አቡ ሱሀይል
1.96K subscribers
610 photos
37 videos
22 files
156 links
ﺑِﺴْﻢِ ﺍﻟﻠَّﻪِ ﺍﻟﺮَّﺣْﻤَﻦِ ﺍﻟﺮَّﺣِﻴﻢِ
"ﺍﻗْﺮَﺃْ ﺑِﺎﺳْﻢِ ﺭَﺑِّﻚَ ﺍﻟَّﺬِﻱ ﺧَﻠَﻖَ"
"አንብብ በዚያ(ሁሉን)በፈጠረው ጌታ ስም"
አል ዐለቅ ምእራፍ/1

በዚህ ገፅ ላይ የተለያዩ ኢስላማዊ መልእክቶችና፣በተለያየ ዘርፍ የሚሰጡ ት/ቶችን በድምፅና በቪዲዮ ያገኙበታል።
Download Telegram
እንዲህ ያሉ የበቁ፣የጠለቁ ጉምቱ ሊቃውንቶችን የእውቀት ማዕድ መሳተፍን ቸል አትበል፣ ምናልባትም ከአንደበታቸው ከሚወጡ ቃላት አንዱ ለህይወትህ መቀየር ምክንያት ይሆናል!!!
ዘይድ አል-ያሚይ(ረ.ዐ) እንዲህ ይላሉ፡-
"አንዲትን ቃል አደመጥኩ፣እናም አላህ በዛች ቃል ለሰላሳ ዓመታት ጠቀመኝ !"

▫️ ሲየር
____
የባላንጣህን ጨለማ ከማኮሰስ፣ቅድሚያ የራስህን ፋኖስ ለኩስ፣ካንተ ሚጠበቀውን በአግባቡ ከውን፤ያኔ ጨለማው በራሱ ሰአት ይጠፋል፣የፊትናው እሳትም ቀስ በቀስ ይከስማል ።
ለዑለሞች ያላችሁን ውዴታና ክብር፣ምስላቸውን ፕሮፋይል ላይ ከመለጠፍና፣አብሮ ፎቶ ከመነሳት ይልቅ ብዙ መስዋዕትነት ከፍለው ያመጡትን ዒልም በመቋደስ ግለፁ፤ዙሪያቸውን ከባችሁ በጥሞና በማድመጥ መስመራቸውን ለመጠበቅ ሞክሩ !!!!
ካለፉ በዃላ ታሪካቸውን ከመዘከር በፊት፣በህይወት እያሉ እንጠቀምባቸው።
___
# በረመዳን ምክንያት ተቋርጦ የነበረው የክቡር ዶክተር ተቀዳሚ ሙፍቲ ሀጅ ዑመር እድሪስ የተፍሲር ፕሮግራም ተጀምሯል ፕሮግራሙም ሰኞ ማክሰኞ ጁመዐ ቅዳሜ ይካሄዳል ።
# አላህ ረዥም እድሜ፣ከዓፊያ ጋር ለሸይኾቻችን ይለግስልን 🤲
እኛም ደረጃቸውን ተረድተን፣ከእውቀታቸው የምንጨልፍ፣ከበረከታቸው የምናተርፍ ያድርገን 🤲
<<<>>>>
T.me/hamidabuhamid
አል መዕዋ ኢስላማዊ ድርጅት የተለያዩ መድረሳዎችን ሐሪማዎችን ኡለማዎችን በመርዳት ላይ ይገኛል። አልመዕዋ እንዴት እንደተመሰረተ እና ምን ምን ስራዎችን በመስራት ላይ እንደሚገኝ ከ አልመዕዋ መስራች ኡስታዝ አንዋር አህመድ ጋር ያደረግነውን ቆይታ በዩቲውብ ይከታተሉ ።
https://youtu.be/-jVv30U1Ozs?si=VFASU-FiAiuSrPr0
https://youtu.be/-jVv30U1Ozs?si=VFASU-FiAiuSrPr0
https://youtu.be/-jVv30U1Ozs?si=VFASU-FiAiuSrPr0
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
{إِنَّا لَنَنصُرُ رُسُلَنَا وَالَّذِينَ آمَنُوا فِي الْحَيَاةِ الدُّنْيَا وَيَوْمَ يَقُومُ الْأَشْهَادُ}

{እኛ መልክተኞቻችንን፣ እነዚያንም ያመኑትን በቅርቢቱ ሕይወት ምስክሮችም በሚቆሙበት ቀን በእርግጥ እንረዳለን፡፡}
[ ሱረቱ አል-ሙእሚን - 51 ]
#ለይለቱል ጁሙዐህ

