ሒዳያ ኢስላማዊ ማዕከል
4.92K subscribers
204 photos
91 videos
74 files
499 links
በሒዳያ ኢስላማዊ ማዕከል ስር በመሆን አስፈላጊና አስተማሪ ንፅፅራዊ ትምህርቶችን፦

- ቪድዬዎችን
- ኦድዬዎችን
- አጫጭር መጣጥፎችን

እያዘጋጀ በሀገርኛ ቋንቋ ያቀርባል፡፡
Download Telegram
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የኔ የዋሆች ምስጥ ብለው ነው የሚሰሙት
የተደበቀው እውነት በምህራችን ወሒድ ዐቃቢ ኢሥላም ሸር ለሁሉም።

"የስላሴ እሳቤ" እና "የተደበቀው እውነት" መጻሕፍ ከአዲስ አበባ በተጨማሪ አዳማ እና ደሴ ይገኛሉ።

አዳማ ማግኘት የምትፈልጉ call +251966640370

ደሴ ማግኘት የምትፈልጉ፦
አረብገንዳ ሸህ አብዱ መክተባ
ሸርፍተራ ፋጡማህ መክተባ
አሕመድ መክተባ ይገኛል

መጽሐፉን መርካርቶ አንዋር መሥጂድ ኢሥላማዊ መጻሕፍት መደብር ውስጥ ያገኙታል፥ የበለጠ ለመረጃ +251920781016 ዐብዱ ብለው ይደውሉ!
የኢየሱስ ወላጆች?

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

19፥34 ይህ የመርየም ልጅ ዒሣ ነው፡፡ ያ ስለ እርሱ የሚከራከሩበት እውነተኛ ቃል ነው፡፡ ذَٰلِكَ عِيسَى ابْنُ مَرْيَمَ ۚ قَوْلَ الْحَقِّ الَّذِي فِيهِ يَمْتَرُونَ

አንጢዲቆማርያጦስ"Antidicomarianites" በ 428 ድኅረ ልደት የተጀመረ እንቅስቃሴ ሲሆን "ኢየሱስ ማርያም እና ዮሴፍ ተራክቦ አርገው የወለዱት የአብራካቸው ክፋይ ነው" የሚል ትምህርት ነው፥ ይህ ትምህርት መሠረቱ እራሱ ባይብል ነው፦
ሉቃስ 2፥33 "አባቱ" እና እናቱ ስለ እርሱ በተባለው ነገር ይደነቁ ነበር። καὶ ἦν ὁ πατὴρ αὐτοῦ καὶ ἡ μήτηρ θαυμάζοντες ἐπὶ τοῖς λαλουμένοις περὶ αὐτοῦ.
And "his father" and his mother marveled at what was said about him. English Standard Version

ዐማርኛው ላይ "ዮሴፍ" ቢለውም ግሪኩ "ፓተር" πατὴρ ብሎ አስቀምጦታል፥ እንዲሁ English Standard Version "his father" በማለት አስቀምጦታል። "ፓተር" πατὴρ ማለት "አባት" ማለት ሲሆን "ሜቴር" μήτηρ ማለት ደግሞ "እናት" ማለት ነው፥ እዚህ ጥቅስ ላይ ማርያም የኢየሱስ "እናት" እንደተባለች ሁሉ ዮሴፍ የኢየሱስ "አባት" ተብሏል። ዮሴፍ የኢየሱስ "አባት" እንደሆነ የሚናገረው ሉቃስ ብቻ ሳይሆን ማርያምም ዮሴፍ የኢየሱስ "አባት" እንደሆነ ለማሳየት ኢየሱስን "አባትህ" ብላዋለች፦
ሉቃስ 2፥48 ባዩትም ጊዜ ተገረሙ፥ እናቱም፦ ልጄ ሆይ፥ ለምን እንዲህ አደረግህብን? እነሆ፥ "አባትህ" እና እኔ እየተጨነቅን ስንፈልግህ ነበርን፡ አለችው።

ዮሴፍ ለኢየሱስ የተባለው "አባት" ብቻ ሳይሆን "ጎኒዩስ" ተብሏል፥ "ጎኒዩስ" γονεύς የሚለው ቃል "ጊኖማይ" γίνομαι ማለትም "ተወለደ" "ተገኘ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ወላጅ"parent" ወይም "አስገኝ"begetter" ማለት ነው፦
ሉቃስ 2፥27 በመንፈስም ወደ መቅደስ ወጣ፤ "ወላጆቹም" እንደ ሕጉ ልማድ ያደርጉለት ዘንድ ሕፃኑን ኢየሱስን በአስገቡት ጊዜ። καὶ ἦλθεν ἐν τῷ Πνεύματι εἰς τὸ ἱερόν· καὶ ἐν τῷ εἰσαγαγεῖν τοὺς γονεῖς τὸ παιδίον Ἰησοῦν τοῦ ποιῆσαι αὐτοὺς κατὰ τὸ εἰθισμένον τοῦ νόμου περὶ αὐτοῦ,
ሉቃስ 2፥41 "ወላጆቹም" በያመቱ በፋሲካ በዓል ወደ ኢየሩሳሌም ይወጡ ነበር። Καὶ ἐπορεύοντο οἱ γονεῖς αὐτοῦ κατ’ ἔτος εἰς Ἱερουσαλὴμ τῇ ἑορτῇ τοῦ πάσχα.
ሉቃስ 2፥43 ቀኖቹንም ከፈጸሙ በኋላ ሲመለሱ ብላቴናው ኢየሱስ በኢየሩሳሌም ቀርቶ ነበር፥ "ወላጆቹም" አላወቁም ነበር። καὶ τελειωσάντων τὰς ἡμέρας, ἐν τῷ ὑποστρέφειν αὐτοὺς ὑπέμεινεν Ἰησοῦς ὁ παῖς ἐν Ἱερουσαλήμ, καὶ οὐκ ἔγνωσαν οἱ γονεῖς αὐτοῦ.

"ጎኒኢስ" γονεῖς የሚለው ቃል "ጎኒዩስ" γονεύς ለሚለው ቃል ብዜት ሲሆን "ወላጆች" ማለት ነው፥ የኢየሱስ ወላጆቹ የተባሉት ማርያም እና ዮሴፍ መሆናቸው የሚደንቅ ነው፦
ሉቃስ 2፥16 ፈጥነውም መጡ ማርያምን እና ዮሴፍን ሕፃኑንም በግርግም ተኝቶ አገኙ። καὶ ἦλθαν σπεύσαντες, καὶ ἀνεῦραν τήν τε Μαριὰμ καὶ τὸν Ἰωσὴφ καὶ τὸ βρέφος κείμενον ἐν τῇ φάτνῃ·

"ዮሴፍ" የተጸውዖ ስም ሲሆን ከፊት ለፊቱ "ቶን" τὸν የሚል አመልካች መስተአምር መግባቱ በራሱ የሰዋስው ችግር አለበት፥ ጽንፈኛ(ወጋዊ) የአዲስ ኪዳን ምሁር ፕሮፌሰር ዳንኤል ዋላስ ከለዘብተኛ(ሐራዊ) የአዲስ ኪዳን ምሁር ከፕሮፌሰር ባርት ሔርማን ጋር ባደረጉት ውይይት ላይ ፕሮፌሰር ዳንኤል ዋላስ፦ "ውስን አመልካች መስተአምር በተጸውዖ ስም ላይ ለምን እንደመጣ አላውቅም" ብለዋል።
በመጀመሪያ መቶ ክፍለ ዘመን ኢቦናይተስ የሚባሉ ክርስቲያኖች፦ "ዮሴፍ የኢየሱስ ወላጅ አባት ነው" የሚለውን ትምህርታቸው መሠረት ያረጉት ከላይ ባሉት አናቅጽ ነው፥ ቅሉ ግን አምላካችን አሏህ ዒሣ ከመርየም የተወለደው ያለ አባት እንደሆነ ይነግረናል፦
3፥47 ፦"ጌታዬ ሆይ! ሰው ያልነካኝ ስኾን ለኔ እንዴት ልጅ ይኖረኛል? አለች፥ "ነገሩ እንዳልሽው ነው፡፡ አላህ የሚሻውን ይፈጥራል፡፡ አንዳችን በሻ ጊዜ ለእርሱ "ኹን" ይለዋል፥ ወዲውኑም ይኾናል" አላት፡፡ قَالَتْ رَبِّ أَنَّىٰ يَكُونُ لِي وَلَدٌ وَلَمْ يَمْسَسْنِي بَشَرٌ ۖ قَالَ كَذَٰلِكِ اللَّهُ يَخْلُقُ مَا يَشَاءُ ۚ إِذَا قَضَىٰ أَمْرًا فَإِنَّمَا يَقُولُ لَهُ كُن فَيَكُونُ

