Hadiya zone communication
1.11K subscribers
1.2K photos
41 videos
9 files
16 links
This is Hadiya Zone Govern. Comm. official Telegram channel.

For more updates please visit Hadiya zone government communication affairs department facebook page
Download Telegram
ሴቶች በልማት ህብረት በማደራጀት ሁለንተናዊ የልማት ተጠቃሚነታቸውን ለማረጋጋት የባለድርሻ ድጋፍና ክትትል ወሳኝ መሆኑን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሴቶችና ህፃናት ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ በይዳ ሙንዲኖ ገለፁ።

ኃላፊዋ በሀድያ ዞን ሆሳዕና ከተማ ሴቶች ልማት ህብረት እየተሰሩ ያሉትን የልማት ስራዎች ተዟዙረው ምልከታ አድርገዋል።

።።።።ሆሳዕና፥ ግንቦት 14/2016 ዓ. ም።።።።

በመስክ ምልከታው ላይ ተገኝተው በሆሳዕና ከተማ የሴቶች ልማት ህብረት እንቅስቃሴን ተዟዙረው የተመለከቱት በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሴቶችና ህፃናት ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ በይዳ ሙንዲኖ እንደገለፁት፧

ሴቶችን በልማት ህብረት በማደራጀት ሁለንተናዊ የልማት ተጠቃሚነታቸውን ለማረጋጋጥ በሚደረገው ሂደት ውጤታማ ተግባራትን ማከናወን እንደሚቻል በሆሳዕና ከተማ ሊች አምባ ቀበሌ ፍቅር የሴቶች ልማት ህብረት ስራ ወጤታማ መሆኑን አንዱ ማሳያ ነው ብለዋል ።

ኃላፊዋ አያይዘውም ሴቶችን በልማት ህብረት በማደራጀት የኢኮኖሚ ተጠቃሚነታቸውን ለማረጋገጥ በሚደረገው ጥረት ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለው፥

በሴቶች ዘርፍ ትኩረት በተደረገባቸው በእርሻ ልማት ፥በእንስሳት እርባታ ፥የሴቶች የገንዘብ ቁጠባና ብድር ፥በሴቶችና ህፃናት ላይ የሚፈጽሙ ጾታዊ ጥቃትን መከላከልና መቀነስ፥ እንድሁም ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን ለመከላከልና ለማስወገድ በተለይ የሴት ልጅ ግርዛትና ያለ ዕድሜው ጋብቻ ላይ ትኩረት አድርገው ከባለድርሻ አካላት ጋር በጋራ በመሆን ተቀናጅተው መስራት እንደሚጠበቅባቸው ኃላፊዋ ወ/ሮ በይዳ አሳስበዋል ።

የሀድያ ዞን ሴቶችና ህፃናት ጉዳዮች መምሪያ ም/ኃላፊ ወ/ሮ አለምፀሐይ ተሰማ በበኩላቸው እንደገለፁት ከዚህ ቀደም ሴቶች በልማት ቡድን ተደራጅተው የመስራት ላይ ክፍተት መኖሩን አንስተው አሁን ላይ ጠንካራ የልማት እንቅስቃሴዎች መኖሩን ጠቁመው በቀጣይም በዞኑ የሚገኙ ሴቶች በልማት ህብረት በማደራጀት የልማቱ ተሳታፊና ተጠቃሚ እንዲሆኑ በማጠናከር ከባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት የተደራጀ የድጋፍና ክትትል ስራዎችን በማከናወን ለተሻለ ውጤትና ተጠቃሚነት በትኩረት እንደሚሰራ ተናግረዋል።

ምልከታ የተደረገባቸው የሴቶች ልማት ህብረት አባላት በበኩላቸው በህብረት በመሆን ርስበርስ ከመመካከር ባለፈ የጀመርነውን ተጠቃሚ የሚያደርገን ተግባር አጠናክረን እንሰራለን በማለት የሚደረግላቸው ድጋፍና ክትትል እንዳይለያቸው አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

በየተደረገው ምልከታም የክልሉ ሴቶችና ህፃናት ቢሮ ኃላፊን ጨምሮ ም/ቢሮ ኃላፊዋ ወ/ሮ ፈቲያ ጀማል ፥የዞኑ ፥የከተማ እና የቀበሌ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።
በሰለሞን ወልዴ
ሁሉሞ በተሰማራበት መስክ ለሀገር ግንባታና ብልጽግና ፋይዳ ያላቸው ተግባራትን በመፈፀም ለሀገሩ አርበኛ ሊሆን ይገባል- የዋቸሞ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት ዶክተር ሀብታሙ አበበ

