Dr Mehret Debebe ምህረት ደበበ
8.12K subscribers
15 links
`` የስነ ልቦና እና የስነ አዕምሮ ምክሮችን ያገኛሉ ።„„
Download Telegram
ስኬትን ፍለጋ

“ስኬትን ከፈለክ ስኬትን ዓላማህ አድርገህ አትያዝ፡፡ የምታምንበትንና የምትወደውን ነገር ከልብህ ስታደርግ ስኬት ራሱ ይመጣል” - David Frost

ለትክክለኛ አላማ መቆም ስኬትን ይቀድማል እንጂ ስኬት አላማን አይቀድምም፡፡ አንዳንድ ሰዎች፣ “ቢሳካልኝ ኖሮ ይህንና ያንን አደርግ ነበር” በማለት በገንዘብና በተለያዩ አቅጣጫዎች “ቢሳካላቸው” ሊያደርጉ ስለሚፈልጉት የወደፊት አላማ ሲናገሩ ይደመጣሉ፡፡ አንድ ማስታወስ ያለባቸው እውነታ ግን አንድን አላማ ይዘው መስራታቸው ወደ ስኬት እንደሚወስዳቸው ነው፡፡ በሌላ አባባል፣ ተሳካላቸው በመባል የሚታወቁ ሰዎች ለስኬት የኖሩ ሰዎች ሳይሆኑ ለአንድ አላማ በጽንአት የኖሩ ናቸው፤ ያንን ሲያደርጉ ስኬት ተከተላቸው፡፡

ለስኬት የሚኖር ሰው ስኬት ያጣ ሲመስለው ያቆማል፡፡ ለአላማ የሚኖር ሰው ግን ስኬት ያላገኘ ቢመስለውም እንኳ ጉዞውን ይቀጥላል፣ ምክንያቱም አላማ የተሰኘውን የስኬቶችን ሁሉ ስኬት በእጁ ጨብጧልና ነው፡፡ “የምትወደውንና መልካም የሆነውን ነገር አድርግ፣ ያንን የምታደርገውን ነገር ደግሞ ውደደው” የሚለው አባባል እውነት ነው፡፡ ስኬትን ፍለጋ ከአላማህ ውጪ የሆነን “ታላቅ” ነገር ከማድረግ፣ አላማን በመከተል አስቸጋሪ ጎዳና መጓዝ ይመረጣል፡፡

በቅንነት ሼር ያድርጉልኝ 👇
http://t.me/Dr_MehretDebebe
“ዛሬ ይቅርታን ለመምረጥ ወስኛለሁ”

ታሪኩ ከተከሰተ ትንሽ ሰንበት ብሏል፡፡ ይህ ታሪክ የሆነው በስፔን ሃገር ነው፡፡ አባትና ልጅ ችላ ቢሉት ቀለል ሊል የሚችልን አንድን የግጭት ሁኔታ በማካበዳቸው ምክንያት ተጣልተዋል፡፡ በጉዳዩ ተጎድቻለሁ ባይ አባት በልጁ ላይ ስለጨከነበትና ይቅር አልለው በማለቱ ምክንያት ልጅ ቤቱን ጥሎ በመሄድ ይጠፋል፡፡ በጊዜው ከነበረበት ንዴት የተነሳ አባት ምንም አልመሰለውም፡፡ ከትንሽ ጊዜ በኋላ ግን ጉዳዩ እያሳሰበው ስለመጣ የልጁን ደህንነት ለማወቅ መፈለግ ጀመረ፡፡ በተለያዩ መንገዶች ሲያጣራ ከቆየ በኋላ ከብዙ ወራት ሙከራ በኋላ በዚያው ከተማ ውስጥ እንደሚኖር አወቀ፤ በትክክል የት እንዳለ ግን ማወቅ አልቻለም፡፡ ልጁ በሕይወት መኖሩንና እጅግም ያልራቀ መሆኑን ሲያውቅ የተከሰተውን ችግር ሁሉ በመርሳት ይቅርታን ሊሰጠው ፈለገ፡፡ ይህንንም ለማድረግ ልጁን ማግኘት ስላልቻለ አንድን የመጨረሻ ሙከራ ለማድረግ ቆረጠ፡፡

በማድሪድ (ስፔን) ከተማ በሚታተመው ብዙ በመነበብ የታወቀ ጋዜጣ ላይ እንዲህ የሚልን መልእክት አወጣ፣ “ልጄ ፓኮ፣ ያለፈውን ስህተተህን ሁሉ ይቅር ስላልኩህ እባክህን ቅዳሜ ከቀኑ በስድስት ሰዓት በዚህ ጋዜጣ ማተሚያ ዋና ቢሮ በር ላይ ላግኝህ፡፡ የሚወድህ አባትህ፡፡” በተባለው ቀን ይህ አባት ልጁን ለማግኘት በተቀጣጠሩበት ቦታ ሲሄድ አንድን አስገራሚ ነገር ተመለከተ፡፡ ስማቸው ፓኮ የሆነና ከአባታቸው ይቅርታን የሚፈልጉ 800 ወጣቶች መልእክቱ የተላከው ከእነሱ አባት ስለመሰላቸው በዚያ ቢሮ በር ላይ ተሰብስበዋል፡፡ በተከሰተው ነገር እጅግ የተገረመው አባት ከዚያ ሁሉ ወጣት መካከል ልጁን ፈልጎ አግኘቶ ከሳመው በኋላ፣ “ዛሬ ይቅርታን ለመምረጥ ወስኛለሁ” አለውና ይዞት ወደቤቱ ወሰደው፡፡

ማሕበራዊ ኑሮ እስካለ ድረስ አለመግባባት የተሰኘው የሕይወት ሂደት የማይቀር ነው፡፡ ይህንን ምስጢር የዘነጉ ሰዎች ትኩረታቸውን ሁሉ በዚያ አለመግባባት ላይ ሲያደርጉ ይገኛሉ፡፡ ትኩታቸውን የሚጥሉበት ነገር የወደፊታቸው ላይ ታላቅ ተጽእኖ እንዳለው የገባቸው ሰዎች ያለፈውን በመተው ወደፊት በመዝለቃቸው ላይ ሲያተኩሩ፣ ሌሎች ግን በአለመግባባትና በጸብ “መንፈስ” ውስጥ የመቆየት ዝንባሌ አላቸው፡፡ ትኩረታቸውን በይቅርታና ከተከሰተው ችግር ባሻገር በመሄድ ላይ ማድረግን ትተው ነገርን በመጎተትና በማካበድ ላይ የሚያደርጉ ሰዎች ወደ ተሻለ ሕይወት ለመዝለቅ የሚያበቃ አመለካከት እንደጎደላቸው አመልካች ነው፡፡

ሁለት በአየር ላይ የሚበሩ ፍጥረታትን አስብ፤ ዝንብንና ንብን፡፡ ዝንብ ቆሻሻው፣ መጥፎ ሽታ ያለውና የሞተው ነገር ሲስባት፣ ንብ ደግሞ ንጹህ፣ መልካም ጠረን ያለውና ሕይወት ያለው ነገር ይስባታል፡፡ ዝንብ ቆሻሻን፣ በሽታንና ሞትን ስታዛምት፣ ንብ ስትሰራ ውላ ጣፋጭ ነገርን በማምረት የብዙዎችን ሕይወት ታጣፍጣለች፡፡

አሁንም ሁለት በአየር ላይ የሚበሩ ፍጥረታትን አስብ፤ ንስርንና ጥንብ አንሳን፡፡ ንስር ሕይወት ያለውን ነገር ተናጥቆ ሲመገብ፣ ጥንብ አንሳ የከረመን፣ የሞተንና የበሰበሰን ነገር ሲያነሳ ይኖራል፡፡ ምርጫው የእኔ ነው፡፡ ያለፈውንና የሞተውን ነገር መከታተልና ያንን “እየተመገቡ” መኖር፣ ወይስ ያንን ትቶ የወደፊቱን፣ ትኩሱንና በይቅርታ የታደሰውን?

መዘንጋት የሌለብህ እውነታዎች …

• ተበደልኩ በማለት ወደኋላ በመመለስ ወደምታስታውሰው የጊዜ ርቀት የመመለስና ኋላ ቀር የመሆን እድልህ የሰፋ ነው፡፡ ለምሳሌ፣ የዛሬ 10 ዓመት የሆነብህን አሁንም የምትቆጥር ከሆነ በአመለካከትህም ሆነ በኑሮ እድገትህ 10 ዓመታት ወደኋላ ተጎትተህ በመመለስ እንዳዘገምክ አትዘንጋ፡፡

• ይቅር ያላልከው ሰው በአንተ ላይ የበላይነት አለው፡፡ አንተ የሆነብህን ስታብሰለስል ምናልባት እርሱ የግሉን፣ የቤተሰቡንና የሕብረተሰቡን ሕይወት እንዴት እንደሚሳድግ እቅድ እያወጣ ወደፊት እየገሰገሰ ነው፡፡

• አንተ ይቅር ያላልከው ሰው ምን እንዳደረገብህ ለልጆችህና ለልጅ ልጆችህ ስታስተላልፍ፣ ምናልባት እርሱ አዳዲስ እውቀቶችንና ስልጣኔዎችን በማስተላለፍ አልፎህ ሄዶ ይሆናል፡፡

እኔ ዛሬ ይቅርታን ለመምረጥ ወስኛለሁ፣ አንተስ? አንቺስ?

