Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
8.41K subscribers
117 photos
1 video
18 files
126 links
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት
Download Telegram
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ

የአፋር እና የሶማሊ ክልላዊ መንግሥታት ለሰላም ስምምነቱ ዘላቂነት ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጥሪ ቀረበ።

ሚያዝያ 12፣ 2016 (አዲስ አበባ) - በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚደንት ክቡር ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም አደራዳሪነት፣ በአፋርና በሶማሊ ወንድማማች ሕዝቦች መካከል የተደረሰው የተኩስ አቁም ስምምነት ዘላቂ እንዲኾን የሁለቱም ክልሎች መንግሥታት ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጥሪ ቀረበ።

ይህ ጥሪ የቀረበው በትናንትናው ዕለት በአፋርና በሶማሊ ክልል ሕዝቦች መካከል የተደረሰውን ስምምነት አስመልክቶ ዛሬ በጠቅላይ ምክር ቤቱ አዳራሽ በተሰጠ መግለጫ ላይ ነው።

በአፋርና በሶማሊ ክልል ወንድማማች ሕዝቦች መካከል ለበርካታ አሠርት ዓመታት አረብቦ የነበረውን የሰላም እጦት ለመፍታት የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት በክቡር ፕሬዚደንቱ ብልኅ አመራር ሰጪነት ውጤታማ ሥራ መሠራቱ በመግለጫው ላይ ተነግሯል።

የጠቅላይ ምክር ቤቱ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚደንት ሼይኽ አብዱልከሪም ሼይኽ በድረዲን በሁለቱ ወንድማማች ሕዝቦች መካከል የነበረውን የሰላም እጦት ችግር ለመፍታት ከሁለቱም ክልሎች የተውጣጡ የሀገር ሽማግሌዎችን ለበርካታ ወራት ሲያወያዩ መቆየታቸውን አስታውሰዋል።

ትላንት ሚያዚያ 11፣ 2016 በአል-ነሀሪ ሆቴል በአፋርና በኢሳ ማኅበረሰቦች መካከል የነበረውን የወንድማማቾች ደም መፋሰስ ለማስቆም ሲደረግ የነበረው የሁለትዮሽ ስምምነት በውጤት መጠናቀቁን ተቀዳሚ ፕሬዚደንቱ ጠቅሰው፣ ይህ የተኩስ አቁም ስምምነት ውጤታማ እንዲሆን የሁለቱ ክልል መንግሥታት ኃላፊነት ከፍተኛ መሆኑን ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የፕሬዚደንቱ ልዩ አማካሪ ዑስታዝ አቡበከር አሕመድ በበኩላቸው፣ በሁለቱ ወንድማማች ሕዝቦች መካከል የነበረው ደም መፋሰስ በምሥራቅ አፍሪካ ረጅም ዘመን ያስቆጠረ መሆኑን አስታውሰዋል።

ይህን አላስፈላጊ ደም መፋሰስ ለማስቆም በተደረገው ተከታታይ ጥረት ውስጥ የሁለቱ ክልሎች ታዋቂ የማኅበረሰብ መሪዎች፣ የእስልምና ጉዳይ ከፍተኛ ምክር ቤቶች፣ የክልሎቹ መንግሥታት የሥራ ኃላፊዎችና ዓሊሞች ሰፊ ተሳትፎ እንደነበራቸው ዑስታዝ አቡበከር ተናግረዋል።

በእስልምና አስተምህሮ የአንድን ሰው ሕይወት ማዳን ዓለምን ማዳን መሆኑን የተናገሩት ዑስታዝ አቡበከር፣ በመነጋገር ችግሮችን የመፍታት አካሄድ የሰላም ችግር ባሉባቸው በሌሎችም የሀገራችን ክልሎች ሁሉ ሊተገበር ይገባል ብለዋል።

በአፋርና በኢሳ ሕዝቦች መካከል የተደረሰው የሰላም ስምምነት ቀጣይ ሥራን በሚመለከት በሚቀጥለው ሳምንት ጠቅላይ ምክር ቤቱ አቅጣጫ እንደሚያስቀምጥ ዑስታዝ አቡበከር ተናግረዋል።

ሰላምን ማስከበር የመንግሥት ኃላፊነት በመኾኑ፣ የፌደራልና የክልል መንግሥታት ለተደረሰው የሰላም ስምምነት ፍሬያማነት የበኩላቸውን ኃላፊነት እንዲወጡ ዑስታዝ አቡበከር ጥሪያቸውን አቅርበዋል።

*****
ሸዋል 11፣ 1445 ዓ.ሂ.
*****​
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት።
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የሐጅ ቪዛ ሳይይዙ ሐጅ ማድረግ እንደማይቻል የሳዑዲ የሐጅ ሚኒስቴር አስጠነቀቀ።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••

ሚያዝያ 21፣ 2016 (አዲስ አበባ) - የሳዑዲ አረቢያ የሐጅ እና ዑምራ ሚኒስቴር፣ የሐጅ ቪዛ ሳይይዙ ሐጅ ማድረግ እንደማይቻል በመግለጽ ዘንድሮ ሐጅ የማድረግ ኒያ ያላቸው ምዕመናን "ሐጅ እናስደርጋለን" በሚሉ የግል ኩባንያዎች እንዳይታለሉ በጥብቅ አስጠነቀቀ።

ሚኒስቴሩ ይህን ማስጠንቀቂያ ይፋ ያደረገው፣ በተለያዩ ሀገራት በማኅበራዊ ትስስር አውታሮች የሐጅ ቪዛ እንሰጣለን የሚሉ ሐሰተኛ ኩባንያዎች በስፋት የሚያሰራጩት ማስታወቂያ መበራከቱን ከተመለከተ በኋላ መኾኑን በመግለጫው ጠቅሷል።

ሐጅ ለማድረግ ሳዑዲ አረቢያ ከመገባቱ በፊት የሐጅ ቪዛ ማግኘት የግድ አስፈላጊ መኾኑን የጠቀሰው ሚኒስቴሩ፣ በጉብኝት ቪዛ፣ በሥራ ቪዛ፣ በቱሪስት ቪዛ፣ በትራንዚት እና በመሳሰሉት ቪዛዎች ሳዑዲ አረቢያ በመግባት ሐጅ ማድረግ እንደማይቻል አሳስቧል።

ሚኒስቴሩ አክሎም፣ ሐጅ ማድረግ የሚቻለው ጉዳዩ የሚመለከተው የሳዑዲ አረቢያ ሚኒስቴር በየሀገራቱ የሐጅና ዑምራ ጉዳይ ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር በመተባበር በሚሰጠው የሐጅ ቪዛ እና፣ እነዚህ ተቋማት በሌሉባቸው ሀገራት ደግሞ "ኑሱክ ሐጅ" በሚሰኘው ፕላትፎርም አማካይነት ብቻ መኾኑን መረዳት ያስፈልጋል ብሏል።

