━┓
🔔 መምህር ዘበነ ለማ
┗━━━━━━━━━━━━━━┛
┏━━━━━━━━━━━━━━┓
🔔 መምህር ሄኖክ ኃይሌ
┗━━━━━━━━━━━━━━┛
┏━━━━━━━━━━━━━━┓
🔔 መምህር ዮርዳኖስ አበበ
┗━━━━━━━━━━━━━━┛
┏━━━━━━━━━━━━━━┓
🔔 አባ ገብረ ኪዳን
┗━━━━━━━━━━━━━━┛
┏━━━━━━━━━━━━━━┓
🔔 መምህር ያረጋል አበጋዝ
┗━━━━━━━━━━━━━━┛
┏━━━━━━━━━━━━━━┓
🔔መጋቢ ሐዲስ እሸቱ አለማየሁ
┗━━━━━━━━━━━━━━┛
┏━━━━━━━━━━━━━━┓
🔔 መምህር እዮብ ይመኑ
┗━━━━━━━━━━━━━━┛
┏━━━━━━━━━━━━━━┓
🔔መምህር ገብረ እግዚአብሔር
┗━━━━━━━━━━━━━━┛
┏━━━━━━━━━━━━━━┓
🔔መምህር አባ ገብረ ኪዳን
┗━━━━━━━━━━━━━━┛

🔗የሁሉንም መምህራን ትምህርት ለማግኘት🔔
🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧
Forwarded from ሥርዓተ ቤተክርስቲያን Tube (Ⓕⓔⓚⓡⓔ 🇦 🇧 🇪)
#ሥርዓተ_ጸሎት_ወስግደት_ዘዓርብ_ስቅለት

ዐርብ ጠዋት በ፲፪ ሰዓት


አቡን

ሃሌ ሃሌ ሃሌ ሉያ(፫) ነአምን ሕማሞ ለዘኢየሐምም ርግዘተ ገቦሁ ነአምን ወቅንዋተ እደዊሁ ነአምን ዬ ዬ ዬ ነአምን ሞቶ ወትንሣኤሁ።

"ለከ ሃይል"ን በል
ከኦሪት ምንባብ እስከ እስከ ተአምረ ኢየሱስ ያለው ምንባብ ይነበባል።

ምስባክ

መዝ: ፳፮ ፣ ፲፪

እስመ ቆሙ ላዕሌየ ሰማዕተ ዐመፃ
ወሐሰት ርዕሰ ዐመፃ
እስመ ቆሙ ላዕሌየ ሰማዕተ ዐመፃ

ከአራቱም ወንጌል ካህኑ ካነበበ በኋላ ቀጥሎ ያለውን ቃል ከስግደት ጋር በዜማ በኅብረት ይበሉ:-

ማቴ: ፳፯ : ፩ - ፲፬ ከተነበበ በኋላ

ወጸቢሆ ተማከሩ ሊቃነ ካህናት : ይስቅልዎ ለኢየሱስ ዲበ ዕፀ መስቀል።

ማር: ፲፭ : ፩ - ፭ ከተነበበ በኋላ

ወጸቢሆ ተማከሩ ሊቃነ ካህናት : አውጽእዎ አፍአ ለኢየሱስ ወወሰድዎ ይስቅልዎ።

ሉቃ: ፳፪ : ፷፮ - ፸፩ ከተነበበ በኋላ

ወጸቢሆ ተማከሩ ሊቃነ ካህናት : አውጽዕዎ ለኢየሱስ ወመጠውዎ ለጲላጦስ።

ዮሐ: ፲፰ : ፳፰ - ፵ ከተነበበ በኋላ

ወጸቢሆ ተማከሩ ሊቃነ ካህናት : አውጽዕዎ ለኢየሱስ ወነበረ ዐውደ ሶቤሃ።


ከዚህ በኋላ ተግሣጻትን የ"ኪርያላይሶን" ጸሎትና ስግደት እስከ ቡራኬ ድረስ ያድርሱ።

ከዚህ በኋላ የሰዓቱን "መልክዐ ሕማማት" ያድርሱ።

የ12 ሰአቱ ስግደት ተፈጸመ የ3 ሰአት ይቀጥላል......

