የአፍሪካ አካዳሚ أكاديمية أفريقيا
6.38K subscribers
179 photos
30 videos
9 files
102 links
አፍሪካ ኦንላይን መድረክ ነፃ የሸሪዓ ትምህርት ማስተማሪያ

ለበለጠ መረጃ የአካዳሚውን ተቆጣጣሪ ያነጋግሩ: @ethio_africaacademy
Download Telegram
አሰላሙ አለይኩም ወረህመቱላሂ ወበረካቱህ ውድና የተከበራቹህ የላይኛው ሂዝብ ፕሮግራም ተካፋይ ተማሪዎቻችን ለማጠቃለያ ፈተናው የተሰጠው ጋዜ ማለቁ ይታወቃል።

ነገር ግን አንዳንዶቻችሁ ያጋጠማችሁን ችግር ታሳቢ በማድረግ ለተጨማሪ አንድ ቀን አራዝመነዋል።በተከታዩ ሊንክ ገብተው ይፈተኑ።

https://am.africaacademy.com/course/view.php?id=231

አላህ እውቀት ፈላጊዎችን የጀነት መንገድ ይከፍትላቸዋልና አላህ ይቀበላቹህ።
በላይኛው ሂዝብ ፕሮግራም ላይ የፈተና ጊዜ ያለቀባቹህ አልያም ውጤትዎ ዝቅ ያለባቹህ አንድ እድል ስለተጠጣቹህ እስከ ነገ እሮብ ምሽቱ 4:00 ድረስ መፈተን ይችላሉ።

በድጋሜ ሰዐቱ እንዳያልቅባቹህ በፍጥነት ይፈተኑ።

መልካም እድል።
  የለውጡ ወር : ረመዳን

ከወራቶች ሁለ አውራው ቁርዐን የወረደበት ወር እንግዳ ሆኖ መጥቶ ተጠቅመህበታልን?

ረመዳን የለውጥ ወር ነው።ባህሪያችንን እንቀይር።ለለውጥ እንነሳ።ህይወታችንን እንለውጥ።
لَيْلَةُ ٱلْقَدْرِ خَيْرٌۭ مِّنْ أَلْفِ شَهْرٍۢ

'መወሰኛይቱ ሌሊት ከሺሕ ወር በላጭ ናት፡፡'

ዉሳኔዎች የሚወሰኑባትን ፤ መላኢኮች የሚወርዱባትን ፤ ያለፈ ወንጀላችንን የምታስምረዋን ና ከ1000 ወር የምትልቀውን ለሊት ለማግኘት ቆርጠን እንነሳ።

አላህ ይወፍቀን
ዘካተል ፊጥር

فرض رسول الله صلى الله عليه وسلم زكاة الفطر طُهرةً للصائم من اللغو والرفث، وطعمةً للمساكين

የአላህ መልክተኛ(ሰ.ዐ.ወ) ዘካተል ፊጥርን ፆመኛ የሰራቸውን ጥፋቶች ማበሻ እና ለድሆች የበዐሉ ቀን መደሰቻ ይሆን ዘንድ ደነገጉ።
የአንድ ቀን ተጨማሪ እድል

ከራሳችን ጋር የምናደርገው ትግል በ29 ቀናት ድል መቀዳጀት አለመቻላችንን ያወቀውና አጨራረሳችንን እናሳምር ዘንድ የባከኑ ሰዐታቶችን ማካካሻ ጭማሪ ደቂቃዎች የሰጠን ልዕለ ሀያሉ ጌታ ምስጋና ይገባው።ነገ ከዚህ ሰዐት ጀምሮ የጀነት በር ተዘግቶ ሸይጧኖች ጋር ለመገዳደር ባለችን አንድ ቀን የቻልነውን ያህል እንሰንቅ።

ነገ የመጨረሻ የረመዳን ቀን እንደሆነችና ዒድ አል-ፊጥር እለተ ረቡዕ መሆኑ ተረጋግጧል።

ያማረ ረመዳን 30
አፍሪካ አካዳሚ
ዒድ ሙባረክ

እንኳን ለ1445ኛው አመተ ሂጅራ የኢድ አል ፈጥር በዐል በሰላም አደረሳቹህ።ኢዱ የደስታ የፍቅርና የመተሳሰብ ይሁንልን።
የላይኛው ሂዝብ ማብራሪያ ፕሮግራም

ከአሁኑ ሰዐት ጀምሮ በአፍሪካ አካዳሚ ድህረ ገፅ ላይ ማግኘት ይችላሉ።በአጫጭር ኮርሶች ዝስዝር ስር ተካቶ የርሶን መምጣት ይጠብቃል።

በፈለገቡበት ሰዐት ገብተው መማር ይችላሉ።ትምህርቱን እንዳጠናቀቁ የምስክር ወረቀት የሚያገኙ ይሆናል።

[https://am.africaacademy.com/course/view.php?id=231]
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ከሺርክ መራቅ አለብን!!
ከአላህ ውጭ ያለን አካል መለመን የለብንም!!