ሐጅ ለማድረግ፣ ሳዑዲ አረቢያ ከመገባቱ በፊት ራሱን የቻለ የሐጅ ቪዛ ማግኘት የግድ አስፈላጊ እንደኾነ የጠቀሰው የሚኒስቴሩ መግለጫ፣ ከሳዑዲ የሐጅና ዑምራ ሚኒስቴር ጋር ግንኙነት ካላቸው የየሀገራቱ የሐጅና ዑምራ ተቋማት ውጪ የሐጅ ቪዛን ማግኘት እንደማይቻል በመግለጽ ምዕመናን ከመታለል እንዲጠነቀቁ አሳስቧል።

"ሐጅ እናስደርጋለን" በሚሉ አጭበርባሪ ኩባንያዎች መታለል ከሚያስከትለው የገንዘብ ኪሳራ በተጨማሪ፣ የጓጉለትን ሐጅ ለማድረግ አለመቻልን በማስከተል ከባድ ሐዘን ላይ ሊጥል እንደሚችል ሚኒስቴሩ አሳስቧል።

*
ሸዋል 20፣ 1445 ዓ.ሂ.
*
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት።
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ

የጠቅላይ ምክር ቤቱ ፕሬዚደንት የ"ጽዱ ጎዳና - ኑሮ በጤና" ንቅናቄን ተቀላቀሉ።

ሚያዚያ 22፣ 2016 (አዲስ አበባ) - የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚደንት የክብር ዶክተር ሼይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ የ"ጽዱ ጎዳና - ኑሮ በጤና" ንቅናቄን ተቀላቀሉ።

ፕሬዚደንቱ ሼይኽ ሐጂ ኢብራሂም በግላቸው ለንቅናቄው የሚውል ብር 10,000.00 (አሥር ሺህ ብር) ለንቅናቄው በተከፈተ የሂሳብ ቁጥር ገቢ አድርገዋል።

****
ሸዋል 21፣ 1445 ዓ.ሂ.
*​***
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት።
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ

ለ1445 የአሏህ እንግዶች የአሠልጣኞች ሥልጠና ተሰጠ።

ሚያዚያ 27፣ 2016 (አዲስ አ በባ) - የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት "የዘመነ መስተንግዶ ለአርረሕማን እንግዶች" በሚል መሪ ቃል ለ1445 ዓ.ሒ (2016 ዓ.ል) የሐጅ ተጓዦች በጠቅላይ ምክር ቤቱ አዳራሽ የአሠልጣኞች ሥልጠና መስጠት ጀመረ።

ሥልጠናውን በንግግር የከፈቱት የጠቅላይ ምክር ቤቱ የሐጅና ዑምራ ዘርፍ ኃላፊ አብዱልፈታህ መሐመድ ናስር በዘንድሮ የሐጅ ጉዞ የሑጃጁን ክብር የጠበቀና ከወትሮ የተለየ ለማድረግ ምክር ቤቱ የቅድመ ዝግጅት ተግባራት ሲያከናውን መቆየቱን ተናግረዋል።

የ1445 ዓ.ሒ. የሐጅ ጉዞ ከሁለት ሳምንት በኋላ እንደሚጀምር የተናገሩት ኃላፊው የአላህ እንግዶች በጉዞ ወቅት በሐገር ዉስጥና በሳዑዲ እርስ በርሳቸው እንዲረዳዱ እና እንዲደጋገፉ አሳስበዋል።

ሑጃጁ የበረራ ጊዜውን እንዲያውቅ ምክር ቤቱ የመረጃ መስጪያ ቁጥር 9933 የከፈተ ሲኾን፣ ከምክር ቤቱ ለሑጃጁ ወቅታዊ መረጃ በEtho Hajj አጭር መልዕክት ማስተላለፊያ እየላከ በመኾኑ ሑጃጁ እንዲከታተል ጥሪ አቅርበዋል።

የሐጅ ጉዞ ቀጥታ ወደ መዲና መኾኑን የተናገሩት ኃላፊዉ ሑጃጁ የሚጓዝበትን የበረራ ቀን እና በመዲና የሚያርፍበትን ሆቴል ከወዲሁ እንዲያውቅ ጠቅላይ ምክር ቤቱ በተለያዩ የመልዕክት ማስተላለፊያ ዘዴዎች እንደሚያሳውቅ ተናግረዋል።

አብዛኛው የሐገራችን ሑጃጅ ከገጠሪቱ የሀገራችን ክፍሎች የሚመጡ በመሆኑ ለሐጅ ሲመዘገቡ በሰጡት የስልክ ቁጥር ሳዑዲ ሆነው ከቤተሰቦቻቸው ጋር መገናኘት እንዲችሉ ጠቅላይ ምክር ቤቱ የቅድመ ዝግጅት ሥራ ማጠናቀቁን ኃላፊው ተናግረዋል።

በዛሬው የአሠልጣኞች ሥልጠና ላይ የተሳተፉት ከመቀሌ፣ ከወራቤ፣ ከአዲስ አበባ፣ ከአዳማ እና ከፉሪ የምዝገባ ጣቢያዎች የተመረጡ ሠልጣኞች ናቸው።
****
ሸዋል 26፣ 1445 ዓ.ሂ.
*​**
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት።
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ

ጠቅላይ ምክር ቤቱ በ2016 ግማሽ ዓመት ስላከናወናቸው ተግባራት ለባለድርሻዎች ገለፃ አደረገ። ተቋሙንም አስጎበኘ።

ሚያዝያ 26፣ 2016 (አዲስ አበባ) - የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት በ2016 ባከናወናቸው ተግባራት ዙርያ በዛሬው ዕለት ለተለያዩ ባለድርሻ አካላት ገለጻ አደረገ።

ምክር ቤቱ በተጨማሪም፣ ተቋሙን ለማጠናከር የተሠሩና በመሠራት ላይ የሚገኙ ተግባራዊ ሥራዎችንም አስጎብኝቷል።

የዓሊሞች ጉባዔ ሥራ አስፈጻሚ አባላት፣ ዳዒዎች፣ የጠቅላይ ምክር ቤቱ ሥራ አስፈጻሚዎች እና ዳይሬክተሮች፣ የተለያዩ ሚዲያ ኃላፊዎች፣ የሴቶችና ወጣቶች ተወካዮች፣ የማኅበረሰብ አንቂዎች እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው ባለድርሻዎች የምክር ቤቱን ገለጻ ታድመዋል።

በገለጻው ላይ የተገኙት የጠቅላይ ምክር ቤቱ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚደንት ሸይኽ አብዱልከሪም ሸይኽ በድረዲን፣ ምክትል ፕሬዚደንቱ ሸይኽ አብዱልአዚዝ አብዱል ወሊ የለውጡ አመራር የሰራቸውን ስራ ለባለድረሻ አካለት ማብራራቱና ማሳየቱ ግልፅነትና አብሮነትን የሚያሳይ አካሄድ መሆኑን ገልጸዋል።