አዘጋጅ #ዲያቆን ፍቅረ አብ
ከሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ቻናል!!


https://www.youtube.com/channel/UCyyw8be1uLS-PdwVLd-zyKw

#subscribe ያርጉ ይቀላቀሉ እና ይማሩ👆👆👆
❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️
💛 @seratebtkrstian 💚
💛 @seratebtkrstian 💚
💛 @seratebtkrstian 💚
💙💙💙💙💙💙💙💙💙

🙏join👍
Forwarded from ሥርዓተ ቤተክርስቲያን Tube (Ⓕⓔⓚⓡⓔ 🇦 🇧 🇪)
ዐርብ ጠዋት በ፫ ሰዓት

አቡን

ሃሌ ሃሌ ሃሌ ሉያ(፫) አርዑተ መስቀል ፆረ (፪) ይስቅልዎ ሖረ ዬ ዬ ዬ ከመ ኪያነ ይቤዙ እግዚእ ኮነ ገብረ።

"ለከ ሃይል"ን በል
ከኦሪት ምንባብ እስከ ተአምረ ኢየሱስ ያለው ምንባብ ይነበባል።

ዲያቆኑ መዝሙር ፴፬ትን ፫ ቦታ ከፍሎ በውርድ ንባብ ይበል።

ይ.ካ ከሕዝቡ ጋር በቅብብል እየተሰገደ:-

ግፍኦሙ እግዚኦ ለእለ ይገፍኡኒ
ጽብኦሙ እግዚኦ ለእለ ይጸብኡኒ
ግፍኦሙ እግዚኦ ለእለ ይገፍኡኒ

ይ.ዲ ምስባክ:- መዝ: ፳፩ : ፲፮

ዐገቱኒ ከለባት ብዙኃን
ወአኃዙኒ ማኅበሮሙ ለእኩያን
ዐገቱኒ ከለባት ብዙኃን።

ማቴ: ፳፯ : ፲፭ - ፲፯ ከተነበበ በኋላ

ጊዜ ፫ቱ ሰዓት : አኃዝዎ ለኢየሱስ ወወሰድዎ ይስቅልዎ።

ማር: ፲፭ : ፮ - ፲፭ ከተነበበ በኋላ

ጊዜ ፫ቱ ሰዓት : አሕየወ ሎሙ በርባንሃ ወወሀበ ሎሙ ኢየሱስሃ ይስቅሉ።

ሉቃ: ፳፫ : ፲፫ - ፳፭ ከተነበበ በኋላ

ጊዜ ፫ቱ ሰዓት : ወሰድዎ ለኢየሱስ ውስተ ዓውደ ምኲናን።

ዮሐ: ፲፱ : ፩ - ፲፪ ከተነበበ በኋላ

ጊዜ ፫ቱ ሰዓት : ቀሠፎ ጲላጦስ ለኢየሱስ ወመጠዎሙ ይስቅልዎ።


ከዚህ በኋላ ተግሣጻትን የ"ኪርያላይሶን" ጸሎትና ስግደት እስከ ቡራኬ ድረስ ያድርሱ።

ከዚህ በኋላ የሰዓቱን መልክዓ ሕማማት ያድርሱ።


አዘጋጅ #ዲያቆን ፍቅረ አብ
ከሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ቻናል!!

https://www.youtube.com/channel/UCyyw8be1uLS-PdwVLd-zyKw

#subscribe ያርጉ ይቀላቀሉ እና ይማሩ👆👆👆
❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️
💛 @seratebtkrstian 💚
💛 @seratebtkrstian 💚
💛 @seratebtkrstian 💚
💙💙💙💙💙💙💙💙💙

