ሑሰይን የዐብደሪይ ወዳጅ - official
2.73K subscribers
208 photos
167 videos
593 links
መርሄ ተምሮ መተግበር እና ለሌሎችም ማስተላለፍ ነው😍 በአሏህ ፍቃድ!

አድሚን
@Yabdery_wedaj

My youtube 👇
https://www.youtube.com/channel/UCEmERZz4bAnnW1C-oAK2jrA
Download Telegram
አሏህ ሆይ! ይቅር ካልካቸው፣ ስራቸውን ከወደድካላቸው፣ ኃጢአታቸውን ከማርክላቸው፣ከእሳት ነፃ ካልካቸው፣ ጀነተን ከፃፍክላቸው፣ባሮችክ አድርገን!

:¨·.·¨: ❀
 `·.ሑሰይን የዐብደሪይ ወዳጅ
T.me/husseyn_y_abdery_wedaj
ጁሙዓህ ሙባረክ 🥰🥰

¨·.·¨: ❀
 `·. T.me/husseyn_y_abdery_wedaj
#ረመዷን_12

በሂጅራህ አቆጣጠር በ597 አ.ሂ ፣ በረመዷን 12 ቀን  ላይ ነበር ዓሊምና ሙሐዲስ የሆኑት “ኢብኑ ጀውዚይ”  በበግዳድ ሀገር ላይ ያረፉት። "ረሒመሁሏህ"

#ረመዷን_13

በሂጅራህ አቆጣጠር በ16ኛው አ.ሂ  አመት  በረመዷን 13 ላይ ነበር ኸሊፋው ዑመር ኢብን አል-ኸጧብ [ረዲየሏሁ ዐንሁ]  የ“በይተል መቅዲስን ” ቁልፍ ለመረከብ ሻም ሀገር የከተሙ

#ረመዷን_15

ከሂጅራ በኃላ በ3ኛው አ.ሂ በረመዷን 15 ላይ ነበር የመልዕክተኛው ﷺ የልጅ ልጅ የሆኑት  “ሐሰን ኢብኑ ዐልይ” የተወለዱት።  (ረዲሏሁ ዐንሁማ)

#ረመዷን_16

በሂጅራህ አቆጣጠር በ58ኛው አ.ሂ ፣በረመዷን በ16 ላይ ነበር  የአቡበክር ሲዲቅ ልጅ፣ የመልዕክተኛው ﷺ ተወዳጅ ባለቤት የሆነችው "እናታችን ዓኢሻህ"(ረዲየሏሁ ዐንሃ) ይችን ዓለም የተሰናበተችው ።

#ረመዷን_17

በሂጅራህ አቆጣጠር በ2ኛው አ.ሂ በረመዷን በ17 ላይ ነበር ... ታላቁ የ#በድር ጦርነት የተካሄደው። አሏህ መልዕክተኛውን ﷺ እና ከእርሳቸው ጋር  የነበሩትን ሱሐባዎች ድል ያጎናፀፈበት ታላቅ  ጦርነት ነበር።

#ረመዷን_18

በሂጅራ  አቆጣጠር በ21ኛው አ.ሂ በረመዷን በ18 ላይ ነበር ... ታላቁ የጦር መሪ "ኻሊድ ኢብኑ ወሊድ" (ረዲዬሏሁ ዐንሁ) ይችን ዓለም የተሰናበቱት።

#ረመዷን_20

ከሂጅራ በኃላ በ8ኛው አ.ሂ በረመዷን 20 ላይ ነበር.... መካ ሀገር በሙስሊሞች የተከፈተችው።

#ረመዷን_21

ከሂጅራ በኃላ በ3ኛው አ.ሂ በረመዷን 21 ላይ ነበር .... መልዕክተኛው ﷺ ለልጅ ልጃቸው "ሑሰይን" ዐቂቃ ያረዱት። (ዐቂቃ ማለት ለተወለደ ልጅ በ7 አመቱ የሚታረድ እርድ ነው )።

:¨·.·¨: ❀
 `·.ሑሰይን የዐብደሪይ ወዳጅ
T.me/husseyn_y_abdery_wedaj
ለእርዚቅ አስፈላጊ ስለሆነ ሒርዝ ላስታውሳችሁ ወደድኩ!