።።።።ግንቦት 14/2016 ዓ.ም ሆሳዕና።።።።

የኢፌዴሪ ሰላም ሚኒስቴር ከዋቸሞ ዩኒቨርስቲ ጋር በመተባባር "ዘመኑን የዋጀ አርበኝነት ለሕብረ-ብሔራዊ አንድነት" በሚል መሪ ቃል የንቅናቄ መድረክ በዩኒቨርስቲው አካሂዷል።

ዜጎች ዘመኑን የዋጀ አርበኝነት ገድል ለመፈጸም የሀገር ሉዓላዊነት ለማስከበር፣ ዘመናዊ ግብርና በመጠቀም ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ፣ የኃይል ሚዛን ማስፋት፣ እኩልነትና ፍትህዊነት በማረጋገጥ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን በማፍለቅ የሀገር ስልጣኔ ማምጣት እንደሚገባ በመድረኩ ተገልጿል።

በንቅናቄ መድረኩ ላይ የተገኙት የዋቸሞ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት ዶክተር ሀብታሙ አበበ እንዳሉት አርበኝነት የሀገር መውደድን በልብ ይዞ በማቆየት ሀገራችን ሉዓላዊና ነፃ ሀገር ሆና እንድትቆይ አባቶቻችን የህይወት መስዕዋትነት በከፈሉት ዋጋ ልክ መሆኑን ገልጸዋል።

ሁሉም በተሰማራበት መስክ የሀገር አንድነትን በማጉላት እኩልነትና ዕድገት አስጠብቆ በመሄድ የነጣለ ትርክቶችን በማስቀረት የወልና የአንድነት ትርክቶችን በማጠናከር የሰላም፣ የዕድገትና የእኩልነት አርበኛ መሆን ይገባል ብለዋል።

ሀገረ መንግስት ለመገንባት በመደማመጥ ፣ አለመግባባቶችን በጠረጴዛ ዙሪያ በመፍታት ለዜጎች የምትመች ሀገር መፍጠር ከሁሉም ይጠበቃል ሲሉ ተናግረዋል።

በዩኒቨርስቲው የሚገኙ ምሁራን ትውልድ በመገንባት ለአካባቢውና ለሀገር የሚጠቅሙ ቴክኖሎጂዎችን በማፍለቅ ችግሮችን በጥናትና በምርምር በማሳወቅ የበኩላቸውን እንዲወጡ አሳስበዋል።

የኢፌዴሪ ሰላም ሚኒስተር ተወካይ አቶ ዘነበ ለማ በበኩላቸው አርበኝነት ለወገን የተሻለ ሀገር እንዲኖር ጉልበቱን፣ ዕውቀቱን ፣ ክቡሩንና ህይወቱን መሰዋዕት ለመክፈል የተዘጋጀ ህብረተሰብ ክፍል ነው ብለዋል።

ዘመኑን የዋጀና ወቅቱን የሚመጥን ህብረ-ብሔራዊ አንድነትን የሚያጠናክሩ ሁነቶች ላይ ማተኮር እንደሚገባ የጠቆሙት አቶ ዘነበ።

በሀገረ መንግስት ግንባታ ሂደት በመሠረታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ በሰከነ መልኩ በመወያየት የጋራ መግባባትን በማጎልበት በተግባር የሚታይ ዴሞክራሲያዊ ሥራዓት በማስፈን በመፈቃቀር ላይ የተመሠረተ ህብረ-ብሔራዊ አንድነት ማጠናከር ያስፈልጋል ነው ያሉት።

አንዳንድ ወገኖች የወቅቱን ነባራዊ ሁኔታ ባለመገንዘብ የራሳቸውን ፖለቲካና ሥልጣን ፍላጎት ለማሳካት አንድነታችንን ለመሸርሸር መሞከር አይገባም ብለዋል።

በመድረኩ የተሳተፉ ምሁራን በሰጡት አስተያየት ዜጎችን አርበኛ የሚያደርጉ ህብረ-ብሔራዊ አስተሳሰብን በማጉላት የጋራ ማንነቶችን በመገንባት ዕድሎችን ማስፋት ይገባል ብለዋል።

በንቅናቄው መድረክ ላይ የዋቸሞ የዩኒቨርስቲ ምክትል ፕሬዝዳንቶች፣ ዲኖች፣ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልልና የሀዲያ ዞን ሰላምና ፀጥታ ኃላፊዎች፣ ከተማሪዎችና ከሌሎችም ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።

