Telkhis (هذه عقيدتنا)
6.46K subscribers
267 photos
150 videos
58 files
994 links
Download Telegram
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
እንኳን ወደ ዑካዝ ጅልባብ እና ኒቃብ መሸጫ በደህና መጡ።
🟢ለፊት ምቹ የሆኑ ረጅም እና አጭር  ኒቃቦች ያገኛሉ።
🟢የጅልባቦቻችን ጨርቆች ጥራት ያላቸው ከውጭ ሀገር እራሳችን ባስመጣናቸው የኮሪያ ጨርቆች የሚሰሩ  ናቸው።
🟢ጥራት ያለው  #Kufnees ጀለቢያ እና ሌሎችም ጀለቢያዎች አሉን።
🟢አባያዎች
🟢ካሪስ ሺቲዎች  እና ሌሎችንም እኛጋ ያገኛሉ።

ብዛት ለሚወስዱና ራቅ ካለ ቦታ መጥተው ለሚገዙ ደንበኞቻችን የዋጋ ቅናሽ እናደርጋለን።

ትእዛዞቻቹሁን በታማኝነት ከሀገር ውጭ እና ሀገር ውስጥ እንልካለን።

📌አድራሻችን አዲስ አበባ
ከአለም ባንክ ወደ አሊ መስጅድ በሚወስደው መንገድ 200 ሜትር ገባ ብለው ያገኙናል።

ለበለጠ መረጃ
📞 @Okaz0913511818
📞 0930611919
በቀጥታ ወይንም በቴሌግራም እና በዋትሳፕ ያናግሩን።

ወደ ጉሩፓችን ተቀላቀሉ
💎

https://t.me/OkazHijab
🌙 የጎዳና ኢፍጣር🌙
===============
🖌 በኢልያስ አሕመድ

በቅድሚያ ይህን ፕሮግራም ለማሰናዳት በቅንነት የሚለፉ ግለሰቦችና ድርጅቶችን አላህ የኒያቸውን እንዲሰጣቸው እንለምናለን፤ ከዚህ በታች ያለው አጭር ፅሑፍ የልፋታቸው መሰረት የተስተካከለ እንዲሆን ታስቦ በተቆርቋሪነት የተከተበ ነው።
››››› ‹‹‹‹‹

በህብረት ማፍጠር ሁለት አይነት አፈፃፀሞች ሊኖሩት ይችላል፦

1ኛ/ ለማፍጠር መሰባሰቡን ዋና ኢላማ ሳያደርጉ በተወሰኑ አጋጣሚዎች በህብረት ማፍጠር ሲሆን ይህም እንደማይወገዝ ግልፅ ነው።
ለምሳሌ፦ ለሰላት ወደ መስጂድ የመጣውን ስብስብ ወይም ድሆችን በአንድ ቦታ ለማስፈጠር የሚኖረው መሰባብሰብ ተቃውሞ ሊነሳበት አይችልም። ዘመድና ጓደኛን ጠርቶ በጋራ ማፍጠርም እንደተራ ግብዣ ሊታይ ይችላል። ፆመኛን ማስፈጠርን አስመልክቶ የተወራውን ምንዳ ለማግኘት ከታሰበ ደግሞ እንደ እሳቤው የተወደደ ሊሆን ይችላል።

ብዙ ዑለማዎች የፈቀዱትም በዚህኛው ምድብ የሚካተተውን ነው።

2ኛው/ ለኢፍጣር መሰባሰቡ ራሱ እንደ ዋና ግብ ታልሞና ይህንንም በሚያሳብቁ ተግባራት ታጅቦ በስፋት የሚተገበር አፈፃፀም ሲሆን ይህ የቢድዓ መገለጫን ሊላበስ ይችላል።

በሀገራችን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የተለመደው የጎዳና ኢፍጣር ይህንን ይዘት እንደተላበሰ ከሚያሳዩ ምልክቶች መካከል፦

👉 እንደ በዓላት የሚጠበቅ ህዝባዊ ኩነት መሆኑ፣ (Grand Iftar 1, 2 እየተባለ ዘንድሮ 4ኛው ላይ ደርሰናል!)

