Nigat Media
133 subscribers
519 photos
22 videos
277 links
Nigat Media ያልተዛባ መረጃን በተለየ አቀራረብ!
👉 https://www.nigatmedia.com
👉 https://www.am.nigatmedia.com
👉 https://www.facebook.com/nigatmedia1
👉 https://www.youtube.com/nigatmedia
Download Telegram
የጠላህን ህዝብ በግድ ካልገዛሁት ብለህ የንጹሃንን ደም እንደማፍሰስ ያለ ወንጀል በምድርም በሰማይም የለም። ይህ ደም እጃቸው ላይ ያለባቸው ሁሉ እንደ ቃየን ሲቅዘበዘቡና የሚሆኑትን ሲያሳጣቸው እያየን ነው።

Fasil Yenealem
የአንበጣ መንጋ‼️

በአፋር ክልል የተከሰተው የአንበጣ መንጋ በአረንጓዴ አሻራ በተተከሉ ችግኞችና ለእንስሳት ምግብ በሚሆኑ የደረሱ ተክሎች ላይ ጉዳት እያደረሰ መሆኑን የክልሉ የእንስሳት፣ እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮ አስታወቀ፡፡

የቢሮው የዕጽዋት ጥበቃ ዳይሬክተር አቶ ሀቢብ አብደላ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ መነሻውን ከቀይ ባህር አካባቢ ያደረገው የአንበጣ መንጋ ከሰኔ 15 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ በአፋር ክልል የትግራይ አጎራባች ዞኖች ላይ ተከስቷል፡፡
የምሽት መረጃ!

#AddisAbaba

አራት ኪሎ አካባቢ ውጥረት ነበር፣ ስልክም ኢንተርኔትም ለስዓታት ተዘግቶ ነበር አሁን ነው የተለቀቀው።
ሰበር ዜና

መከላከያ ተቆጣጥሬዋለሁ ሰላማዊ እንቅስቃሴው ተመልሷል እያለ በሚያቅራራበት ፍኖተሰላም ከተማ ውስጥ አደባባዩ ላይ አካባቢ የሚገኝ የነዳጅ ማደያ ላይ የድሮን ጥቃት በማድረስ በቁጥር ያልተገለፁ ንፁሃን ሰዎች ተገድለዋል።
በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ደራ ወረዳ በታጣቂዎች ጥቃት ከ10 በላይ ሰላማዊ ሰዎች መገደላቸውን ነዋሪዎች ተናግረዋል።

ታጣቂዎቹ መስከረም 20 እና 21 የብሄር ማንነትን መሠረት አድርገው ጥቃቱን የፈጸሙት፣ በርበሬ፣ ቆሮ፣ ራቾ፣ ሰለልኩላና ሳላይሽ በተባሉ የወረዳው የገጠር ቀበሌዎች ነው። ነዋሪዎች፣ ጥቃቱን የፈጸሙት የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ናቸው ብለዋል።

በወረዳው ዋና መቀመጫ ግንደ መስቀሉ ከተማ የሠፈሩ የመከላከያ ሠራዊት፣ ፌደራል ፖሊስና የኦሮሚያ ክልል ጸጥታ ኃይሎች ጥቃቱን ለማስቆም በታጣቂዎቹ ላይ ርምጃ እንዳልወሰዱ ታውቋል።

በጥቃቱ ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ቁጥር ከፍተኛ መኾኑንና ኾኖም መንገዶች በመዘጋታቸው ለተጎጂዎች የሕክምና ዕርዳታ መስጠት እንዳልተቻለ በጉንደ መስቀሉ በአንድ የግል ጤና ተቋም የሚሠሩ ሐኪም ለዋዜማ ሬዲዬ ተናግረዋል።
"ታፍነው የተወሰዱ ወጣቶች ይመለሱልን" የአፋር ወጣቶች‼️