ኡስታዝ ሙሀመድ ፈረጅ

#አፍሪካ_አካዳሚ
#ሁለተኛ_ዙር_የሸሪዐ_ዲፕሎማ_ፕሮግራም
يوم الجمعة

قال رسول الله صلى الله عليه وسلم "إنَّ مِن أفضَلِ أيَّامِكم يومَ الجُمُعةِ؛ فأكثِروا عليَّ مِن الصَّلاةِ فيه؛ فإنَّ صَلاتَكم معروضةٌ عليَّ"




ጁምዐ

ፀሀይ ከወጣችበት ቀናት በሙሉ በላጯ ቀን ጁምዐ ናት።በበላጯ ቀን እኔ ላይ ሰለዋት አብዙ ሰለዋታችሁ ይደርሰኛልና።

اللهم صل وسلم وبارك على سيدنا محمد
የተፈቀዱ የተወሱል አይነቶች
-በአላህ ስም ተወሱል ማድረግ
-በኢማንና በመልካም ስራ
-በተውሂድ
-ድክመትን በመግለፅ
-ወንጀልን በማመን
-በህይወት ባሉ ደጋግ የአላህ ባሮች

#አፍሪካ_አካዳሚ
#ሁለተኛ_ዙር_የሸሪዐ_ትምህርት _ዲፕሎማ_ፕሮገራም
وَلَسَوْفَ يُعْطِيكَ رَبُّكَ فَتَرْضَىٰٓ (٥)

"ጌታህም ወደፊት (ብዙ ስጦታ) በእርግጥ ይሰጥሃል ፣ ትደሰታለህም!"

ሰረቱ-ዱሃ
ከኢልሀድ መጠበቂያ መንዶች
-የተከበረውን ቁርዐን ማንበብና ማስተንተን
-ኢማንን ወደማስረፅና ወደሚያፀና ነገር የሚያግዝ ነገር ላይ መስራት
-አላህን ማውሳት(ዚክር)
-ወደ ኢልሀድ የሚገፋፉ መንገዶችን መዝጋት
-ከደጋግ የአላህ ባሮች ጋር መቀላቀልና መኗኗር
ከትናንሽ የቂያማ ምልክቶች መካከል

-የእውቀት መነሳትና የመሀይምነት መስፈን
-የአረብ ምድር ወደ አረንጓዴነትና ወንዝነት መመለስ
-የመሬት መንቀጥቀጥ መብዛት
-የደጋግ ሰዎች መሞትና የመጥፎ ሰዎች መቅረት
-የታማኝነት መጥፋት
-ከመከራ ብዛት ሞትን መመኘት
اللهم صل على محمد
ወደ ሺርክ የሚያደርሱ መንገዶችን መዝጋት አስፈላጊ ነው።ከማሳያዎቺዙ መካከል፦

-መቃብሮችና ዶሪሆች በነርሱ ተበሩክ ማድረግ
-ነብዩ(ሰ.ዐ.ወ) ፀሀይ ስትወጣና ስትገባ መስገድ ከልክለዋል።
-ወደ መቃብሮች ጓዝ ጭኖ መጓዝ
-መቃብር ዘንድ ማረድ
-በሸሪዐ ያልተፈቀደን ሩቅያ ማድረግ
ደጋግ ቀደምቶቻችን የእውቀትን ፋይዳ ሲናገሩ እንዲህ ይላሉ፦

በእውቀት ስራ ይስተካከላል ያምራል።
በስራ ደሞ ጥበብ ይገኛል።
በጥበብ ለዱንያ ግድ ያለመስጠት ምንነት ይገባናል።
ለዱንያ ግድ ከለለን ከዱንያ እስር ቤት እንላቀቃለን።
የዛኔ አኺራን እንወዳለን።እንናፍቃለን።
አኺራን በመናፈቅ ደሞ የአላህ ውዴታ ይገኛል።
የአላህ ፍቃድ ሆኖ የአፍሪካ አካዳሚ ሁለተኛ ዙር የዲፕሎማ ፕሮግራም ተማሪዎች ሁለተኛ ሴሚስተር የመጀመሪያውን ኮርስ (የአቂዳ ኮርስ) በተሳካ ሁኔታ አጠናቋል።

ይህ ኮርስ በዋንኛነት የዳሰሳቸው ነጥቦች የሚከተሉት ናቸው፦

1, ተውሒድን የሚያበላሹና የሚያጎድሉ ነገሮች
2, የኩፍር(የክህደት) አይነቶች
- በትልቁ ክህደትና በትንሹ ክህደት መካከል ያሉ ልዩነቶች
3, ሺርክ እና አይነቶቹ
  - የትልቁ ሺርክ አይነቶች
   - የትልቁ ሺርክ መገለጫዎች
   -ወደ ሺርክ የሚያደርሱ መንገዶችን መዝጋት
   - ትንሹ ሺርክና ክፍልፍሎቹ
   - ዘመናዊው መጥፎ ገድ (ተሻኡም)
   -ከፍ ካለው ከአላህ ውጭ በሌላ መማልና መጥፎ ገድ ማየት
4, በኩፍርና ሺርክ መካከል ያለው ልዩነት
5, የቢድዐ መለኪያዎች
6, የማክፈር መለኪያዎች
7, የትንሳኤ ምልክቶች
8, ሶሀቦችና የነብዩ ቤተሰቦች
9, ወልዮችና ከራማቸው
10, ምልጃ

ለሁለተኛ ዙር ተማሪዎቻችን እንኳን ደስ አላችሁ ማለት እንወዳለን።አላህ የዕውቀትን ደረጃ እንዲሰጣችሁና እንዲቀበላችሁ ዱዐችን ነው።

#አፍሪካ_አካዳሚ
#ዲፕሎማ_የሸሪዓ_ትምህርት