👉 ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የበድር ዘመቻ የተካሄደበት የረመዳን 17ኛው እለት ለዚህ አመታዊ መሰባሰቢያ እንዲሆን በተደጋጋሚ መመረጡ፣

👉 ሰዎች በነቂስ ወጥተው እንዲታደሙ ሰፊ ጥሪ መደረጉ፣

👉 በታዳሚያን ብዛት ከሌሎች አገራት ጋር ፉክክር ውስጥ የተገባበት መሆኑ፣

እና ሌሎች አባሪ ሂደቶች ሊጠቀሱ ይችላሉ።

የነዚህ ሂደቶች ስብስብ ተግባሩን ራሱን የቻለ አዲስ የሙስሊሞች ይፋዊ ምልክት (ሺዓር) እያደረገው ነው።

📌 ታላቁ ኢማም #ኢብኑ_ተይሚያህ በዲን ውስጥ ስለሚጨመሩ የፈጠራ በዓላት በሚያብራሩበት አውድ ስለ በዓላት ምንነት ሲያስረዱ የሚከተለውን ይላሉ፦
«“ዒድ” (በዓል) በተለመደ መልኩ ለሚደጋገም ሁሉን አቀፍ መሰባሰብ የሚሰጥ ስያሜ ሲሆን በየአመቱ፣ በየሳምንቱ፣ በየወሩ ወይም በተመሳሳይ ሁኔታ (በውስን ቀናት) የሚመላለስ ነው።
በዓል የተወሰኑ ነገሮችን አቅፎ ይይዛል፤ ከነሱ መካከል፦
እንደ ዒድ አል-ፊጥር እና እንደ ጁሙዓ የሚመላለስ ቀን፣ (በቀኑ) መሰባሰብ፣ ይህን ተከትለው የሚመጡ አምልኳዊ ወይም ልማዳዊ ተግባራት ይገኛሉ።
በዓል በውስን ቦታ የተገደበ ሊሆን ይችላል፤ ያልተገደበም ሊሆን ይችላል፤ እነዚህ ነገሮች ሁሉ (በነጠላ) ዒድ ሊሰኙ ይችላሉ....
“ዒድ” የሚለው ቃል ለእለቱና በውስጡ ላለው ተግባር ጥምረት የሚሰጥ ስም ሊሆን ይችላል፤ ይህም አብዛኛው (አጠቃቀሙ) ነው።»
[“ኢቅቲዷኡ’ሲራጢ’ል’ሙስተቂም” (1/496 – 497)]

📌 በሌላ ቦታም እንዲህ ብለዋል፦
«ከተደነገጉት መሰባሰቦች ውጪ ሳምንታት፣ ወራት፣ ወይም አመታት በተደጋገሙ ቁጥር የሚደጋገም መሰባብሰብን በቋሚነት መያዝ ለአምስቱ ሰላቶች፣ ለጁሙዓ፣ ለሁለቱ ዒዶችና ለሐጅ ከመሰባብሰብ ጋር ይመሳሰላል፤ ፈጠራና አዲስ ተግባር ማለት ይህ ነው!))
[“ኢቅቲዷኡ’ሲራጢ’ል’ሙስተቂም” (2/140)]

📌 አለፍ ብለውም እንዲህ ይላሉ፦
«ከነዚህ (ከተደነገጉት) መሰባሰቦች ባሻገር የሚለመድ ተጨማሪ መሰባሰብ ከተጀመረ አላህ ከደነገገውና ካፀደቀው ፈለግ ጋር የሚመሳሰል ይሆናል …. - ለብቻው የሆነ ግለሰብ ወይም ውስን ስብስቦች አንዳንዴ ከሚሰሩት በተለየ መልኩ!))
[“ኢቅቲዷኡ’ሲራጢ’ል’ሙስተቂም” (2/144)]

ይህ ማብራሪያ ሰዎች በየውስን ጊዜ በታወቀ ቀጠሮ የሚፈፅሙት ህዝባዊ ስብስብ እንደ በዓል ባይታቀድ እንኳ በዓላዊ ይዘትን እንደሚላበስ ያሳያል።