አፋር ክልል ኤላ-ውሃ ከተማ መውጫ ላይ ከ3:00 ጀምሮ መንገድ በድንጋይ ተዘግቶ ጎማ እየተቃጠለ ውሏል። ምክንያቱ ደግሞ ሁለት ወጣቶች በክልሉ የፀጥታ ሃይሎች ታፍነው ተወስደዋል፣ይመለሱልን የሚል ነው።

አብዱ ኤሊ ወሃ እና ሰዲቅ በድሩ የተባሉት ወጣቶች ሃሳባቸው ስለገለፁ ነው የታሰሩት ይፈቱ ሲሉ መንገዱን የዘጉት ፍትህ ጠያቂዎች ገልፀዋል። ከፌደራል መንግስቱ ጋር ምንም ችግር የለብንም ችግሩበየክልሉ ነው ሲሉም ገልፀዋል።

ከ10:00 በኋላ መንገዱን ለማስከፈት የክልሉ ልዩ ሀይል ከአካባቢ አስተዳደሮች ጋር ሲመክሩ ቆይተው 12:00 መንገዱ መከፈቱን  ምንጮቼ ነግረውኛል።
"ከፈጣሪ ትዕዛዝ ተሰጥቶኛል" ያለ ፓስተር የጊምቢቹን ከተማ ስያሜ ለመለወጥ ሲያደርገዉ የነበረዉ ጥረት በከተማ አስተዳደሩ እንዲቋረጥ ተደረገ‼️

"ረዕይ ታይቶኛል" ያለ አንድ "የሀይማኖት መምህር" በሀድያ ዞን የምትገኘዉ የጊምቢቹ ከተማን ስያሜ ለመለወጥ ሲያደርግ የነበረዉ ጥረት እንዲቋረጥ መደረጉን የከተማ መስተዳድሩ የኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ባለሙያ አቶ አብነት ሞገስ ለብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥን ተናግረዋል።

የሀይማኖት መምህሩ አርፊጮ የሚባል የቤተ-እምነት መሪ ሲሆን 4 ወራትን ጾም ጸሎት በመያዝ ካሳለፈ በኋላ "ራዕይ ታይቶኛል ከፈጣሪም ትዕዛዝ ተሰጥቶኛል" በሚል የጊሚቢቹ ከተማ ስያሜን "ኤንጃሜ" በሚል ቀይሯል ነዉ የተባለዉ።

ለዚህም ደግሞ ጊምቢቹ የሚለዉ መጠሪያ ነዋሪዉን የማይወክል ነዉ በሚል ለመለወጥ እንዳነሳሳዉ አቶ አብነት ተናግረዋል።ይህም በቤተ እምነት ተቋሙ አንዳንድ ተከታዮች በኩል ተቀባይነት ያለዉ ጉዳይ ነዉ ያሉት አቶ አብነት ፤ ሆኖም የከተማዉ ነዋሪም ሆነ መስተዳድሩ በዚህ የስም ቅያሪ እንደማይስማማ ተናግረዋል። የከተማዋን ስያሜ ለመወለጥ ቢፈለግም በከተማዉ ም/ቤት ቀርቦ ድምጽ ሊሰጥበት ይገባል ብለዋል።

መምህሩ አዲስ ለከተማዋ የሰጠዉ ስያሜ በቅድሚያ በቤተ እምነት ተቋሙ አካባቢ የጀመረ ሲሆን በኋላ ታፔላ እና ባነር እንዲሁም ባንዲራ ጭምር በማሰራት በወጣቶች ማዘዉተሪያ ላይ ለጥፏል ብለዋል። ከዚህም ድርጊት በኋላ ነዋሪዉ በማህበራዊ ሚዲያዎች ተቃዉሞዉን በማሰማቱ የከተማዋ ከንቲባ በተገኙበት ድርጊቱ እንዲቋረጥ ተደርጓል ብለዋል።