የጠቅላይ ምክር ቤቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ሐጂ ከማል ሐሩን በአዲሱ የጠቅላይ ምክር ቤቱ አመራር በግማሽ ዓመት ውስጥ ስላከናወናቸው ተግባራት ና ስለ ገጠማቸው ተግዳሮት ለታዳሚው ሰፋ ያለ ገለጻ አደርገዋል።

የሐጅና ኡምራ ዘርፍ ኃላፊውም ሐጅ አብዱልፈታህ ሙሐመድ በበኩላቸው በሐጅና ዑምራ ዘርፍ ያለውን ችግር ለመቅረፍ ቀልጣፋና ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር ጠቅላይ ምክር ቤቱ የተጓዘበትን እርቀት አብራርተዋል።

በምክር ቤቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ከኃላፊዎቹ ለባለድርሻዎች የተደረገው ገለጻ በአመዛኙ ጠቅላይ ምክር ቤቱ በ2016 የመጀመሪያዎቹ ስድስት ወራት በሠራቸው ዐበይት ሥራዎች ላይ ያተኮረ ነው።

በገለጻው ላይ፣ በምክር ቤቱ ባለፉት ስድስት ወራት ከተሠሩ ዐበይት ሥራዎች መካከል፣ ሕገ መጅሊሱ እንዲፀድቅ መደረጉ እና በተለያዩ ክልሎች የሕዝበ ሙስሊሙን አንድነት ለመጠበቅ የተሠሩ ሥራዎች ተጠቅሰዋል።

በአደረጃጀት ረገድ የክልል መጅሊሶች መዋቅር ከክልል እስከ መስጂድ እንዲወርድ መደረጉ የተገለፀ ሲኾን፣ በመጅሊሱ የአምስት ዓመት ስትራቴጂያዊ ዕቅድ ዙርያ ከተለያዩ ባለሙያዎች ጋር ውይይት መካሄዱ ተነግሯል።

የመጅሊስ ምርጫን አስመልክቶ የምርጫ ሕግ ተረቅቆ ለሥራ አስፈፃሚው አካል መቅረቡ የተነገረ ሲኾን፣ የሸሪዓ ፍርድ ቤት አዋጅ እንዲሻሻል የተለያዩ ሥራዎች መሠራታቸውም ተጠቅሷል።

የሐጅ መስተንግዶን ለማዘመን በርካታ ሥራዎች መሠራታቸው የተጠቀሰ ሲኾን፣ ከእነዚህም መካከል፣

- ካለፈው ዓመት ልምድ በመውሰድ፣ 18 ብቻ የነበሩትን የሐጅ ምዝገባ ጣቢያዎች ወደ 30 ማሳደግ መቻሉን፣ 116 ያህል ሠራተኞች በመቅጠር ሰፊ የሐጅ መስተንግዶ ሥራዎች መሰራታቸው ተገልጿል።

በዚህም መሠረት በዘንድሮው ሐጅ ከ12 ሺህ በላይ ሑጃጆች ተመዝግበ የሐጅ ቪዛቸውን እየጠበቁ እንደሚገኙ ተነግሯል።

የተለያዩ የሐጅ ንዑሳን ኮሚቴዎችን በማቋቋም ሰፋፊ ሥራዎች መሠራተቸውም ተጠቅሷል።

ሑጃጆች ከጉዞ እስከሚመለሱ ድረስ አስፈላጊውን አገልግሎት እንዲያገኙ የሚያስችል ሥርዓት መዘርጋቱና ዶላርን በተመለከተም ከተለያዩ ባንኮች ጋር ስምምነት መደረጉ ተነግሯል።

የምክር ቤቱን የፋይናንስ አጠቃቀም በተመለከተ፣ ጠቅላይ ምክር ቤቱ ለመጀመሪያ ጊዜ በውጭ ኦዲተር የሒሳብ ምርመራ (ኦዲት) ማስደረጉ ተጠቅሷል።

በጠቅላይ ምክር ቤቱ ስር የሚገኘው የኢትዮጵያ ሙስሊሞች የልማት ኤጀንሲን በአዲስ መልክ ለማንቀሳቀስ፣ ምክር ቤቱ በኤጀንሲው ለሚካሄዱ የልማት ተግባራት የስድስት ሚሊየን ብር በጀት መመደቡ ተነግሯል።

የምክር ቤቱን የተሽከርካሪ ፍላጎት ለማሟላት ለ9 ነባር ተሽከርካሪዎችን ጥገና በማስደረግ ወደሥራ ማስገባት እንደታቻለና በተጨማሪም የአምስት አዳዲስ ተሽከርካሪዎች ግዢ እንደተፈፀመ ተነግሯል።

የኡለማ ጉባዔ አደረጃጀትን ከማጠናከር አኳያ፣ እስካሁን ከትግራይ በስተቀር በሁሉም ክልሎች የኡለማ ጉባኤ እንዲደራጅ የተደረገ ሲኾን፣ የትግራይ የኡለማ ምክር ቤት ምሥረታ በሂደት ላይ መሆኑ ተጠቅሷል።

በዚሁ የስድስት ወር ጊዜ ከተካሄዱ ተግባራት አንዱ የኡለማዎች ጉባኤ መካሄዱ ተጠቅሷል። በግዮን ሆቴል በተካሄደው የኡለማ ጉባዔ ላይ ከ15 ያላነሱ ጥናታዊ ጽሑፎች መቅረባቸውና፣ በተለያዩ ጥያቄዎች ላይ ፈትዋዎች መሰጠታቸው ተወስቷል።

በተጨማሪም፣ ለየክልሉ እስልምና ጉዳዮች አመራሮች በጠቅላይ ምክር ቤቱ አማካይነት የተለያዩ የአቅም ግንባታ ሥልጠናዎች መሰጠታቸው ተነግሯል።

ባለፉት አንድ ዓመት ከስድስት ወራት ውስጥ ለክልል የእስልምና ጉዳይ ምክር ቤቶች ከ60 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ መደረጉም ተነግሯል።

የጠቅላይ ምክር ቤቱን የውጭ ግንኙነት በተመለከተ፣ በርካታ ሥራዎች መሠራታቸውን እና የጠቅላይ ምክር ቤቱ ፕሬዚደንት ክቡር ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ በተለያዩ ዓለም አቀፍ መድረኮች ላይ ተጋብዘው በንቃት መሳተፋቸው ተወስቷል።

ገለጻው ላይ የታደሙ ጋዜጠኞች በሙስሊሙ ላይ የሚደርሱ የተለያዩ በደሎችን የተመለከቱ ጥያቄዎች የተነሱ ሲኾን፣ የጠቅላይ ምክር ቤቱ ሥራ አስኪያጅ ለቀረቡት ጥያቄዎች ምላሽ እና ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በሙስሊሙ ማኅበረሰብ የሚነሱ የተለያዩ ማኅበረሰብ ተኮር ጥያቄዎችን ምክር ቤቱ አግባብ ላላቸው የመንግሥት አካላት ማቅረቡን ተናግረዋል።