በዛሬው #21ኛው የረመዷን ለይል ከፈጅር (ጉህ ከቀደደ በኃላ) ፀሃይ ከመውጣቷ በፊት ባለው ጊዜ መካከል 100 ጊዜ "ياباسط" ብሎ መፃፍ በአሏህ ፍቃድ አመቱን ሙሉ እርዚቅ ያሰፋል ብለዋል ሸይኸና ሸይኽ ዐብደሏህ አል-ሐረሪይ (ረሕማቱሏሂ ዐለይሂ)።

እንደዚሁም በረመዷን #27ኛው ለይል ከፈጅር ሶላት በኃላ በሰገዱበት ቦታ ላይ ተቀምጦ 100 ጊዜ "ياباسط" ብሎ ጽፎ መያዝ በአሏህ ፍቃድ እስከ ቀጣዩ አመት ረመዷን ድረስ ለእርዝቅ ይጠቅማል።


:¨·.·¨: ❀
 `·.ሑሰይን የዐብደሪይ ወዳጅ
T.me/husseyn_y_abdery_wedaj
ረመዷን ሆይ! እርምጃህ ምን ያህል ፈጣን ነው!፣ በናፍቆት መጥተህ በችኮላ ታልፋለክ!፣ እባክህን ቀስ በል!!

አሏህ ሆይ! ያሳለፍነውን መልካም ተቀበለን፣ ቀሪዎቹን አግዘን፣ ለይለተል ቀድርን ወፍቀን፣ ከእሳት ነፃ ከተባሉ ባሮችህ አድርገን!🤲

:¨·.·¨: ❀
 `·.ሑሰይን የዐብደሪይ ወዳጅ
T.me/husseyn_y_abdery_wedaj
#ረመዷን_22

ከሂጅራ በኃላ በ40ኛው አ.ሂ፣ በረመዷን 22 ላይ ነበር ሐሰን ኢብኑ ዐልይ አባታቸው ከተገደሉ  በኃላ ኺላፋነትን የተረከቡት። (ዐለይሂመ ሰላም)

#ረመዷን_23

በሂጅራ አቆጣጠር በ9ኛው አ.ሂ፣ በረመዷን 23ተኛው ቀን ላይ ነበር ... ሱሓቢዩ  "ሙጊራ ኢብኑ ሹዕባ"   ሙሽሪኮች የሚገዙትን "አል-ላት" የተባለን ጣኦት ያፈረሰው።

ረመዷን_24

በዑመር ኢብን አል-ኸጧብ ትዕዛዝ ዐምር ኢብን አል-ዐስ በሂጅራ አቆጣጠር  በ20ኛው አ.ሂ ግብፅን ከፍተዋል። በ21ኛው አ.ሂ፣ በረመዷን 24 ደግሞ በግብፅ ሚገኘው "ዐምር ኢብን አል-ዐስ" በመባል በስማቸው የተሰየመው  መስጅድ ግንባታው ተጠናቋል።

#ረመዷን_25

ከሂጅራ በኃላ በ8ኛው አ.ሂ፣ በረመዷን 25  ነበር መልእክተኛው ﷺ ኻሊድ ኢብኑ ወሊድን ጣኦታትን እንዲያፈርስ የላኩት፤ እንዲያፈርስ ከተላከበት ጣኦታት መካከል "ዑዛ" የተባለ ጣኦት ይገኝበታል። እንደዚሁም ዐምር ኢብን አል- ዐስ "ሱዋዕ" የተባለን ጣኦት እንዲያፈርስ  የተላከው እንዲሁም ኢብኑ ዘይድ አል-አሽሃሊይ "መናት" የተባለን ጣኦት እንዲያፈርስ የተላከው በዚህ ተመሳሳይ ቀን ነበር ።