አንድ ነገር በጥቅሉ የሚፈቀድ፣ ብሎም የሚደነገግ ከመሆኑ ጋር በአፈፃፀሙ ረገድ የሚኖሩ ተጓዳኝ ነገሮች ብይኑ እንዲቀየር ሊያደርጉ ይችላሉ።
📌 ታዋቂው ዓሊም #ኢብኑ_ደቂቅ_አል_ዒድ አንዳንድ ሸሪዓዊ አፈፃፀሞችን ለመተግበር በደካማ የሐዲሥ ዘገባ ላይ ስለመመርኮዝ የሚነሳውን ውዝግብ አስመልክቶ እንዲህ ይላሉ፦
«የ“መውዱዕ” (የተቀነባበረ የውሸት ሐዲሥ) ክልል ውስጥ ያልገባ ደዒፍ (ደካማ) ከሆነ በዲን ላይ አዲስ ይፋዊ ምልክት “ሺዓር” የሚፈጥር ከሆነ ይከለከላል፤ ካልሆነ ደግሞ ምልከታ የሚቸረው ይሆናል...» [“ኢሕካሙ’ል-አሕካም” (1/501)]

👉 አንድን ተግባር እንደ “ሺዓር” ከሚያስቆጥሩት የአፈፃፀም ሂደቶች መካከል ሰዎች ተጠራርተው የሚሰባሰቡበት ኩነት መሆኑ ነው። ይህን የሚያብራራ አንድ ምሳሌ እንጥቀስ፦

ሰዎች በተሰባሰቡበት አጋጣሚ አንዳንዴ ዱዓ ማድረግ የሚቻል ከመሆኑ ጋር ይህን በህብረት ለመፈፀም መጠራራትን ብዙ የኢስላም ሊቃውንት አይደግፉም።
📌 #አል_ኢማም_አሕመድ እንዲህ ተብለው ተጠየቁ፦ «ሰዎች ተሰባስበው አላህን መለመናቸውና እጃቸውንም ማንሳታቸው ይጠላል?»
እርሳቸውም፦
«مَا أَكْرَهُهُ لِلْإِخْوَانِ إذَا لَمْ يَجْتَمِعُوا عَلَى عَمْدٍ إلَّا أَنْ يَكْثُرُوا»
= «ሆን ብለው ካልተሰባሰቡ ለ(ዲን) ወንድማማቾች አልጠላውም – ካልበዙ በስተቀር!»

📌 #አል_ኢማም_ኢስሓቅ ኢብኑ ራሀወይህ ሲጠየቁም ተመሳሳይ መልስ ሰጥተዋል።

«ካልበዙ በስተቀር» ሲሉ ልማድ በማድረግ እስካልተበራከቱ ድረስ ማለታቸው እንደሆነ ጠያቂው (ኢስሓቅ ኢብኑ መንሱር) ተናግረዋል!
[“መሳኢሉ’ል-ኢማሚ አሕመድ ወኢስሓቅ” (9/4879)፣ “ኢቅቲዷኡ’ሲራጢ’ል’ሙስተቂም” (2/140)]፣
“አል-ኣዳብ አሽ-ሸርዒይ-ያህ” ሊ’ብኒ ሙፍሊሕ (2/103)]

👉 ስለሆነም ነገሩ ከዚህ በላይ ሳያድግ መግታቱ አስፈላጊ ነው።
ይህ ከዚህ በፊት የተስተዋሉ የአፈፃፀም ግድፈቶችን ከግምት ሳናስገባ የምንደርስበት መደምደሚያ ሲሆን፤ ያለ በቂ ምክንያት መንገድ መዘጋጋት፣ አግባብ ያልሆነ የወንድና የሴት መቀላቀል፣ የሴቶች ምስል በሚዲያ የሚሰራጭበት ቀረፃ፣ ሴቶች በምሽት መንገላታታቸው፣ በሙዚቃ መሳሪያ የታጀበ "ነሺዳ"፣ የምግብ ብክነት እና መሰል ጥፋቶች የሚታከሉበት ከሆነ ደግሞ በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ ይሆናል።

አዎን! ፕሮግራሙ ከዚህ በፊት ሞራላዊ ጥቅምን አስገኝቶ ሊሆን ይችላል፤ ነገር ግን በውስጡ ከላይ የጠቆምነውን አመዛኝ ጉዳት ማካተቱ ለመታቀብ በቂ እንደሆነ አስባለሁ።