በደገለ ባምቦሬ
የትራንስፖርት አገልግሎት አቅራቢዎች የሕዝብ አገልጋይነትን መንፈስ በመላበስ እንዲሠሩ ተጠየቀ

የሀዲያ ዞን ትራንስፖርትና መንገድ ልማት መምሪያ ለማህበረሰቡ ቀልጣፋ የትራንስፖርት አገልግሎት ለማረጋገጥ የሚያስችል የምክክር መድረክ ከባለድርሻ አካላት ጋር አካሄደ

።።።።ግንቦት 14/2016 ዓ.ም ሆሳዕና።።።።።

ሁሉም የትራንስፖርት ጉዳይ የሚመለከተዉ ባለድርሻ አካላት የሕዝብ አገልጋይነትን መንፈስ በመላበስ እንዲሠሩ የሀዲያ ዞን ትራንስፖርትና መንገድ ልማት መምሪያ ሀላፊ አቶ መስፍን ቆጠራ ጠይቀዋል።

በመድረኩ የተገኙት የሀዲያ ዞን ትራንስፖርትና መንገድ ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ መስፍን ቆጠራ ባስተላለፉት መልዕክት ማህበረሰቡን በትራንስፖርት አገልግሎት አሰጣጣችን ለማርካት በቁርጠኝነት መሥራት ከሁላችንም ይጠበቃል በማለት።

የትራንስፖርት አገልግሎት በአንድ አካባቢ ብቻ የማይወሰን ድንበር ዘለል በመሆኑ በጥቂት አካላት ርብርብ ብቻ የሚፈለገዉን ዉጤት ማስመዝገብ እንደማይቻል ገልፀዋል።

አልፎ አልፎ የሚስታወሉ መስተካከል የሚገባቸው ጉዳዮችን በመለየት ዘርፉን ዉጤታማ ለማድረግ ተቋሙ በቅንጅት እየተሰራ ነው ብለዋል።

የዞኑ ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ ፀጋዉ ሙሉጌታ በበኩላቸዉ እንደ ንግድ ተቋም በትራንስፖርት ጉዳይ ከተቋሙ ጋር በመቀራረብ በጋራ እየሰሩ መሆኑን ገልፀው

ከናፍጣና ቤንዚን አቅርቦትና ስርጭት አኳያ ዘርፈ ብዙ ማሻሻያ ተግባራትን ቢከናወንም አሁንም ዘርፉ በርካታ ተግዳሮቶች ያሉት በመሆኑ የባለድርሻ አካላት ድጋፍ ያስፈልጋል ብለዋል።

ተሳታፊዎች በሰጡት አስተያየት ከንግግር ባለፈ ተግባሩን ለማሳለጥ የባለድርሻ አካላት የቁርጠኝነት ማነስ መኖሩን ተናግረዋል።

አሽከርካሪዎች የሚጠበቅባቸዉን ግዴታ አሟልተዉ ያለመስራት ፣ የነዳጅ ማደያዎች አቅርቦት እጥረትና የፍትሃዊነት ችግር ስለመኖሩ ያነሱት ተሳታፊዎች

የንግድ ተቋም ባለሙያዎች በማደያዎች ላይ የሚያደርጉት ቁጥጥር የላላ መሆንና መሰል ችግሮችን በጋራ በማረም የተጀመረዉን ለውጥ ማስቀጠል እንደሚገባ ተናግረዋል።
በኤልያስ ተሰማ
በሳይንስ፣ ኢንፎርሜሺንና ቴክኖሎጂ የሙያ ዘርፍ የሰለጠነ የሰዉ ኃይል በየዘርፉ ለሚከናወኑ ተግባራት ውጤታማነት ፋይዳው የጎላ መሆኑን የሀድያ ዞን ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጅ መምሪያ አስታወቀ።

መምሪያው ከዞን፣ ከወረዳና ከተማ አስተዳዳሮች ለተወጣጡ ባለሙያዎች በሳይንስና ቴክኖሎጂ የአቅም ግንባታ ስልጠና ሰጥቷል።
።።።ሆሳዕና፣ ግንቦት 15/2016 ዓ.ም።።።
በስልጠና ማስጀመሪያ መድረኩ ላይ ንግግር ያደረጉት የሀድያ ዞን ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ ኃላፊ አቶ ታምራት አኑሎ ባስተላለፉት መልዕክት የሰው ኃይል ውጤታማነትን ለማሳደግ ሴክተሩ በዓመቱ ካስቀመጠዉ ግብ አንዱ የሠራተኞችን አቅም የማጎልበት ስልጠና መሆኑን አንስተው ለዚህም በዞኑ ከሚገኙ ሁሉም መዋቅሮች ለተወጣጡ ባለሙያዎች ስልጠናውን መሰጠት እንደሆነ ጠቁመዋል ።