#በቅንነት ሼር ያድርጉልኝ! 👇
http://t.me/Dr_MehretDebebe
ስህተትን የማመን ነጻነት

አንደኛው ምርጫህ ራስህን ስህተት-የለሽ አስመስሎ በማቅረብ ከስህተት የመማርንና የይቅርታን ጣእም ሳታጣጥም ማለፍ ነው፡፡ ሌላኛው ምርጫህ ግን ስህተትን በማመንና ይቅርታን በመጠየቅ ውስጥ የሚገኘውን ነጻነት መጎናጸፍ ነው፡፡

አምባ-ገነን መሪዎች ከሚታወቁበት ዋነኛ ባህሪያቸው ያው እንደ ስማቸው የፈለጉትን ነገር በፈለጉበት ጊዜ፣ ሁኔታ መጠን የማድረግ መብት እንዳላቸው የሚያምኑና ያንንም ከማድረግ ወደኋላ የማይሉ ሰዎች በመሆናቸው ነው፡፡ ከ1740 እስከ 1786 የፕሩዢያ ገዢ የነበረ ፍሬደሪክ ግን ምንም እንኳን የአምባ-ገነንነት ባህሪይ እንደነበረው ቢታመንና ይህም ስም ቢሰጠው፣ ለየት ያለ ባህሪይ እንደነበረው ይነገራል፡፡ ሆኖም፣ ፍሬደሪክ ከሚታወቅበት ባህሪይ እንዱ አምባ-ገነንነት የአመራር ስልቱን ለሕዝቡ ጥቅም የማዋል ሁኔታ አንዱ ነበር፡፡

አንድ ቀን በአንድ በግዛቱ ውስጥ በሚገኝ ማረሚያ ቤት ከአጃቢዎቹ ጋር ሲዘዋወር ሳለ አንድ አስገራሚ ነገርን ተመለከተ፡፡ ገና ታላቁ ፍሬደሪክ ለጉብኝት ወደማረሚያ ቤቱ ይመጣል ተብሎ እንደተነገረ ታራሚዎች በሙሉ ተዘጋጅተው ይጠብቁ ነበር፡፡ ይህ ሰው ካለው አምባ-ገነንነት ባህሪይ የተነሳ እንዲሆንና እንዲደረግ የፈለገውን ነገር ሊያስደርግ እንደሚችል ታራሚዎቹ በሚገባ ያውቃሉ፡፡ ምናባትም ወደ እነሱ ተመልክቶ ወይም ጩኸታቸውን ሰምቶ ትንሽ ከራራላቸው፣ ወዲያው እንዲፈቱ የማዘዝ አቅም እንዳለው ያውቃሉ፡፡ ለዚህ ነው በጉጉት የሚጠብቁት፡፡

ፍሬደሪክ ልክ ወደ ማረሚያ ቤቱ ግቢ እንደገባ ታራሚዎች በሙሉ መጮህ ጀምረዋል፡፡ አንዱ በዚህ በኩል፣ “ንጉስ ሆይ፣ እኔ አንድ ነገር ሳልበድል ነው የታሰርኩት፣ እባከህ አስፈታኝ” ይላል፡፡ ሌላኛው በዚያ በኩል፣ “ንጉስ ሆይ፣ እኔ ንጹህ ሰው ነኝ፣ ፍጹም ወንጀል የሌለብኝ ሰው ነኝ” ይላል፡፡ ሌሎችም እንዲሁ በግራና በቀኝ ምን ያህል ስህተት-የለሽ እንደሆኑና ፍትህ በጎደለው መልኩ ማረሚያ ቤት እንደገቡ እንዲሰማላቸው ይጮሃሉ፡፡

ንጉሱም ይህን ያህል ሰው ፍትህ የለሽ በሆነ መልኩ ወደማረሚያ ቤት እንዴት ሊገባ ይችላል በማለት እያሰበ ወደ አንድ አቅጣጫ ዘወር ሲል በአንድ ጥግ ዝም ብሎና አቀርቅሮ የተቀመጠ ታራሚ ተመለከተ፡፡ ይህ ታራሚ እንደሌሎቹ አይጮህም፡፡

ንጉሱ ወደዚህ ታራሚ ቀረብ በማለት፣ “ይህ ሁሉ ታራሚ ንጹህ እንደሆነ ይናገራል፣ አንተ ምነው ዝም አልክ? የአንተስ ሁኔታ ምንድን ነው?” በማለት ጠየቀው፡፡ ታራሚውም ቀና በማለት፣ “እኔ የሰራሁትን አውቃለሁ፣ ጥፋተኛ ነኝ፣ የሚገባኝን ነው ያገኘሁት” ብሎ ከተናገረ በኋላ መልሶ አቀረቀረ፡፡

ታላቁ ፍሬደሪክ ይንን ከሰማ በኋላ፣ ወደ አጃቢዎቹና ወደ ማረሚያ ቤቱ ጠባቂዎቸ ዘወር በማለት አንድ ትእዛዝ አስተላለፈ፣ “እነዚህ ሁሉ ታራሚዎች ንጹህ ነን ብለዋል፡፡ ይህ ሰው ደግሞ ስህተተኛ እንደሆነ አምኗል፡፡ በሉ፣ ይህ ስህተተኛ ሰው በብዙ ንጹሆች መካከል ሆኖ የእነሱን ባህሪ እንዳያበላሽ አሁኑኑ ይፈታ፡፡” ንጉሱ ይህንን በተናገረ በጥቂት ደቂዋዎች ውስጥ ይህ “ስህተተኛ” ታራሚ ነጻ በመውጣት ወደቤቱ እንዲሄድ ተፈቀደለት፡፡

ምንም ስህተት እንደሌለበት የሚያስብ ሰው እንደዚያ በማሰቡ ሌላ ተጨማሪ ስህተት እየሰራ ነው፡፡ ከዚህ የከፋው ደግሞ በስህተቱ መዘዝ ውስጥ ራሱን ሲያገኘው የሰራውን ስህተት ላለማመን የሚታገል ሰው በመሆኑ ነው፡፡ ከዚህኛው ስህተትን ካለማመን ምርጫ የተሻለው መንገድ ለሰራነው ስህተት ሃላፊነት በመውሰድና ይቅርታን በመጠየቅ ወደፊት መገስገስ ነው፡፡

ሁል ጊዜ ስህተትህን ከማመን ይልቅ የክህደትን ምርጫ የምትከተል ከሆንክ ለብዙ ጠንቆች ራስህን ታጋልጣለህ፡፡ ከላይ እንደተጠቀሰው፣ ሃላፊነት ያለመውሰድ ሌላ ስህተት የመስራትህ ሁኔታ አንዱ ነው፡፡ በተጨማሪም ከስህተት ያለመማርና ስህተትን የመደጋገም እንቅፋት ይገጥምሃል፡፡ ይህ ደግሞ ራሱን የቻለ የስሜት እስረኛ ያደርግሃል፡፡ ዛሬ አንድን ያጠፋኸውን ሰው ሰው ይቅርታ ጠይቅና ነጻ ውጣ፡፡

በቅንነት ሼር ያድርጉልኝ!! 👇
http://t.me/Dr_MehretDebebe
የመገደድ ስሜት

ውስጥህ ካለማቋረጥ ይናገርሃል፡፡ ውስጥህን ማድመጥ ግን የአንተ ሃላፊነት ነው፡፡ ስህተት ስትሰራ ህሊናህ እንደሚናገርህና እንዲሁም ሲያምህ፣ ሲርብህና ሲጠማህ አካልህ እንደሚናገርህ ሁሉ ውስጥህ ከሚነግርህ በርካታ ጠቃሚ ነገሮች አንዱ በሰዎች የመገደድን ስሜትህን ነው፡፡

በሰዎች የመገደድን ስሜት ማድመጥ ማለት ከማንነታችን የሚያወጣንን የሰዎች ግፊት መለየት ማለት ነው፡፡ በአካባቢያችን የሚገኙ ሰዎች የማናምንበትን ነገር እንድናደርግ፣ የማንፈልገውን ውሳኔ እንድንወስንና ምቾት ወደማይሰማን የሕይወት ቀጠና ውስጥ እንድንገባ ካለማቋረጥ ግፊት ያደርጉብናል፡፡

አንዳንድ ሰዎች የሚጫኑንና የሚያስገድዱን ለእኛ መልካም የሰሩ እየመሰላቸው ሲሆን፣ ሌሎች ግን እኛን የመቆጣጠር ዝንባሌ ስላላቸው ነው፡፡ በዚህች አለም ላይ ስትኖር ራስህን ከአስገዳጅና ከተቆጣጣሪ ሰዎች ነጻ ማውጣት ከቻልክ የድሎችን ሁሉ ድሎች ተጎናጽፈሃል፡፡ ከዚህ በፊት ብዙ ጊዜህን ካባከንክ በኋላ የባነንክባቸውን ሁኔታዎች መለስ ብለህ ብታጤናቸው በሰዎች ግፊት ምክንያት ካደረካቸው ወይም ከማድረግ ከተቆጠብክባቸው ሁኔታዎች ጋር ተዛምደው ታገኛቸዋለህ፡፡

ከዚህ ሁኔታ ለመዳን ከፈለክ፣ ምንም አሰብክ ምንም ሃሳቡ ከውስጥህ የወጣ ወይም ውስጥህ ያመነበት መሆን አለበት፡፡ ስለዚህም፣ በሰዎች ከመገደድ አዙሪት ነጻ ለመውጣት መውሰድ የምትችላቸው እርምጃዎች አሉ፡፡

1. የሕይወት መመሪያ ይኑርህ
የሕይወትህን መመሪያ በመለየትና በማወቅ ያንን ማዳበርና በዚያ እውቀት መደላደል አስፈላጊ ጉዳይ ነው፡፡ ራስህን ካልመራህ የመጣው ሰውና ገጠመኝ ይመራሃል፡፡ ራስህን ስትመራ ግን ሁሉን የምትመዝን ትሆናለህ፡፡

2. ገደብህን እወቅ
ለሰዎች ብለህ የት ድረስ መሄድ እንዳለብህ ለይተህ እወቅ፡፡ የሰዎችን ሃሳብ ማድመትም ሆነ ለሰዎች ስትል ዋጋ መክፈል ታላቅ ብስለትና ጨዋት የመሆኑ እውነታ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ ያንን ማድረግ ያለብህ ግን በመገደድ ስሜት ሳይሆን ውስጥህ ስላመነበትና ያንን ለማድረግ ስለወሰንክ መሆን አለበት፡፡

3. ለሰዎች ገደብን አብጅላቸው
ያላመንክበትን ነገር ካለምንም የጥፋተኝነት ስሜት እምቢ ማለትን መልመድ መልካም ልማድ ነው፡፡ የሰው ስሜት ላለመጉዳትና ክፉ መስሎ ላለመታየት ለሁሉም ነገር እሺ ማለት ማንነትህን እንደሚሸረሽረውና ዘመንህን በከንቱ እንደሚበላው አትርሳ፡፡

ከፈዘዝክበትና ከደነዘዝክበት ሁኔታ ተነሳና ውጣ! ለማን ሰውና ለምን አይነት ሁኔታ እሺ እንደምትል ለይተህ እወቅ! የራስህ ጉዞ ከሰዎች እጅ አውጣና ወደራስህ እጅ አስገባ!

በቅንነት ሼር ያድርጉልኝ !!
http://t.me/Dr_MehretDebebe
ይቅርታን መጠየቅ ለምን ያስቸግረናል?

ባለፈው ይቅርታን ከመጠየቅ ስለመገኝ ነጻነት “በፖሰትኩት” መሰረት አንዳንዶች ከጠየቋቸው ጥያቄዎች በመነሳት አንድ ምርቃት ልጨምር፡፡

“ይቅርታ ያለፈውን ነገር አይለውጠውም፣ የነገውን ግን የላቀና ያማረ ያደርገዋል” - Paul Boese

በአለም ላይ በጉልበታማነታቸው ከታወቁ የሰው-ለሰው ግንኙነቶች መካከል አንዱ የይቅርታ ኃይል ነው፡፡ ይቅርታ የሚጠይቅ ሰው ያንን ይቅርታ ለመቀበል ፈቃደኛ ከሆነው ሰው ትክክለኛውን ምላሽ ሲያገኝ የሚፈጠረው ኃይል ግለሰቦቹን ብቻ ሳይሆን ሕብረተሰብን የመፈወስ ጉልበት አለው፡፡ ይህም ሆነ አንዳንድ ሰዎች ይቅርታ መጠየቅ ይከብዳቸዋል፡፡ ለምን?

1. ተቀባይነት የማጣት ፍርሃት
አንዳንድ ሰዎች ይቅርታን ሲጠይቁ ያኛው ወገን ጥያቄቸው ባለመቀበል “የሚያሳፍራቸው” ስለሚመስላቸው ከዚያ ተግባር ይገታሉ፡፡ ይህ ብዙ ሰዎች የሚታገሉት ስሜት ነው፡፡ ይህንን የስሜት ጫና ለማለፍ ግን ሃላፊነታችን ላይ ማተኮር አስፈላጊ ነው፡፡ የእኛ ሃላፊነት ላጠፋነው ጥፋት ይቅርታን የመጠየቅ ሃላፊነት እንጂ ሰዎች ይቅርታችንን እንዲቀበሉ የማስገደድ አይደለም፡፡ ትኩረታችንን በእኛ ሃላፊነት ላይ ብቻ ስናደርግ ለይቅርታ የተነሳሳ ልቦና ይኖረናል፡፡

2. የኋላ ኋላ ብቅ የሚል ሰበብን ፍርሃት
“ዛሬ ስህተቴ ነው ብዬ አምኜ የተቀበልኩት ነገር ነገ ማስረጃ ይሆንብኛል” ብለው የሚሰጉ ሰዎች አሉ፡፡ እንደዚህ አይነት ሰዎች ይቅርታን እንዳይጠይቁ እንቅፋት የሚሆንባቸው ስህተታቸውን የማመናቸውን ሁኔታ ተጠቅሞ ሌላኛው ወገን የክስንና የበላይነት ስፍራ ይይዝብኛል ብለው ስለሚሰጉ ነው፡፡ እዚህ ላይ ማስታወስ ያለብን ግን ይቅርታ የገደለውን ስህተት ማንም ሰው እንደገና ሕይወት ሊዘራበት እንደማይችል ነው፡፡ ቢሞክርም እንኳ ብዙም ሳይቆይ ሃሳቡ መሞቱ አይቀርም፡፡

3. ተሸናፊ ሆኖ የመታየት ስጋት
ይቅርታ መጠየቅን እንደደካማነትና እንደተሸናፊነት የሚያዩ ሰዎች ብዙ ናቸው፡፡ ስለዚህም፣ ምንም እንኳ ስህተተኛ እንደሆኑ ቢያውቁትና ሁኔታዎች ሁሉ የሚጠቁሙት ወደ እነርሱ ስህተተኛነት ቢሆንም፣ ሁኔታውን ወጥረው በመያዝ ሸፋፍነው ለማለፍ ይጣጣራሉ፡፡ ይህ የአልሸነፍም ባይነትና እንደተሸናፊ መስሎ የመታየት ፍርሃት ለጉዞአቸው ታላቅ ጠንቅ ነው፡፡

4. ተስፋ መቁረጥ
አንዳንድ ሰዎች ቶሎ ተስፋ ቆራጮች ናቸው፡፡ አንድ ችግር እንደተከሰተ ነገሮች ሁሉ እንዳከተመላቸው የማሰብና በነገሮች ላይ ተስፋ የመቁረጥ ዝንባሌ አላቸው፡፡ ይህ ሁኔታ የሚመጣው፣ ይቅርታ ቢጠየቅም ባይጠየቅም ግንኙነቱን ለማደስ ጊዜው አልፎአል ብሎ ከማሰብ ነው፡፡ አንዳንድ ሰዎች ምንም ያህል ይቅርታ ብንጠይቃቸው እንኳን ነገር ከነከሱ አይለቁምነቀ ተስፋ ሊያስቆርጡን ይችላሉ፡፡ ያም ሆነ ይህ ግን ለይቅርታ እድልን መስጠት ጠቃሚ ነው፡፡

በቅንነት ሼር ያድርጉልኝ!

በቴሌግራም ይቀላቀሉ
http://t.me/Dr_MehretDebebe
የማንነትህ መለኪያ ስኬት አይደለም

“በቅርጫ ኳስ ጨዋታ ዘመኔ 9 ሺህ ኳሶችን ሞክሬ ስቼአለሁ፡፡ 300 ውድድሮችን ተሸንፌአለሁ፡፡ ባስቆጥረው ቡድኔን ለዋንጫ የሚያበቃውን ኳስ እንድወረውር አምነው ሰጥተውኝ ስቼ አውቃለሁ፡፡ በሕይወቴ ደግሜና ደጋግሜ ወድቄአለሁ፡፡ ለዚህ ነው ስኬታማ የሆንኩት” - Michael Jordan

አብዛኛው ሰው ውስጡን የሚነዳው አንድ ጥማት አለው፡፡ ይህ ጥማት የተመሰከረለትና ጥንቅቅ ያለ ስኬታማ ሆኖ ለመታየት ያለው ጥማት ነው፡፡ “እንደዚህ ባደርግ፣ ይህኛውና ያኛው ነገር ቢኖረኝ፣ እዚያኛው ደረጃ ብደርስ ኖሮ … እረካና ሙሉ ስኬት ውስጥ እገባ ነበር” የሚል የውስጥ ጩኸት በብዙ ሰዎች ውስጥ ሲያስተጋባ ይሰማል፡፡ ስለዚህም፣ አንዳንድ ሰዎች ይህንን ጥማት ለማርካት ምንም ነገር ከማድረግና የትኛውንም ድንጋይ ከመፈንቀል አይመለሱም፡፡

የዚህ አመለካት ምንጩ፣ “ሙሉ ማንነት እንዲኖረኝ በኑሮዬ ስኬታማ መሆን አለብኝ” የሚለው አመለካከት ነው፡፡ የዚህ አመለካከትና የሕይወት ዘይቤ ውጤቱ ደግሞ “ስውር” ፍርሃት ነው፡፡ ሙሉ ማንነት እንዲኖረው ስኬታማ መሆን እንዳለበት ያመነ ሰው አለመሳካትን፣ ስህተትንና መውደቅን እጅግ የሚፈራ ሰው ነው፡፡ የሚሰራው ማንኛውም ስራ ስኬታማ የመሆኑና ያለመሆኑ ጉዳይ ከማንነቱ ዋጋ ጋር ምንም አይነት ግንኙነት እንደሌለው ባለማወቁ ምክንያት ለብዙ ስነ-ልቦናዊ ጥቃት ራሱን ያጋልጣል፡፡

የአንድ ሰው ማንነት የሚለካው በተሳካለትና ባልተሳካለት ነገር ከሆነ፣ ለዚያ ሰው ሩጫ ማቆሚያ፣ ለውድድሩም መጨረሻ የለውም፡፡ ይህ አይነቱ የሕይወት ዘይቤና አመለካከት የሚያስከትለው ዋነኛ መዘዝ የመውደቅ ወይም ስኬት የማጣት ፍርሃት ነው፡፡ ከዚህ የተዛባ የማንነት መመዘኛ ቀውስ ለመውጣት በስኬት ላይ ያለንን አመለካከት መቃኘት አስፈላጊ ነው፡፡

1. ስኬት ዘርፈ-ብዙ ነው
ለምሳሌ፣ አንድ ሰው በስራው ወይም በንግዱ አለም የተዋጣለት ሆኖና ያሰበው ደረጃ ደርሶ፣ በማሕበራዊውም ሆነ በቤተሰባዊው ኑሮው የተበላሸ ሁኔታ ውስጥ ራሱን ሊያገኘው ይችላል፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ፣ አካላዊም ሆነ ስሜታዊ ጤንነቱን ችላ ብሎ እውቀትን ወይም ንብረት ሲሰበስብ የሚኖር ሰው በቀኑ መጨረሻ “ስኬታማ ነኝ” ብሎ እንዲናገር የሚያደርገው ነገር ምንድን ነው? ስለዚህም፣ ስኬት የብዙ መሰረታዊና አስፈላጊ እውነታዎች ጥርቅም ነች እንጂ አንድ ገጽታ ብቻ የላትም፡፡

2. ስኬት የሂደት ጉዳይ ነው
ስኬት የአንድ ጊዜ ክስተት ሳይሆን የሂደት ጉዳይ ነው፡፡ ስኬት፣ “አንድ ደረጃ ካልደረስኩ አልረጋጋም” ማለት ሳይሆን ጉዞውን በመጀመራችንና በሂደት ላይ በመሆናችን መርካትና መረጋጋት ማለት ነው፡፡ ዘርፈ-ብዙ የሆነው የስኬት ምስጢር ዘርፈ-ብዙ የሆነ ጥረትና ትጋት ይጠይቃል፡፡ ስኬታማ ሰው በሁሉም አቅጣጫ በአንድ ጊዜ ጥሩ ደረጃ ላይ የደረሰ ሰው ነው ብሎ ማሰብ ከእውነት እንድንርቅ ያደርገናል፡፡