አላህ ይበልጥ አዋቂ ነው።

ረመዳን 15/1445

ሸይኽ ኢልያስ አህመድ حفظه الله
*ሹክረን* ላለ ሰው
*ዐፍወን* ብሎ መመለስ ይቻላል። ይቅርታ; ብዙም የሚያስመሰግነኝን አላደረግኩምኮ፣ የሚጠበቅብኝ ብዙ ነበር እንደማለት ነው።

ሆኖም ግን ሁለቱንም በተሻሉ ሸሪዐዊ ቃላት መተካት በላጭ ነው።
*ሹክረን* ከምንል " *ጀዛከሏሁ ኸይረን* " ብንል

*ዐፍወን* ከምንል " *ወአንተ ጀዛከሏሁ ኸይረን"* ወይም "ወጀዛከ" ወይም "ወኢያከ" ብንል የተሻለ ነው።
የዒድ ሶላትን በጀመዓ በመስገጃ ቦታ ለመስገድ ያልቻለ
ባለበት ይሰግዳል።
ልክ ኢማሙ እንደሚያሰግደው አስመስሎ። የዒድ ሶላትን አሰጋገድ ጠብቆ መስገድ ካልቻለ ደግሞ
እንደማንኛውም ሶላት ሁለት ረከዓ ድምጹን ከፍ አድርጎ ይሰግዳል።
ተጨማሪ ተክቢራዎቹ ሱንና እንጅ ግዴታ አይደሉም።
በመከራ ምክንያት ከአላህ መንገድ ከሚስተው ኸልቅ ይልቅ በድሎትና በምቾት ምክንያት የሚጠመው በእጅጉ ይበዛል። ኧረ እንዳውም ብዙሃኑ ሰዎች መከራ ሲያጋጥማቸው ወደፈጣሪያቸው መጠጋትን ነው የሚመርጡት።
ስለዚህ በችግር ምክንያት መንገድ መሳትን ከምትፈራው በላይ አብዝተህ መጠንቀቅ ያለብህ በድሎትና ምቾት ከመንገድ መውጣትን ነው።

T.me/telkhis
Forwarded from Yusuf App (ዩሱፍ)
ሱነኑ አቢ ዳውድ ቁ.❷ سنن أبي داود.apk
418.1 MB
「𑁍📲አዲስ አፕ | ተለቀቀ 𑁍」

    ╭──────╮
📲 ቁጥር ➋
│ ╰──────╯
📖 ሱነኑ አቢ ዳውድ

│ ከሐዲስ 1269-2184
╰────────────────╯   
🎙የደርሱ አቅራቢ:-
├─┈┈┈
│✑በሸይኽ ሙሐመድ ዘይን ኣደም
╰──────────────
╭⎘  ለመሰል ስራዎች ይቀላቀላሉን

🖇http://t.me/Yusuf_App1
╰─╼╺╼╺╼╺╼╺╼╺╼╺╼
#ሳዑዲ እና #ዱባይ ያላችሁ እንኳን ደስ አላችሁ😍
ልክ እንደ እናት እጅ ንፁህ እና ጣፋጭ የሆኑ እንዲሁም ጤናማ የሆኑ ባልትናዎችን አዘጋጅተንላችኋል 🥰......
ለማዘዝ 0921335204/0943034361 መጠቀም ትችላላችሁ