#ረመዷን_26

በሂጅራ አቆጣጠር በ9ነኛው አ.ሂ ፣ በረመዷን 26  ነበር  መልእክተኛው ﷺ ከሱሓቦቻቸው ጋር ከተቡክ ዘመቻ የተመለሱት።

#ረመዷን_27

በሂጅራ አቆጣጠር በ2ኛው አ.ሂ፣ በረመዷን 27  ነበር  "ዘካተል ፊጥር" ግዴታ የሆነው።

:¨·.·¨: ❀
 `·. ሑሰይን የዐብደሪይ ወዳጅ
T.me/husseyn_y_abdery_wedaj
አሏህ ሆይ! ከሺህ ወር በላጭ ናት ብለህ የገለጽካትን "ለይለተል ቀድር" ከተጎናፀፉ ባሮችህ አድርገን!

አዛኙ ጌታችን ሆይ! በዚህ የተባረከ ለይል የሁለት ሀገር ደስታ፣ የተቅዋ ስንቅ፣ ከፍ ያለ ደረጃን ወፍቀን!

ይቅር ባይ የሆንከው ጌታችን ሆይ! ያንተ ጭፍሮች አሸናፊ ናቸውና ከጭፍሮችህ፣ ያንተ ወልዮች ፈርሃትና ሐዘን የለባቸውምና ከወልዮችህ አድርገን!

በራስህ የተበቃቃህ፣ ህያው የሆንከው ጌታችን ሆይ! ይህን የተባረከ ወር በይቅርታህ፣ በማርታህ፣ በውዴታህ እንዲሁም ከእሳት ነፃ ተብለው ከሚጨርሱ ባሮችህ አድርገን!

ያ! ዘል ጀላሊ ወል ኢክራም
ያ! ሐዩ  ያ! ቀዩም
ያ! አርሐመ አራሒሚን

አሏሁመ አሚን ያ! ረበል ዓለሚን 🤲

:¨·.·¨: ❀
 `·. ሑሰይን የዐብደሪይ ወዳጅ
T.me/husseyn_y_abdery_wedaj
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ዒድ ሙባረክ ኩሉ ዓም ወአንቱም ቢኸይር!🥰

:¨·.·¨: ❀
 `·. ሑሰይን የዐብደሪይ ወዳጅ
T.me/husseyn_y_abdery_wedaj
[ስሟ መስጅድ ላይ የተፃፈው የአሮጊት ሴትዮ ታሪክ]

በድሮ ጊዜ ከነግስታት መካከል አንድ ንጉስ በከተማው ላይ መስጂድ ለመስራት ፈልጎ  በዚህም መስጅድ ስራ በገንዘብም ሆነ በሌላ ነገር ማንም ሰው እንዳይሳተፍ አዘዘ።

በእርግጥም ንጉሱ በፈለገው መልኩ ያለምንም የሌላላ ሰው እገዛ የመስጅዱ ግንባታ ተጠናቆ በበሩ ላይም ስሙ እንዲፃፍ አዘዘ።

አንድ ቀን ሌሊት ንጉሱ በህልሙ ከሰማይ መላኢካ ወርዶ የሱን ስም ከመስጂዱ ደጃፍ ላይ ሰርዞ በስፍራው ላይም የሴት ስም ሲጽፍ ተመለከተ።

ታዲያ ንጉሱ ከእንቅልፉ በፍርሐት በመንቃት በመስጂዱ በር ላይ ስሙ መኖሩን  ለማረጋገጥ ወታደሮቹን ላከ፤ ወታደሮቹ ተመልሰው ስሙ  እንዳለ ነገሩት።

በሁለተኛው ሌሊት ንጉሱ ያንኑ ህልም አይቶ ከእንቅልፉ በተነሳ ጊዜ ስሙ  መኖሩን ለማረጋገጥ ወታደሮቹን ለሁለተኛ ጊዜ ላካቸው፤  እነርሱም ሄደው ተመልሰው  ስሙ እንዳለ ነገሩት፤ ንጉሡም በጣም ተገረመ።