3. ስኬት ተለዋዋጭ ነው
ትናንት ቀለል ያለው ሁኔታ ዛሬ ከበድ ሲል፣ ዛሬ የጨመረው ሁኔታ ነገ ሊቀንስ፣ ዛሬ የተነሳሳውና የጋለው ፍላጎት ነገ ቀዝቀዝ ሊል ይችላል፡፡ እንደ ሁኔታውና እንደ እለቱ ስሜት ጥረቱን የሚቀያይር ሰው እንደዚያው አይነት ውጤትን ያተርፋል፡፡ እንደ እለቱ ሁኔታና ስሜት ሳይሆን ከዓላማው አንጻር የሚሰራ ሰው ደግሞ ከዚያው አንጻር ስኬታማ ይሆናል፡፡ ይህ በፍጹም የማይለወጥ ሕግ ነው፡፡

በቅንነት ሼር ያድርጉልኝ !
http://t.me/Dr_MehretDebebe
የማንነትህ መለኪያ ተቀባይነት አይደለም

“የብዙ ሰዎች ተቀባይነት የማጣት ፍርሃታቸው ምንጩ በሰዎች ለመወደድ ያላቸው ጥማት ነው፡፡ ሰዎች በአንተ ላይ ካላቸው አመለካከት ተነስተህ የማንነትህን ተመን አታውጣ” - Harvey Mackay

የምንኖርባት አለም በእነሱ ተቀባይነትን እንድናገኝ የግድ እነሱን ማስደሰት እንዳለብን ግፊትና ተጽእኖ የሚያሳድሩብን ሰዎች የሞሉበት አለም ነች፡፡ ስለዚህም፣ ሳናስበውም የስሜታችንን ከፍታና ዝቅታ የሚወስነው ሰዎች በእኛ ላይ ያላቸው አመለካከት ስለሚሆን፣ እኛ መኖራችንን እናቆምና የሰዎች አመለካከት በእኛ ውስጥ መኖር ይጀምራል፡፡

ማንነታቸውን በሰዎች ባላቸው ተቀባይነት ላይ የመሰረቱ ሰዎች ያላቸው አመለካከት የሚከተለው ነው፡- “የማንነቴን ዋጋ ለማወቅ ሰዎች እንዲቀበሉኝ የማደርገውን የግል ጥረቴንና በሰዎች ያለኝን ተቀባይነት መደመር ነው” (ጥረት + የሌሎች አመለካከት = ማንነት)፡፡ የዚህ የተዛባ ስሌት ችግር ተቀባይነት የማጣትና የመገፋት ስሜት ነው፡፡ “ሰዎች ስለ እኔ ምን ያስቡ ይሆን? ሰዎች እኔ በሌለሁበት ምን ያወሩ ይሆን? ሰዎች ካልተቀበሉኝ፣ ካልወደዱኝና ካላቀረቡኝ ምን ይውጠኝ ይሆን? ይህኛው ነገርና ያኛው ነገር ቢኖረኝ ኖሮ ልክ እንደ እገሌ ሁሉም ሰው የሚቀበለኝ ሰው እሆን ይሆን? እነሱ የሚያደርጉትን ነገር ባደርግ ይቀበሉኝ ይሆን? ሰዎች የማይቀበሉኝ ማንነቴ ላይ ችግር ስላለብኝ ይሆን? … ” አእምሮ የሚያዞረው ጥያቄ ማለቂያ የለውም፡፡

የሚከተሉትን የተቀባይነት እውነታዎች አትዘንጋቸው፡-

ሁሉም ሰው ሊቀበልህ አይችልም
ከሁሉ በፊት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ልትቀበለው የሚገባህ እውነታ፣ ሁሉም ሰው ካለምንም ቅድመ-ሁኔታ፣ እንዲሁም ሙሉ ለሙሉ ሊቀበልህ የሚችልበት ጊዜ ሊመጣ እንደማይችል ነው፡፡ ይህንን እውነታ አምኖ መቀበል ይህ ነው የማይባልን መረጋጋት በውስጥህ እንደሚፈጥርልህ አትጠራጠር፡፡ በተጨማሪም፣ ይህንን እውነታ አምኖ መቀበል ሰዎች አንተን የመቀበልና ያለመቀበል መብት እንዳላቸውና ያንንም መብት ልትሰጣቸው እንዲሚገባህ አምነህ እንድትቀበል ውስጥህን ያሳምነዋል፡፡

በሚቀበሉህ ላይ አተኩር
ሁሉም ሰው ካለምንም ቅድመ-ሁኔታ ሙሉ ለሙሉ ሊቀበልህ እንደማይችል አምነህ ከተቀበልክ በኋላ በመቀጠል የሚገፉህንና የማቀበሉህን ሰዎች ሁኔታ ተወት በማድረግ የሚቀበሉህና አንተን ማግኘት የሚፈልጉት ላይ ማተኮር ይገባሃል፡፡ የማይፈልጉህንና የሚሸሹህን ስትከታተል የሚፈልጉህንና ለአንተ ግድ የሚላቸውን ሰዎች እንዳታጣ ልታስብበት የሚገባ ጉዳይ ነው፡፡ በማይቀበሉህ ሰዎች ላይ ማተኮር ለድርብ-ክስረት የሚያጋልጥህ ጉዳይ ነው - የሚወዱህን ሰዎች ከማጣትና ከስሜት ቀውስ የሚመጣ ክስረት፡፡

በሰዎች አመለካከት ላይ አትደገፍ
ሰው ተለዋዋጭ ፍጥረት ነው፡፡ አንዳንድ ሰዎች እንዲሁ የወረተኝነትና በአንድ ሃሳብ ያለመጽናት ዝንባሌ እንዳላቸው ጥያቄ የለውም፡፡ አንዳንድ ሰዎች ግን ተለዋዋጭ የሚሆኑት ክፉና ወረተኛ ስለሆኑ ላይሆን ይችላል፡፡ የወቅቱ እውነታ፣ የሚለዋወጠው ሁኔታቸውና እይታቸው፣ እንዲሁም ሌሎች ከቁጥጥራቸው ውጪ የሆኑ ጉዳዮች በላያቸው ላይ ስለሚለዋወጡ እነሱም ከመለወጥ ውጪ ምርጫ እንዳይኖራቸው ይገደዳሉ፡፡ ስለሆነም፣ ዛሬ የደገፈህና አብሮህ የሆነ ሰው ነገ ከአቅሙ በላይ በሆነ ምክንያት ሊለወጥ ስለሚችል ይህንን ሊለወጥ የሚችል የሰው ሁኔታ ተስፋ በማድረግ የማንነትህን ዋጋ ከዚያ ጋር ማያያዝ የስህተት ሁሉ ስህተት ነው፡፡

በቅንነት ሼር ያድርጉልኝ !!
http://t.me/Dr_MehretDebebe
ጭንቀት

አንዳንድ ሰዎች በየምክንያቱ ይጨናነቃሉ፡፡ እንደ እውነቱ ከሆነ ግን አብዛኛዎቹ የምንጨነቅባቸው ነገሮች ቀድሞውኑ መሰረት የሌላቸው ናቸው፡፡ ለምሳሌነት የሚከተለውን የአንድ ጥናት ውጤት እንመልከት፡፡ የምንጨነቅባቸው ነገሮች . . .

>> 40% በፍጹም ለማይደርስብን ነገር ...
>> 30% ምንም ልንለውጠው ስለማንችለው ስላለፈው ነገር ...
>> 12% ሰዎች ስለእኛ ስለሚናገሩብን ፍርድ፣ ወሬና ሃሜት ...
>> 10% ስለጤንነታችን (ስለተጨነቅን የሚብስ) ...
>> 8% ስለእውነተኛ ልናስብበት ስለሚገባ ሁኔታ ...

በፍጹም ለማይደርስብን ነገር …
ያለን አማራጭ ምክንያታዊነትን ማዳበር ነው፡፡ ሁኔታው ሊደርስብንና ላይደርስብን የሚችልበትን የእድል መጠን አመዛዝነን ያለመድረሱ ሁኔታ ካመዘነ፣ መጨናነቅን የማቆምን ሂደት መጀመርና እየተዉ መሄድ የግድ ነው፡፡ አንዳንድ ሰዎች ግን እንዲሁ ምክንያት ፈልገው የመጨነቅ “ሱስ” አለባቸው፡፡ ይህ ዝንባሌ የሚመጣው ለረጅም ጊዜ በአጣብቂኝ ሁኔታ ከማሳለፍና ስሜታችን የጭንቀት ሰለባ ሆኖ ከመክረሙም የተነሳ ሊሆን ይችላል፡፡ ያም ሆነ ይህ ፍጹም የማይደርስ ነገር ተለይቶ ሊታወቅና ከስሜታችን የደም ዝውውር ውስጥ ሊወገድ ይገባዋል፡፡

ምንም ልንለውጠው ስለማንችለው ስላለፈው ነገር …
ያለን አማራጭ ፈጽሞ አንዴ የሆነ ነገር መሆኑንና ምንም ብናደርግ ልንለውጠው እንደማንችል በመቀበል አእምሮን በአዳዲ ነገሮች መሙላት ነው፡፡ ይህን ማድረግ ካልፈለግን ግን እስቲ አንዴ የሆነውንና ያለፈውን ነገር ለመለወጥ የአንድ ወር ጊዜ እንስጠውና የምንችለውን ያህል እንሞክርና ካልቻልን ነገሩን ለመተው ለራሳችን እድል እንስጠው፡፡

ሰዎች ስለእኛ ስለሚናገሩብን ፍርድ፣ ወሬና ሃሜት …
ያለን አማራጭ መቆጣጠር የማንችለውን የሰውን ባህሪይ ለመቆጣጠር ከመጦዝ ይልቅ መቆጣጠር የምንችለውን የራሳችንን በሆነ ባልሆነው የመጨነቅ ዝንባሌ ለመቆጣጠር መስራቱ ይመረጣል፡፡ ሰዎች ስለአንተና በአንተ ላይ የሚሉት ነገር አንተ ካልፈቀድክለት በስተቀር ምንም ሊያደርግህም እንደማይችል አትዘንጋ፡፡ ብትችል ወሬው አንተ ጋር የማይደርስበትን መንገድ ፍጠር፡፡ ካልቻልክ ደግሞ ወሬው ወደ ስሜትህ የማይደርስበትን ጥንካሬ አዳብር፡፡

ስለጤንነታችን (ስለተጨነቅን የሚብስ) …
ያለን አማራጭ ስለጤነታችን የሚያሳስበን ሁኔታ ካለ ያንን ለማስቀረት ወይም ለመቀልበስ የምንችለውን ያህል መሞከር ነው፡፡ ጭንቀታችን ግን “ምናልባት እታመም ይሆን” የሚል ከሆነ፣ ይህ የራስ በራስ ትንበያ እንደሚፈጸም አትጠራጠር፡፡ ጭንቀት በሽታን የመሳብ ባህሪይ አለውና፡፡