🙏join👍
Forwarded from ሥርዓተ ቤተክርስቲያን Tube (Ⓕⓔⓚⓡⓔ 🇦 🇧 🇪)
🌹ዐርብ በስድስት ሰዓት🌹

አቡን
ሃሌ ሃሌ ሃሌ ሉያ(፫) ተሰቅለ (፫) ወሐመ ቤዛ ኲሉ ኮነ ዬ ዬ ዬ በመስቀሉ ቤዘወነ እሞት ባልሐነ።

"ለከ ሃይል"ን በል

ከኦሪት ምንባብ እስከ ተአምረ ኢየሱስ ያለው ምንባብ ይነበባል።

ዲያቆኑ ከሐዋርያው ከቅዱስ ጳውሎስ መልዕክት ከገላትያ በውርድ ንባብ ይበል።

ይ.ካ ከሕዝቡ ጋር በቅብብል በዜማ እየተሰገደ:-

ለመስቀልከ ንሰግድ ኦ ሊቅነ : ወለትንሣኤከ ቅድስት ንሴብሕ ኲልነ : ይእዜኒ ወዘልፈኒ።

ይ.ዲ ምስባክ መዝ: ፳፩ : ፲፮

ቀነዉኒ እደውየ ወእገርየ
ወኆለቊ ኲሎሙ አዕፅምትየ
ቀነዉኒ እደውየ ወእገርየ

ከአራቱም ወንጌል ካህኑ ካነበበ በኋላ : ቀጥሎ ያለውን ቃል ከስግደት ጋር በኅብረት ይበሉ።

ማቴ: ፳፯ : ፳፯ - ፵፭ ከተነበበ በኋላ
ጊዜ ፮ቱ ሰዓት : አልበስዎ አልባሲሁ ለኢየሱስ ወወሰድዎ።

ማር: ፲፭ : ፲፮ - ፴፫ ከተነበበ በኋላ
ጊዜ ፮ቱ ሰዓት : ዐበጥዎ ለስምኦን ከመ ይፁር መስቀሉ።

ሉቃ: ፳፫ : ፳፯ - ፵፬ ከተነበበ በኋላ
ጊዜ ፮ቱ ሰዓት : ሰቀልዎ ለኢየሱስ በቀራንዮ መካን።

ዮሐ: ፲፱ : ፲፫ - ፳፯ ከተነበበ በኋላ
ጊዜ ፮ቱ ሰዓት : ቀትር ሶቤሃ ሊቃነ ካህናት ሰቀልዎ ለኢየሱስ ማዕከለ ፪ኤ ፈያት።

ከዚህ በኋላ ተግሣጻትን የ"ኪርያላይሶን" ጸሎትና ስግደት እስከ ቡራኬ ድረስ ያድርሱ።

ከዚህ በኋላ የሰዓቱን መልክዐ ሕማማት ያድርሱ።


አዘጋጅ #ዲያቆን ፍቅረ አብ
ከሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ቻናል!!

https://www.youtube.com/channel/UCyyw8be1uLS-PdwVLd-zyKw

#subscribe ያርጉ ይቀላቀሉ እና ይማሩ👆👆👆
❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️
💛 @seratebtkrstian 💚
💛 @seratebtkrstian 💚
💛 @seratebtkrstian 💚
💙💙💙💙💙💙💙💙💙

🙏join👍
Forwarded from ሥርዓተ ቤተክርስቲያን Tube (Ⓕⓔⓚⓡⓔ 🇦 🇧 🇪)
🌹ዐርብ በዘጠኝ ሰዓት🌹

አቡን
ሃሌ ሃሌ ሃሌ ሉያ(፫) ሶበ ሰቀልዎ(፫) ለእግዚእነ ፀሐይ ጸልመ ወወርኅ ደመ ኮነ ዬ ዬ ዬ አድለቅለቀት ምድር ወተከሥቱ መቃብራት።