اللَّهمَّ صلِّ صلاةً كاملةً، وسلِّم سلامًا تامًّا، علىٰ نبيٍّ تنحلُّ به العقدُ، وتنفرجُ بهِ الكُرَبُ، وتُقْضَىٰ بهِ الحوائجُ، وتُنالُ بهِ الرَّغائبُ، وحسنُ الخواتيم، ويُسْتَسْقىٰ الغمامُ بوجههِ الكريم، وعلىٰ آلهِ.
ከደረጃው በላይ ከፍ ያደረግከው
ከደረጃህ በታች ዝቅ ያደርግሃል።
- ኢማም ዐሊይ ቢን አቢ ጣሊብ(ቁ.ሲ)
#ከቁርኣን ማዕድ
_
ዐረቦች በምድረ በዳ ላይ ለብቻዋ የምትገኝን ነጠላ ዛፍ “ضالة” ብለው ይጠሯታል፣ለመንገዳቸውም ጠቋሚ ሆና ይመሩባታል፤ኃያሉ አላህም ﷻ ለነቢያችን ሙሐመድ ﷺ
{وَوَجَدَكَ ضَاۤلࣰّا فَهَدَىٰ}
{በሐይማኖትህም ላይ ብቸኛ ሆነህ አገኘህ፣ባንተም ሌሎችን መራ}
__
ኢማም አል-ቁርጡቢ በ [አል-ጃሚዕ ሊ–አሕካሚል–ቁርኣን] ላይ ከጠቀሱት
# እውቀትን በማርከስ ……… መሀይማንን አታንግስ
__
  እውቁ የቋንቋ ሊቅ ሲيበወይህ (ረ.ዐ) ሐዲስን ፍለጋ ወደ ሐዲሱ ሊቅ ሐም’ማድ ቢን ሰለማህ (ረ.ዐ) ዘንድ ተቀምጠው ሳለ፣በአንድ ሐዲስ ንባብ ወቅት የዐረብኛ ሰዋሰዋዊ ስህተት ይሳሳታሉ
ሸይኹም:– ሲበወይህ…ተሳስተሃል! በማለት ያዟቸው
ተማሪው ሲበወይሂም:“ፈፅሞ ስህተት የማታገኝብኝን እውቀት ሄጄ እቀስማለው” በማለት ቃል ገብተው … ወደ ቋንቋው ሊቀ ሊቃውንት ወደ ኸሊል ቢን አሕመደል–ፈራሂዲይ(ረ.ዐ) ያቀናሉ፤ከስራቸውም ለረዥም በመቆየት በነሕው እውቀት የላቁ፣የበቁ፣የመጠቁ ታላቅ ሊቅ ሆኑ!!!
   __
ሹዕባህ ቢን ሐጃጅ (ረ.ዐ) የትኛውም ሰው ነሕውን ሳይማር ወደ ሐዲስ ዘገባ እንዳይሸጋገር ይከለክሉ እንደነበር ተዘግቧል።
እንዲህም በማለት ያወግዛሉ :–

«مَنْ طَلَبَ الْحَدِيثَ فَلَمْ يُبْصِرِ الْعَرَبِيَّةَ، فَمَثَلُهُ مَثَلُ رَجُلٍ عَلَيْهِ بُرْنُسٌ وَلَيْسَ لَهُ رَأْسٌ»
“ ዐረብኛ ሳያጠና ሐዲስን መማር የሚፈልግ ሰው ምሳሌ፣ ራስ ሳይኖረው፣ረዥም ኮፊታ እንዳጠለቀ ሰው ነው ”

ሐም’ማድ ቢን ሰለማህም (ረ.ዐ) እንዲህ ብለዋል፡-

{ من طلب الحديث ولم يتعلم النحو - أو قال العربية - فهو كمثل الحمار تعلق عليه مخلاة ليس فيها شعير .}
  “ነሕው” ወይም ዐረብኛን ሳይማር፣ሐዲስን የፈለገ ሰው፣ገብስ የሌለው ዘንቢል እንደተንጠለጠለበት አህያ ነው።
__

መሠረታዊ የሸሪዓ ምንጭ የሆኑት ቁርኣንና ሐዲስን  ለመገንዘብ እንደ መገልገያነት የተቀመጡ የሸሪዓ እውቀቶችን ማናናቅ፣በቁርኣንና ሐዲስ ንበት ወቅት የሚፈጠሩ ሰዋሰዋዊ ስሕተቶችን –ዋናው መልእክቱ ነው–በሚል የሰነፍ አባባል አመኻኝቶ እንደ ተራ መቁጠር ብዙኃኑ ዘንድ ለእውቀት ዋጋ ማነስ፣ለመሀይምነት መስፋፋት ዋነኛ ምክንያት መሆኑ በደማቁ ሊሰመርበት ይገባል።
  ሲቀጥልም የቁርኣንና ሐዲስ ክብርን በልባቸው ያነገሱ፣የዒልም ዋጋን የተገነዘቡ፣በሸሪዓ ጉዳይ ማንም እየተነሳ አፉን እንዳይከፍት ብርቱ የእውቀት አጥርን ያበጁ፣እውቀቶችን በየ ፈርጁ፣እንደየ ደረጃው ያደራጁ የቀደምት ሊቃውንትን የእድሜ ልክ ልፋት እውቅና መንፈግ፣ከምንም ያለመቁጠር የከፋ ድንቁርና ማንፀባረቂያም ነው።
____
በትንሹም ቢሆን ቀደምቶች ሸሪዓን ጠብቀው ወዳንተ ለማድረስ የከፈሉትን መስዋአት፣እውቀቱን አበጥረውና አንጥረው ከትውልድ ትውልድ ያሸጋገሩበትን አስቸጋሪ ሒደት ለመረዳት ይህንን በምስሉ ላይ ያስቀመጥኩልህ የሸይኽ ዐብዱል ፈት’ታሕ አቡ ጙድ’ዳን (ረ.ዐ) መጽሐፍ አንብብ።
____
ወስ’ሰላም 🙏
# ተውሒድ
ከ “እኔ” እና ከ“መሰሎቹ” መንፃት ነው!!
"ለመታየት ሳይሆን ለማየት … ከፍ በሉ"
# ሰዪዱና ዐሊይ(ከ.ወ)
# የኸሚስ ምሽት …… ብስራት
_
ኢማም አሕመድ በሙስነድ የሐዲስ ጥራዛቸው ላይ እንዳሰፈሩት
ሰሓቢዩ ኢብኑ ዐባስ (رضي الله عنه ) እንዲህ አሉ:“አንድ ቀን የአላህ መልእክተኛ ﷺ ወደ ዘምዘም ውሃ ዘንድ መጡ፣ከጉድጓዱ ቀድተን አንድ አኮሌን አቀበልናቸውና ጠጡ፤ከዛም ምራቃቸውን ተፉበት፤እኛም ወደ ዘምዘም(ጉድጓድ)ውስጥ ጨመርነው”