መርየም ወንድ ሳይነካት በተአምር ዒሣን ፀንሳ ወልዳለች፥ አሏህ ያለ ወንድ ዘር እንቁላሉን "ኹን" በማለት ሰው መፍጠር ይችላል። ስለዚህ የዒሣ ልጅነት የሚጠጋው ወደ መርየም ብቻ ስለሆነ አሏህ በ 23 ቦታ ዒሣን "የመርየም ልጅ" ብቻ ብሎታል፦
19፥34 ይህ የመርየም ልጅ ዒሣ ነው፡፡ ያ ስለ እርሱ የሚከራከሩበት እውነተኛ ቃል ነው፡፡ ذَٰلِكَ عِيسَى ابْنُ مَرْيَمَ ۚ قَوْلَ الْحَقِّ الَّذِي فِيهِ يَمْتَرُونَ

እዚህ አንቀጽ ላይ “ፊ” فِي የሚለው መስተዋድድ “ዐን” عَنْ ማለትም “ስለ”about” በሚል የመጣ ነው፥ ስለ ዒሣ የሚከራከሩበትን ነገር አሏህ በቁርኣኑ የነገረን ሁሉ እውነተኛ ቃል ነው። በትንሳኤ ቀን እየተከራከሩ በሚወዛገቡት ነገር አሏህ ይፈርዳል፦
3፥55 ከዚያም መመለሻችሁ ወደ እኔ ነው፥ በእርሱ ትለያዩበትም በነበራችሁት ነገር በመካከላችሁ እፈርዳለሁ፡፡ ثُمَّ إِلَيَّ مَرْجِعُكُمْ فَأَحْكُمُ بَيْنَكُمْ فِيمَا كُنتُمْ فِيهِ تَخْتَلِفُونَ

አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://t.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ውይይት
የነብያት መንገድ | طريق الأنبياء
●▯ውይይት ▯●

◍ ወንድም ዒምራን
◍ ወንድም ሳላህ
🆅🆂
◍ ወገናችን አብርሽ
◍ ወገናችን ጌዲዮን
ሳጥናኤል

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

6፥162 «ሶላቴ፣ መስዋዕቴም፣ ሕይወቴም፣ ሞቴም ለዓለማቱ ጌታ ለአላህ ነው» በል፡፡ قُلْ إِنَّ صَلَاتِي وَنُسُكِي وَمَحْيَايَ وَمَمَاتِي لِلَّهِ رَبِّ الْعَالَمِينَ

"ሳጥናኤል" የሚለው የግዕዝ ቃል በዕብራይስጥ "አዛዝኤል" עֲזָאזֵל ሲሆን የሁለት ቃላት ውቅር ነው፥ "አዛዝ" עֲזָא ማለት "ጥንካሬ" ማለት ሲሆን "ኤል" זֵל ማለት አምላክ ማለት ነው። በጥቅሉ "አዛዝኤል" ማለት "አምላክ ጥንካርዬ ነው" ማለት ነው፥ ይህ ስም ዲያብሎስ ወይም ሰይጣን የሚባል ጂን ከመሰይጠኑ በፊት የነበረው ስም እንደሆን በአፈ ታሪክ ይነገራል። ይህ ጋኔን በመጽሐፈ ሄኖክ ላይ ከሃያ አንዱ አጋንንት አንዱ ሆኖ ተገልጿል፦
ሄኖክ 3፥10 በአዛዝኤል ሥራ እና ትምህርት ምድር ሁሉ ጠፋች፥ የሰውን ሁሉ ኃጢአት በእርሱ ጻፍበት አለው።
ሄኖክ 15፥7 "በአዛዝኤል" ይፈረድበታል፥ በወገኖችሁ ሁሉ እና በመላእክት ጌታ ስም ባላመኑ በሰራዊቱም ሁሉ ይፈረድባቸዋል።
ሄኖክ 19፥10-12 የእነዚያ የአጋንንት ስማቸው እንደዚህ ነው፦አለቃቸው ስማዝያ፣ ሁለተኛውም አርስጢኪፋ ነው፣ ሥስተኛውም አርሚን ነው፣ አራተኛውም ኮክብኤል ነው። አምስተኛውም ጡርኤል ነው፣ ስድስተኛውም ሩምያል ነው፣ ሰባተኛውም ዳንኤል ነው፣ ስምንተኛውም ምቃኤል ነው፣ ዘጠነኛውም በራቃኤል ነው፣ አስረኛውም “አዛዝኤል” ነው፣ አስራ አንደኛውም አርማሮስ ነው፣ አስራ ሁለተኛውም በጠርያል ነው።

አሮንም በሁለቱ ፍየሎች ላይ ዕጣ ይጥልባቸዋል፥ አንዱን ዕጣ ለያህዌህ ሌላውንም ዕጣ ለአዛዝኤል ይሆናል፦
ዘሌዋውያን 16፥8 አሮንም በሁለቱ ፍየሎች ላይ ዕጣ ይጥልባቸዋል፥ አንዱን ዕጣ ለያህዌህ ሌላውንም ዕጣ "ለአዛዝኤል"። וְנָתַן אַהֲרֹן עַל-שְׁנֵי הַשְּׂעִירִם, גֹּרָלוֹת–גּוֹרָל אֶחָד לַיהוָה, וְגוֹרָל אֶחָד לַעֲזָאזֵל.

ዐማርኛው ላይ "ሚለቀቅ" ብሎ ቢያስቀምጠውም ዕብራይስጡ ግን እንቅጩን ፍርጥ አርጎ "አዛዝኤል" עֲזָאזֵל ብሎ አስቀምጦታል። ዐረቢኛውም ባይብል ሳያቅማማ "ዐዛዚል" عَزَازِيل ብሎታል፥ እንዲሁ በእንግሊሹ Good News Translation በትክክሉ "Azazel" ብሎታል። ከሥነ አምክኖ አንጻር እስቲ እዩት! አንዱ ለፈጣሪ ሁለተኛው ለሳጥናኤል ፍየል ይገበራል? "ከያህዌህ በቀር ለአንዳች አምላክ የሚሠዋ ፈጽሞ ይጥፋ" ተብሏል እኮ፦
ዘጸአት 22፥20 ከያህዌህ በቀር ለአንዳች አምላክ የሚሠዋ ፈጽሞ ይጥፋ።

ከአንዱ አምላክ ውጪ ለሌላ ማንነትና ምንነት መስዋዕት መሰዋት ይህንን ያክል ከባድ ወንጀል ከሆነ እንግዲያውስ ለሳጥናኤል የፍየል መስዋዕት ይቀርባል የሚለውን የብርዘት ውጤት ትታችሁ ለዓለማቱ ጌታ ለአሏህ ብቻ እንድትሰዉ ጥሪያችንን እናቀርባለን። ሙሥሊም መስዋዕቱ ለፈጠረው ለዓለማቱ ጌታ ለአሏህ ብቻ ነው፦
6፥162 «ሶላቴ፣ መስዋዕቴም፣ ሕይወቴም፣ ሞቴም ለዓለማቱ ጌታ ለአላህ ነው» በል፡፡ قُلْ إِنَّ صَلَاتِي وَنُسُكِي وَمَحْيَايَ وَمَمَاتِي لِلَّهِ رَبِّ الْعَالَمِينَ

አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://t.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ውይይት
husu negn ሁሱ ነኝ
●▯ውይይት ▯●

◍ ኡሥታዝ ወሒድ ዐቃቢ ኢሥላም
🅅🅂
◍ አይሁዳዊው ወገናችን ጌዲዮን
سوره النور🥀

🌠የብረሀን/ ምዕራፍ🏞
🌇

🕌በመድና፣የወረደ🕌

ራሀቱል፣ቀልብ❤️
@slmatawahi
ይገደል!