"ለከ ሃይል"ን በል

ከኦሪት ምንባብ እስከ ተአምረ ኢየሱስ ምንባብ ይነበባል።

ይ.ካ ከሕዝቡ ጋር በቅብብል በዜማ እየተሰገደ

ኦ ዘጥዕመ ሞተ በሥጋ : ኦ ዘጥዕመ ሞተ በሥጋ : ኦ ዘጥዕመ ሞተ በሥጋ።

ዲያቆኑ ከሐዋርያው ከቅዱስ ጳውሎስ መልዕክት ከ ግብረ ሕማማት በውርድ ንባብ ይበል።

ሶስት ካህናትና አንድ ዲያቆን ጥቁር ልብሰ ተክህኖ ለብሰው በስዕለ ስቅለት ፊት ይቀመጡ : ከአንዲት መብራት በቀር ሌላውን ያጥፉና አንድ ግምጃ በራሳቸውና ገፃቸው ላይ ያድርጉ (ምዕመናን ደግሞ በነጠላቸው ይሸፈኑ) : አንገታቸውን ዝቅ አድርገው በዕዝል ዜማ በታላቅ ድምጽ በሀዘንና በፍርሃት በለቅሶና በዕንባ ጭምር ካህኑና ሕዝቡ በመቀባበል "አምንስቲቲ"ንና "ተዘከረነ እግዚኦ"ን እያንዳንዱን ሦስት ሦስት ጊዜ ይዝለቁ : እስከ አራት ዙር (አጠቃላይ ቊጥሩ ፸፪ እስኪሞላ ድረስ) ይበሉ : እንደገናም "አምንስቲቲ"ንና "ተዘከረነ እግዚኦ"ን እያንዳንዱን አንድ አንድ ጊዜ በመቀባበል በሁለት ዙር (አጠቃላይ ቊጥሩ ፲፪ እስኪሞላ ድረስ) ይበሉ : ዲያቆኑም በየክፍሉ በሐዘን ዜማ (በውርድ ንባብ) እያስገባ ያንብብ።

ይ.ካ ከሕዝቡ ጋር በቅብብል

አምንስቲቲ ሙኪርያ አንቲ ፋሲልያሱ
አምንስቲቲ ሙዓግያ አንቲ ፋሲልያሱ
አምንስቲቲ ሙዳሱጣ አንቲ ፋሲልያሱ

ይ.ካ ከሕዝቡ ጋር በቅብብል

ተዘከረነ እግዚኦ በውስተ መንግሥትከ : ተዘከረነ እግዚኦ ኦ ሊቅነ : ተዘከረነ እግዚኦ በውስተ መንግሥትከ።
ይ.ሕ በከመ ተዘከርኮ ለፈያታዊ ዘየማን እንዘ ሀሎከ ዲበ ዕፀ መስቀል ቅዱስ።

ይ.ዲ ምስባክ መዝ: ፷፰ : ፳፮

ወወደዩ ሐሞተ ውስተ መብልዕየ
ወአስተዩኒ ብሒዐ ለጽምዕየ
ወወደዩ ሐሞተ ውስተ መብልዕየ

ከአራቱም ወንጌል ካህኑ ካነበበ በኋላ : ቀጥሎ ያለውን ቃል ከስግደት ጋር በኅብረት ይበሉ።

ማቴ: ፳፯ : ፵፮ - ፶ ከተነበበ በኋላ
ጊዜ ተስዓቱ ሰዓት : ጸርሐ ኢየሱስ በቃሉ ወይቤ ኤሎሄ ኤሎሄ

ማር: ፲፭ :፴፬ - ፴፯ ከተነበበ በኋላ
ጊዜ ተስዓቱ ሰዓት : ገዓረ ኢየሱስ በቃሉ ወወጽአት መንፈሱ ሶቤሃ።

ሉቃ: ፳፫ : ፵፭ - ፵፯ ከተነበበ በኋላ
ጊዜ ተስዓቱ ሰዓት : ከልሐ ኢየሱስ በቃሉ ወአማኅጸነ ነፍሶ ሶቤሃ።

ዮሐ: ፲፱ : ፳፰ - ፴ ከተነበበ በኋላ
ጊዜ ተስዓቱ ሰዓት : አጽነነ ርእሶ ኢየሱስ ወይቤ ተፈጸመ ኲሉ።

ከዚህ በኋላ ተግሣጻትን የ"ኪርያላይሶን" ጸሎትና ስግደት እስከ ቡራኬ ድረስ ያድርሱ

አዘጋጅ #ዲያቆን ፍቅረ አብ
ከሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ቻናል!!

https://www.youtube.com/channel/UCyyw8be1uLS-PdwVLd-zyKw

#subscribe ያርጉ ይቀላቀሉ እና ይማሩ👆👆👆
❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️
💛 @seratebtkrstian 💚
💛 @seratebtkrstian 💚
💛 @seratebtkrstian 💚
💙💙💙💙💙💙💙💙💙

🙏join👍
Forwarded from ሥርዓተ ቤተክርስቲያን Tube (Ⓕⓔⓚⓡⓔ 🇦 🇧 🇪)
🌹ዐርብ በአስራ አንድ ሰዓት🌹

አቡን
ሃሌ ሃሌ ሃሌ ሉያ(፫) ንዜኑ (፫) ዘአምላክነ ኂሩተ ትሕትና ወየውሃተ ዘእንበለ ዐቅም ዬ ዬ ዬ እንዘ ይጼዕልዎ ኢጸዐሎሙ እንዘ ያሐምምዎ ኢተቀየሙ።