በሦስተኛው ሌሊትም ያንኑ ህልም ተደጋገመበት..... ንጉሡ  ከእንቅልፉ በነቃ በሕልሙ መስጅዱ ላይ ስሟ የተጻፈላትን ሴትዮ ሥሟን ሸምድዶ ስለ ነበር ወታደሮቹ እሷን ፈልገው ወደሱ እንዲያመጧት አዘዘ።

ወታደሮቹም እስኪያገኟት ድረስ ተበታተነው  ፈልገው  ወደ ንጉሡም አቀረቧት ፤ ሴትዮዋ ሚስኪን አሮጊት ነበረች፤ ወደ ንጉሱ ስትቀርብ በፍርሃት ተንቀጠቀጠች።

በመቀጠልም ንጉሱም «እኔ በሰራሁት መስጅድ ላይ ረድተሻል?» በማለት ጠየቃት። እሷም፡- «ንጉሥ ሆይ! እኔ ምስኪን አሮጊት ነኝ፣ በምትሰራው መስጅድ ላይ  ማንም በምንም ነገር  እንዳይረዳህ ስትከለክል ሰምቻለሁ» አለች።

እሱም፦ «በአሏህ እጠይቅሻለሁ ይህን መስጅድ ለመስራት ምን አስተዋፅኦ አድርገሻል?» አላት።

እሷም፦«ከዕለታት አንድ ቀን በመስጅዱ ጎን ሳልፍ ለመስጅ ስራ የሚውል እንጨትና የግንባታ መሳሪያ የተሸከመች እንስሳ ውሃ ተጠምታ ተመለከትኩ፤ የታሰረችበት ገመድ አጭር በመሆኑ ምክንያት በአቀራቢያዋ ከነበረ የውሃ ባልዲ  ደርሳ መጠጣት  አልቻለችም። በዚህ ሰኣት ለአሏህ ብዬ ውሃው ወደሷ አስጠግቸላት እስክትጠግ ጠጥታ ከሞት ተረፈች፤ እኔ ያደረኩት ይህ ብቻ ነው አለች።

ንጉሱም በመገረም «ሱብሐን አሏህ! አንቺ ለአሏህ ብለሽ በመስራት ተቀባይነት አገኘሽ፣ እኔ ግን  የሰራሁት የንጉሱ መስጊድ ተብሎ እንዲጠራ ስለነበር አሏህም ሳይቀበለው ቀረ»አለ።

በመቀጠልም ንጉሱ ተውባ አደረገ፤ የአሮጊቷ ስምም በመስጅዱ በር ላይ እንዲፃፍ ካደረገ በኃላ እስከ መጨረሻው እድሜዋ በድሎት ምትኖርበትን ገንዘብ ሰጦ ሸኛት።

<ማንኛውም መልካም ስራ ከአሏህ ዘንድ ተቀባይነት ሚያገኘው በኒያ ልክ ነው>

አሏህ መልካም ስራቸው ለሱ  ከሆኑ ባሮች ያድርገን!

:¨·.·¨: ❀
 `·. ሑሰይን የዐብደሪይ ወዳጅ
T.me/husseyn_y_abdery_wedaj
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
አሏህ ከዓለማት የተብቃቃ፣ የማይቀያዬር ጌታ ነው። By zahraa toameh

:¨·.·¨: ❀
 `·. T.me/husseyn_y_abdery_wedaj
[ የሚስጢር ባለቤት ሆይ! ሚስጢሩ ተጋለጠ!!]