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

17፥33 ”ያቺንም አላህ እርም ያረጋትን ነፍስ ያለ ሕግ አትግደሉ”፡፡ وَلَا تَقْتُلُوا النَّفْسَ الَّتِي حَرَّمَ اللَّهُ إِلَّا بِالْحَقِّ

“ዘንብ” ذَنب ማለት “ኃጢአት” ማለት ነው፥ በሥነ-ኃጢአት ጥናት”hamartiology” ውስጥ “ኃጢአት” ማለት “አሏህ ያዘዘውን መልካም ነገር አለማድረግ፥ የከለከለውን ክፉ ነገር ማድረግ” ማለት ነው። ኃጢአት “ከባኢሩ አዝ-ዘንብ” كَبَائِر الْذَنب እና “ሶጋኢሩ አዝ-ዘንብ” صَغَائِر الْذَنب ተብለው ለሁለት ይከፈላሉ፥ “ከባኢር” كَبَائِر ማለት “ዐብይ” “ታላቅ” ማለት ሲሆን “ሶጋኢር” صَغَائِر ማለት ደግሞ “ንዑስ” “ትንሽ” ማለት ነው። ከዐበይት ኃጢአቶች መካከል አንዱ ነፍስን ያለ ሕግ መግደል ነው፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 83, ሐዲስ 53
ዐብደሏህ ኢብኑ ዐምሪው እንደተረከው፦ “ነቢዩም”ﷺ” አሉ፦ ”ዐበይት ኃጢአቶች በአሏህ ላይ ማሻረክ፣ ወላጆችን አለማክበር፣ ነፍስን መግደል እና የውሸት መሓላ ናቸው”። عَنْ عَبْدِ اللَّهِ بْنِ عَمْرٍو، عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ “‏ الْكَبَائِرُ الإِشْرَاكُ بِاللَّهِ، وَعُقُوقُ الْوَالِدَيْنِ، وَقَتْلُ النَّفْسِ، وَالْيَمِينُ الْغَمُوسُ ‏”‌‏.‏

“ቀትሉ አን-ነፍሥ” قَتْلُ النَّفْس የሚለው ቃል ይሰመርበት! አምላካችን አሏህ ነፍስን መግደል ሐራም አርጓል፦
17፥33 ”ያቺንም አላህ እርም ያረጋትን ነፍስ ያለ ሕግ አትግደሉ”፡፡ وَلَا تَقْتُلُوا النَّفْسَ الَّتِي حَرَّمَ اللَّهُ إِلَّا بِالْحَقِّ

“እርም ያረጋት” ለሚለው የገባው ቃል “ሐረመ” حَرَّمَ መሆኑ ልብ አድርግ! “ሐራም” حَرَام የሚለው ቃል እራሱ “ሐረመ” حَرَّمَ ማለትም “ከለከለ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “የተከለከለ” ማለት ነው። "ሕግ" ተብሎ የተቀመጠው ቃል "ሐቅ" حَقِّ ሲሆን በሐቅ፣ በእውነት፣ በፍትሕ ነፍስ ሊገደል ይችላል። ለምሳሌ በባይብል የአምላክን ስም የሰደበ እንዲገደል ወፍራም ትእዛዝ አለ፦
ዘሌዋውያን 24፥16 የእግዚአብሔርንም ስም የሚሰድብ ፈጽሞ "ይገደል"።

"ይገደል" ብሎ ትእዛዝ የሰጠው ሙሴ ሳይሆን የሙሴ አምላክ እንደሆነ ዐውደ ንባቡ ላይ፦ "እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው" የሚል ቃል አለ፦
ዘሌዋውያን 24፥1 "እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው"።

አንድ ሰው ከአንዱ አምላክ ውጪ ሌላ ማንነትን "እናምልክ" ብሎ ቢያስተምርህ ፈጽመህ "ግደለው" የሚል መመሪያ አለ፦
ዘዳግም 13፥6-9 የእናትህ ልጅ ወንድምህ ወይም ወንድ ልጅህ ወይም ሴት ልጅህ ወይም በብብትህ ያለች ሚስትህ ወይም እንደ ነፍስህ ያለ ወዳጅህ በስውር፦ ና፥ ሄደን ከምድር ዳር ጀምሮ እስከ ምድር ዳር ድረስ ወደ አንተ የቀረቡት ከአንተም የራቁት አንተን ከብበውህ ያሉ አሕዛብ ከሚያመልኩአቸው አማልክት፥ አንተም አባቶችህም የማታውቋቸውን ሌሎች አማልክት "እናምልክ" ብሎ ቢያስትህ፥ እሺ አትበለው፥ አትስማውም፤ ዓይንህም አይራራለት፥ እትማረውም፥ አትሸሽገውም፤ ነገር ግን ፈጽመህ "ግደለው"፤ እርሱን ለመግደል በፊት የአንተ እጅ፥ ከዚያም በኋላ የሕዝቡ ሁሉ እጅ በላዩ ትሁን።

አስመላኪው ብቻ ሳይሆን ከአንዱ አምላክ ውጪ ለሌላ ማንነትን የሚሠዋ ይገደላል፥ እንዲሁ የእስራኤልንም አምላክ የማይፈልግ ይገደል ዘንድ መሐላ አለ፦
ዘጸአት 22፥20 ከእግዚአብሔር በቀር ለአንዳች አምላክ የሚሠዋ ፈጽሞ "ይጥፋ"።
ዘዳግም 17፥3 ሄዶም ሌሎች አማልክትን ያመለከ፥ እኔ ላላዘዝኋቸው ለፀሐይና ለጨረቃ ለሰማይም ሠራዊት ሁሉ የሰገደ ቢገኝ፥
ዘዳግም 17፥5 ይህን ክፉ ነገር የሠሩትን ያን ወንድ ወይም ያችን ሴት ወደ በርህ ታመጣቸዋለህ፥ እስኪሞቱም ድረስ በድንጋይ ትወግራቸዋለህ።
2 ዜና 15፥13 የእስራኤልንም አምላክ እግዚአብሔርን የማይፈልግ፥ ታናሽ ወይም ታላቅ፥ ወንድ ወይም ሴት ቢሆን፥ ይገደል ዘንድ ማሉ።

የጥንቆላ አምልኮ ከአንድ አምላክ ውጪ ስለሆነ "ጠንቋዮች ፈጽመው ይገደሉ" የሚል ትእዛዝ አለ፦
ዘሌዋውያን 20፥27 ሰው ወይም ሴት መናፍስትን ቢጠሩ ወይም ጠንቋዮች ቢሆኑ ፈጽመው ይገደሉ፤ በድንጋይ ይውገሩአቸው፤ ደማቸው በላያቸው ነው።

በተጨማሪም አባቱን ወይም እናቱን የሚሰድብ "ይገደል" ተብሏል፦
ዘጸአት 21፥17 አባቱን ወይም እናቱን የሚሰድብ ፈጽሞ "ይገደል"።

ማናቸውም ሰው ከእንስሳ ጋር ተራክቦ ቢያደርግ "ይገደል" ተብሏል፦
ዘሌዋውያን 20፥15 ማናቸውም ሰው ከእንስሳ ጋር ቢገናኝ ፈጽሞ "ይገደል"፥ እንስሳይቱንም ግደሉአት።

ግብረ ሰዶም የሚያደርጉ "ይገደሉ" ተብሏል፦
ዘሌዋውያን 20፥13 ማናቸውም ሰው ከሴት ጋር እንደሚተኛ ከወንድ ጋር ቢተኛ ሁለቱ ጸያፍ ነገር አድርገዋል፤ ፈጽመው ይገደሉ፤ ደማቸው በላያቸው ነው።

ከላይ "ይገደል" ወይም "ይገደሉ" የሚለው ፈጣሪ እንደሆነ ልብ አድርግ! በአዲስ ኪዳንም ቢሆን እነዚህ ሕግጋት አልተሻሩም፦
ማቴዎስ 5፥17-18 እኔ ሕግንና ነቢያትን ለመሻር የመጣሁ አይምሰላችሁ፤ ልፈጽም እንጂ ለመሻር አልመጣሁም። እውነት እላችኋለሁ፥ ሰማይና ምድር እስኪያልፍ ድረስ፥ ከሕግ አንዲት የውጣ ወይም አንዲት ነጥብ ከቶ አታልፍም፥ ሁሉ እስኪፈጸም ድረስ።

ሰማይ እና ምድር እስኪያልፍ ድረስ ከሕግ አንዲት አትሻርም። የፈጣሪን ሕግ የማይረባ እና ደካማ ብሎ በመንቀፍ "ተሽራለች" ያለው ጳውሎስ ነው፦
ዕብራውያን 7፥18 ስለዚህም የምትደክም የማትጠቅምም ስለሆነች የቀደመች ትእዛዝ "ተሽራለች"።

የጳውሎስ ትክክለኛ ስሙ "ሳውል" ሲሆን በኃላ ላይ ለራሱ ያወጣው ስም "ጳውሎስ" ነው፥ "ጳውሎስ" ማለት ትርጉሙ "ታናሽ" ማለት ነው። እንግዲህ ከነዚህ ከሁሉ ካነሱት ትእዛዛት አንዲቱን የሚሽር ለሰውም ተሽሯል ብሎ የሚያስተምር ሳውል በመንግሥተ ሰማያት ከሁሉ "ታናሽ" ነው፦
ማቴዎስ 5፥19 እንግዲህ ከነዚህ ከሁሉ ካነሱት ትእዛዛት አንዲቱን የሚሽር ለሰውም እንዲሁ የሚያስተምር ማንም ሰው በመንግሥተ ሰማያት ከሁሉ "ታናሽ" ይባላል።

ስለዚህ የተቆላበት እያለ የተጋፈበትን መጠየቅ አግባብ አይደለም። አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://t.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ሰይጣን በክርስትና
የነብያት መንገድ | طريق الأنبياء
- "ቁርዓን ከአላህ ለመውረዱ ማስረጃ"
- "ሰይጣን በክርስትና አስተምህሮ"
- "የገድላት ቅሌት"


◍ ወንድም ሳላህ
◍ ወንድም አቡ ሳላህ
◍ እኅት ዛህራ
እነዚያ «ጌታችን አላህ ነው» ያሉ ከዚያም ቀጥ ያሉ «አትፍሩ፤ አትዘኑም፤ በዚያችም ተስፋ ቃል ትደረግላችሁ በነበራችሁት ገነት ተበሰሩ» በማለት በነሱ ላይ መላእክት ይወርዳሉ፡፡

«እኛ በቅርቢቱም ሕይወት በመጨረሻይቱም #ረዳቶቻችሁ ነን! ለእናንተም በእርሷ ውስጥ ነፍሶቻችሁ የሚሹት ሁሉ አልላችሁ፡፡ ለእናንተም በእርሷ ውስጥ #የምትፈልጉት ሁሉ አልላችሁ፡፡

@slmatawahi
ሁሉን ቻይ አምላክ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

2፥284 አላህም በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነው፡፡ وَاللَّهُ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرٌ

አንድ አምላክነት ያለው ማንነት በራሱ ሁሉን ነገር ማድረግ ይችላል። ለምሳሌ አምላካችን አሏህ ሁሉን ነገር በማድረግ ቻይ ነው፦
2፥284 አላህም በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነው፡፡ وَاللَّهُ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرٌ

በባይብልም ቢሆን የኢየሱስ ፈጣሪ እና አምላክ፦ "በውኑ እኔን የሚያቅተኝ ነገር አለን?" በማለት ይጠይቃል፥ መልሱ ለፈጣሪ የሚሳነው ምንም ነገር የለም፦
ኤርሚያስ 32፥28 በውኑ እኔን የሚያቅተኝ ነገር አለን?
ዘፍጥረት 18፥14 በውኑ ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር አለን?
ሉቃስ 1፥37 ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር የለምና።
ኢዮብ 42፥2 ሁሉን ታደርግ ዘንድ ቻይ እንደ ሆንህ፥ አሳብህም ይከለከል ዘንድ ከቶ እንደማይቻል አወቅሁ።

ቅሉ ግን ኢየሱስ አብ ሲያደርግ እያየ የሚያደርግ እንጂ ከራሱ ሊያደርግ ምንም አይችልም፦
ዮሐንስ 5፥19-20 ስለዚህ ኢየሱስ መለሰ፥ እንዲህም አላቸው፦ እውነት እውነት እላችኋለሁ አብ ሲያደርግ ያየውን ነው እንጂ ወልድ ከራሱ ሊያደርግ ምንም አይችልም፥ ያ የሚያደርገውን ሁሉ ወልድ ደግሞ ይህን እንዲሁ ያደርጋልና። አብ ወልድን ይወዳልና፥ የሚያደርገውንም ሁሉ ያሳየዋል፤ እናንተም ትደነቁ ዘንድ ከዚህ የሚበልጥ ሥራ ያሳየዋል።

"ያ" የሚለውን የሩቅ አመልካችን ተውላጠ ስም አብ ለኢየሱስ ለማሳየት የሚያደርገውን ሥራ ያመላክታል፥ "ይህን" የሚለው የቅርብ አመልካችን ተውላጠ ስም "ያ" የሚለውን ተክቶ የመጣ ሲሆን አብ ለወልድ እንዲያደርግ የሚያሳየውን ሥራ ያመላክታል። አንድ አምላክነት ያለው ማንነት ምን መሥራት እንዳለበት ሌላ ማንነት እንዴት ያሳየዋል? ኢየሱስ የሚያደርገውን ሁሉ አብ እያሳየው ብቻ ነው፥ "ከዚህ የሚበልጥ ሥራ ያሳየዋል" ሲል የሚሠራውን ሥራ ፈጣሪ እያሳየው ያደርጋል ማለት ነው። ወልድ ምን ምን ማድረግ እንዳለበት አብ ያሳየዋል ማለት ወልድ ሙታንን እንዲያስነሳ፣ ለምጻም እንዲያነጻ፣ ሽባ እንዲተረትር መመሪያ፣ ሥልጣን እና ኃይል ይሰጠዋል ማለት ነው፥ ለምሳሌ ፈሪሳውያን በሰይጧን ዘንድ ያዩት ያደርጋሉ ማለት ሰይጧን መመሪያ እየሰጣቸው ያደርጋሉ ማለት እንደሆነ ሁሉ ኢየሱስም በአብ ዘንድ ያየውን ያደርጋል ማለት አብ መመሪያ እየሰጠው ያደርጋል ማለት ነው፦
ዮሐንስ 8፥38 እኔ በአባቴ ዘንድ ያየሁትን እናገራለሁ፤ እናንተም ደግሞ በአባታችሁ ዘንድ ያያችሁትን ታደርጋላችሁ።

ኢየሱስ ተአምር እንዲሠራ የጌታ ኃይል ሆኖሎት እንጂ ከራሱ አንዳች ሊያደርግ አይቻለውም። ኢየሱስ ከራሱ ምንም ማድረግ ካልቻለ ሁሉን ቻይ አምላክ አይደለም፦
ሉቃስ 5፥17 እርሱም እንዲፈውስ የጌታ ኃይል ሆነለት።
ዮሐንስ 5፥30 እኔ "ከ"-"ራሴ" አንዳች ላደርግ አይቻለኝም።

"እኔ" የሚለው ባለቤት "እኔነትን" እንጂ ስጋን አያሳይም፥ ስጋ ብቻውን ማንነት ስላልሆነ "እኔ" አይልም። ነገር ግን ኢየሱስ ከምንነቱ ምንም ማድረግ ስለማይችል "ራሴ" የሚል ድርብ ተውላጠ ስም ይጠቀማል። ጭራሽ ኢየሱስ የሚያደርገው ሥራ በፈጣሪ ስም ሲሆን እርሱ ነቢይ ስለመሆኑ የሚመሰክር ነው፦
ዮሐንስ 10፥25 እኔ በአባቴ ስም የማደርገው ሥራ ስለ እኔ ይመሰክራል።
ዮሐንስ 5፥36 አብ ልፈጽመው የሰጠኝ ሥራ ይህ የማደርገው ሥራ አብ እንደ ላከኝ ስለ እኔ ይመሰክራልና።

ኢየሱስ የሚያደርገው ሥራ ሁሉ መልእክተኛ ስለመሆኑ ምስክር እንዲሆን በስጦታ ያገኘው ስለሆነ "አብ ልፈጽመው የሰጠኝ ሥራ" በማለት እንቅጩን ፍርጥ አድርጎ ይናገራል፦
ዮሐንስ 17፥4 እኔ ላደርገው የሰጠኸኝን ሥራ ፈጽሜ በምድር አከበርሁህ፤

"የሰጠኸኝን ሥራ" የሚለው ኃይለ-ቃል ይሰመርበት። ኢየሱስ ሲያደርግ የነበረውን ሥራ ሙት ማስነሳት፣ ሽባ መተርተር፣ ዕውር ማብራት ወዘተ በእርሱ የሚያምን ሰው ሊያደርገው ይችላል፥ እረ ኢየሱስ ካደረገው በላይ የሚበልጥ ያደርጋል፦
ዮሐንስ 14፥13 እውነት እውነት እላችኋለሁ በእኔ የሚያምን እኔ የማደርገውን ሥራ እርሱ ደግሞ ያደርጋል፥ ከዚህም የሚበልጥ ያደርጋል።

እውነት ኢየሱስ ሁሉን ቻይ አምላክ ቢሆን ኖሮ ሁሉን የሚችል አምላክ ሊያደርግ የሚችለውን ሰው ሊያደርግ ይችላልን? ከሁሉን የሚችል አምላክ በላይ የሚበልጥ ሥራ ሊሠራ ይችላልን? ስለዚህ ኢየሱስ የሚያደርገው ሥራ የአምላክነት ሥራ ሳይሆን በጸጋ እና በስጦታ እንዲሥራ የታዘዘው ሥራ ነው፥ ከፈጣሪ እያየ የሚሠራ ማንነት እራሱ ፈጣሪ ከሆነ አንዱ የሚያሳይ ሁለተኛው እያየ የሚኮርጅ ሁለት ፈጣሪ ይሆን ነበር። ነገር ግን ኢየሱስ ከራሱ ምንም ማድረግ የማይችል ፍጡር ብቻ ነው።

ክርስቲያኖች ሆይ! የኢየሱስን ፈጣሪ እና አምላክ አንዱን አምላክ እንድታመልኩ ወደ ኢሥላም እንጠራችኃለን። አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://t.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ውይይት
የነብያት መንገድ | طريق الأنبياء
●▯ውይይት ▯●

- "የዮሐንስ ራዕይ"
- "ኢየሱስ ፍጡር ነው"
- "ባይብል ተበርዟል"


◍ ወንድም እስሚዝ
🆅🆂
◍ ወገናችን ሐና

ሌሎችም የተሳተፉበት
♡ ቲላዋ ♡ ……………🍃

@slmatawahi
የዓኢሻህ"ረ.ዐ." ትዳር

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

61፥8 *"የአላህን ብርሃን በአፎቻቸው ሊያጠፉ ይሻሉ፡፡ አላህም ከሓዲዎቹ ቢጠሉም እንኳ ብርሃኑን ገላጭ ነው"*፡፡ يُرِيدُونَ لِيُطْفِئُوا نُورَ اللَّهِ بِأَفْوَاهِهِمْ وَاللَّهُ مُتِمُّ نُورِهِ وَلَوْ كَرِهَ الْكَافِرُونَ

አንዲት እንስት ወጣት ናት፥ በሙሥሊሞች ዘንድ በአውንታዊ መልኩ በኢሥላም ታሪክ ላይ አሻራዋን ካስተቀመጡ እና ጉልህ ሚና ከተጫወቱት ሰዎች አንዷ ናት። ይህቺ ወጣት ከነቢያችን"ﷺ" ሰምታ ስለ ነቢያችን"ﷺ" ሕይወትና አኗኗር፣ ስለ ውርስ፣ ስለ ጋብቻ፣ ስለ መጨረሻው ዘመን ትምህርት ወዘተ 2,210 የሚደርሱ ሐዲሳትን ተርካለች፥ ቁርኣን የምእመናት እናቶች ከሚላቸው አንዷ ናት፦
33፥6 *"ነቢዩ በምእምናን ከራሳቸው ይበልጥ ተገቢ ነው፥ ሚስቶቹም እናቶቻቸው ናቸው"*፡፡ النَّبِيُّ أَوْلَىٰ بِالْمُؤْمِنِينَ مِنْ أَنفُسِهِمْ ۖ وَأَزْوَاجُهُ أُمَّهَاتُهُمْ

ይህችም ወጣት ሴት "ኡመል ሙእሚኒን" أُمِّ الْمُؤْمِنِين ማለትም "የምእመናን እናት" በሚል ማዕረግ የምትጠራ ዓኢሻህ"ረ.ዐ." ናት፥ በአንድ ወቅት ዝሙት ሠርታለች ተብላ የሐሰት ክስ ቀርቦባት አምላካችን አሏህ ሡረቱ አን-ኑር 24፥11-20 ያለውን አንቀጽ ስለ ንጽህናዋ አውርዷል፦
24፥15 *"በምላሶቻችሁ በምትቅበባሉት ጊዜ ለእናንተም በእርሱ ዕውቀት በሌላችሁ ነገር በአፎቻችሁ በተናገራችሁና እርሱ አላህ ዘንድ ከባድ ኀጢአት ኾኖ ሳለ ቀላል አድርጋችሁ ባሰባችሁት ጊዜ ከባድ ቅጣት በነካችሁ ነበር*፡፡ إِذْ تَلَقَّوْنَهُ بِأَلْسِنَتِكُمْ وَتَقُولُونَ بِأَفْوَاهِكُم مَّا لَيْسَ لَكُم بِهِ عِلْمٌ وَتَحْسَبُونَهُ هَيِّنًا وَهُوَ عِندَ اللَّهِ عَظِيمٌ
ሡነን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 43, ሐዲስ 447
ዓኢሻህ"ረ.ዐ." እንደተረከችው፦ "ነቢዩም"ﷺ"፦ *"ዓኢሻህ ሆይ አብሽሪ! አሏህ ስለ ንጽህናሽ ወሕይ አውርዷል፥ ከዚያም ለእርሷ የቁርኣኑን አንቀጽ ቀሩላት። ወላጆቿም፦ "የአሏህ መልእክተኛን"ﷺ" ግንባር ሳሚ!" አሏት፥ እርሷም፦ "ለእናንተ ሳይሆን ለአሏህ ምስጋና ይሁን!" አለች"*። أَنَّ عَائِشَةَ، رضى الله عنها قَالَتْ ثُمَّ قَالَ تَعْنِي النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ أَبْشِرِي يَا عَائِشَةُ فَإِنَّ اللَّهَ قَدْ أَنْزَلَ عُذْرَكِ ‏"‏ ‏.‏ وَقَرَأَ عَلَيْهَا الْقُرْآنَ فَقَالَ أَبَوَاىَ قُومِي فَقَبِّلِي رَأْسَ رَسُولِ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏.‏ فَقَالَتْ أَحْمَدُ اللَّهَ لاَ إِيَّاكُمَا ‏.‏
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 64, ሐዲስ 188
አቢ ኢብኑ መለይካህ እንደተረከው፦ *"ዓኢሻህ፦ "በምላሶቻችሁ በምትቅበባሉት ጊዜ" የሚለውን አንቀጽ ትቀራ ነበር፥ "አል-ወልቅ" ቅጥፈት ነው" ትል ነበር። አቢ ኢብኑ መለይካህም፦ "ይህን አንቀጽ ስለ እርሷ እንደሚናገር ከማንም ይልቅ ታውቅ ነበር" አለ"*። حَدَّثَنِي يَحْيَى، حَدَّثَنَا وَكِيعٌ، عَنْ نَافِعِ بْنِ عُمَرَ، عَنِ ابْنِ أَبِي مُلَيْكَةَ، عَنْ عَائِشَةَ ـ رضى الله عنها ـ كَانَتْ تَقْرَأُ ‏{‏إِذْ تَلِقُونَهُ بِأَلْسِنَتِكُمْ‏}‏ وَتَقُولُ الْوَلْقُ الْكَذِبُ‏.‏ قَالَ ابْنُ أَبِي مُلَيْكَةَ وَكَانَتْ أَعْلَمَ مِنْ غَيْرِهَا بِذَلِكَ لأَنَّهُ نَزَلَ فِيهَا‏.‏

ዓኢሻህ"ረ.ዐ." አባቷ አቡበከር አስ-ሲዲቅ እናቷ ኡሙ ሩማን ሲሆኑ የነቢያችን"ﷺ" ባልደረቦች ናቸው፥ ዓኢሻህ ለነቢያችን"ﷺ" ሚስት እንድትሆን ለቤተሰቦቿ አሳቡን ያመጣችው የነቢያችን"ﷺ" ሴት ባልደረባ የነበረችው ኸውላህ ቢንት ሐኪም"ረ.ዐ." ናት። ቅሉ ግን ዓኢሻህ ለነቢያችን"ﷺ" ሚስት እንደምትሆን ነቢያችን"ﷺ" በሕልማቸው ሁለት ጊዜ አይተዋታል፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 67, ሐዲስ 16
ዓኢሻህ እንደተረከችው፦ "የአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"በሕልሜ ሁለት ጊዜ አይቼሻለው፥ አንድ ሰው(ጂብሪል) በሐር ጨርቅ ተሸክሞሽ፦ "ይህቺ የአንተ ሚስት ናት" አለኝ። ስገልጥ እነሆ አንቺ ነበርሽ። እኔም ዓኢሻህ ለራሴ፦ "ይህ ሕልም ከአሏህ ከሆነ ይፈጸማል" አልኩኝ"*። عَنْ عَائِشَةَ، قَالَتْ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ أُرِيتُكِ فِي الْمَنَامِ مَرَّتَيْنِ، إِذَا رَجُلٌ يَحْمِلُكِ فِي سَرَقَةِ حَرِيرٍ فَيَقُولُ هَذِهِ امْرَأَتُكَ، فَأَكْشِفُهَا فَإِذَا هِيَ أَنْتِ، فَأَقُولُ إِنْ يَكُنْ هَذَا مِنْ عِنْدِ اللَّهِ يُمْضِهِ

ዓኢሻህ ለነቢያችን"ﷺ" የተዳረችው በስድስት ዓመቷ ሲሆን ለዐቅመ-ሐዋህ እስክትደርስ ድረስ ለሦስት ዓመት ከተጠበቀ በኃላ በዘጠኝ ዓመቷ ወደ ነቢያችን"ﷺ" ቤት ገብታለች፦
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 16, ሐዲስ 82
ዓኢሻህ እንደተረከችው፦ *"ነቢዩ"ﷺ" ሲያገቡኝ የስድስት ዓመት እንስት ነበርኩኝ፥ የዘጠኝ ዓመት እንስት ስሆን ወደ ቤቱ ገባሁኝ"*። عَنْ عَائِشَةَ، قَالَتْ تَزَوَّجَنِي النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم وَأَنَا بِنْتُ سِتِّ سِنِينَ وَبَنَى بِي وَأَنَا بِنْتُ تِسْعِ سِنِينَ
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 67, ሐዲስ 69
ዓኢሻህ"ረ.ዐ." እንደተረከችው፦ *"ነቢዩ"ﷺ" ሲያገቧ የስድስት ዓመት ነበረች፥ የዘጠኝ ዓመት እንስት ሲሆናት ደረሱባት"*። عَنْ عَائِشَةَ ـ رضى الله عنها ـ أَنَّ النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم تَزَوَّجَهَا وَهْىَ بِنْتُ سِتِّ سِنِينَ
ሥነ-ጋብቻ ጥናትMatrimony" እንደሚያትተው አንዲት እንስት ለዐቅመ-ሐዋህ ለመድረስ ከሚታዩ ምልክቶች አንዱ ሐይድ ማየት ነው። "ሐይድ" حَيْض ማለት "የወር አበባ" ማለት ነው፥ የወር አበባ ላይ ያለች ሴት ደግሞ "ሓኢድ" حَائِض ትባላለች። አንዲት እንስት የወር አበባ ልታይበት የምትችለው አማካኝ ዕድሜ ከ 12-13 ሲሆን እንደየ እንስቷ ሁኔታ ከ 12 በታች እስከ 9 ቶሎ ሊመጣ አሊያም ከ 13 በላይ እስከ 16 ሊዘገይ ይችላል። በኢሥላማዊ መዛግብትም አጥ-ጦበሪን ጨምሮ እንደተዘገበው የአንዲት እንስት የወር አበባ የምታየበት ትንሹ እድሜ ዘጠኝ መሆኑ እንዲህ ተዘግቧል፦
አልካፊ ፊ ፊቅህ ኢብነ ሀንበል፣ ጥራዝ 1፣ ገጽ 74፣ ሸርህ አል– ዑምዳ፣ ጥራዝ 1፣ ገጽ 480
*"ትንሹ የሴት ልጅ የወር አበባ የምታይበት እድሜ ዘጠኝ ዓመት ነው"*።

የጋብቻ ጊዜ በጥንታዊ ጊዜ፣ በዘመናዊ ጊዜ፣ በድኅረ-ዘመናዊ ጊዜ ከትውልድ ወደ ትውልድ፥ ከባህል ወደ ባህል ይለያያል። ኢንሳይክሎፒዲያ ብሪታኒካ እንዲህ ይላል፦
*“ለጋብቻ ትንሹ የዕድሜ ገደብ በፊት 12 ዓመት አልያም ከዚያም ያነሰ የነበረው ሲሻሻል እና ከፍ ሲል ቆይቶ በአብዛኛው አገሮች አሁን በ15 እና በ21 ዕድሜ መካከል ሆኗል"*፡፡ Encyclopedia Britannica 2006 page 171.
የጋብቻ ጥናት ምሁር ብራውን ዮናታን፦ *"አብዛኛው የጋብቻ ምሁራን ዓኢሻህ በዘጠኝ ዓመቷ ለዐቅመ-ሔዋን ደርሳለች ብለዋል"*።
Brown, Jonathan (2014). Misquoting Muhammad: The Challenge and Choices of Interpreting the Prophet's Legacy. Oneworld Publications. pp. 143–4.