ከገለጻው በኋላም፣ ባለድርሻዎች የምክር ቤቱን ተቋማዊ ቁመና ለማሳደግ በተለያዩ ዘርፎች የተሠሩ እና በመሠራት ላይ የሚገኙ ሥራዎችን እየተዘዋወሩ ጎብኝተዋል።

****
ሸዋል 20፣ 1445 ዓ.ሂ.
****
የኢ.እ.ጉ.ጠ. ም/ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eias
የሃጅ ቪዛ የተሰራላችሁ ሃጃጆች በዚህ ሊንክ የፓስፖርት ቁጥር እና ስም በማስገባት የቪዛ ኮፒ ማውረድ ትችላላችሁ።
https://visa.mofa.gov.sa/visaservices/searchvisa
سْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ

ማሳሰቢያ
ለ1445 ዓ.ሒ (2016 ዓ.ል) ለሐጅ ተጓዦች

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የ1445 ዓ.ሒ (2016 ዓ.ል) በኢትዮጵያ እና በሳውዲ አየር መንገዶች የሚበሩ የሐጅ ተጓዦችን ረቂቅ የበረራ መርሐ ግብር በጠቅላይ ምክር ቤቱ የመረጃ ማግኛ ማስፈንጠሪያ (ሊንክ ) https://hajj.et/hajj-status አማካኝነት ይፋ ማድረጉ ይታወቃል።

በተወሰኑ በረራዎች ላይ የበረራ መርሐ ግብር ለውጥ የተደረገ መሆኑ እያሳወቅን አዲሱን የበረራ መርሐ ግብር ከሰዓታት በኋላ የምናሳውቅ በመሆናችንንና መረጃውን በቋት ዉስጥ እስከምናስገባ ድረስ ቋቱን (ሊንኩን) ለጊዜዉ የምንዘጋ መሆናችንንና እያሳወቅን የተከለሰው መርሐ ግብሩ ቀድሞ ከተጫነው የበረራ ቀንና ሰዓት ልዩነት ሊኖረው ስለሚችል ሑጃጆች ይህንን ተገንዝባችሁ አዲስ በመረጃ ቋት ማስፈንጠሪያ ሊንክ የሚጫነውን መረጃ ብቻ እንድትጠቀሙ እናሳስባለን ።

ለቀጣይ የሃጅ መስተንግዶ የተመለከቱ አዳዲስ መረጃዎች ከላይ በተጠቀሰው ማስፈንጠሪያ እና በ9933 ቀጥታ በመደወል እንድትከታተሉ በዚሁ አጋጣሚ እናስታውሳለን።

ግንቦት 2፥ 2016 ዓ.ል
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት።
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1
سْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ

ማስታወቂያ

ለ1445 ዓ.ሒ (2016 ዓ.ል) ለሐጅ ተጓዦች

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የ1445 ዓ.ሒ (2016 ዓ.ል) በኢትዮጵያ እና በሳውዲ አየር መንገዶች የሚበሩ የሐጅ ተጓዦችን የበረራ መርሐ ግብር በጠቅላይ ምክር ቤቱ የመረጃ ማግኛ ማስፈንጠሪያ (ሊንክ ) https://hajj.et/hajj-status አማካኝነት የበረራ መረጃችሁን የምታገኙ መሆኑን እየገለፅን ።

ለተጨማሪ የሃጅ መስተንግዶ በተመለከ አዳዲስ መረጃዎች ከላይ በተጠቀሰው ማስፈንጠሪያ በተጨማሪ በ9933 ቀጥታ በመደወል እንድትከታተሉ በዚሁ አጋጣሚ እናስታውቃለን።

ግንቦት 3፥ 2016 ዓ.ል
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት።
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1
سْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ

ማስታወቂያ ለ1445 የሐጅ ተጓዦች

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠ ቅላይ ምክር ቤት የ1445 ዓ.ሒ የሐጅ ተጓዦችን የመሔጃና የመመለሻ ቀን የጉዞ መርሐ ግብር ከወዲሁ ጠቅላይ ምክር ቤቱ በከፈተው የመረጃ ማግኛ ማስፈንጠሪያ (ሊንክ) https://hajj.et/hajj-status አማካኝነት ማሳወ ቃችን ይታወቃል።

በመረጃ ማግኛ ማስፈንጠሪያዉ (ሊንክ) ላይ ከተቀመጠው መርሐ ግብር ውጪ ጉዟችሁን የምትሰርዙ ሑጃጆች የበረራ ቦታ ከተገኘ ብቻ አየር መንገዶቹ ያስቀመጡትን ቅጣት ከፍላችሁ የምትስተናገዱ ሲሆን በተጨማሪም በዞን አደረጃጀቱ መሰረት በተያዘላችሁ የማረፊያ ቦታ ላይ አሉታዊ ችግር የሚፈጥርባችሁ መሆኑን ከ ወዲሁ ተገንዝባችሁ በተያዘላችሁ የጉዞ መርሐ ግብር መሰረት ብቻ ጉዟችሁን እንድታከናውኑ ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ሰዓት ጀምሮ በምዝገባ ጣቢያችሁ በመገኘት የጉዞ መርሐግብራችሁን እንድታረጋግጡ እያሳወቅን ። በተቀመጠላችሁ የጉዞ መርሐ ግብር መሰረት የማትስተናገዱ ሐጃጆች ለሚደርስባችሁ እንግልት ጠቅላይ ምክር ቤቱ ኅላፊነት የ ማይወስድ መሆኑን ከወዲሁ እናሳዉቃለን።

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት

ግንቦት 4/2016 ዓ.ል
ዙል ቃይዳ 4/1445
ግንቦት 5፣ 2016 | ዙል ቂዳህ 5፣ 1445 ዓ.ሂ.

بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የዓለም ሙስሊም ሊቃውንት የምክክር ጉባዔ ተጀመረ።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••

የዓለም ሙስሊም ሊቃውንት የምክክር ጉባዔ በቱርክዬ ትልቋ ከተማ ኢስታንቡል ተጀመረ።

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚደንት የክብር ዶክተር ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ ለሁለት ቀናት በሚቆየው በዚህ ጉባዔ በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ።

የምክክር ጉባዔው በቱርክዬ የሃይማኖት ጉዳዮች ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ዓሊ ዔርባሽ ንግግር የተከፈተ ሲኾን፣ ክቡር ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂምን ጨምሮ የተለያዩ ሀገራት ሙስሊም ሊቃውንት በጉባዔው ላይ ጥናታዊ ጽሑፍ ያቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በቱርክዬ ኢስታንቡል በሚካሄደው ዓለም አቀፍ የሙስሊም ሊቃውንት ጉባዔ ላይ ከተለያዩ የዓለም ሀገራት የተጋበዙ ሙፍቲዎች፣ ዓሊሞች፣ ዳዒዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ታድመዉበታል።

የዓለም አቀፉ የሙስሊም ሊቃውንት የምክክር ጉባዔ ታዳሚዎች ትናንት ምሽት በኢስታንቡል በቱርክዬ ፕሬዚደንት ረጀብ ታይብ ኤርዶዋን አማካይነት የእራት ግብዣ ተደርጎላቸዋል።

•••••••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት።
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc13
ግንቦት 7፣2016 ፣ዙል ቂዳህ 7፣ 1445 ዓ.ሂ.

بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ

ከ ሐጅ ቪዛ ውጪ ሐጅ ማድረግ እንደማይፈ ቀድ የሳውዲ የሐጅ ሚኒቴር አስጠነቀቀ።

ግንቦት 7፣ 2016( አ ዲስ አበባ) የሳውዲ አረቢያ የሐጅና ዑምራ ሚኒስቴር ፣ ከሐጅ ቪዛ ዉጪ በማንኛውም የቪዛ አይነቶች ሐጅ ማድረግ እንደ ማይፈቀድ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ገለፀ።

የጉብኝት ፣ የቱሪስት ፣ የትራንዚት : የስራና መሰል በሳውዲ አረቢያ የሚሰጡ ቪዛዎችን በመጠቀም ሐጅ ለማድረግ የሚሞክሩ ከዚህ ተግባራቸው እንዲቆጠቡ ከወዲሁ የሚኒስተር መስሪያ ቤቱ አስጠንቅቋል።

ሐጅ ለማድረግ ሳዑዲ አረቢያ ከመገባቱ በፊት የሐጅ ቪዛ ማግኘት የግድ አስፈላጊ መኾኑን የጠቀሰው ሚኒስቴሩ፣ በጉብኝት ቪዛ፣ በሥራ ቪዛ፣ በቱሪስት ቪዛ፣ በትራንዚት እና በመሳሰሉት ቪዛዎች ሳዑዲ አረቢያ በመግባት ሐጅ ማድረግ እንደማይቻል አሳስቧል።

ሚኒስቴሩ አክሎም፣ ሐጅ ማድረግ የሚቻለው ጉዳዩ የሚመለከተው የሳዑዲ አረቢያ ሚኒስቴር በየሀገራቱ የሐጅና ዑምራ ጉዳይ ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር በመተባበር በሚሰጠው የሐጅ ቪዛ እና፣ እነዚህ ተቋማት በሌሉባቸው ሀገራት ደግሞ "ኑሱክ ሐጅ" በሚሰኘው ፕላትፎርም አማካይነት ብቻ መኾኑን መረዳት ያስፈልጋል ብሏል።

ሐጅ ለማድረግ፣ ሳዑዲ አረቢያ ከመገባቱ በፊት ራሱን የቻለ የሐጅ ቪዛ ማግኘት የግድ አስፈላጊ እንደኾነ የጠቀሰው የሚኒስቴሩ መግለጫ፣ ከሳዑዲ የሐጅና ዑምራ ሚኒስቴር ጋር ግንኙነት ካላቸው የየሀገራቱ የሐጅና ዑምራ ተቋማት ውጪ የሐጅ ቪዛን ማግኘት እንደማይቻል በመግለጽ ምዕመናን ከመታለል እንዲጠነቀቁ አሳስቧል።

"ሐጅ እናስደርጋለን" በሚሉ አጭበርባሪ ኩባንያዎች መታለል ከሚያስከትለው የገንዘብ ኪሳራ በተጨማሪ፣ የጓጉለትን ሐጅ ለማድረግ አለመቻልን በማስከተል ከባድ ሐዘን ላይ ሊጥል እንደሚችል ሚኒስቴሩ አሳስቧል።

* ዙል ቂዳህ 7፣ 1445 ዓ.ሂ.
*​
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት።
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eia
ግንቦት 13፣ 2016 | ዙል ቂዳህ 13፣ 1445 ዓ.ሂ.
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
إِنَّا لِلَّهِ وَإِنَّآ إِلَيْهِ رَٰجِعُونَ
"እኛ ለአላህ ነን፤ እኛም ወደርሱ ተመላሾች ነን።"
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
አዲስ አበባ |
በክብር ዶክተር ሼይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ የተመራ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ከፍተኛ የአመራር ቡድን በኢራኑ ፕሬዚደንት ኢብራሂም ረኢሲ እና በውጭ ጉዳይ ሚኒስትራቸው ሑሴይን አሚር አብዱላሂያን ድንገተኛ ኅልፈት የተሰማቸውን ጥልቅ ሐዘን ገለፁ።

በክብር ዶክተር ሼይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ የተመራው የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ከፍተኛ የአመራር ቡድን አዲስ አበባ በሚገኘው የኢራን እስላማዊ ሪፐብሊክ ኤምባሲ በመገኘት ሐዘናቸውን ገልፀዋል።

የጠቅላይ ምክር ቤቱ ዋና ፀሐፊ ሸይኽ ሐሚድ ሙሳ ጠቅላይ ምክር ቤቱን በመወከል በተዘጋጀው የሐዘን መግለጫ መዝገብ ላይ የሐዘን መልዕክታቸውን አስፍረዋል።

ክቡር ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ፣ ፕሬዚደንት ኢብራሂም ረኢሲ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሑሴይን አሚር አብዱላሂያን ከትናንት በስቲያ በአስቸጋሪ የአየር ሁኔታ ሳቢያ በተፈጠረ የሄሊኮፕተር አደጋ ከሌሎች ባለሥልጣናትና ከአብራሪዎቹ ጋር ሕይወታቸው ማለፉን እጅግ በከባድ ሐዘን እንደሰሙ ተናግረዋል።

ክቡር ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም ለሟቾቹ አላህ ሱብሃነሁወተዓላ እዝነቱን እንዲቸራቸው፣ ለሀገሪቱ ጠቅላይ መሪ አያቶላህ ዓሊ ኻመነዪ እና ለመላዉ የኢራን ሕዝብ እና በአዲስ አበባ ለሚገኙት የኢራን እስላማዊ ሪፐብሊክ ልዑካን እና ማኅበረሰብ መጽናናትን እንዲሰጣቸው ተመኝተዋል።

°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
የኢ.እ.ጉ.ጠ. ም/ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | twitter.com/eiasc
ግንቦት 13፣ 2016 | ዙል ቂዳህ 13፣ 1445 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የመጀመሪያዎቹ 312 የ1445 ዓ.ሒ ሑጃጆች ወደ መዲነቱል ሙነወራ ተሳፈሩ።
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
ዘንድሮ የሐጅ ሥርዓትን ለመፈፀም ከተመዘገቡ ኢትዮጵያውያን መካከል የመጀመሪያዎቹ 312 የ1445 ዓመተ ሒጅራ ሑጃጆች በዛሬው ዕለት ወደ ሳዑዲ አረቢያ ቅድስቲቱ ከተማ መዲነቱል ሙነወራ አሸኛኘት ተደረገላቸው።