*አስገራሚና አስተማሪ ታሪክ*

...ማሊክ ኢብኑ ዲናር (ረሒመሁሏህ) እንዲህ ይላል፡- በስራ ከተማ ገባሁ ...አንድ ቀን ሰዎች በታላቁ መስጂድ ከዙሁር ሶላት ጀምረው እስከ ዒሻእ ሶላት በኃላ ድረስ ተሰብስበው አሏህን ሲለምኑ ተመለከትኩ .... "ምን አጋጠማችሁ ?"  አልኳቸው።

እነሱም "ሰማይ ውሃ ከማውረድ ተቆጠበ፣ ወንዞቹም ደረቁ፣አሏህ ዝናብ እንዲያወርድልን ዱኣ እያደረግን ነው" አሉ።

ማሊክ እንዲህ ይላል፡- "ከዛም ሁሉም ወደ ቤታቸው ሄዱ፤ ለሀገሪቷ እንግዳ ስለነበርኩ በመስጅድ ውስጥ ተቀምጬ ቆዬሁ። በዚህ ሰኣት አንድ ጥቁር፣ አፍንጫው አጭር፣ ሆዱ የገፋ ፣ ከድህነቱ የተነሳ በአንድ ቁራጭ ልብስ  እፍረተ ገላውን የሸፈነ፣ ሌላኛውን ጫንቃው ላይ ያደረገ ሰውዬ ወደ መስጅድ ገብቶ ሁለት ረከዓ ሰገደ፤ ከዛም በመስጅዱ ውስጥ ሰው መኖሩን ለማረጋገጥ ግራ ቀኝ ዞረ... እኔ ያለሁበት ቦታ ትንሽ የተደበቀ ስለነበር ሳያዬኝ ቀርቶ ሰው የለም በማለት ወደ ቂብላ ዞሮ እጆቹን በማንሳት፡- "አሏህ ሆይ! ባሮችህን ስርኣት ለማስያዝ ዝናብ እንዳይወርድ አግደሃል፤ በባሮችህ ኃጢኣት ላይ ታጋሽና ይቅር ባይ የሆንከው ጌታ ሆይ!  ባሮችህን ውሃ ታጠጣቸው ዘንድ እማፅንሃለሁ!" አለ።

እጆቹን ከማውረዱ ሰማዩ ጨለመ፣ ደመናም ከየቦታው መጦ ከደመነ በኃላ ዝናቡ ዘነበ። ሰውዬው በጣም ስላስደነቀኝ ከመስጅድ ወጥቶ ወደ ቤቱ ሲሄደ ተከተልኩት... የተወሰነ ከተጓዘ በኃላ አንድ ቤት ውስጥ ገባ፤ ቤቱን በማግስቱ ለማግኘት ብዬ በሩ ላይ በጭቃ ምልክት አደረኩና ተመለስኩ።

በማግስቱ ፀሀይ ስትወጣ መንገዶቹን ተከትዬ ምልክት ያደረኩበትን ቤት ደረስኩ፤ ቤቱ የባሪያ መሸጫ ቤት ነበር ። የባሪያ ነጋዴውን "ባሪያ መግዛት እፈልጋለሁ" አልኩት። ነጋዴውም ረዢምና አጭር የተለያዩ ባሪያዎችን አሳዬኝ... የፈለኩትን ስላላገኘሁ "ከነዚህ ውጪ ሌላ አለህ?" አልኩት።

ባሪያ ነጋዴው፡- "ከነዚህ ውጭ የሚሸጥ ምንም የለኝም" አለ።
ማሊክ፦"ተስፋ ቆርጬ ከባሪያዎች ቤት ውጭ ተቀምጬ ባለሁበት ሰኣት ከበሩ አቅራቢያ ከእንጨት የተሰራ ጎጆ አየሁና..በዚህ ጎጆ ውስጥ ሰው አለ ወይ? " አልኩ።

ባሪያዎቹ " አንተ ባርያ መግዛት ነው የምትፈልገው በዚህ ውስጥ ያለው ባሪያ ግን ላንተ የሚገባ ባሪያ አይደለም አይመጥንህም" አሉ።

ማሊክ ፦"ላየው ፈልጋለሁ ይውጣ ብያቸው ባሪያው ከጎጆው ሲወጣ ያ! ትላንት በመስጅድ ውስጥ ሲሰግድ ያዩሁት ሰውዬ ነበር" አለ።

ማሊክ ለባሪያ ነጋዴው "ልገዛው እፈልጋለሁ" አለ።
ነጋዴው፦ " ይህ ባሪያ ለምንም ነገር ስለማይሆን ከሸጥኩልህ በኃላ ምናልባት አታሎ ነው የሸጠልኝ ብለህ ስሜን ታጠፋ ይሆናል!" አለ።
ማሊክ፦"እንዳሰብከው አይደለም ልገዛው ስለፈለኩ ነው" አለ....ነጋዴውም በርካሽ ዋጋ ሸጠለት ።