በዛሬዉ እለትም የእምነት ተቋሙን መሪ እና ተከታዮች የከተማ መስተዳድሩ ተወካዮች ችግሩን በንግግር ለመፍታት መወያየታቸዉን አቶ አብነት ጨምረዉ ለጣቢያችን ተናግረዋል፡፡

Via ዳጉ_ጆርናል
ህወህሓቶች ሄርሜላ አረጋዊ ከስራ እንድትታገድ አድርግናል በማለት ጮቤ እየረገጡ ነው:: ይህ ለፍትህ ሃይሎች ሽንፈት ነው:: ለዚች ጀግና ያልሆንን ለማን ልንሆን ነው? አሁንም አልረፈደም:: አሜሪካ ያላችሁ ኢትዮጵያውያን ዛሬውኑ ከታች በተቀመጠው ስልክ እየደወላችሁ ለሄርሜላ ያላችሁን ድጋፍ ግለፁ: : ይህ የአፈና መንገድ ነገ በሁላችንም ላይ ይከሰታል:: ውጭም ሆነን በነፃነት ሰርተን እንዳንኖር ሊያደርጉን ነው? የእብሪታቸው ልክ ድንበር ተሻግሯል:: ገዢዎች ይህ መንገድ መስራቱን ካዩ ነገም እኛም እንተግብረው ማለታቸው አይቀርም::


URGENT‼️Call everyday! Call Congresswoman Waters’ DC office now 202-225-2201 She is from LA! Tplf ites have been calling so they may stop you and assume you’re calling on their side. 🚨 BUT MAKE SURE THEY KNOW YOU ARE CALLING IN SUPPORT OF HERMELA 🚨 Tell her she shouldn’t give into the mob that is attacking Hermela. We know exactly who they are. They’ve done it to us for decades.
Call her office now and let her know: 202-225-2201
Via Fasil Yenealem
የሰሜን ወሎ ሀገረስብከት ጽ/ቤት የሚሰራጨው መረጃ ሀሰት ነው ብሏል ብሏል። የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ ታፍነዋል በሚል የሚሰራጨው መረጃ ሀሰት ነው ሲል ጽ/ቤቱ ገልጧል።
የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ለባላገሩ ቴሌቪዥን

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ለባላገሩ ቴሌቪዥን የመጨረሻ የፅሁፍ ማስጠንቀቂያ መስጠቱ ታውቋል። ቴሌቪዥን ጣቢያው በየትኛው ፕሮግራሙ የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ እንዳሰጠው ተነጥሎ አልተገለፀም።

Via - Wasu
ሰበር ዜና
======
ደብረብርሃን ሙሉ በሙሉ በፋኖ ቁጥጥር  ስር ሆናለች :: የሰሜን ሸዋ  ዋና ከተማ የሆነችውን ደብረብርሃን ነፃ ያወጡት ጀግኖቹ ፋኖዎች:-
1- መብረቁ ብርጌድ
2- ጋጠው ብርጌድ እና
3- አስራት ወልደየስ ሻለቃ ናቸው::
በኦፕሬሽኑ የደብረብርሃን እና የአካባቢው ህዝብ ከፍተኛ ተጋድሎ ፈፅሟል::
የሶማሊያ ፕሬዝዳንት #ከግብጽ እና #ከኳታር መሪዎች ጋር በስልክ ያወሩ ሲሆን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትራቸው ከሩቶ ጋር በናይሮቢ መክረዋል‼️

የሱማሊያው ፕሬዝዳንት ሀሰን ሸክ ማህሙድ ከግብጹ ፕሬዝዳንት አብዱል ፈታህ አል ሲሲ እና ከኳታሩ ኢሚር ታሚም አል ታኒ ጋር በስልክ በሁለትዮሽ ግንኙነታቸው እና በቀጠናዉ ጉዳይ ዙሪያ ማውራታቸው ተገለጸ።