https://t.me/+c0qaN3fIRjc1OGI0

የቴሌግራም ግሩፓችንን ተቀላቀሉ እዘዙ አብራችሁን ስሩ!
"ሶላትን የሰተው በርግጥም ክዷል"
አህመድና ቲርሚዚይ ዘግበውታል
°°°°°°°°°°°°°°°°°°
ዐረቦች የአንድን ነገር የመጨረሻ ውጤትና ፍጻሜ ለመነሻው ጉዳይ በመስጠት የመጥራት ባህል አላቸው።
ሶላት መተው የክህደት ጅማሬ ስለሆነና በዚሁ የቀጠለ ሰው የመጨረሻ እጣ ፋንታው ከኢስላም የሚያወጣው ክህደት ላይ መገኘት መሆኑ አይቀርምና ነብዩም صلى الله عليه وسلم የፍጻሜውን ብዪን ለመነሻው ሰጡትና ሶላት የተወ ሰው ከሀዲ ነው ብለው በየኑ። የዚህ ሀዲስ አምሳያው
" المراء في القرآن كفر " رواه ابو داود
የሚለው ሌላኛው ሀዲሳቸው ነው።
ይሄም ሀዲስ እንድሁ በሆነች አጋጣሚ በቁርአን ዙሪያ መከራከርና መጨቃጨቅ በአንዴ ከኢስላም ያባርራል ለማለት ሳይሆን
በቁርአን ዙሪያ ክርክርን ያበዛ ሰው የመጨረሻው ፍጻሜ ከባዱ ክህደት ነው ማለታቸው ነው።

ይህ ኢብኑ ሂባን رحمه الله ሶሂሃቸው ላይ ያሰፈሩት የጥንት ገለጻ ነው።

ስለዚህ
በመሳነፍና በመዳከም አልፎ አልፎ ሶላቶችን የማይሰግድ ወይም የሚሰግድ ሰው ሙስሊም ነው። ፍጻሜው ክህደት ላይ መውደቅ ይሆንበታል ተብሎ ግን ይሰጋለታል።

T.me/telkhis
በጥቅሉ የስራ መዝገቦቻችን በሶስት መልኩ ይከፈላሉ ይላሉ ነብዩ صلى الله عليه وسلم።

1ኛው- በፍጹም አላህ ይቅር የማይለውና የማይምረው ወንጀል የተጻፈበት መዝገብ ሲሆን ይህም የሺርክ ወንጀል የተጻፈበት ነው።

2ኛው- አላህ ብዙም ቦታ የማይሰጠውና የማያጠብቀው እሱ ከፈለገ ይቅር የሚለው፣ የሚሰርዘውና ግለሰቡንም ለጀነት የሚያበቃው አይነት የስራ መዝገብ ነው። በዚህ መዝገብ ውስጥ የሚካተቱት ባርያ በራሱ እና በጌታው መካከል የፈጸማቸው ጥፋቶች ናቸው። በሀዲሱ ላይ እንደምሳሌ የተጠቀሱትም ያልጾማቸው ቀናቶች ያሉበት ወይም #ሆን_ብሎ_ያልሰገዳቸው_ሶላቶች ያሉበት ግለሰብን ነው።

3ኛው የስራ መዝገብ ደግሞ አላህ በፍጹም የማያልፈው (የማይተወው) የስራ መዝገብ ነው። በዚህ መዝገብ ውስጥ የሚካተቱት ወንጀሎች ፍጡራኖች ላይ የተፈጸሙ ግፎች ናቸው። ስርቆት፣ ስም ማጠልሸት፣ ግድያ፣ ስድብ፣ እርግማን፣ ድብደባ እንደምሳሌነት ሊጠቀሱ ይችላሉ።

ሀዲሱን ያስተላለፈችው እናታችን ዐኢሻ رضي الله عنها ስትሆን አህመድ፣ ሀኪምና በይሀቂይ ዘግበውታል። ከፊል የሀዲስ ሊቃውንቶች ይህንኑ ሀዲስ ትክክለኛና ተቀባይነት ያለው መሆኑን ሲገልጹ ሌሎች ደካማ ነው ብለውታል።
ሸይኽ አልባኒ رحمه الله ይሄ ሀዲስ ደካማ መሆኑን ቢገልጹም ነገር ግን በዚህ ሀዲስ ውስጥ የተገለጹት መልእክቶች ፍጹም ትክክለኛና ተቀባይነት ባላቸው በሌሎች መረጃዎች የተደገፉ ናቸው ይላሉ።

T.me/telkhis
3 ውስብስብ የፊቅህ ትምህርት ምእራፎች
---------------------------------------

ታዋቂው የዘመናችን የሀዲስ ሊቅ
ሸይኽ ዐብዱልሙህሲን ዐባድን
ከሀይድ ጋር የሚያያዝ አንድ ጥያቄ ጠየቅኳቸው።
እኔ 3 ጉዳዮችን በተመለከተ ለሚቀርቡልኝ ጥያቄዎች ምላሽ አልሰጥም። ይልቁኑም ወደሌሎች መሻይኾች ነው የማስተላልፈው ብለው መለሱልኝ።