ማሊክ እንዲህ ይላል ፦ ይህን ባሪያ ወደ ቤቴ ወስጄው የተወሰነ ከተቀመጠ በኃላ አንገቱን ቀና አደረገና ጌታዬ ሆይ! ጥንካሬን ከፈለግክ ከኔ የሚበረታ አለ፣ ዝናን ከፈለክ ከኔ የበለጠ ቆንጆ አለ፣ ለስራ ከሆነ ደግሞ ከኔ የበለጠ አዋቂ አለና ለምን ገዛኸኝ?" አለ።

ማሊክ፦ "ትላንት የበስራ ከተማ ነዋሪዎች በሙሉ ባጋጠማቸው ድርቅ ምክንያት በመስጅድ ውስጥ ከዙሁር ሶላት እስከ ዒሻእ ሶላት በኃላ ድረስ ዱኣ ሲያደርጉ ቆይተዋል...
ነገር ግን ልምናቸው ተቀባይት አላገኘም ነበር። አንተ ግን መስጅድ ገብተህ እጆችህን አንስተህ አሏህን በለመንክ ሰኣት ልመናህ ተቀባይነትን አግኝቶ ዝናብ ወረደ” አለው።

አገልጋዩ፡-" ምናልባት ሌላ ይሆናል! ምንስ አሳወቀህ ምናልባት ያየኸው ሌላ ሰው ሊሆን ይችላል” አለ።

ማሊክ፦"ይልቁንስ! አንተ ነህ" አልኩት፤ አገልጋዩም፡- "አውቀኸኛል?"አለ፤
ማሊክ፦"አዎ!" አለ፤
አገልጋዩ ፡- "እርግጠኛ ነህ? " አለ፤
ማሊክ "አዎ!"አለ።

ማሊክ እንዲህ ይላል፦ "በአሏህ እምላለሁ! ከዛ በኋላ ወደኔ አልተመለከተም፤ ወዲያውኑ ለአሏህ ሱጁድ ወረደ...ስግደቱንም አራዘመ፤ ወደሱ በደንብ ስቀርብ፦ «የሚስጢሩ ባለቤት ሆይ! ሚስጥሩ ተጋለጠ፣ ይህ ሚስጢር ተስፋፍቶ ህይወትን መቋቋም አልችልም።» ሲል ሰማሁ ... ብዙም ሳይቆይ ነፍሱ ከሱ ተለይታ ይችን ዓለም ተሰናበተ።" #ሱብሐን_አሏህ

አንዳንድ የአሏህ ባሮች መልካም ስራቸውንም ሆነ ከአሏህ ዘንድ ያላቸውን ደረጃ በዚህ ልክ ነበር የሚደብቁ፤ እኛስ በኛና በአሏህ መካከል የቱን ያህል የመልካም ስራ ሚስጢር አለን!።

አሏህ ሆይ! ነውራችን ሸፍንልን፣ ላንተ ያለንን ፍራቻ ከአለት የጠና አድርግልን!
አሏህ ሆይ! ከንፁህ፣ ጨዋ፣ ታማኝ፣ አንተን ሲቀርቡ ከሚጽናኑ፣ መልካም ስራቸው ላንተ ከሆኑ ባሮች ያድርገን!
አሏህ ሆይ! በፍላጎትህና ውሳኔህ ደስተኞች አድርገን፣ቃል በገባህላቸው የዘላለም ደስታ ከሚጠቃቀሙ ባሮችህ አድርገን!።

:¨·.·¨: ❀
 `·. ሑሰይን የዐብደሪይ ወዳጅ
T.me/husseyn_y_abdery_wedaj