ሶማሊያ ደህንነቷን እና መረጋጋቷን ለማስጠበቅ በምታደርገው ጥረት ግብጽ ከጎኗ እንደምትቆም አጽንኦት ሰጥተው አልሲሲ በስልክ ውይይታቸው ወቅት መግለጻቸውን ጽ/ቤታቸው ጠቁሟል።

#የኬንያው ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ የሶማሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አሊ ሞሃመድ ኦመርን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው ማነጋገራቸውን የኬንያ መገናኛ ብዙሃን አስታውቀዋል። ሁለቱም ባለስልጣናት በመከሩበት ወቅት በኬንያ የደቡብ #ሱዳን ልዩ ልዑክ አኮል ኩር ኩክ መታደማቸውንም ዘገባዎቹ አመላክተዋል። 

የውይይታቸው ዋነኛ አጀንዳ የቀጠናውን ግጭቶች በሰላማዊ መንገድ መፍታት በሚቻልበት መንገድ እና አልሸባብን መዋጋት በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ እንደነበር ተጠቁሟል።
ሁለት አስቸኳይ መረጃዎች - ደብረብርሃን!

በዛሬው እለት ደብረብርሃን ያለው የጠላት ኃይል በፋኖ ጀግኖቻችን ክፉኛ ተመቶ ፋኖ ቁልፍ ቦታዎችን ተቆጣጥሯል:: ሁለት አሁናዊ መረጃዎች:-

▪️ደብረብርሃን ሰፍሮ የነበረው የጠላት ኃይል መመታቱን ተከትሎ በሸኖ ከተማ በሄሊኮፕተር አራዊት ሰራዊት እየወረደ እንደሆነ ታውቋል።

▪️ከደብረብርሃን ኢንዱስትሪ ፖርኩ ፊለፊት ባለው መድሃኒያለም ቤተክርስቲያን ውስጥ አራዊት ሰራዊቱ በመግባት ምሽግ እየቆፈሩ እንደሆነ ለወገን ኃይል መረጃው ይድረስ።
አስቸኳይ መረጃ  ደብረ ብርሃን

12 መኪና የአብይ ገዳይ አራዊት አሁን 44 ማዞሪያን ያለፈ ሲሆን፣  በተመሳሳይ ከመንድዳ የተነሳ 8 መኪና ድሽቃና ዙ-23 ያጠመደ መከላከያ ደግሞ ደብረ ብርሐን አቅራቢያ ደርሷል ።
አይሻ ሰዒድ ብርጌድ‼️

📌 "ወለጋ ላይ ወላሂ ሁለተኛ አማራ አልሆንም" እያለች በተገደለችው እህታችን በአይሻ  ሰዒድ ስም አንድ የፋኖ ብርጌድን ተመሰርቷል።
ጐንደር | ጋይነት

ፋኖ በተሽከርካሪ ሲጓዙ የነበሩ ከፍተኛ የብልጽግና የጦር መኮነኖችን ጋይንት አካባቢ በቁጥጥር ስር አውሏል። የመረጃ ምንጮቻችን 4 ያህሉ የኮለኔል ማዕረግ ያላቸው እንደሆኑ ገልፀዋል።
ጋዜጠኛ አስፋዉ መሸሻ ከዚህ አለም በሞት ተለየ😭

የኢቢኤስ ቴሌቪዥን የመዝናኛ ፕሮግራም አዘጋጅ እና መሪ የነበረዉ ጋዜጠኛ አስፋዉ መሸሻ ከዚህ አለም በሞት መለየቱ በዛሬው እለት ተሰምቷል። ጋዜጠኛዉ ለወራት በህመም መቆየቱ የሚታወስ ሲሆን ህክምናዉንም በአሜሪካ ሲከታተል እንደነበር ይታወሳል።
ዛሬ የካቲት 15/2016 ዓም ምሽት በአክሱም ፂዮን ማርያም በተነሳ እሳት በህዝቡ ከፍተኛ ርብርብ በቁጥጥር ስር መዋሉን ከስፍራው የደረሠው መረጃ ያመለክታል።
@nigat_media1