ስለእውነተኛ ልናስብበት ስለሚገባ ሁኔታ …
ያለን አማራጭ በቅድሚያ፣ ሁኔታው በትክክልም የሚያሳስብና በቅጡ ካልያዝነውም የሚስጨንቅ ጉዳይ ስለሆነ ማሰባችንና በመጠኑም ቢሆን መጨነቃችን ትክክለኛው መሆኑን አምኖ መቀበል አስፈላጊ ነው፡፡ ሲቀጥል ያሳሰበንን ሁኔታ በምን መልኩ ብንጋፈጠው ልናሸንፈው እንደምንችል በሚገባ ማሰብን ይጠይቃል፡፡ አእምሮን በጭንቀት ከመሙላት ይልቅ ትክክለኛውን ምላሽ በማሰብ መሙላት በብዙ እጥፍ ይመረጣል፡፡ በጉዳዩም ላይ ሰውን ማማከሩም አንዱ መንገድ ነው፡፡

በቅንነት ሼር ያድርጉልኝ !!
http://t.me/Dr_MehretDebebe
ጊዜ …

ህይወት እረቂቅ ምስጢር ናት። አምላክ በጥበቡ በዚህ አለም ላይ ይህችን ምስጢራዊ ህይወት እድሜ በሚባል አነስተኛ የጊዜ ከረጢት አደለን። ይህችንም ከረጢት በውስጧ እድል በተሰኙ ፈርጦች ተሞልታለች።

ከረጢቷ እንዳትሰረቅ ያለ ጊዜዋ አርጅታ ከጥቅም ውጭ እንዳትሆን ፣ ሀላፊነቱን ፈጣሪ ለኛው ነው የሰጠን።

በከረጢትዋ ውስጥ ያሉት ፈርጦች አንድ ባንድ፣ አንዳንዴም ካንድ በላይ ባንዴ እያብለጨለጩ ከባለ ከረጢቱ እጅ ላይ ይወድቃሉ።

ከጊዜ ጋር የተቆራኙ ናቸውና በጊዜ ያልተጠቀምንባቸው የዕድል ፈርጦች ከጊዜው ጋር ላይመለሱ ትዝታቸውን አስታቅፈው ይነጉዳሉ ። ስኬት በትጋትና በስራ የተለወጡ ዕድሎች እንጂ ሌላ ምንም አይደሉም። ድህነት የባከኑ ዕድሎችና ያልተጠቀምንበት ዕድሜ ውጤት ነው እንጂ የአርባ ቀን ዕድል አይደለም።

# ምንጭ :- የተቆለፈበት ቁልፍ በዶ/ር ምህረት ደበበ

በቅንነት ሼር በማድረግ አዳርሱ
Telegram.me//Dr_MehretDebebe
ፈር ቀዳጅ ፋና ወጊ …

"በየትኛውም ስልጣኔ ውስጥ ፈር ቀዳጅና ፋና ወጊ ተብለው ለውጥ ያመጡ ሰዎች: መጀመሪያ ወንጀለኛ፣ ከዚያም አሳሳች ተብለው መፈረጃቸው የተለመደ ነው። በእርግጥም እነዚህ ጥቂት ብርቅዬ ከዋክብት ከሕ/ሰቡ በሠላሳና በአርባ ዓመት ቀድመው ወደፊት የሄዱ ስለሆነ ከሰው አይገጥሙም ። ሠው አንድም ባለበት ስለሚረግጥ፣ አንድም የኋልዮሽ እንሽርት ጨዋታ ላይ ስለሚባትል እነሱን ይፈራቸዋል፤ ስለዚህም ይጠላቸዋል። ምንም እንኳ እንደ እውነት ፀር እና አሳች መሲህ ቢታዩም በሚቀጥለው ትውልድ ግን ሁሌም ብሩህ ከዋክብት ተብለው ይሞገሳሉ። የመታሰቢያ ሐውልትም ይሰራላቸዋል።

"የሚቀጥለው ትውልድ ደግሞ በነሱ ሐውልትና ትምህርት ዙርያ ሲርመሰመስ፤ ሳያስበው ወደኋላ ተንሸራቶ በራሱ ጨለማ ውስጥ ይገባና የራሱን ዘመን ፋና ወጊዎችና እውነት ገላጮች እያሳደደ ዕድሜውን ያቃጥላል። የኛም ህዝብ ከዚህ የተለየ አይደለም። እኔም እንደሚመስለኝ ለእኛም አገር አቅጣጫ ጠቋሚና ፈር ቀዳጅ መሪዎች በዋናነት ያስፈልጋሉ። እነዚህ በአስተሳሰባቸው ብዙኋኑን ከእንቅልፍ ቀስቃሾች፣ የስልጣኔ አድማስ አመላካቾች ከወጡልን ሀብት ብቻ አይደለም ስልጣኔም በምድራችን እንደሀይለኛ ጅረት እንደገና የማይፈስበት ምክንያት የለም። ስለዚህ የት እንጀምር? ካለንበት… መቼ እንጀምር? …አሁን… ማን ይጀምር? … እኔና አንቺ… የት ለመድረስ? …ሰው የደረሰበት ያልደረሰበት… ትልቁና ከባዱ እንዴት እንጀምር ነው?" ብለው ትንሽ ዝም አሉ።

"ሐሳብ አመንጪዎችና ባለራዕዮች ሲጠፉ ሕዝብና አገርም ይጠፋሉ። ሌላው ተከታይ ቴክኒሻን ነው። ሳይንስም ሆነ ቴክኖሎጂ የስልጣኔ ባለሟሎች እንጂ ደራሲዎች አይደሉም። ፈላስፎቹና ባለራዕይ አርቆ ተመልካቾቹ ጋር ነው ቁልፉ ያለው። እነሱ እንድናስብና እንድናይ ያደርጉናል። የግሪክ ፈላስፎች ዛሬም ለማሰብ ዓለምን ይኮረኩራሉ፤ የሬኔሳንስ ዘመኖቹ እነ ዳቪንቺ እና ጉተንበርግ አይናችንን ለመክፈት በሩን ከፍተው ወደዚህ እለፉ ይሉናል። እንዲሁም የሪፎርሜሽኖቹን ሉተርን እና ኤራስመስን መሳዮቹ እምነታችንን እንደገና እንድንመረምር፣ ከልማድም ትብታብ እንድንላቀቅ ይሞግቱናል። እኛም አገር ሰሚ ያጡ እዕምሮአቸው ውጪ እንደሆኑ ተቆጥረው ህብረተሰቡ ያወገዛቸው፣ ታሪካቸው ብቻ ስላልተፃፈ የሌሉ የሚመስለን ብሩህ ከዋክብት ነበሩ። አሁንም እነሱን ያብዛልን። አሉና አቶ ኦላና በረጅሙ ተንፍሰው ያነባበሩትን እግራቸው አቀያየሩ።

® ምህረት ደበበ
#ምንጭ :- "የተቆለፈበት ቁልፍ" ገፅ 81-83

በቅንነት ሼር ያድርጉልኝ
Telegram.me//Dr_MehretDebebe
ከአፍ የወጣ ……..

በቀን ምን ያህል ክፉ ንግግሮችን እንናገር ይሆን ? ምን ያህል መልካም ያልሆኑ ሃሳቦች አዕምሯችንን ሽው ይሉት ይሆን?

መቼም አሁን በተያያዝነው የአኗኗዋር ዘይቤ ……አስተሳሰባችን አነጋገረራችን አስተያየታችን ግራውን መከተሉን ለምዷል። ከራሳችን፤ከቤተሰቦቻችን፤ከጓደኞቻችን ጋር የምንጋጭበት ጊዜ ብዙ ነው።ከህጉ ጋር ከማህበረሰቡ
ጋር ከእምነቱ ጋር የምንላተምበት አጋጣሚዎች ጥቂት የሚባሉ አይደሉም ። አኗኗራችን አስተሳሰባችንን ጠምዝዞት የተጣመመ ባህሪያችንን እንዳንመለከተው አድርጎናል።

መልካም ንግግር ከዘመናዊነት የራቀ ባህሪ እየመሰለን ቃላቶቻችን ቅርፃቸውን ለውጠዋል ።ይህንን ሁሉ ያስባለኝ፤ ስለክፉ ንግግር የተፃፈች አንዲት ድንቅ ታሪክ አስታውሼ ነው……! እነሆ አንድ አባት አንድ ትዕግስት የጎደለው ወጣት ልጅ ነበረው። ይህ ወጣት በትንሹም በትልቁም ቱግ እያለ ሰዎችን ያስቀይም ነበር።

ከአንደበቱ ክፉ ቃላቶችን ስለሚያወጣ ከሰው ጋር
መስማማት አልቻለም ። ትዕግስት ፈፅሞ የለውም።ይህ ነገር እጅግ ያሳሰበው አባት ልጁን የሚለውጥበት ዘዴ ሲያወጣ ሲያወርድ ቆይቶ አንድ መፍትሄ ላይ ደረሰ። አንድ ቀንም በቀረጢት ሙሉ ሚስማር ያዘና ልጁን አስጠርቶ እንዲህ አለው “ልጄ ሆይ … ይህን በቀረጢት ያለውን ሚስማር ተቀበለኝ ሁሌም ትዕግስት በጎደለህ ጊዜ እና ሰው ባስቀየምክ ቁጥር አንድ ሚስማር የእንጨቱ አጥር ላይ ሰካ” አለው።

ልጁ ምንም ግራ ቢገባውም አባቱ እንዳዘዘው ማድረግ ጀመረ ። በመጀመሪያ ሰሞን በጣም ብዙ ሚስማሮችን ሰካ …. ቀስ እያለ ግን በቀን እንጨቱ ላይ የሚሰካቸው ሚስማሮች ቁጥር እየቀነሰ መጣ…. እያለ… እያለ በመጨረሻ ምንም ክፉ ያልተናገረ ቀን አንድም ሚስማር ሳይሰካ ዋለ። ልጁ በጣም ታጋሽ ሆኖ ባህሪው ተስተካከለ ማለት ነው። ይህንንም ለአባቱ አበሰረ አባትየውም “ እሰይ ልጄ …… አሁን ደግሞ ምንም ያልተናደድክ ቀን እና ክፉ ያልወጣህ ቀን በፊት ከሰካሃቸው ሚስማሮች ውስጥ አንዱን ንቀል” አሉት።