እነዚህ 3 ጉዳዮች
1- ከወር አበባ ደም ጋር የሚያያዙን ጥያቄዎች
2- ከፍቺ ጋር የሚያያዙን ጥያቄዎችና
3- ሰዎችን ከእስልምና በማስወጣት ዙሪያ ላይ የሚቀርቡልኝ ጥያቄዎች ናቸው ብለው መለሱልኝ ይላል
ሸይኽ ዐሲም ቀርዩቲ

حفظهما الله

T.me/telkhis
አብዛኛው ኢጅማዕ አለበት በሚል የሚነገረው ቅርንጫፋዊ የፊቅህ እይታ
በዑለማኦች ሁሉ ስምምነት ላይ የተደረሰበት አይደለም። ይሄን እጅግ በበርካታ ጉዳዮች ላይ አረጋግጫለሁ። ምሳሌዎችን እንጥቀስ ቢባል መድረኩ አይበቃንም።

ስለዚህ አንዳንድ ምሁራኖች
በሆነ ጉዳይ ላይ ለሚኖር አለመግባባት "የዑለማኦች ስምምነት አለበት" የሚልን መከራከርያ በማቅረብ የሚቃወማቸውም ምሁር ጸጥ ለማስባል መሞከራቸው ሊያስደነግጥ አይገባም።

ሸይኽ አልባኒ

T.me/telkhis
ሱጁድ
እጅግ ያማረው የሶላት ክፍል ነው። ለዚህም ሲባል
የሚሰገድባቸው ቦታዎች ራሱ መስጅድ ነው የሚባሉት። መስጅድ ማለት ሱጁድ የሚደረግበት ቦታ ማለት ነው።
ይህም ሱጁድ እጅግ ወሳኙ የሶላት ክፍል ባይሆን ኖሮ
የመስገጃ ቦታዎች መስጅድ ሳይሆን መርከዕ ወይም መቃም የሚል መጠሪያ ይሰጣቸው ነበር። (የሩኩዕ ወይም የቂያም ቦታዎች)

ሶላት እንደጥቅልም ሱጁድ የሚል ስም የተሰጠው እንድሁ ወሳኝነቱን ለመግለጽ ነው።
ክቡር ነብያችንስ صلى الله عليه وسلم ቢሆኑ እስኪ ሱጁድ በማብዛት አግዘኝ ብለውት የለ ከርሳቸው ጋር በጀነት ስለመጎራበት የጠየቀውን ባልደረባቸውን ኸላድን رضي الله عنه ።
ሱጁድ አብዛ ማለታቸው ሶላትን አብዛ ለማለት አይደለ?

በሱጁድ ላይ እንበርታ!!

T.me/telkhis
#በለተሞ_መንጋ የምርቃና ስብከት ለተጠለፋችሁ ሁሉ!
~
1ኛ፦ እነዚህ ሰዎች የመንሀጅ ግንዛቤያቸው የተንሻፈፈ፣ የግል አመላቸውንና ሰለፊያን የሚያምታቱ ስለሆነ የሰለፊያን ግንዛቤ ከነዚህ ሰዎች አትውሰዱ። ይልቁንም ጊዜው የሚመች ነውና ከነ ኢብኑ ባዝ፣ አልባኒይ፣ ኢብኑ ዑሠይሚን፣ ፈውዛን፣ ዐብዱልሙሕሲን አልዐባድ፣ ... ኪታቦችና የድምፅ ቅጂዎች ተጠቀሙ። ከነሱም በላይ የቀደምት ዑለማዎችን አካሄድ በሚገባ ፈትሹ። እነዚህ ሰዎች ሰለፊያ ነው ብለው የሚያቀርቡላችሁ ከክፉ አመላቸውና ሸውራራ ግንዛቤያቸው ጋር የተቀላቀለ ቡድንተኛ አካሄድ ነው። የሱና ዑለማኦችን የሚያጣቅሱት ለሽፋን ያህል ነው።