ዛሬ በተደረጉ ሁለት በረራዎች በሳዑዲ አየር መንገድ 45፣ በኢትዮጵያ አየር መንገድ 267 በድምሩ 312 የአሏህ እንግዶች ወደ ሳዑዲ አረቢያ ቅድስቲቱ ከተማ መዲና ተጉዘዋል።

በ1445 ዓ.ሒ ተመዝግበው ዛሬ ወደ ሳዑዲ አረቢያ ቅድስቲቱ ከተማ መዲነቱል ሙነወራ ለተጓዙት የአሏህ እንግዶች በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚደንት ክቡር ሼይኽ ሐጂ ኢብራሒም ቱፋ የተመራ የጠቅላይ ምክር ቤቱ ከፍተኛ አመራር ሽኝት ተደርጎላቸዋል።

የዛሬውን ሽኝት ምክንያት በማድረግ ጋዜጣዊ መግለጫ የሰጡት የጠቅላይ ምክር ቤቱ ዋና ፀሐፊ ሼይኽ ሐሚድ ሙሳ የዘንድሮው የሐጅ ጉዞ የተሳካ እንዲሆን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ያደረገውን ጉልህ አስተዋጽዖ ጠቅሰው፣ በራሳቸውና በጠቅላይ ምክር ቤቱ ስም አመስግነዋል።

በዘንድሮ ዓመት ሐጅ ለማድረግ ከተመዘገቡ 12 ሺህ (አሥራ ሁለት ሺህ) ሑጃጆች ውስጥ 8 ሺህ 500 (ስምንት ሺህ አምስት መቶ) የሚኾኑት በኢትዮጵያ አየር መንገድ ይጓዛሉ ተብሎ ይጠበቃል ብለዋል።

ዛሬ ሽኝት የተደረገላቸው የተከበሩ የአሏህ እንግዶች መዲና ሲደርሱ በጠቅላይ ምክር ቤቱ የሐጅና ዑምራ ዘርፍ ምክትል ኃላፊ ሼይኽ አብዱልሐሚድ አሕመድ በሚመራ የልዑካን ቡድን አማካኝነት አቀባበል እንደሚደረግላቸው ሼይኽ ሐሚድ ሙሳ ተናግረዋል።

የ1445 ዓ.ሒ የሐጅ መስተንግዶ "የዘምመነ መስተንግዶ ለአል-ረህማን እንግዶች" በሚል መሪ ቃል በጠቅላይ ምክር ቤቱ የሐጅና ዑምራ ዘርፍ ኃላፊ ሼይኽ አብዱልፈታህ ሙሐመድ ናስር መጀመሩን ተናግረዋል።

በዛሬው የሑጃጆች የአሸኛኘት ስነ ሥርዓት ላይ የጠቅላይ ምክር ቤቱ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚደንት ሼይኽ አብዱልከሪም ሼይኽ በድረዲን ተገኝተዋል።

ከአሁን በፊት የሐጅ ምዝገባ በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ብቻ ይከናወን እንደነበረና ከክልል የሚመጡ ሑጃጆች እንግልት ይደርስባቸው እንደነበር ኃላፊው አስታውሰዋል።

ካለፈው ዓመት ጀምሮ የሐጅ መስተንግዶ ምዝገባ፣ በ18 የምዝገባ ጣቢያዎች የተካሄደ መሆኑን የተናገሩት ኃላፊው፣ ዘንድሮ የሙስሊሙን ማኅበረሰብ ጥያቄ መሠረት በማድረግ የሐጅ የምዝገባ ጣቢያዎች ቁጥር ወደ 30 እንዲያድግ መደረጉን ተናግረዋል።

ዛሬ በረራ ያደረጉት ሁሉም ሑጃጆች ቪዛና የአውሮፕላን ቲኬቶቻቸውን በተመዘገቡበት የሐጅ ምዝገባ ጣቢያ እንዲቀበሉ መደረጉንም ኃላፊው ተናግረዋል።

የተከበሩ የአሏህ እንግዶች እርስ በእርሳቸው እንዲረዳዱና እንዲደጋገፉ ለማስቻልም በአንድ አሚር ስር 45 ሑጃጆችን የማደራጀት ሥራ መሠራቱንም ኃላፊው ተናግረዋል።

ጠቅላይ ምክር ቤቱ የዘንድሮው የአሏህ እንግዶች ከሌሎች ሀገራት ሑጃጆች የሚለዩበት መለያ ልብስ (ዩኒፎርም) ያዘጋጀ ሲኾን፣ የተከበሩ የአሏህ እንግዶች ዩኒፎርሙን በአግባቡ እንዲጠቀሙ ኃላፊው አሳስበዋል።

የዘንድሮ የሐጅ መስተንግዶ የዘመነ እንዲሆን የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ በየደረጃው የሚገኙ የእስልምና ጉዳይ ምክር ቤቶች፣ የIT ባለሙያዎች፣ የኢሚግሬሽንና የዜግነት ጉዳዮች መምሪያ፣ ኢትዮ ቴሌኮም እና የመንግሥትና የግል ባንኮችን ኃላፊው አመስግነዋል።
​••••••••••••••••••••••••••••••••••

የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1
ግንቦት 12፣ 2016 ዓ.ል | ዙል ቂዳህ 12፣ 1445 ዓ.ሂ.
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የሳዑዲ ጀርመን የግል ሆስፒታል በሐጅ ወቅት ለሚገጥም ድንገተኛ ህመም የነፃ ሕክምና ለመስጠት ከሳዑዲ የሐጅ ሚኒስቴር ጋር ተፈራረመ።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••

ግንቦት 12፣ 2016 (መዲና) - መዲና የሚገኘው የሳዑዲ ጀርመን የግል ሆስፒታል በሐጅ ወቅት ለሚያጋጥም ድንገተኛ የጤና መታወክ ነፃ ሕክምና ለመስጠት ከሳዑዲ አረቢያ የሐጅ ሚኒስቴር የጤና ዘርፍ ጋር የጋራ ስምምነት ተፈራረመ።

ስምምነቱ የሐጅ ቪዛ ያላቸው ሐጃጆች ለሚገጥማቸው ድንገተኛ የጤና እክል መንግሥት ከሚሰጠው ነጻ የህክምና አገልግሎት በተጨማሪ መኾኑን ለማወቅ ተችሏል።

የጋራ ስምምነቱን የሳዑዲ አረቢያ የሐጅ ሚኒስትር ሲም አልዴራስ ጋኒም እና የሳዑዲ ጀርመን ሆስፒታል የሽያጭ ሥራ አስኪያጅ ዶ/ር ታመር አልዳማክ ተፈራርመዋል።