ልጁ እንደተባለው አደረገ ከቀናት በኋላ ሁሉንም ሚስማሮች ነቅሎ ጨረሰ ወደ አባቱም ሄዶ ሚስማሮችን አስረከበ። አባትየውም አንዲህ አለው “አየህ ልጄ አሁን የሰካሃቸውን ሚስማሮች ነቅለህ ጨርሰሃል። በጣም ታጋሽ ሆነሃል ማለት ነው ነገር ግን እስቲ አጥሩን ተመለክት ፈጽሞ እንደ ድሮው ሊሆን አይችልም፤ ሚስማሩ ቢወጣም ተበሳስቷል። ክፉ ንግግርም ልክ እንደ ሚስማር ነው ሺህ ጊዜ ይቅር ብትልም እንደሚስማሩ ጠባሳ ጥሎ ያልፋል ።እናም ልጄ በህይወት ትዕግስት ይኑርህ አንደበትህን ቆጥብ” ብሎ አስተማረው።
~
አንደበት ይገራል አንደበትን የሚገራው መልካም አስተሳሰብ ነው። በክፉ ንግግር ፤ በጭቅጭቅ በስድብ እስከዛሬ ምን
መልካም ነገሮች ሲፈጠሩ አየን? ስህተቶቻችን እየጎለጎልን
በመነካከስ ምን ልዩነቶችን አጠበብን?
~

”ቃላት” ለሰው ልጅ የኑሮ የእስትንፋስ ያህል ዋጋ አለው በቃላት ጦርነት ይነሳል በቃላት ሰላም ይሰፍናል.. እስቲ ለጥቂት ቀናት እራሳችንን እንፈትነው- መልካም መልካሙን በመናገር!!

መልካም እናስብ መልካም እናድርግ መልካም እንሁን!

ከዶ/ር ምህረት ደበበ
በቅንነት ሼር በማድረግ አዳርሱ
http://Telegram.me//Dr_MehretDebebe
ሰላም ! ውድ የቴሌግራም ቤተሰቦቼ በሙሉ በያላችሁበት ሁሉ ሰላምታዬ ይድረሳችሁ ውድ የሀገሬ ልጆች በሀገር ከሀገር ውጪ ለምትኖሩ የዚህ ቻናል ታዳሚዎች አንባቢዎች በሙሉ ሰላም ብያለሁ ። ምህረት ደበበ

በቅርብ የተለያዩ የስነ ልቦና እና የስነ እምዕሮ ምክሮች ፁሁፎችን አጫጭር ኮርሶችን መልዕክቶችን እያስተላለፍክ እገኛለሁ ። ይበልጥ ከዚህም በተጨማሪ ጠቃሚ መልዕክቶች በተከታታይ ሰለማቀርብ የቴሌግራም ቻናሌ ቤተሰቦች ተከታታዮች አንባቢዎች አድማጭ ለመጨመር ግዴታ ሰለሆነ ሁላችንም ሰዎች ወደ ቻናሌ እንዲቀላቀሉ ወዳጆ ሼር በማድረግ እንዲያስተላልፉልኝ በአክብሮት በታላቅ ፍቅር እጠይቃለሁ ።

በቅንነት የቴሌግራም ቻናሌ ለወዳጆ ሼር በማድረግ እንዲቀላቀሉ ከእርሶ የሚጠበቀው የቻናሉ ሊንኩ ለወዳጆ ያስተላልፉ ።

https://t.me/joinchat/AAAAAFdeqyIP5yap-9dXPQ

ከ 3 ሺ አባል ወስጥ አንድ ሰው ቢያንስ ለ100 ሰው ቻናሉ እንዲቀላቀል በማድረግ የበኩል መልካም ስራ እንዲያደርግልን በአክብሮት እጠይቃለሁ ። ለቻናል ባለቤቶችም በቻናላችሁም ሼር በማድረግ እንዲያግዙን እጠይቃለሁ ።

http://Telegram.me//Dr_MehretDebebe
http://Telegram.me//Dr_MehretDebebe
ድህነት እና አስተሳሰብ ያላቸው ትስስር ምን ይመስላል ?

ምን መሰለህ? አንዴ አስተሳሰብ ድህነትን ከፈጠረ በኋላ ድህነት ደግሞ አስተሳሰብን እየወለደ ይቀጥላል፡፡ ከዛ በኋላ መውጫ ቢስ አዙሪት ይፈጠራል፡፡ አሁን መጀመሪያ የቱ መጣ የሚለውን ነገር ስታስብ የዶሮ እና እንቁላል ይመስላል ነገሩ፡፡ ግን እኔ ዝም ብዬ ሳስበው መጀመሪያ ሰው ሁሉ ደሀ ነበረ ወይስ ሰው ሁሉ ሀብታም ነበረ?

የሚለውን ጥያቄ ወደ ኋለ ሄደን ላንመልሰው እንችላለን፡፡ በአጠቃላይ ሰው ሁሉ ሀብታም ነበረ ባንል እንኳ ሰው ሁሉ ደሀ እንዳልነበረ መናገር ይቻላል፡፡ ከዛ የሚመጣው ምንድን ነው? ሁለት ሰዎች የአስተሳሰብ እና ቁሳዊ ሀብት ደሀ ቢሆኑ፤ ለአንዱ አስተሳሰቡን ብትቀይርለት ለአንዱ ደግሞ ጎደለኝ የሚለውን ቁስ ብትቀይርለት እና ከአምስት አመት በኋላ ብትመጣ ምንድን ነው የምታገኘው? ጥናቶች የሚያሳዩት ምንድን ነው? በሚሊዮን ዶላር የሚቆጠር ሎተሪ የደረሳቸው ሰዎች ከሁለት አመት በኋላ ስትመለከታቸው ከ90 % በላይ የሚሆኑት የበለጠ ደሀ ሆነው ታገኛቸዋህ፡፡

በብሩ የተነሳ ግማሹ ይጣላል፣ ግማሹ ይፋታል፤ ቀውስ ውስጥ ይገባሉ፤ የነበራቸውን እንኳ ያጣሉ፡፡
ሌላ ሌላ ዐይነት ድኅነት ውስጥም ይገባሉ ማለት ነው?
በትክክል፣ እነኚህ ድኅነቴን አመልጥባቸዋለሁ የምትላቸው ነገሮች ድህነትህን ሊገልጡብህ፣ ሊያባብሱብህ ይችላሉ፡፡ ሰዎች ይህንን ድህነታዊ የሆነ የእጥረት አስተሳሰብ ስትቀይርላቸው በቀላሉ ሕይወታቸው ሊቀየር ይችላል፡፡ በነገራችን ላይ ደሀ ብለን ስናስብ ልብሱ የተቀዳደደ፣ የሚበላው ያጣ ምናምን ብቻ ልንል እንችላለን፡፡ ግን በጣም ቤተ መንግስት የሚመስል ቤት የሚኖሩ፣ ሜርሴዲስ መኪና የሚነዱ፣ በቁሳዊ ሀብት እጅግ በጣም የበለፀጉ ደሀ ሰዎች ሊኖሩ ይችላሉ፡፡

ከልጆቻቸው ከጎረቤቶቻቸው ከሕይወት ጋር የሚኖራቸው ግንኙነት፣ ለራሳቸው የሚሰማቸው ስሜት ለመኖር እንኳን በብዙ አደንዛዥ እፅ ተሸፋፍነው ነው፡፡ እሱ ድህነት አይደለም ወይ? ደግሞ በጣም ውስን ሀብት ኖሯቸው በአንፃሩ በጣም የበለፀገ ሕይወት የሚኖሩ ሰዎች አሉ፡፡

በአጠቃላይ ግን ድህነት በአስተሳሰብ ላይ ተፅዕኖ የለውም ወይ? የምንል ከሆነ መልሱ “አለው” ነው፡፡ ልጆችህን ጥሩ ጥሩ ትምህርት ቤት መላክ አትችልም፤ ለብዙ ጥሩ ጥሩ ነገሮች ላትጋለጥ ትችላለህ፡፡ ድህነት በሰው ልጅ ላይ ውስንነት ይፈጥራል፡፡ ነገር ግን ድህነት በሰው ላይ ከሚፈጥረው ውስንነት ይልቅ አስተሳሰብ በሰው ላይ የሚፈጥረው ውስንነት ይበልጣል፡፡

ሁኔታዬ አስተሳሰቤን ሊለውጠው ቢችልም አስተሳሰቤ ግን ሁኔታዬን ይበልጥ ሊለውጠው ይችላል ስለዚህ መንገዱ ሁለትዮሽ ነው ፡፡ ድህነት አስተሳሰብን ሊለውጥ አስተሳሰብም ድህነትን ሊለውጥ ይችላል፡፡ ስለዚህ አንዱን ልትለውጥልኝ የምትችል ከሆነ ሁኔታዬን ከምትለውጥልኝ ይልቅ አስተሳሰቤን ብትለውጥልኝ እመርጣለሁ ፡፡
ይሄ ምርጫ ከመጽሐፍ ቅዱሱ ጠቢቡ ሰለሞን ልመና ጋር የሚመሳሰል መስለኛል ፡፡

አዎ እንደውም እሱ “ጥበብ አይነተኛ ነገር ነው” ይላል ጥበብ የበላይ የሆነ ነገር ነው፡፡ የትኛውንም ነገር በጥበብ ልትለውጥ ትችላለህ፡፡ ወደ ሌላ ርዕሰ ጉዳይ ልውሰድህና የአእምሮና አካል ትስስር (Mind-Body Connection) እስከምን ድረስ ነው? በተለይ ጤናማ ከመሆንና ጤናማ ካለመሆን ጋር በተያያዘ ፡፡ አንዳንድ መጽሐፍት የበሽታና ህመም ምንጩ በሙሉ አእምሮአችን ነው” ይላሉ፡፡

እንደውም አንድ ቅርብ ጊዜ ያነበብኩት “Emotions Buried Alive Never Die” የሚል መጽሐፍ ላይ “መሰረታዊው የህመም ምክንያት ያለ ቅድመ ሁኔታ ማፍቀር አለመቻል ወይም በቅድመ ሁኔታ ማፍቀር ነው” ይላል፡፡ አንተ እንዴት ትመለከተዋለህ? አንድን እውነት ለማስተላለፍ ሌሎች እውነቶችን በሙሉ መግደል የለበትም፡፡