በዚህ ሰዓት

"ለከ ሃይል ፣ ኪርያላይሶንና መልክዐ ሕማማት" የለም።

የሰዓቱን ምንባባትም በቅዳሜ ሌሊት ማንበብ ይቻላል።

🌹ሥርዓተ እግዚኦታ🌹
ካህናቱ ወደ ቤተ መቅደስ ገብተው ሥርዓተ ግንዘትን ይስሩ : ሦስት ካህናትም ሥርዓተ ግንዘቱን በእጃቸው አቅፈው ይያዙት : አንድ ካህን መስቀልና ጽንሐሕ ይዞ በኋላቸው ይከተል : አንድ ዲያቆን ደግሞ መስቀልና መብራት በመያዝ ፊት ለፊት ይምራ : በምዕራብ በኩል ፊታቸውን ወደ ምሥራቅ አዙረው ይቁሙ : ከዚህ በኋላ በአራቱም ማዕዘናት እየዞሩ እግዚኦታ ያድርሱ አደራረሱም ካህናቱና ሕዝቡ በግራና በቀኝ በአራቱም አቅጣጫ በአራት ተመድበው በመቆም:-

በዐቢይ ዜማ አምስት አምስት ጊዜ : በንዑስ ዜማ ባለአምስቱን ዘጠኝ ዘጠኝ ጊዜ : እንደገና በዐቢይ ዜማ አምስት አምስት ጊዜ : በንዑስ ዜማ በእንተ ማርያም ዘጠኝ ዘጠኝ ጊዜ።

ምሕላው ከተፈጸመ በኋላ ካህኑ "አቡነ ዘበሰማያት" ይስጥ : እስከ ትንሣኤ ድረስ የኑዛዜ ጸሎት ስለሌለ ካህኑ ፵፩ ጊዜ ኪርያላይሶን ይበል : ሕዝቡም እንደርሱ ይበሉ።

#ከዚህ_በኋላ_በቅኔ_ማኅሌት_ሁሉም_ይሰብሰቡ_መቋሚያ_ይዘው_በመካከላቸው_ጧፍ_አብርተው_ይያዙ_የዳዊትንና_የነቢያትን_ጸሎት_እየተቀባበሉ_ያንብቡ_አንብበው_ሲጨርሱ_በመካከላቸው_ያለውን_መብራት_በያዙት_መቋሚያ_ያጥፉት_የዲያቢሎስ_ገዢነት_መደምሰስ_ምሳሌ_ነው_ከዚያም_መዘምራን_ንሴብሖን_ይዘምሩ_ካህናትም_ሕዝቡን_በወይራ_ቅጠል_እየጠበጠቡ_እና_ስግደት_እያዘዙ_ወደ_ቤታቸው_ይሸኟቸው


አዘጋጅ #ዲያቆን ፍቅረ አብ
ከሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ቻናል!!

https://www.youtube.com/channel/UCyyw8be1uLS-PdwVLd-zyKw

#subscribe ያርጉ ይቀላቀሉ እና ይማሩ👆👆👆
❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️
💛 @seratebtkrstian 💚
💛 @seratebtkrstian 💚
💛 @seratebtkrstian 💚
💙💙💙💙💙💙💙💙💙

🙏join👍
ሥርዓተ ቤተክርስቲያን Tube
https://www.tiktok.com/@fikreabe?_r=1&_d=dle13if12b18ke&sec_uid=MS4wLjABAAAAAdEBaYq70YXELEeY0ZN7ysy8HiE19TjkJG4tkdc4siLXZHb6T_eGatWJvjsFxihl&share_author_id=6916860250339705862&sharer_language=en&source=h5_m&u_code=dge9mm917h6gl1&timestamp=1714737364&user…
በዚህ በዲያቆን ፍቅረ አብ የtiktok ገጽ ላይ የሁሉንም አገልግሎቶች በድምጽ ታገኛላችሁ! like follow እና shear እንዳይረሳ!🥰
Forwarded from ✟☨ ማኅቶት ፕሮሞሽን ☨✟