በመዲና የሚገኘው የኢትዮጵያ አስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የጤና ቡድን መሪ ዶ/ር መሐመድ ሳኒ ቲጃኒ እና ዶ/ር መሐመድ ጀይላን በፊርማ ስነ ሥርዓቱ ላይ ተገኝተዋል።

ዶክተር መሐመድ ሳኒ ቲጃኒ፣ ለሐጃጆች ድንገተኛ የጤና እክል የህክምና አገልግሎት በመንግሥት ብቻ ይሰጥ እንደነበር አስታውሰው፣ በ1445ዓ.ሂ ለመጀመሪያ ጊዜ ተጨማሪ የግል የሕክምና አገልግሎት ሰጪ በነፃ እገዛ ለማድረግ ውል መግባቱ በጤና አገልግሎቱ ዘርፍ የነበረውን ጫና በማቅለል ረገድ ትልቅ እገዛ እንደሚያደርግ ተናግረዋል።

••••••••••••••••••••••••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1
ግንቦት 13፣ 2016 | ዙል ቂዳህ 13፣ 1445 ዓ.ሂ.
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የአል-ረህማን እንግዶችን መዲነቱል ሙነወራ ይዞ ገባ።
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
መዲና |

በኢትዮጵያ አየር መንገድ የተሳፈሩት የ1445 ዓ.ሒ የመጀመሪያዎቹ የአል-ረህማን እንግዶች መዲነቱል ሙነወራ ገቡ።

ሐጃጆቹ መዲና አይሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ፣
በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የሐጅና ዑምራ ዘርፍ ምክትል ሰብሳቢና የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል ሸይኽ አብዱልሃሚድ አሕመድ እና የጠቅላይ ምክር ቤቱ የሰላምና ፀጥታ ዘርፍ ምክትል ኃላፊ ሸይኽ ዛኪር ኢብራሂም አቀባበል አድርገውላቸዋል።

በኢትዮጵያ አየር መንገድ መዲነቱል ሙነወራ የገቡት የአል-ረህማን እንግዶች 263 ሲኾኑ፣ ከእነዚህ ውስጥ 55 ያህል ሴቶች መሆናቸውን የአቀባበል አሥተባባሪው አቶ አብዲ ሲራጅ ተናግረዋል።

መዲነቱል ረሱል (ሶ.ዐ.ወ.) የገቡት ሐጃጆች በቆይታቸው ማድረግ ስለሚገባቸው ጥንቃቄ እና ስለ ጤናቸው ጉዳይ አስፈላጊ ማብራሪያ ተሰጥቷቸዋል።

የ1445 ዓ.ሂ. የአል-ረህማን እንግዶች በመዲና በሚያደርጉት የሁለት ቀናት ቆይታ መስጂድ ቂብለተይንን፣ ኡሑድ ተራራን፣ በዚሁ ስፍራ ሸሂድ የሆኑትን የነሐምዛን ቀብር ይዘይራሉ።

በመጨረሻም በመስጂደል ነበዊ የሚገኘውን ረውዳ በቡድን ኾነው ከዘየሩ በኋላ፣ ወደ መካ እንደሚጓዙ ከመስተንግዶ ኮሚቴው ለማወቅ ተችሏል።

••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1
ግንቦት 13፣ 2016 | ዙል ቂዳህ 13፣ 1445 ዓ.ሂ.
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ                     
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
በጉብኝት ቪዛ ሐጅ ማድረግ እንደማይፈቀድ የሳዑዲ የሐጅ ሚኒስቴር አስታወቀ።
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
ሳዑዲ አረቢያን ለመጎብኘት በሚስሰጥ የጉብኝት ቪዛ (Visit Visa) የሐጅ ሥርዓተ ክንዋኔ ላይ መሳተፍ አይፈቀድም ሲል የሐገሪቱ የሐጅ ሚኒስቴር አሳሰበ።

ሚኒስቴሩ በማሳሰቢያው የጉብኝት ቪዛን በመጠቀም ወደ ቅዱሳን ስፍራዎች ለመድረስ የሚደረግ ሙከራ ከሀገሪቱ ለመባረር የሚዳርግ የሕግና የደንብ ጥሰት መኾኑን ጠቅሷል።

እንዲህ ላለው ቅጣት ላለመዳረግ ሕግ እና ደንብ ማክበር የግድ አስፈላጊ እንደኾነ ሚኒስቴሩ አስታውሷል።

••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1
ግንቦት 14፣ 2016 | ዙል ቂዳህ 14፣ 1445 ዓ.ሂ.
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
በኮምቦልቻ ከተማ ሀገር አቀፍ የሰላም፣ የአብሮነትና የወንድማማችነት ጉባዔ ይካሄዳል
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
አዲስ አበባ |

"አንድነታችን ለሰላማችን" በሚል መሪ ቃል የፊታችን እሑድ ግንቦት 17 እና 18፣ 2016 ዓ.ል በኮምቦልቻ ከተማ ሀገር አቀፍ የሰላም፣ የአብሮነትና የወንድማማችነት ጉባዔ እንደሚካሄድ ተነገረ።

ጉባዔው ሀገራችን ኢትዮጵያ የተለያዩ ሃይማኖቶች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች በአንድነት ተሰባስበው የሚኖሩባትና ታላቅ የአብሮነት እሴትን ይዛ የኖረች ሀገር የመኾኗን ፋይዳ ለአዲሱ ትውልድ የማስገንዘብ ዓላማ ያለው መኾኑ ተነግሯል።

የጉባዔው አዘጋጅ ኮሚቴ በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት አዳራሽ ዛሬ በሰጠው መግለጫ፣ ጉባዔው በአማራ ክልል ኮምቦልቻ ከተማ ግንቦት 17 እና 18፣ 2016 ዓ.ል የተለያዩ ዝግጅቶችን በማካተት እንደሚካሄድ ተናግሯል።

የጠቅላይ ምክር ቤቱ ዋና ፀሐፊ ሼይኽ ሐሚድ ሙሳ ሀገር አቀፍ ጉባዔው በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የበላይ ጠባቂነት፣ በአማራ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት አዘጋጅነት እንደሚካሄድ ተናግረዋል።

ከጂማ ቀጥሎ ለአራተኛ ጊዜ በኮምቦልቻ ከተማ በሚካሄደው የሰላም፣ የአብሮነትና የወንድማማችነት ጉባዔ ላይ ከተለያዩ የሀገራችን ክልሎች የሚመጡ ዓሊሞች፣ ዱዓቶችና ምሁራን ይሳተፋሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ሼይኽ ሐሚድ ተናግረዋል።

የጉባዔው ዝግጅት ኮሚቴ ሰብሳቢ ሼይኽ ዩሱፍ አበራ በዚህ ደማቅ ሀገር አቀፍ ጉባዔ ላይ መላው ማኅበረሰባችን እንዲታደም ጥሪ አቅርበዋል።