አእምሮአችን ወይም አስተሳሰባችን በጤናችን ላይ ትልቅ ተፅዕኖ አለው ፡፡ እሱ ምንም ጥያቄ የለውም፡፡ ሰውነታችንም ግን በአስተሳሰባችን ላይ እኩል ተፅዕኖ አለው ፡፡ አሁን ለምሳሌ በጠኔ ውስጥ ሆኜ፣ በጣም ተርቤ ሁሉ ነገሬ ደህና ሆኖ፣ ዶክትሬት ድግሪ ኖሮኝ ለሶስት ቀን ምግብ ባልበላ ዶክትሬት ድግሪ እንዳለው ሰው ማሰብ አልችልም፡፡

ከዛ በኋላ ምግብ እስከማገኝ ድረስ ያ ሁሉ እኔነቴ ዋጋ ላይኖረው ይችላል ፡፡ ለምርምር ወደ አርባምንጭ ሄጄ ወባ ቢይዘኝ ወባ የአስተሳሰብ ውጤት አይደለም የፍቅር እጦትም አይደለም ፡፡ ፕላዝሞዲየም የሚባለው የወባ ተውሳክ ገብቶ ቀይ የደም ሴሎችን ድምጥማጥ ያጠፋል፤ እንደ ወባው አይነት ራስን እስከ መሳትም ሊደረስ ይችላል፡፡ ሰውነቴ በትክክል እስካልተያዘ ድረስ አስተሳሰቤ ሰማይ የነካ ቢሆንም ምንም ለውጥ የለውም ፡፡

ስለዚህ ምግብ፣ እረፍት፣ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ፣ ጤነኛ የሆነ አከባቢ ውስጥ መኖር መሰረታዊ ነገሮች ናቸው፡፡ አሁን ይሄ ኮምፒውተር ቻርጅ ካላደረከው ምን ይጠቅምሀል? ከልክ በላይም ሆነ ከልክ በታች ቻርጅ ብታደርገው አገልግሎት አይሰጥም ፡፡ ስለዚህ ሚዛኑ ምንድን ነው? ሁሉ ነገር በፍቅር አይደለም፡፡

በፍቅር ተጥለቅልቀህም ሶስት ቀን ካልተኛህ ታብዳለህ፡፡ ስለዚህ የሰውነታቸው ጤንነት ወሳኝ ነው ለአስተሳሰብም ጭምር፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ሰውነታችን ሁሉ ነገር ተሟልቶለት ውጥረት ውስጥ ብንሆን፣ አስተሳሰባችን ልክ ባይሆን ሰውነታችን ላይ ችግር ይፈጥራል፡፡

ለምሳሌ፣ “ዲፕሬሽን” ውስጥ፣ ውጥረት ውስጥ ያለ ሰው የሚያመነጨው ሆርሞን አጥንት ላይ ጉዳት ያደርሳል፣ በሽታ የመከላከል አቅምን ይቀንሳል፣ ለተለያየ አይነት “ኢንፌክሽን” አጋልጦ ይሰጣል፡፡ አእምሮአችንም አካላችን ላይ ቀጥተኛ ተፅዕኖ ያሳድራል፡፡ “ሳይኮኢሚዮኖሎጂ” አሁን በጣም አስደናቂ የምርምር ዘርፍ ሆኗል፡፡

ጤንነታችን በስነ-ልቦናዊ ሁኔታችን በእጅጉ ይወሰናል፡፡ ለምሳሌ፣ የፈተና ሰሞን ለምንድን ነው ጉንፋን የሚበዛው? ፈታና ውጥረት ነው ፡፡ ውጥረት ደግሞ በሽታ የመከላከል አቅምን ይቀንሳል ሁልጊዜ የፈተና ሰሞን ጉንፋን የሚይዛቸው የሚታመሙ ሰዎች አሉ ፡፡ በጥቅሉ አእምሮአችን የአካላችንን ጤንነት ይወስናል፤ አካላችንም የአእምሮአችንን ጤንነት ሊወስን ይችላል፡፡

ሲግመንድ ፍሮይድ የሕይወት ግብ ደስታ ነው” ይላል በዚህ ብዙ ሰዎችም ይስማማሉ ብዬ አስባለሁ ከዚህ አኳያ ደስታ አስተሳሰብ እና ጤና ያላቸው ትስስር ምን ይመስላል ቀደም ሲል ስለ “ዲፕሬሽን” አንስቻለሁ “ዲፕሬሽ” ሀዘን ነው፡፡ “ዲፕሬሽን” ውጥረት የሚያመነጩዋቸው ሆርሞኖች ፀረ ጤና ናቸው ፡፡ ለረጅም ጊዜ ሰውነታችን ውስጥ ሲቆዩ ስኳር፣ ደም ግፊት፣ ውፍረት፣ የአጥንት መሳሳት ወዘተ ያስከትላሉ፡፡ በአንፃሩ ደስታ ውስጥ ስንሆን አንጎላችን የሚያመነጫቸው ሆርሞኖች የዛ ተቃራኒ ውጤት አላቸው፡፡

ለምሳሌ፣ በጣም በምንስቅበት ወቅት የሚመነጩት ኢንዶርፊን፣ ኢንካታሊንስ የሚባሉ ሆርሞኖች ከሄሮይን እና ከኮይን በጣም በብዙ እጥፍ ጠንካራ የሆኑ ሰውን የማስደሰት እና ሀይል የመስጠት አቅም ያላቸው ሆርሞኖች ናቸው፡፡ ለዚህ ነው ከሳቅን በኋላ ሰውነታችን እፅ የወሰደ ያህል የሚፍታታው፡፡ ለዚህ ነው ለሚያስቁን ሰዎች ገንዘብ የምንከፍለው፡፡ ኮሜዲያኖች በጣም ሀብታሞች ናቸው፡፡

ደስተኛ ሰዎች ረጅም እድሜ ይኖራሉ፤ ደስተኛ ሰዎች ለሰውም ረጅም እድሜ ይሰጣሉ፡፡ ሌላው የደስታ ጥቅም ምንድን ነው? በደስታ ውስጥ ስንሆን በከፍተኛ ሁኔታ የማሰብ እና የመፍጠር አቅማችን ይጨምራል፡፡ በተቃራኒው ሀዘን፣ ብስጭት፣ ውጥረት ውስጥ ስንሆን ቀደም ሲል የዘረዘርናቸው የማሰብ፣ የመፍጠር ወዘተ የአእምሮ ስራዎች በሙሉ እስራት ው
ስጥ ይገባሉ፡፡

ሶማሌ ክልል ውስጥ ቢወጣ ኢትዮጵያን ሊጠቅም የሚችል ሀብት ምንድን ነው? ብለህ ስትጠይቅ እሰማለሁ በትክክል ካስታወስኩ መጽሐፍህ ውስጥም ይህንን ሀሳብ አንስተሀል እሰኪ ስለዚህ ሀብት ንገረን አዎ ! ብዙ ጊዜ በተለይ ስልጠና ስሰጥ “ሶማሌ ክልል ውስጥ ቢወጣ ኢትዮጵያን ሊጠቅም የሚችል ትልቅ ሀብት ምንድን ነው ?” ብዬ እጠይቃለሁ ሰዎች “ነዳጅ ነው” ይላሉ እኔ ደግሞ አልስማማም፡፡

ነዳጅ ቢወጣ ልንባላ ሁሉ እንችላለን፡፡ ሀገራዊ አልሆነም፡፡ ሶማሌ ክልል ውስጥ የሚገኘው ትልቁ ሀብት የሶማሌ ህዝብ ነው፡፡ የሶማሌዎች ጭንቅላት ነው ትልቁ ሀብት፡፡ በነገራችን ላይ ትግራይ ውስጥም፣ ጉራጌ ውስጥም፣ ኮንሶ ውስጥም፣ ሁሉም ቦታ ተመሳሳይ ነው፡፡

በየትኛውም አከባቢ ትልቁ ሀብት የዛ አከባቢ ህዝብ አእምሮ ነው ያልተቆፈረ ድንግል መሬት አለን ይባላል አእምሮአችንስ ምን ሰርቶ ያውቃል ? ገና ምንም አልተነካም እኮ የትም ብንሄድ መሬት ውስጥ ያለው ሳይሆን ሰው ጭንቅላት ውስጥ ያለው ነገር ነው ትልቁ ሀብት ፡፡ እሱን ትተን መሬት ውስጥ ያለው ሀብት ላይ ብናተኩር መልሚያችን ሳይሆን መጥፊያችን ሁሉ ሊሆን ይችላል ፡፡

በቅንነት ሌሎችም ሼር ያድርጉልኝ!!
http://t.me//Dr_MehretDebebe
መራራ እውነታዎች

ምንም ነገር ለዘላም አይቆይም ፡፡ ችግሮችህ፣ የከበቡህ ሰዎች ስራህ ትዳርህና ግንኙነቶችህ ሁሉ ለጊዜዉ ነዉ፡፡ የሁሉም ነገር ፍፃሜ የሆነ ቀን ላይ ሲሆን ታየዋለህ፡፡ በህይወቴ ሁሉ አብረዉኝ ይኖራሉ ያልካቸዉ ነገሮች እንኳን ሳይቀሩ ሲፈረካከሹ ታያቸዋለህ

ለሁሉም ነገር ተራ አለዉ፡፡ ሰዉን ብትጠቅም ጊዜዉን ጠብቆ አምላክህ ይከፍልሃል፡፡ ብትጎዳም እንዲሁ...በሰፈርከዉ ማንነት ጊዜዉ ሲደርስ ትሰፈራለህ

ማንም ሰዉ ስላንተ አይጨነቅም ፡፡ 20% ፐርሰንቱ ብቻ ስላንተ ሲጨነቁ እነሱም የቅርብ ጓደኞችህና ቤተሰቦችህ መሆናቸዉን አትዘንጋ) 80 ፐርሰንቱ ግን ኑር አትኑር አንዳች ቅንጣት ስላንተ አያስቡም፡፡ ችግሮችህን ለነዚህ ለ 80% ፐርሰንት መናገር እራስህን ማባከን ነዉ ምክንያቱም ችግርህ ለነሱ ምናቸዉም አይደለምና! የራሳቸዉ ጉዳይ ብቻ ያሳስባቸዋልና ቆጠብ በል

ሰዎች በህይወትህ ይመጣሉ ደግሞም ይሄዳሉ፡፡ አንድ ቀን ለብቻህ ሰዉ በሌለበት ልትሞት ትችላለህና ሰዎችን አትደገፍ

ከ5-6 የልብ የምትላቸዉ ሰዎች በቀር ፌስቡክ ላይ ያሉት የጓደኛ ጋጋታ ምንም አይጠቅሙህም፡፡ ብትሞት እንኳ ቀብርህ ላይ የማይመጡ ብዙዎች መሆናቸዉን እወቅ

የስራ አለቃህ እንድታድግና የተሻለ ቦታ እንድትይዝ ሊመኝ ይችላል ግን መቼም እንድትበልጠዉ አይፈልግም፡፡ ምንም ሽልማትና ጭብጨባ ቢበዛልህ ከሱ እንደምትበልጥ ካሰበ አንተን ለመገፍተር ወደ ኋላ አይልም ።

98 % ፐርሰንቱ ሰዉ መቼ እንደተወለድክ እንኳን አያዉቅም 2 % ፐርሰንቱ መቼም እነማን እንደሆኑ መገመት አያቅትህም ፡፡ ካላመንከኝ ሞክረህ እየዉ!