2ኛ፦ ደዕዋችሁ የአካባቢያችሁን ተጨባጭ ያገናዘበ ይሁን። አዲስ ብሄርተኛ ይመስል መንሀጅ በተገነዘባችሁ ማግስት በትንሽ በትልቁ ሌሎች ጋር አትላተሙ። እነዚህ የሚያጋጯችሁ አካላት ከምትገቡበት አጣብቂኝ እንድትወጡ የሚያግዝ ይሄ ነው የሚባል ሃሳብ እንኳ ማቅረብ አይችሉም። እነሱ እንደሆኑ ለራሳቸው ጥቅም ሲሆን ካሜራ ውስጥ እንዳይገቡ እየተሹለከለኩ፣ ማስክ እያጠለቁ የሚጣዱ ናቸው። እነሱን ተከትላችሁ ደዕዋችሁ ቢሰናከል ብዙ ርቀት ወደ ኋላ ይመልሷችኋል።

3ኛ፦ ለፍረጃና ለተብዲዕ አትቸኩሉ። በቂ የመንሀጅ ግንዛቤ ያልያዘ ሰው ፈፅሞ ለተክ -ፊርና ለተብዲዕ ብቁ አይደለም። ነገሩ በሚገባ ተገልጦልናል ብላችሁ በምታምኑበት ጉዳይ ራሱ በመናገራችሁ የሚገኘውን ትርፍና ኪሳራ አስሉ። የደመ ነፍስ አካሄድ ማንንም አይጠቅምም።

4ኛ፦ የለተሞ ጭፍራዎች ጋር መጓዝ መስጂዶቻችሁን ያሳጣችኋል። ከማህበረሰብ ጋር ያጋጫችኋል። በሂደት ደዕዋችሁን ወይ ሙሉ ለሙሉ ያጠፋዋል። ወይ ደግሞ በእጅጉ ያቀጭጨዋል። ብዙ ካበላሻችሁ በኋላ ግራ ቀኝ አይታችሁ የተሻለ መስለሐ ያለበትን ውሳኔ ብትወስኑ ራሱ እነዚህ እባቦች ከማንም በላይ የሚናደፉት እናንተን ነው። የቻግኒው ሸይኽ ከማል አፍሪ ጉዳይ ለዚህ ጥሩ ምሳሌ ይሆናል። ቀድመው በነዚህ አካላት የተሳሳተ አቅጣጫ ይዘው ነበር። አሁንም ምን ያህል እንደነቁ አላውቅም። የተሻለ መስለሐ አይተው መስጂድ ገብተው ሲያስተምሩ እድሜያቸውንም፣ ውለታቸውንም በማይመጥን መልኩ እያብጠለጠሏቸው ነው። "ያሳደጉት ውሻ፣ ያሳጣል መድረሻ!"

5ኛ፦ የአካባቢያችሁን መስለሐ ራሳችሁ ወስኑ። በሩቅ ያለ ሰው ያላችሁበትን ተጨባጭ ላያውቅ ይችላል። በተለይ እነዚህ ከህሊናቸው የተጣሉ አካላትን ፈፅሞ አታማክሩ። እንኳን ለናንተ ለራሳቸውም የሚሆኑ አይደሉም። አስፈላጊ ሲሆንና ከተቻላችሁ ዑለማኦችን አማክሩ። እነዚህ የሚጮሁትን የማይኖሩ ደናቁራን እንዳያሳስቷችሁ። ለተሞ በራሱ ምስክርነት ከ10 አመት በላይ ኢኽዋንን ሲያደንቅና አብሮ ሲጓዝ የኖረ ሰው ነው። አሁንም ከተወሰኑት ጋር ያፋጠጠው የጥቅም ግጭት ነው። እንጂ የጥቅም ቃል ሲገባለት እንኳን ከነዚህ ጋር ይቅርና ቀድሞ ተብዲዕ ካደረጋቸው ሰዎች ጋር ራሱ ሊታረቅ እልል ሲል ነበር። አሁንም የተሻለ ካየ ለሌላ ይፈርማል። ባህሩም ከሙብተዲዕ ጋር መቀማመጥ ሲል ለዲን ተቆርቁሮ አይደለም። የራሱ አንዱ ጋሻጃግሬ ከሚያወግዛቸው አካላት ጋር የመስጂድ ኮሚቴ አባል ነው። ኮሚቴው በመጅሊስ መዋቅር ስር እንደሆነ አስተውሉ። የባህርዳሩም ጭፍራ ዲን አይደለም ከመርከዝ ኢብኑ መስዑድ ጋር ያፋጠጠው። "ለኛ የተላከ ኪታብ ወስደውብን ..." እያለ ነው የህፃን ለቅሶ የሚያለቅሰው። ራሳቸው በቡኻሪ መስጂድ የመርከዝ ኢብኑ መስዑድን ፕሮግራም አስተዋውቀው ሲያበቁ እነዚህ ከህዝቡ ብር ሲሰበስቡ ጊዜ ጨርቃቸውን ጣሉ። በቀናት ልዩነት ውስጥ ተነስተው አስጠነቀቁ። ስሜታቸውን የማይቆጣጠሩ፣ ይሉኝታ የማያውቁ ጉዶች ናቸው። እንጂ ዛሬ ለተብዲዕ የሚመዙትን ጉዳይ እየጠቀሱ ተብዲዕ ግን አናደርግም ሲሉ እንደነበር የድምፅ መረጃ አለ።