የአማራ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ዋና ፀሐፊ ሼይኽ አብዱራህማን ሱልጧን በበኩላቸው በኮምቦልቻ የሚካሄደው ዝግጅት የክልሉን ተጨባጭ ሁኔታ ባገናዘበ መልኩ በሶደቃና በዱዓ እንዲሁም በዓሊሞች፣ በምሁራን እና በወጣቶች የፓናል ውይይት የታጀበ እንደሚሆን ተናግረዋል።

ሀገራችን ኢትዮጵያ የተለያዩ ሃይማኖቶች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች በአንድነት ተሰባስበው የሚኖሩባት የጋራ ቤታችን ናት ያሉት ሼይኽ አብዱራህማን፣ ወጣቱ ትውልድ ይህን እሴት ማስቀጠል ይችል ዘንድ መሰል ጉባዔዎችን ማካሄድ አስፈላጊ ነው ብለው እንደሚያምኑ ተናግረዋል።

ለሁለት ቀናት በሚካሄደው ሀገር አቀፍ የሰላም፣ የአብሮነትና የወንድማማችነት ጉባዔ ላይ የጠቅላይ ምክር ቤቱ ከፍተኛ ኃላፊዎች፣ አሊሞች፣ አዲስ አበባና ድሬደዋን ጨምሮ የሁሉም ክልሎች የእስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ፕሬዚደንቶች፣ የተለያዩ የሃይማኖት ተቋማት መሪዎች፣ ምሁራንና ተጽዕኖ ፈጣሪ የማኅበረሰብ መሪዎች ይታደማሉ ተብሎ ይጠበቃል።

••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1
ግንቦት 14፣ 2016 | ዙል ቂዳህ 14፣ 1445 ዓ.ሂ.
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
በሀገራዊ ምክክሩ ሙስሊሙ ማኅበረሰብ ተገቢ ውክልና ሊያገኝና በንቃትም ሊሳተፍ ይገባል ተባለ።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
ሲዳማ |
በሀገራችን እንደሚካሄድ የሚጠበቀው ሀገራዊ ምክክር ሰላማዊ፣ አካታችና ፍሬያማ ይኾን ዘንድ፣ ሙስሊሙ ማኅበረሰብ በአግባቡ ሊወከልና በንቃት ሊሳተፍ እንደሚገባ ተነገረ።

ይህ የተነገረው፣ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ከሲዳማ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ጋር በመተባበር በሀገራዊ ምክክርና በወቅታዊ የሰላም ጉዳይ ከክልሉ የሙስሊም ማኅበረሰብ ተወካዮች ጋር ዛሬ (ግንቦት 14) ባካሄደው የውይይት መድረክ ላይ ነው።

መድረኩ በሀገራችን እንደሚካሄድ የሚጠበቀው ሀገራዊ ምክክር ሰላማዊ፣ አካታችና ፍሬያማ ይኾን ዘንድ፣ ከሙስሊሙ ማኅበረሰብ በሚጠበቀው የነቃ ተሳትፎ ዙርያ ግንዛቤ በማስጨበጥ ዓላማ እንደተዘጋጀ ተነግሯል።

የውይይቱ ተሳታፊዎች በቀረበው አጀንዳ ዙርያ ባደረጉት ውይይት ሀገራዊ ምክክሩ ለሀገራችን ዘላቂ ሰላም መሠረት በመኾኑ፣ የሙስሊሙ ማኅበረሰብ ድምጽ በአግባቡ ሊሰማበት እንደሚገባ አሳስበዋል።

ለዚህም የሀገሪቱ ሙስሊሞች በሀገራዊ የምክክር መድረኩ ላይ ተመጣጣኝ ውክልናና የተሳትፎ ዕድል ሊያገኙ እንደሚገባ የመድረኩ ተሳታፊዎች በአጽንዖት ተናግረዋል።

የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ የምክክር መድረኮች በሙሉ አካታችና የተለያዩ የሀገሪቱ ማኅበረሰቦች በአግባቡ የሚወከሉበት መኾኑን የማረጋገጥ ኃላፊነት እንዳለበት ተጠቅሷል።

የውይይት መድረኩ ተሳታፊዎች በዚህ ሐሳብ ላይ የጋራ መግበባት ላይ በመድረስ መድረኩ በስኬት ተጠናቅቋል።

በሐዋሳ ከተማ ፓራዳይስ ሆቴል አዳራሽ በተካሄደው በዚህ የውይይት መድረክ ላይ ከክልሉ ሁሉም ዞኖችና ወረዳዎች የእስልምና ጉዳይ ምክር ቤት ሥራ አስፈጻሚዎችና አባላት፣ የዑለማ ምክር ቤት አባላት፣ የመስጂድ ኢማሞች፣ ዱዓቶች፣ የማኅበረሰብ ተወካዮች፣ የወጣቶችና የሴቶች ተወካዮች ተሳትፈውበታል።

​••••••••••••••••••••••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1
ግንቦት 15፣ 2016 | ዙል ቂዳህ 15፣ 1445 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
520 የአሏህ እንግዶች መስጂደል ነበዊ በሚገኘው የረዉዷ ሸሪፍ ዚያራ አደረጉ።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
መዲና |

ከቀናት በፊት ወደ መዲነተል ሙነወራ ከተጓዙት የ1445 ዓ.ሒ የአሏህ እንግዶች 520 የሚኾኑት በመስጂደል ነበዊ የሚገኘውን ረውዷ ሸሪፍ በመዘየር ዱዓ አደረጉ።

የሐጃጆቹ የረውዷ ሸሪፍ ዚያራ መዲና በሚገኘው የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የሑጃጅ መስተንግዶ ቡድን አማካኝነት በተያዘ መርኃግብር አማካይነት እንደተካሄደ ለማወቅ ተችሏል።

በተከበረው ረውዳ ውስጥ ሶላት መስገድ የሚያስገኘውን ከፍተኛ አጅር (ምንዳ) ለማግኘት ከመላው ዓለም የሚመጡ ምዕመናን ቁጥር ከጊዜ ወደጊዜ በመጨመሩ አስቀድሞ በ"ኑሱክ" መተግበሪያ ማመልከትና ፍቃድ ማግኘት እንደሚያስፈልግ መዲና የሚገኘው የመስተንግዶው አስተባባሪ ሙጃሒድ አብዱልጀሊል ነግረውናል።

የ1445 ዓ.ሒ ሐጃጆች ይህን የጉብኝት ዕድል እንዲያገኙ የመስተንግዶ ቡድኑ ቀጠሮ የማስያዝ ሥራ እየሠራ በመሆኑ በቀጣዮቹ ቀናት መዲና የሚገቡ የአሏህ እንግዶች በሚያዝላቸው ቀጠሮ ተጠቃሚ እንዲኾኑ አስተባባሪው አሳስበዋል።

•••••••••••••••••••••••••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1