የዉሸት ጓደኞችህ የተሻለ ህይወት እንድትመራ በፍጹም አይፈልጉም ፡፡ ነገሮች መልካም ሲሆኑ የሚሰበሰቡ ሰዎች ሊያስገርምህ አይገባም አንድ ቀን ህልምህ 'ወለም' ብሎ ካዩ እጃቸዉን ቀስረዉ ይስቁብሃል፡፡ የዛኔ ያልሳቁብህን የልብ ጓደኞችህ አድርጋቸዉ

ገንዘብ ያለዉና ፀዳ ብሎ የሚመላስን ሰዉ ብዙዎች ሲያከብሩት ትመለከታለህ ፡፡ የማያዉቅህ እንኳን ቢሆን ፀዳ ካልክበት ሊያከብርህ ሲዳዳዉ ታየዋለህ

ለሰዎች ምክር መስጠት በጣም ቀላል ነዉ ነገር ግን ምክርን ወደተግባር መቀየር ከባዱና አስቸጋሪዉ ነገር ነዉ፡፡ አንዳንዴ ሰዉን ካለበት ማጥ ለማዉጣት ካሰብክ ከምክር በላይ የሆነ ስብዕና ሊኖርህ ይገባል፡፡

አንድ ዉሸታም ጓደኛህ ከ 100 ጠላትህ ጋር እኩል ጥፋት ያደርሳል፡፡ ጠላቶችህን ተከታተላቸዉ ጓደኞችህን ደግሞ በጣም ተከታተላቸዉ

ነገሮች መልካም እንዲሆኑና እንዲሳኩ ያለ የሌለ ጥረትህን አድርገህ ሳይሳካልህ ቀርቶ ይሆናል፡፡ ይሄ ያንተ ደካማነት ሳይሆን ህይወት እንዲህ አይነት ገፅታም ስላላት ነገሩን ተቀበለዉ፡፡

ለመወደድ ልዩ ሰዉና ሁሉንም ሞካሪ መሆን አይጠበቅህም ፡፡ እንዳንዴ ሰዉ ሁሉ ባይወድህ እንኳን ይሄ ምንም ማለት እንዳልሆነ ተረዳ ፡፡ በሰዎች መጠላትንም ቀለል አድርገህ ዉሰደዉ ምክንያቱም እንዴት እራስህን ማሳደግ እንዳለብህ ማጤን ወሳኙ ነገር ሲሆን የሰዎችን ስሜት እያዳመጥክ ከፍና ዝቅ እያልክ መኖር አይጠበቅብህም፡፡

የራስህ አስተሳስብ ይኖርሃል ፡፡ ሌሎችም እንዲሁ...ሰዎች በሀሳብህ አለመስማማታቸዉ አንተነትህ ላይ የሚያመጣዉ ነገር የለም ፡፡ ሃሳብህን ለማሳመን የሰዎችን አስተሳሰብ ረጋግጠህ አትዉጣ፡፡ የሰዎችን ሃሳብ አክብር ሰዎችም ሃሳብህን እንዲያከብሩ አድርግ

ይቺ አለም የምትፈልግህ ጠቃሚ ነገር አንተ ጋር እንዳለ ስታምን ብቻ ነዉ፡፡ ባጠቃላይ አለም እራስ ወዳድ ናት

ሰዎች ስለ ደስታ አጋነዉ ሲያወሩ ትሰማ ይሆናል፡፡ በኣጭሩ ደስታ ማለት ስሜትህ ሳይሆን አእምሮህ ያለበት ሁኔታ ነዉ፡፡ ደስተኛ ሆነህ በሰዎች ልትጎዳ ትችላለህ፡፡

ህይወት እኩል አይደለችም ፡፡ በሆነ ነገር ጎበዝ ብትሆን ካንተ የበለጠ በጣም ጎበዝ ሰዉ አለ...እኩልነት ዉሸት ነዉ፡ ስለዚህ በመኖርህ ብቻ ተደሰት ፡፡

በቅንነት ያንብቡ ዘንድ #SHARE ሼር ያድርጉልኝ

የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ
http://t.me//Dr_MehretDebebe
መብራቱን አብራው!

አንድ ጊዜ በጎንደር ከተማ አንድን ስልጠና ለመስጠት በነበርኩበት ጊዜ የተከሰተ የግል ልምምዴን ላካፍላችሁ፡፡ ያረፍኩበት ሆቴል ከፍ ያለ ኮረብታ ላይ ስለነበረና አካባቢው በዛፎች በመከበቡ ምክንያት የራሱ ውበት ስላለው በዚያ ማረፍን እመርጣለሁ፡፡ በዚያ ባደርኩበት አንድ ሌሊት ግን አንድ ነገር ተከሰተ፡፡

ሌሊት ነቅቼ ወደ መታጠቢያ ቤት መሄድ ስላስፈለገኝ ከአልጋዬ ለመውጣት ተንቀሳቀስኩኝ፡፡ ከውጪ በመስኮት በኩል በመጋረጃው ሾልኮ የሚገባው ደብዛዛ ብርሃን ለእንቅስቃሴዬ በቂ ስለነበር ልክ ከአልጋዬ ስወርድ ወደ መታጠቢያ ቤቱ በሚወስደው አቅጣጫ አንድ “እባብ” ተጋድሞ አየሁኝ፡፡ ከብርሃኑ ደካማነት የተነሳ ይህንን “እባብ” ቅርጹን እንጂ መልኩንና ሁኔታውን መለየት አልቻልኩም፡፡ በጣም ደነገጥኩ፣ በጣምም ፈራሁ፡፡

ወደኋላዬ በመሰብሰብ ሁለንተናዬን ትራሴ ላይ አገኘሁት፡፡ ብዙ አሰብኩኝ፡፡ ብዙ አወጣሁኝ፣ አወረድኩኝ፡፡ ትንሽ ጊዜ ካቃጠልኩኝ በኋላ፣ በመጨረሻ ያለኝ ብቸኛ አማራጭ እንደምንም የእባቡን ክልል አለፌ መብራቱን ማብራት ነው፡፡ ትንሽ ከወላወልኩኝ በኋላ የፈጣሪዬን ስም እየጠራሁ፣ ጨለማውን ለማሸነፍ አይኖቼን አፍጥጬ፣ ጥግ ጥጉን ተራምጄ መብራቱን ልክ ሳበራው ለካ ያየሁት “እባብ” ማታ በድካም ስሜት ወደ አልጋ ስቸኩል የጣልኩት ቀበቶዬ ነበር፡፡

በዚህ ገጠመኜ የገባኝ ነገር ይህ ቀበቶ እባብ መስሎኝ በነበረበት ሰዓት፣ ልክ እውነተኛ እባብን ብጋፈጥ የሚሰማኝን የፍርሃት ስሜት ነው የሰጠኝ፡፡ ከዚህ ስሜት የተነሳ ልጮህ እችል ነበር፣ እዚያው አልጋዬ ላይ ሆኜ እስከሚነጋ አፍጥጬ ልጠብቅ እችል ነበር፣ ሰዎች ጋር ስልክ በመደወል ልበጠብጥ እችል ነበር . . .፡፡ በፍርሃት ተወጥሮና ታስሮ የነበረውን ማንነቴን ነጻ ያወጣው እውነቱን ለማወቅ መብራቱን ማብራቴ ነው፡፡

ለካ እይታ የእውነታን ያህል ጉልበት አለው፡፡ በሕይወታችን አንድ ነገር ባይኖርም እንኳን፣ እንዳለ ከቆጠርነውና ከፈራን ማንነታችንን አስሮ ሊያስቀምጠን እንደሚችል በሚገባ የተገነዘብኩት ያን ጊዜ ነው፡፡ መድሃኒቱ መብራቱን ማብራት ነበር፡፡

አንዳንድ ሰዎች ገና ለገና ሆኖብኛል . . . ሳይሆንብኝ አይቀርም . . . አለብኝ . . . ሳይኖብኝ አይቀርም . . . ሊሆን ነው . . . መሆኑ አይቀርም ከሚሉት ምክንያት-የለሽ ፍርሃት የተነሳ ታስረው አመታት ያሳልፋሉ፡፡ ይህ ፍርሃት፣ እምቅ ብቃታቸውን አፍኖ፣ ነጻነታቸውን ነፍጎ፣ የሌለውን ችግር እንዳለ አድርጎ፣ ያለውን ችግር ደግሞ እጅግ አግዝፎ በማሳየት ከሰው በታች ያደርጋቸዋል፡፡

መፍትሄው መብራቱን ማብራት ነው!!! መብራቱን ማብራት ማለት እውነታውን ለመጋፈጥ አይንን መግለጥ፣ ስለሁኔታችን ከበሰለ ሰው ጋር መወያየት፣ ምንም ነገር ቢሆን በፍርሃት ታስሮ ከመኖር እውነታውን ተጋፍጦ በነጻነት መኖር እንደሚመረጥ መገንዘብ ማለት ነው፡፡ አይህንን አትርሳ፣ መፍራት እስከምታቆም ድረስ መኖር አትጀምርም!

የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ
http://t.me//Dr_MehretDebebe