ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛ
102K subscribers
5.65K photos
97 videos
6 files
903 links
Journalist-at-large
Download Telegram
"ውድድሩ (በተለይ የማራቶን ሩጫው) በዛ ሙቀት ዶሀ ላይ መካሄዱ ስህተት ነበር። እንዴ፣ ሞትም እኮ ሊከሰት ይችላል! እኔ በሩጫ ውስጥ እንዳለፈ ሰው ሳየው ጉዳዩ ተቀባይነት የለውም"--- አትሌት ሀይሌ ገ/ስላሴ ዛሬ ከነገረኝ እና ዋሽንግተን ፖስት ላይ የወጣ ⬇️

https://www.washingtonpost.com/sports/the-latest-gebrselassie-says-runners-could-have-died/2019/09/30/45d04a62-e382-11e9-b0a6-3d03721b85ef_story.html?outputType=amp

@eliasmeseret
ዳዊት ጥበቡ ይባላል!

በጋዜጠኝነት የሰለጠነ ሲሆን ምርጥ ፎቶግራፈርም ነው። በአሁን ሰአት ቶሮንቶ፣ ካናዳ የሚገኝ ሲሆን በመንገድ ላይ የሚያገኛቸውን የተለያዩ ሰዎች ፎቶ በማንሳት እና ታሪካቸውን በማጋራት እውቅና እያገኘ መጥቷል። በቅርቡም በቪኦኤ እና ግሎባል ኒውስ ላይ ቀርቦ ነበር።

ስራዎቹን ተጋበዙልኝ: https://www.guzostories.com/

@eliasmeseret
አልሸባብ ፕሬዝደንት ኦባማ ላይ ኢትዮጵያ ውስጥ አደጋ ሊያደርስ አስቦ ነበር ተብሏል!

የቀድሞዋ የአሜሪካ የተመድ አምባሳደር ሱዛን ራይስ ፕሬዝደንት ኦባማ ኢትዮጵያን በ2015 በጎበኙበት ወቅት አልሸባብ ጥቃት ለማድረስ እንቅስቃሴ አድርጎ እንደነበር ገልፀዋል።

አክለውም በወቅቱ የኢትዮጵያ የደህንነት ሀላፊ የነበሩት ተጠርጣሪው በክትትላቸው ስር እንደሆነ ቢነግሯቸውም እነሱ ግን ጥርጣሬ ነበራቸው።

በመጨረሻም የደህንነት ሀላፊው ከተጠርጣሪው ጋር አየር መንገድ እንዳሉ (ተይዞ መሆኑ ነው) ሲነግሯቸው በፍጥነት ከነበሩበት የአፍሪካ ህብረት ወጥተው ወደ አየር ማረፊያው በማምራት ከኢትዮጵያ እንደወጡ በቴክሳስ ትሪብዩን ፌስቲቫል ላይ ተናግረዋል።

ስለዚህ የሚያወራው ክፍል 30ኛው ደቂቃ አካባቢ ይጀምራል።

https://www.c-span.org/video/?464645-2/susan-rice-speaks-texas-tribune-festival

@eliasmeseret
የ2020 የአለም ቱሪዝም ፎረምን የሚያዘጋጀው ሀገር ማን ነው?

ፓኪስታን:
https://travelnewsbuzz.com/261810/world-tourism-forum-2020-will-undoubtedly-be-held-in-islamabad-pakistan/

አንጎላ: https://macauhub.com.mo/2019/05/27/pt-angola-recebe-forum-mundial-do-turismo-em-2020/

ኢትዮጵያ: https://www.facebook.com/157746334716558/posts/674315563059630/

የቱን እንመን? ጉዳዩ እንደ ዋካንዳው የባህር ዳር ፕሮጀክት ሿሿ እንዳይሆን በደንብ ሊታይ ይገባዋል።

@eliasmeseret
⬆️
በዶኃ አትሌቲክስ ሻምፒዮና በማራቶን የተወዳደሩ የኢትዮጵያ አትሌቶች ለ3 ወር ውድድር እንዳያደርጉ ተከለከሉ!

በ17ኛው የዶኃ አለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የተወዳደሩ የኢትዮጵያ አትሌቶች ለሶስት ወር ከማንኛውም ውድድር ውጭ እንዲሆኑ ተወሰነ። የፌዴሬሽኑ አመራር ባሳለፈው ውሳኔ መሰረት በዶኃ አትሌቲክስ ሻምፒዮና በማራቶን የተወዳደሩ የኢትዮጵያ አትሌቶች በሙሉ ናቸው ለሶስት ወራት ከውድድር ውጭ እንዲሆኑ የተደረገው።

በፌዴሬሽኑ ውሳኔ መሰረትም አትሌቶቹ ጤንነትና ለአስተዳደራዊ አሰራር ሲባል ከ3 ወር በፊት ምንም አይነት ውድድር ማድረግ የለባቸውም። ይህንን ውሳኔ የሚመለከታቸው ሁሉ እንዲያከብሩ በጥብቅ ፌዴሬሽኑ አሳስቧል። ውሳኔውን መተላለፍ ከበድ ያለ እርምጃ እንደሚያስከትልም ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

Via FBC

@eliasmeseret
በአንዋር መስጅድ ዙርያ እሳት ተነስቶ የነበረ ሲሆን አሁን በቁጥጥር ስር መዋሉ ታውቋል!

Via Abdurahim Ahmed

@eliasmeseret
በሌላ ዜና:

ዛሬ ቀን 9:20 ላይ ኤግዚቢሽን ማእከል ጀርባ በደረሰው የእሳት አደጋ የ78 ሰዎች መኖርያ የሆኑ 14 ቤቶች የወደሙ ሲሆን ግምቱ 7 ሚልየን ብር የሆነ ንብረትም ተቃጥሏል። ተጎጂዎች ጊዜያዊ መጠለያ ውስጥ ናቸው።

Via Tesfaye Getnet

@eliasmeseret
በቅርቡ በግብፅ የተቀሰቀሰውን አመፅ ተከትሎ የታሰሩ ሰዎች ቁጥር ከ2,000 አልፏል!

በተነሳው ግርግር ድንጋጤ ውስጥ የገቡት ፕሬዝደንት አብደልፈታህ አልሲሲ እስካሁን ያገኙት ግልፅ ድጋፍ "የምወደው አምባገነን መሪ" ብለው በአንድ ወቅት ከገለፁዋቸው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ ብቻ ይመስላል።

@eliasmeseret

https://www.washingtonpost.com/opinions/global-opinions/trumps-favorite-dictator-panics/2019/09/30/a9cd9590-e3a2-11e9-a331-2df12d56a80b_story.html
⬆️
ጭልጋ!

"ችግሩ የተፈጠረው ቅማንት ኮሚቴውን መያዝ መቻል አለብን፤ ወንጀለኛ ነው ብሎ ነው እያሰማራ ያለው ይሄን ፋኖ፤ ወደ 8 -9 ሰው ሞቶብናል፤ 7-8 ሰው ቁስለኛ አለ። ፋኖ የሚባለው እራሱን የቻለ ልብስ ነው ያለው። ፋኖ ነው የሚለው..." የቅማንት ማህበረሰብ አባል

"ፋኖ የሚባል ጦር የለም! እውነታው ይሄ ነው" የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አበረ አዳሙ

"በክልሉ ውስጥ በህዝቦች መካከል ግጭት እንዲነሳ ለማድረግ አጀንዳ ይዞ የሚሰራ ኃይል አለ" የአማራ ክልል ሰላምና ግንባታ ደህንነት ቢሮ ኃላፊ አቶ አገኘው ተሻገር

@eliasmeseret

Via VOA/TIKVAH
⬆️
#FakePageAlert

ይህ ከ260,000 ሰው በላይ ተከታይ ያለውና በገጣሚ ሜሮን ጌትነት ስም የተከፈተው የፌስቡክ ገፅ ሀሰተኛ ነው። እጅግ በሚገርም ሁኔታ በገፁ የሚሰራጩት መልእክቶችን በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ላይክ እና ሼር ያደርጉታል። ፖስት የሚደረጉት ፎቶዎችም ከኢንስታግራም ገጿ የሚወሰዱ ናቸው።

ከወራት በፊት ገጣሚዋ በኢንስታግራም ገጿ እሷ የምትጠቀምበት የፌስቡክ አካውንቷ Meron Ghetnet የሚል ላይክ ፔጅ ያልሆነ (አካውንት) እንደሆነ ገልፃ ነበር። የዚህ ትክክለኛ ገፅ ሊንክ:

https://www.facebook.com/meron.ghetnet

@eliasmeseret

Via TIKVAH- ETH
⬆️
ትናንት ቁጣ በሚመስል መግለጫ "የማራቶን ሯጮች ለ3 ወር እንዳይሮጡ ታግደዋል" ብሎ የነበረው የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን አሁን ደግሞ "ሯጮቹ ላይ ምንም አይነት የእገዳ ውሳኔ አልተላለፈም" እያለ ነው!

ከአትሌቶቹ ጋር ኳታር የሚገኙት የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የቴክኒክ ዳይሬክትር ዱቤ ጂሎ ለቢቢሲ አማርኛ እንዳሉት በዶሃ እየተካሄደ ባለው 17ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ በማራቶን ውድድር ላይ የተሳተፉት አትሌቶች ለቀጣዮቹ ሦስት ወራት እረፍት አድርገው እንዲያገግሙ እንጂ እገዳ አለመሆኑን ገልጸዋል።

"ውሳኔው ከ42 ኪሎሜትሮች በላይ በሚሮጥበት ከባድ በሚባለው የማራቶን ውድድር ላይ የሚሳተፉ ሯጮችን ጤንነትና ደህንነት ለመጠበቅ የሚወሰድ ተቀባይነት ያለው እረፍት ነው" ብለዋል ዱቤ ጂሎ።
⬆️
የጠ/ሚሩ የማህበራዊ ዘርፍ አማካሪ ወ/ሮ ጠይባ ሀሰን መኖርያ ግቢ ውስጥ በቅርቡ ተከስቶ የነበረው ችግር ምንድን ነበር?

ማረጋገጥ የቻልኩት ጉዳይ ቢኖር የዛሬ ሳምንት ማክሰኞ ለሊት ለእሮብ አጥቢያ ከለሊቱ 10:30 ላይ ግርግር ተፈጥሮ ነበር:

- ግቢው ውስጥ አራት መንግስት የመደባቸው ጥበቃዎች ነበሩ፣ ነገር ግን የወ/ሮ ጠይባ መኪና ተሰባብሮ በዛውም ላፕቶፕ እንደተወሰደ ተነግሮኛል። ነገር ግን ሁኔታው ዘረፋ ብቻ ይሁን ወይስ ሌላ በሀላፊዋ ላይ ያነጣጠረ እንደነበር ገና እየተጣራ ነው ተብሏል።

- አራቱ ጠባቂዎች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸው ነው ተብሏል። ሌላው የተረዳሁት ነገር ይህ ሁኔታ ሲከሰት በግቢው ውስጥ አራት ሌሎች መኪናዎች እንደነበሩ እና ሰበራ እና ዘረፋ የተደረገበት ሀላፊዋ የሚጠቀሙበት መኪና ብቻ መሆኑን ነው።

- ሌሎች ተጨማሪ መረጃዎችም ከመኪናው ስር ትናንት እንደተገኙ ተነግሮኛል።
በትናንትናው የሬድዮ ፕሮግራም ካቀረብኩት የተወሰደ መረጃ ⬇️ ያድምጡት!
Audio
AudioLab
ልዩ መረጃ ከኤልያስ ጋር
በኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8

በTIKVAH-ETH ስም እየተሰራጨ ስለነበረው የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ዩኒፎርም ጉዳይ ሀሰት ስለመሆኑ በAPው ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት!


@tsegabwolde @tikvahethiopia
Audio
AudioLab
ያዳምጡ⬆️

ልዩ መረጃ ከኤልያስ ጋር
በኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8


የጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ የማህበራዊ ዘርፍ አማካሪ ወ/ሮ ጠይባ ሀሰን መኖርያ ግቢ ውስጥ በቅርቡ ተከስቶ የነበረው ችግር ምንድን ነበር?

በAPው ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት ማረጋገጥ የተቻለው የዛሬ ሳምንት ማክሰኞ ለሊት ለእሮብ አጥቢያ ከለሊቱ 10:30 ላይ ግርግር ተፈጥሮ ነበር፦

- ግቢው ውስጥ አራት መንግስት የመደባቸው ጥበቃዎች ነበሩ፣ ነገር ግን የወ/ሮ ጠይባ መኪና ተሰባብሮ በዛውም ላፕቶፕ እንደተወሰደ ተሰምቷል። ነገር ግን ሁኔታው ዘረፋ ብቻ ይሁን ወይስ ሌላ በሀላፊዋ ላይ ያነጣጠረ እንደነበር ገና እየተጣራ ነው ተብሏል።

- አራቱ ጠባቂዎች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸው ነው ተብሏል። ሌላው ይህ ሁኔታ ሲከሰት በግቢው ውስጥ አራት ሌሎች መኪናዎች እንደነበሩ እና ሰበራ እና ዘረፋ የተደረገበት ሀላፊዋ የሚጠቀሙበት መኪና ብቻ መሆኑን ነው።

- ሌሎች ተጨማሪ መረጃዎችም ከመኪናው ስር ትናንት እንደተገኙ ተሰምቷል።

Via Elias Meseret - ልዩ መረጃ በኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Audio
AudioLab
ያዳምጡ⬆️

ልዩ መረጃ ከኤልያስ ጋር
በኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8


አልሸባብ የሽብር ቡድን በቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝደንት ባራክ ኦባማ ላይ ኢትዮጵያ ውስጥ አደጋ ሊያደርስ አስቦ ነበር ተብሏል!

የቀድሞዋ የአሜሪካ የተመድ አምባሳደር #ሱዛን_ራይስ ፕሬዝደንት ኦባማ ኢትዮጵያን በ2015 በጎበኙበት ወቅት አልሸባብ ጥቃት ለማድረስ እንቅስቃሴ አድርጎ እንደነበር ገልፀዋል። አክለውም በወቅቱ የኢትዮጵያ የደህንነት ሀላፊ የነበሩት ተጠርጣሪው በክትትላቸው ስር እንደሆነ ቢነግሯቸውም እነሱ ግን ጥርጣሬ ነበራቸው።

በመጨረሻም የደህንነት ሀላፊው ከተጠርጣሪው ጋር አየር መንገድ እንዳሉ (ተይዞ መሆኑ ነው) ሲነግሯቸው በፍጥነት ከነበሩበት የአፍሪካ ህብረት ወጥተው ወደ አየር ማረፊያው በማምራት ከኢትዮጵያ እንደወጡ በቴክሳስ ትሪብዩን ፌስቲቫል ላይ ተናግረዋል።

ልዩ መረጃ ከኤልያስ ጋር
በኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8


@tikvahethiopia @tsegabwolde