ስልጠናውም የሰዉ ኃይልን በአቅም ማጎልበት በሳይንስና ቴክኖሎጂ በፈጠራና በልየታ ትኩረት ያደረገ ነዉም ብለዋል።

ስልጠናዉ እስከታች ላሉ ሴክተር መ/ቤቶች የሚሰጥ መሆኑን አብራርተው በሀገር ደረጀም ይሁን በአካባቢ ደረጀ በስፋት የሚስተዋለውን ስራ አጥነትን ለመቀነስ በፈጠራ ስራ ትኩረት በመስጠት በቅድሚያ ባለሙያዎች ሰልጥነው ሌለውን መደገፍ እንዲችሉ የሚያግዝ ስልጠና ነው ብለዋል

አቶ ታምራት አክለውም በተለያዩ አካባቢዎች ያሉ ትምህርት ቤቶች በሳይንስ ክበባት በተሟላ መልኩ መደራጀት እንዲችሉ የሚያግዝ ስልጠና መሆኑን አንስተዋል፡

በቀጣይ በዞን ደረጃ የፈጠራ እግዚቢሺን እንደሚደረግ የገለጹት የመምሪያዉ ኃላፊ አቶ ታምራት አኑሎ በእግዚቢሽኑም ይሁን በተለያዩ የስራ ዘርፎች የተሰማሩ የፈጠራ ዉጤት ባለቤቶች እንዴት ይስታፋሉ ምን ዓይነት የፈጠራ ወጤቶችን ማቅረብ አለባቸው የሚል ሀሳብ ላይ ስልጠና መሰጠቱንም ኃላፊው አስረድተዋል ።

ተቋሙም በቀጣይ በግብርና በኢንዱስትሪና በሌሎች ዘርፎች የማህበረሰባችንን ችግሮች የሚፈቱ የፈጠራ ዘርፎች ላይ የሚሠማሩ ግለሰቦችንና ተቋማትን እንደሚያበረታና ድጋፍና ክትትል እንደሚያደርጉም የመምሪያዉ ኃላፊ አቶ ታምራት ጠቁመዋል ።

ከስልጠና ታሳታፊዎች መካከል አቶ ዘለቀ ሀንድሶ ከሆሳዕና ከተማ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ፅ/ቤት እንዲሁም አቶ ዳና አብቼ ከጎምቦራ ወረዳ ሳይንስና ኢንፎርሜሺን ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት በሰጡት አስተያየት ስልጠና በሰው ሀብት መመሪያና ደንብ እንዲሁም በትምህርት ቤቶች የሳይንስና ኢንፎርሜሺን ቴክኖሎጂ ክበባት ከማቋቋምና ባለፈ በፈጠራ ስራ ላይ ያተኮረ መሆኑን አንስተው ከስልጠናው በቂ ግንዛቤ ማግኛታቸዉን ገልጸዋል።

ሰልጣኞቹ አክለውም ከዚህ ስልጠና በኋላ ባገኙት ዕዉቀት በተመደቡበት የስራ ዘርፍ ላይ ማህበረሰቡን በቁርጠኝነት ለማገልገል ቁርጠኛ መሆናቸዉን ተናግረዋል።
በኤልያስ ተሰማ
ግንቦት 16/2016
እያንዳንዱ ከተማ ስለማ ኢትዮጵያ ትለማለች የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እንዳሻው ጣሰው

ርዕሰ መስተዳድሩ ይህን ያሉት በሆሳዕና ከተማ አስተዳደር የተሰሩ የተለያዩ የልማት ስራዎችን ተዟዙረው በጎበኙበት ወቅት ነው።

በከተማው  በ2.2 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ የተለያዩ የልማት ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸውን የሆሳዕና ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ደዊት ጡምደዶ ገልፀዋል።

ርዕሰ መስተዳድር አቶ እንዳሻው ጣሰው በጉብኝት ወቅት እንደተናገሩት በከተማው በህብረተሰብ ተሳትፎና በመንግስት እየተሰሩ ያሉ መሰረተ ልማቶቾ አበረታች ናቸው ብለዋል።

በከተማው እየተሰሩ ካሉ መሰረተ ልማቶች ውስጥ የውስጥ ለውስጥ የአስፋልት መንገድ፣ የእግረኞች መንገድ፣ የውሃ መውረጃ ቦህዎች፣ የከተማ የኮርደር አረንጓዴ ልማት ልማት ስራዎች ቶሎ ተጠናቅቆ ለህብረተሰቡ አገልግሎት እንዲሰጥ ከመረባረብ ያስፈልጋል ብለዋል።

ሆሳዕና ከተማ በተፈጥሮም አረንጓዴ የበዛበት ከተማ  በመሆኑ በደንብ መንከባከብና መጠበቅ ያስፈልጋል ነው ያሉት።

ከተማው ከተለያዩ ክልሎችና ከተሞች ጋር የሚያስተሳስር ኮርደር በመሆኑ እና ከፍተኛ የሆነ የንግድ እንቅስቃሴ ያለባት ከተማ በመሆኑ ህብረተሰቡ እራሱን በማዘጋጀት በልዩ ልዩ ልማቶችን ላይ መሳተፍ ያስፈልጋል ነው ብለዋል።

በሀገር ውስጥም ይሁን ከሀገረ ውጪ ያሉ ተወላጆች ከተማውን እንዳያለሙም ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።

በከተማም ይሁን በዞን በተለያዩ ስራ ድርሻ የሚሰሩ የስራ ኃላፊዎች ከተማውን የበለጠ ለማሳደግ ከልብ ሆነው ህዝብን እንዲያገለግሉ  አሳስበዋል።

ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ለከማው እድገት እያበረከተ ላለው አስተዋጽኦ አመስግነው ንብረትነቱ ፕረሚድ ኮንስትራክሽን የሆነው የአስፋልት ፕላንት ማሽን ማህበረሰቡንና ተማሪዎችን በማይረብሽ መልኩ ስራ እንዲጀምር አቅጠጫውን አስቀምጠዋል።

የሆሳዕና ከተማ ከንቲባ አቶ ዳዊት ጡምደዶ  በከተማ አስተዳደሩ በውስጥ ገቢ፣ በዘኑ ድጋፍና በህብረተሰቡ አጠቃላይ ተሳትፎ   14.13  የውስጥ ለውስጥ ኮንክሪት ስፓልት መንገድ ግባታ እየተካሄደ መሆኑን አንስተው

  ከዚህ ጎን ለጎን  በሶስት ሳይቶች የ 5.5 ኪ.ሜ ነባሩን መንገድ ወደ ኮንክሪት ስፓልት የማሳደግ ስራ እንዲሁም በኢትየጵያ መንገዶች ባለስልጣን እየተገነባ ያለውን የ 5 ኪ.ሜ ጨምሮ በጥቅሉ በከተማው የ25 ኪ.ሜ ስፓልት መንገድ ግንባታ እየተካሄደ እንደሚገኝ አብራርተዋል ፡፡

በከተማው  ከ2 መቶ 86 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተጀመሩ  የተለያዩ 22 ፕሮጀክቶች ግንባታ እና ከ260 ሚሊዮን ብር በላይ የተጀመሩ የውሃ ፕሮጀክቶችን ጨምሮ ከ2.2 ቢሊዮን ብር ባላይ ወጪ የተለያዩ መሰረተ ልማቶች እየተሰሩ እንደሆነ ገልፀዋል።

በኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን እየተሰራ ያለው 5 ኪ.ሜ የአስፋልት መንገድ በዕቅዱ መሰረት ተጠናቆ አገልግሎት ባለመስጠቱ የመልካም አስተዳደር ችግር እየሆነ  በመምጣቱ የክልሉ መንግስት እገዛ እንዲያደርግ ጠይቀዋል።

ልማቱ ተጠናቆ ለህብረተሰቡ አገልግሎት እንዲሰጥ ሁሉም ሰው ርብርብ ሊያደር ይገባል ብሏል።

በጉብኝቱም የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል  ርዕሰ መስተዳድር፣ የሀዲያ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ማቲዎስ አኒዮን ጨምሮ የክልል፣ የዞን የሆሳዕና ከተማ አስተዳደር የስራ ኃላፊዎች እና ሌሎች የማህበረሰብ ክፍሎች ተገኝተዋል ።

በአድነው አሰፋ