ዘምዘም ከውሃዎች ኹላ ምርጥ እና በላጭ ውሃ ነው፤ዓለም ላይ ከተፈጠሩት ነገራት ኹላ በላጭ የሆኑትን ውድ ነቢይ ﷺ ትፍታ አግኝቶ በረከትነቱ እጅጉን ላቀ፤እናም ከዛች ትፍታ በዃላ ከዘምዘም ውሃ የጠጣ ሰው፣ከሰዪዳችን ﷺ ምራቅ ድርሻውንም እንዳገኘ ይህ ሐዲስ ያበስረዋል !!!

# በሰለዋት የሚገኘውን በረከት፣በዛሬዋ ሌሊት የምናገኝ ያድርገን

اللهم صل وسلم علىٰ سيدنا محمد ﷺ
#ለመጓተትም የጋራ የሆነ ገመድ ያስፈልጋል !!!

አዋቂ የሆነ ሰው ከመሃይም ወይም ከደረቅ ጋር በፍፁም መሟገት የለበትም !
መሀይም … ሙግትን ያለ ምስጋና እውቀት መቅሰሚያ መንገድ ያደርገዋል !!!

# ኢብኑ ዐብዲል–በር
# ጃሚዑ በያኒል–ዒልሚ ወፈድሊህ/213
=====
ሙግትም ሆነ ክርክር የራሱ የሆኑ ስርኣቶችና መርሆች ተበጅተውለታል፣ከመጣ ከሄደው ጋር እየተሟገትክ፣እውቀትን አታራክስ !!!
“ዐንተራ”ን ከአንድ በሬ ሲሸሽ የተመለከቱት ሰዎች
አንተ ዐንተራ አይደለህ እንዴ!ድፍረትህስ የት ሄደ? እንዴት ትሸሻለህ?! ይሉታል
እርሱም
ዐንተራ መሆኔን በሬው መች ያውቅና!!
ሲል መለሰላቸው !!! ይባላል
____
እናም! የእውቀት ጡንቻህን በመሀይም ሰው ፊት ለማሳየት አትሞክር !!!
# ይህን ሐዲስ በልብህ ላይ አኑረው፣ምላሹንም ተዘጋጅበት !!!

مَا مِنِ امْرِئٍ يَخْذُلُ امْرَأً مُسْلِمًا فِي مَوْضِعٍ تُنْتَهَكُ فِيهِ حُرْمَتُهُ، وَيُنْتَقَصُ فِيهِ مِنْ عِرْضِهِ؛ إِلَّا خَذَلَهُ اللهُ فِي مَوْطِنٍ يُحِبُّ فِيهِ نُصْرَتَهُ.
وَمَا مِنِ امْرِئٍ يَنْصُرُ مُسْلِمًا فِي مَوْضِعٍ يُنْتَقَصُ فِيهِ مِنْ عِرْضِهِ وَيُنْتَهَكُ فِيهِ مِنْ حُرْمَتِهِ؛ إِلَّا نَصَرَهُ اللهُ فِي مَوْطِنٍ يُحِبُّ نُصْرَتَهُ.
نبينا ﷺ
“ክብሩ በሚነካበት፣መብቱ በሚጣስበት ቦታ ላይ አንድ ሙስሊም ወንድሙን ከመርዳት የታቀበ ሰው፣የአላህን እርዳታ በሚፈልግበት ቦታ ላይ አላህ ያዋርደዋል

ክብሩ በሚነካበት፣መብቱ በሚጣስበት ቦታ ላይ አንድ ሙስሊም ወንድሙን የረዳ ሰው፣የአላህን እርዳታ በሚፈልግበት ቦታ ላይ አላህ ይረዳዋል”

#ረሱለላህ
# አቡ ዳውድ ዘግበውታል