ጋብቻ ማለት በሁለት ተቃራኒ መካከል ያለ ስምምነት ነው፥ አንድ ተባእት አንዲትን እንስት አስገድዶ ማግባት ሐላል አይደለም። ነቢያችንም”ﷺ” ዓኢሻን ሊደርሱባት ሲሉ ፈቃደኝነቷን ጠይቀዋታል፦
4፥19 እናንተ ያመናችሁ ሰዎች ሆይ! *”ሴቶችን ያስገደዳችሁ ኾናችሁ ልትወርሱ ለእናንተ አይፈቀድም”*፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا لَا يَحِلُّ لَكُمْ أَن تَرِثُوا النِّسَاءَ كَرْهًا
አል-ሙሥተድረክ አል-ሐኪም ጥራዝ 4 ገጽ 11
ሰዒድ ኢብን ከሲር ከአባቱ አባቱ ከዓኢሻህ "ረ. ዐ." እንዳስተላለፈው፦ *የአሏህ መልእክተኛ"ﷺ" ለአዒሻ እንዲህ አሏት፦ *“በዱንያህ ሆነ በአኺራ የእኔ ባለቤት መሆንን አትፈልጊምን? እርሷም፦ “ወሏሂ እፈልጋለሁ እንጂ” አለች፡፡ እርሳቸውም፦ "አንቺ በዱንያህ ሆነ በአኺራም የእኔ ባለቤቴ ነሽ" አሏት"*፡፡ عن سَعِيدُ بْنُ كَثِيرٍ عَنْ أَبِيهِ ، قَالَ حَدَّثَتْنَا عَائِشَةُ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهَا أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قال لعائشة -رضي الله عنها-: «أَمَا تَرْضَيْنَ أَنْ تَكُونِي زَوْجَتِي فِي الدُّنْيَا وَالْآخِرَةِ؟» قُلْتُ: بَلَى وَاللَّهِ، قَالَ: «فَأَنْتِ زَوْجَتِي فِي الدُّنْيَا وَالْآخِرَةِ».

ሚሽነሪዎች ዓኢሻህ ለነቢያችን"ﷺ" መዳሯ የሚያንገበግባቸው፣ ልወቅልሽ እና ልቆርቆርልሽ የሚሏት አስብቶ አራጅ እና ቅቤ አንጓች ሆነው እንጂ ለእርሷ አስበው አይደለም። እርሷ ጋብቻውን ወዳ እና ፈቅዳ የገባችበት ጉዳይ ነው፥ ለነቢያችን"ﷺ" ልዩ ፍቅር የነበራት ሴት ነበረች፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 63, ሐዲስ 43
ዓኢሻህ"ረ.ዐ." እንደተረከችው፦ *"በማንም ሴት እንደ ኸዲጃህ ቅናት ተሰምቶኝ ዐያውቅም፥ የአሏህ መልእክተኛ"ﷺ" ብዙ ጊዜ ያነሷት ነበር። እኔን ያገቡኝ እርሷ በሞተች በሦስት ዓመቷ ነው፥ ከጌታቸው ዐዘ ወጀል ወይንም ከጂብሪል"ዐ.ሠ." እርሷ በጀነት ጨፌ ሥርፋ እንዳላት ይበሰሩ ነበር"*። عَنْ عَائِشَةَ ـ رضى الله عنها ـ قَالَتْ مَا غِرْتُ عَلَى امْرَأَةٍ مَا غِرْتُ عَلَى خَدِيجَةَ، مِنْ كَثْرَةِ ذِكْرِ رَسُولِ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم إِيَّاهَا‏.‏ قَالَتْ وَتَزَوَّجَنِي بَعْدَهَا بِثَلاَثِ سِنِينَ، وَأَمَرَهُ رَبُّهُ عَزَّ وَجَلَّ أَوْ جِبْرِيلُ ـ عَلَيْهِ السَّلاَمُ ـ أَنْ يُبَشِّرَهَا بِبَيْتٍ فِي الْجَنَّةِ مِنْ قَصَبٍ‏.‏

በሞተችው ሚስታቸው በኸዲጃህ የምትቀናው ፍቅር ካልሆነ ምንድን ነው? ዓኢሻህ ከነቢያችን"ﷺ" ጋር የነበራትን መስተጋብር ለምእመናን ጋብቻ አርአያ እንዲሆነ ብዙ ጊዜ ታነሳለች። ለምሳሌ አንዲት እንስት ከባሏ ጋር ከተራክቦ በኃላ በአንድ ገንዳ ውስጥ መታጠብ እንደሚችሉ ለማስተማር እርሷ ከባለቤቷ ከነቢያችን"ﷺ" ጋር ከተራክቦ በኃላ በአንድ ገንዳ ትታጠብ እንደነበር ትናገራለች፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 5, ሐዲስ 3
ዓኢሻህ እንደተረከችው፦ *"እኔ እና ነቢዩ"ﷺ" አል-ፈረቅ በሚባል አንድ ገንዳ እየቀዳን እንታጠብ ነበር"*። عَنْ عَائِشَةَ، قَالَتْ كُنْتُ أَغْتَسِلُ أَنَا وَالنَّبِيُّ، صلى الله عليه وسلم مِنْ إِنَاءٍ وَاحِدٍ مِنْ قَدَحٍ يُقَالُ لَهُ الْفَرَقُ‏.‏
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 5, ሐዲስ 16
ዓኢሻህ እንደተረከችው፦ *"እኔ እና ነቢዩ"ﷺ" ከጀናባህ በኃላ በአንድ ገንዳ እንታጠብ ነበር"*። عَنْ عَائِشَةَ، قَالَتْ كُنْتُ أَغْتَسِلُ أَنَا وَالنَّبِيُّ، صلى الله عليه وسلم مِنْ إِنَاءٍ وَاحِدٍ مِنْ جَنَابَةٍ‏.‏
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 5, ሐዲስ 14
ዓኢሻህ እንደተረከችው፦ *"እኔ እና ነቢዩ"ﷺ" በአንድ ገንዳ እየቀዳን እንታጠብ ነበር፥ እጆቻችንን በገንዳ ውስጥ ይተካኩ ነበር"*። عَنْ عَائِشَةَ، قَالَتْ كُنْتُ أَغْتَسِلُ أَنَا وَالنَّبِيُّ، صلى الله عليه وسلم مِنْ إِنَاءٍ وَاحِدٍ تَخْتَلِفُ أَيْدِينَا فِيهِ‏.‏
አንዲት እንስት ከባሏ ጋር በወር አበባዋ ጊዜ መነካካት፣ መብላት እና መጠጣት ወዘተ እንደምትችል ለማስተማር እርሷ ከነቢያችን"ﷺ" ጋር በወር አበባዋ ጊዜ ትነካካ፣ ትበላ እና ትጠጣ ወዘተ እንደነበር ትናገራለች፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 6, ሐዲስ 4
ዓኢሻህ እንደተረከችው፦ *"ነቢዩ”ﷺ” እኔ የወር አበባ ላይ እያለሁኝ ጭኔ ላይ ተደግፈው ቁርኣን ይቀሩ ነበር"*። أَنَّ عَائِشَةَ حَدَّثَتْهَا أَنَّ النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم كَانَ يَتَّكِئُ فِي حَجْرِي وَأَنَا حَائِضٌ، ثُمَّ يَقْرَأُ الْقُرْآنَ‏.‏
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 3, ሐዲስ 10
ዓኢሻህ እንደተረከችው፦ *"የወር አበባ ላይ ሆኜ የአሏህን መልእክተኛ"ﷺ" ጠጉር አጥብ ነበር"*። عَنْ عَائِشَةَ، قَالَتْ كُنْتُ أَغْسِلُ رَأْسَ رَسُولِ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم وَأَنَا حَائِضٌ
ሡነን ነሣኢ መጽሐፍ 1, ሐዲስ 279
ዓኢሻህ እንደተረከችው፦ *"የወር አበባ ላይ ሆኜ የአሏህን መልእክተኛ"ﷺ" ጠጉር አበጥር ነበር"*። عَنْ عَائِشَةَ، - رضى الله عنها - قَالَتْ كُنْتُ أُرَجِّلُ رَأْسَ رَسُولِ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم وَأَنَا حَائِضٌ
ሡነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 1, ሐዲስ 686
ዓኢሻህ እንደተረከችው፦ *"እኔ በወር አበባ ጊዜ አጥንት እግጥ ነበር፥ የአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" ስጋውን ከእኔ ይወስዱና አፌ ያረፈበት ቦታ ላይ አፋቸው በማሳረፍ ይግጡ ነበር። እንደዚሁም የወር አበባ ላይ እያለሁ በእቃ ስጠጣ የአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" እቃውን ይወስዱና አፌ ያረፈበት ቦታ ላይ አፋቸውን በማሳረፍ ይጠጡ ነበር"*። عَنْ عَائِشَةَ، قَالَتْ كُنْتُ أَتَعَرَّقُ الْعَظْمَ وَأَنَا حَائِضٌ، فَيَأْخُذُهُ رَسُولُ اللَّهِ ـ صلى الله عليه وسلم ـ فَيَضَعُ فَمَهُ حَيْثُ كَانَ فَمِي وَأَشْرَبُ مِنَ الإِنَاءِ فَيَأْخُذُهُ رَسُولُ اللَّهِ ـ صلى الله عليه وسلم ـ فَيَضَعُ فَمَهُ حَيْثُ كَانَ فَمِي وَأَنَا حَائِضٌ ‏.‏
ሡነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 1, ሐዲስ 675
ዓኢሻህ እንደተረከችው፦ "የአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" ለእኔ፦ *"ከመሥጂድ ሰሌኑን አምጪልኝ" አሉኝ፥ እርሷም፦ "በወር አበባ ላይ ነኝ" አልኩኝ" አለች። እርሳቸውም፦ "የወር አበባሽ እኮ በእጅሽ ውስጥ አይደለም" አሉ"*። عَنْ عَائِشَةَ، قَالَتْ قَالَ لِي رَسُولُ اللَّهِ ـ صلى الله عليه وسلم ـ ‏"‏ نَاوِلِينِي الْخُمْرَةَ مِنَ الْمَسْجِدِ ‏"‏ ‏.‏ فَقُلْتُ إِنِّي حَائِضٌ ‏.‏ فَقَالَ ‏"‏ لَيْسَتْ حَيْضَتُكِ فِي يَدِكِ ‏

አንዲት እንስት ከባሏ ጋር በፆም ጊዜ ከተራክቦ በስተቀር መነካካት፣ መሳሳም እና አብሮ መተኛት ወዘተ እንደምትችል ለማስተማር እርሷ ከነቢያችን"ﷺ" ጋር በፆም ጊዜ ትነካካ፣ ትሳሳም ወዘተ እንደነበር ትናገራለች፦
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 13, ሐዲስ 89
ዓኢሻህ"ረ.ዐ." እንደተረከችው፦ *"በፆም ወር ውስጥ የአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" ይስሟት ነበር"*። عَنْ عَائِشَةَ، - رضى الله عنها - قَالَتْ كَانَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم يُقَبِّلُ فِي شَهْرِ الصَّوْمِ
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 16, ሐዲስ 79
ዓኢሻህ"ረ.ዐ." እንደተረከችው፦ *"የአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" ፆመኛ እያሉ ከሚስታቸውን አንዷን(ዓኢሻህን) ይስሙ ነበር፥ ከዚያም ደስ ይላት ነበር"*። عَنْ عَائِشَةَ، - رضى الله عنها - قَالَتْ كَانَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم يُقَبِّلُ إِحْدَى نِسَائِهِ وَهُوَ صَائِمٌ ‏.‏ ثُمَّ تَضْحَكُ ‏
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 13, ሐዲስ 83
ዓኢሻህ"ረ.ዐ." እንደተረከችው፦ *"የአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" ፆመኛ እያሉ ሚስታቸውን ይስሙ ነበር፥ ከእናንተ ይልቅ እሳቸው ስሜታቸውን ይቆጣጠሩ ነበር"*። عَنْ عَائِشَةَ، - رضى الله عنها أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم كَانَ يُقَبِّلُ وَهُوَ صَائِمٌ وَكَانَ أَمْلَكَكُمْ لإِرْبِهِ

"ስሜታቸውን ይቆጣጠሩ ነበር" የሚለው ኃይለ-ቃል በፆም ጊዜ ተራክቦ ማድረግ ክልክል መሆኑን ለማሳየት ነው። አንዲት እንስት ከባሏ ጋር የጨዋታ ጊዜ ሊኖራት እንደምትችል ለማስተማር እርሷ ከነቢያችን"ﷺ" ጋር የጨዋታ ጊዜ እንደነበራት ትናገራለች፦
ሡነን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 15, ሐዲስ 102
አቢ ሠለማህ ከዓኢሻህ"ረ.ዐ." እንደዘገበው፦ "ዓኢሻህ ከነቢዩ"ﷺ" ጋር በጉዞ ላይ ሳለች እንዲህም አለች፦ *"ከነቢዩ"ﷺ" ጋር ሩጫ ተወዳደሩኝ እኔም አሸነፍኳቸው፥ ያሸነፍኳቸው ሳልወፍር በፊት ነበር፡፡ ከወፈርኩ በኃላ ግን ተወዳደርኳቸው አሸነፉኝ። እንዲህም አሉኝ፦ "ብድር መለስኩኝ"*። وَعَنْ أَبِي سَلَمَةَ، عَنْ عَائِشَةَ، رَضِيَ اللَّهُ عَنْهَا أَنَّهَا كَانَتْ مَعَ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم فِي سَفَرٍ قَالَتْ فَسَابَقْتُهُ فَسَبَقْتُهُ عَلَى رِجْلَىَّ فَلَمَّا حَمَلْتُ اللَّحْمَ سَابَقْتُهُ فَسَبَقَنِي فَقَالَ ‏ "‏ هَذِهِ بِتِلْكَ السَّبْقَةِ ‏"‏ ‏.‏

እውነት ሚሽነሪዎች እንደሚሉት ዓኢሻህ በነቢያችን"ﷺ" የሥነ-ልቦና እና የተክለ-ሰውነት ጥቃት ደርሶባት ቢሆን ከላይ ያለውን የፍቅር፣ የመተሳሰብ፣ የመግባባት ጊዜ ለአማንያን ይጠቅማል ብላ ትተርክ ነበርን? ነቢያችን"ﷺ" ነቢይ ሆነው በተነሱበት ጊዜ የነበሩ የኢሥላም ጠላት ነቢያችንን"ﷺ"፦ "ጠንቋይ፣ ደጋሚ፣ መተተኛ፣ ዕብድ" ወዘተ ሲሉ በዓኢሻህ እና በእሳቸው መካከል የነበረውን ጋብቻ ለምን አልተቹም? እርሷ ስለ ጋብቻዋ በአሉታዊ መልኩ አንድም ቀን አምርራና አማራ የማታውቀውን ሚሽነሪዎች ዙሪያ ገቡን ሳያዩ ኢሥላምን ለማጠልሸት እና ሙሥሊሙን ለማብሸቅ "አስገድዶ መድፈር" የሚሉት የአእምሮ ስንኩላን ስለሆኑ ነው። ብዙ ጊዜ በጥላቻ የአላህን ብርሃን በአፎቻቸው ሊያጠፉ ይሻሉ፥ ነገር ግን አላህም ብርሃኑን ገላጭ ነው፦
61፥8 *"የአላህን ብርሃን በአፎቻቸው ሊያጠፉ ይሻሉ፡፡ አላህም ከሓዲዎቹ ቢጠሉም እንኳ ብርሃኑን ገላጭ ነው"*፡፡ يُرِيدُونَ لِيُطْفِئُوا نُورَ اللَّهِ بِأَفْوَاهِهِمْ وَاللَّهُ مُتِمُّ نُورِهِ وَلَوْ كَرِهَ الْكَافِرُونَ

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://t.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ሳኡድዎች ይህን መጽሐፍ
የምትፈልጉ በቴሌ ግራም አናግሩኝ

https://t.me/Zhara_mustefa
ቃል ነበረ
የነብያት መንገድ | طريق الأنبياء
▯▩ ወይይት ▩▯

"መጀመሪያ ቃል ነበረ"

◍ ወንድም እስሚዝ
🆅🆂
◍ ወገናችን ሳዳም
◍ ወገናችን ሣምሪ
• من سورة ق .. 🌸 ..° } ..•

@slmatawahi
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
سورة الكهف كاملة تلاوة هادئة وراحة نفسية في يوم الجمعة تريح الأعصاب محمد
ديبيروف Surah al kahf
አዳምጡ