6ኛ፦ በደዕዋ ላይ ተመዩዝ አስፈላጊ ነው። ተመዩዝ ማለት ግን በራስ ላይ በር ዘግቶ መጮህ አይደለም። ከሆነላችሁ ያለ ንክኪ አስተምሩ። መድረክ ካገኛችሁ አቋማችሁ የተጠበቀ እስከሆነ ድረስ በሱፊዮች መስጂድ እንኳ ቢሆን አስተምሩ። ታላላቅ መሻይኾች በሱፊያ መስጂዶች ያስተማሩበት ተጨባጭ አለ። ለምሳሌ ሸይኽ ረቢዕ ሱዳን ውስጥ በሱፊያ መስጂድ አስተምረዋል። "በአቋም ቢገናኙ ነው ከነ እንትና መስጂድ የሚያስተምሩት" የሚለው የነዚህ ሰዎች ጩኸት ዝቅ ቢል ድንቁርናቸውን ከፍ ቢል አታላይነታቸውን ነው የሚያሳየው። ለአመታት ሂዝቢዮች ላይ ቁጭ ብለው ሲማሩ ነው የኖሩት። ባህሩ፣ ሁሴን ሲልጢ እና ጠሀ ኸዲር ለዚህ ምሳሌ መሆን ይችላሉ። ራሳቸው የሳዑዲ ጃሚ0ዎች በሒዝቢዮች የተጥለቀለቁ እንደሆኑ ይገልፃሉ። ራሳቸው በንዲህ አይነት ተቋማት ቁጭ ብለው እየተማሩ እኛ ጋር መጥተው እንትናን ከእንትና ጋር አየነው እያሉ አድብተው ይጠብቃሉ።
በሰሜን ወሎ፣ ጉራጌ፣ ስልጤ ዞኖች የመጅሊስ መዋቅር ውስጥ የገቡ አሉ። ለተሞ በሚያብጠለጥላቸው የየመን መራኪዝ የሚማሩ የለተሞ መንጋዎች አሉ። የመን መዕበር ድረስ ሄደው ሙሐመድ አልኢማም ዘንድ የሚማሩ ሁሉ አሉ። እዚሁ ኢትዮጵያ ውስጥ ዐረብኛ ትምህርት በሚሰጥባቸው ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ሙመይዐ ከሚሏቸው እና ኢኽዋኒዮች ዘንድ ቁጭ ብለው የሚማሩ አሉ። ከዚህም የባሰ ሱፊዮች ዘንድ ሳይቀር ሉጋ የሚማሩ አሉ። ራሳቸው በሚሰሩት ጉዳይ ሌሎችን ተብዲዕ የሚያደርጉ የማፊያ ስብስብ ናቸው።
ጩኸታቸው የእውነት መስሏችሁ እነሱን የተከተላችሁ በጊዜ ብትነቁ ይሻላችኋል። ጥሪዬ በተለይ መሬት የረገጠ ደዕዋ ላላችሁ ነው። ደዕዋችሁን ሳታጡት በፊት ደጋግማችሁ አስቡበት።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor