ᴛʜᴇ ɴᴇᴡs Ʀᴇᴘᴏʀᴛ
921 subscribers
903 photos
105 videos
1.01K links
International Affairs, Breaking News, Politics, Sports, Trends and Global Happenings from Africa to Middle East and beyond!

♠️ Kingdom of Ethiopia
Download Telegram
የቤጂንግ እና የታይዋን ፍጥጫ!
#China #Taiwan

  ቤጂንግ ታይዋንን አጣብቂኝ ውስጥ የሚከት ወታደራዊ ልምምድ በታይዋን አቅራቢያ መጀመሯ ቤጂንግ ከተቻለ በሰላም ካልሆነ ጊዜ ጠብቃ ታይዋንን ወደ ግዛቷ የማስገባቷ ነገር ጥያቄ ውስጥ እንኳን የማይገባ ነው ይላሉ ተንታኞች። ታይዋን ከ1949 ጀምሮ ራሷን ከቻይና አግልላ ማየት ብትጀምርም ቻይና ግን እስከዛሬ ድረስ ታይዋንን እንደ አንድ ግዛቷ እንደምታያት ደጋግማ ገልፃለች።

  በ1979 በዛን ወሳኝ ወቅት ዩናይትድ ስቴትስ ከቻይና ሕዝባዊ ሪፐብሊክ (ታይዋን) ጋር መደበኛ ግንኙነት በመፍጠር ታሪካዊ ዲፕሎማሲያዊ ለውጥ ጀመረች። ይህ ወሳኝ ውሳኔ አሜሪካ ከቻይና ሪፐብሊክ ጋር ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቷ እንዲቋረጥ እና የጋራ መከላከያ ውላቸው እንዲፈርስ ምክንያት ሆኗል።

ዩናይትድ ስቴትስ ከደሴቲቱ ጋር ጥብቅ እና ጠንካራ ይፋዊ ያልሆነ ግንኙነት በመመሥረት ለሠራዊቷ አስፈላጊ የሆኑ የመከላከያ መሳሪያዎችን ማቅረቧን አላቆምም ማለቷ ቤጂንግ ዋሽንግተን እነዚህን የጦር መሳሪያዎች ሽያጭ እንድታቆም እና ከታይፔ ጋር ያለውን ግንኙነት እንድታቋርጥ እንድትጠይቅ አድርጓታል። 
  በነዚህ ሀይሎች መካከል እየታየ ያለው የጂኦፖለቲካዊ ዳንስ የአለም አቀፍ ግንኙነቶችን መልክዓ ምድራዊ አቀማመጥ መለወጡ አይቀርምና ቤጂንግ የጦር ሃይሏን ተጠቅማ ይህንን ለማስተካከል ዝግጁ መሆኗን እያሳየች ነው የሚሉም አይጠፉም።

  ቻይና ታይዋንን እንዴት እና መቼ ታጠቃለች የሚለው ጥያቄ በባለሙያዎች መካከል የጦፈ የክርክር ርዕሰ ጉዳይ እንደሆነ ቀጥሏል። እ.ኤ.አ. በ2021 በኢንዶ-ፓሲፊክ ውስጥ የነበረ አንድ የአሜሪካ ከፍተኛ ወታደራዊ አዛዥ ቻይና በሚቀጥሉት አስርት ዓመታት ውስጥ ወረራ ልትሞክር እንደምትችል የሚጠቁም ከባድ ማስጠንቀቂያ ሰጥቶ የነበረ ሲሆን ይህ ማስጠንቀቂያ ለሰላማዊ መፍትሄ መስኮቱ እየጠበበ ሊሆን ይችላል በሚለው ሰፊ ስልታዊ ስጋት አጽንኦት ተሰጥቶታል።

  አንዳንድ ተንታኞች፣ ምናልባት 2049 ለቻይና ትልቅ ምዕራፍ ነው ብለው የወረራውን የጊዜ ግምት ሲያስቀምጡ ሌሎች ግን ቀጣይ አስርት አመታት ለቻይና አመቺ ሊሆናት ይችላል ሲሉ መላምታቸውን ገልጸዋል።

በ2022 መጀመሪያ ላይ ሩሲያ በዩክሬን ላይ ባደረገችው ድፍረት የተሞላበት ወረራ የጂኦፖለቲካው ስሌት የበለጠ የተወሳሰበ ነበር። ይህ ያልተጠበቀ ጥቃት ክርክሩን እንደገና በመቀስቀስ ተንታኞች በታይዋን ላይ ያላቸውን አንድምታ ዳግም እንዲከፋፈሉ አድርጓቸዋል። አንዳንዶች የሩሲያ ድርጊት ቤጂንግ የሞስኮን ቁርጠኝነት እንደ አንድ ምሳሌ በመመልከት ተመሳሳይ መንገድ እንድትከተል ሊያበረታታት ይችላል ብለው ሲወስዱ በአንጻሩ ሌሎች ሩሲያ ያጋጠሟት ጉልህ ተግዳሮቶች እና አለማቀፋዊ ምላሾች እና ማዕቀቦች ቤጂንግ ከፍተኛ ጥንቃቄ እንድታደርግ ሊያደርጋት እንደሚችል ያምናሉ።

የCFR ባልደረባ ዴቪድ ሳክስ የሩሲያ እርምጃዎች ቻይና በታይዋን ላይ ኃይል ለመጠቀም ባላት ፈቃደኝነት ላይ በቀጥታ ተጽዕኖ ሊያሳድሩ እንደማይችሉ እና የተሳሳተ አመለካከት ነው ሲል በመግለፅ ይልቁንም የቻይና መሪዎች የሩሲያን የአሠራር ውድቀት በቅርበት እንደሚመረምሩ እና እነዚህን ግንዛቤዎች በመጠቀም የራሳቸውን ወታደራዊ ስልቶች በማጣራት እና ተመሳሳይ አደጋዎችን ለማስወገድ ይሰራሉ ሲል መላምቱን ያስቀምጣል።

በዚህ ውስብስብ የፖለቲካ ጨዋታ አለም ሌላ ጦርነት ማስተናገድ ትችል ይሆን..?!

ቴሌግራም፦ T.me/TheNewsReports
#JUST_IN ፡ የተመድ ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ፦ "ከዚህ ገዳይ ግጭት መሸሸጊያ የሚፈልጉ በርካታ ንፁሃን ዜጎችን የገደለውን የእስራኤልን ድርጊት አወግዛለሁ። በጋዛ ውስጥ ምንም አስተማማኝ ቦታ የለም። ይህ ጭካኔ መቆም አለበት"

Share | T.me/TheNewsReports
#BREAKING ፡ የእስራኤል ጦር ታንክ መሃል ጋዛ ከተማ ገብቷል።

- Reuters

T.me/TheNewsReports
#JUST_IN ፡ የቀድሞ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንታዊ እጩ እና የቀድሞ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አምባሳደር ኒኪ ሃሌይ በሰሜናዊ እስራኤል በሚገኘው የእስራኤል ቦምብ ቅርፊት ላይ "ጨርሷቸው! አሜሪካ እስራኤልን ትወዳለች" ስትል ፅፋለች።

Share | T.me/TheNewsReports
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#NEW ፡ አየርላንድ የፍልስጤምን ባንዲራ በፓርላማዋ ፊት ለፊት ሰቅላለች።

አየርላንድ፣ ኖርዌይ እና ስፔን ለፍልስጤም ሀገርነት በይፋ እውቅና መስጠታቸው ይታወሳል።

Share | T.me/TheNewsReports
#NEW ፡ ሰሜን ኮሪያ በቆሻሻ እና ፍግ የተሞሉ 150 ፊኛዎችን ወደ ደቡብ ኮሪያ ልካለች። ፊኛዎቹ ለሊቱን በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች ወድቀዋል።

Share | T.me/TheNewsReports
እውቁ የቀድሞ የማንችስተር ዩናይትድ ተጫዋች የነበረው ዴቪድ ቤካም በኢንስታግራም ገፁ ያጋራው ምስል

T.me/TheNewsReports
#BREAKING ፡ ብራዚል እስራኤል ያለውን አምባሳደሯን መጥራቷ ተሰምቷል።

Share | T.me/TheNewsReports
#BREAKING ፡ ስሎቬንያ ለፍልስጤም እውቅና ልትሰጥ ነው።

በዛሬው እለት የስሎቬንያ መንግስት እንዳስታወቀው ለፍልስጤም መንግስት እውቅና ለመስጠት አስፈላጊ የሆነውን ህግ በፓርላማ ፊት ለማቅረብ ተዘጋጅቷል።

Share | T.me/TheNewsReports
እጅግ ወሳኝ መረጃ!

አንዱ ገጠመኙን እንዲህ ይተርክልናል።
*
ደንበኛዬ:- "የራሴ ስልክ በእጄ እያለ ምሽት አራት ሰዓት ገደማ ላይ የማላውቃቸው ሰዎች ሞባይል ባንኪንግ በምጠቀምበት SIM ካርዴ ከባንክ አካውንቴ ብዙ ብር ወደ ራሳቸው አካውንት አስተላለፉ" አለኝ።

እኔ:- 'OTP Text አልተላከልህም?' OTP means One Time Password፣ 'ገንዘብ በMobile ባንኪንግ ለማስተላለፍ ስትሞክር ማረጋገጫ የይለፍ ኮድ ይላክልሃል'; አልኩት፣

ደንበኛዬ:- "አጭር Text  ከባንኩ ሲላክልኝ ነበር፣ ምንነቱ ስላልገባኝ ዝም አልኩ" አለኝ።

እኔ:- 'ከዛስ' አልኩት፣

ደንበኛዬ:- "አራት ጊዜ OTP TEXT ገባልኝ ቀጥሎ ተራ በተራ ገንዘብ ማስተላለፌን የሚገልጽ TEXT ከባንኩ ገባልኝ፣ ከዛ ደንግጬ ስልኬን Flight አረኩት ለ15 ደቂቃ ያክል፣ ከዛ መልሼ Flighቱን ሳነሳ ሌላ ተጨማሪ OTP Text ገባልኝና ቀጥሎ ስልኬን አጠፋሁ" አለኝ።

እኔ:- 'ቀን ላይ በዛው ሞባይል ባንኪንግ የምትጠቀምበት ባንክና SIM ገንዘቡ ለተላለፈላቸው ሰዎች የሂሳብ ቁጥር ብር ለማስተላለፍ ሞክረሃል?' አልኩት፣

ደንበኛዬ:- "አረ በጭራሽ፣ ባንኩ ፎቶና መታወቅያቸውን ሰጥቶኛል ግን ፈጽሞ ሰዎቹን አላውቃቸውም" አለኝ። 

ልብ በሉ ስልክህ SIM ካርድህ በእጅህ እያለ የተላከውን OTP Text ወዴትም ሳትልክ ብሩ ግን ወደ ሌላ ሰዎች ተላለፈ።

'ይህ የወንጀል ተግባር ስለሆነ ፖሊስ ምርመራውን እንድያካሂድ አሳውቅ" አልኩትና ሸኘሁት።

ምን አለ መሰላችሁ፣
1️⃣ ስለ SIM CLONING ሰምታችሁ ታውቃላችሁ? SIM Cloning is basically creating a duplicate SIM from the original number Or SIM cloning is the procedure through which a genuine SIM card is reproduced.

ሞባይል ባንኪንግ Technology  ላይ Authorize ሚደረገው  SIMሙ (የSIM ቁጥሩ)  እንጂ SIMሙ የገባበት Device ( ስልክ) ስላልሆነ  SIMሙ Clone (Same Copy) ከተደረገ በቀላሉ የሰውን ሀብት ከማዛወር ባሻገር ከባድ ወንጀሎችም ሊፈጸሙበት ይችላሉ። የማህበራዊ ሚድያዎትም በዛው የSIM ቁጥር ከተከፈተ ሊጠለፍ ይችላል ማለት ነው።

አንድ SIM ካርድ ወይም ያንተው የSIM ቁጥር በሌላ SIM ሲወጣ ማለት ነው። አንድ የስልክ ቁጥር 2 SIM ላይ ሲሰራ ማለት ቀለል ተደርጎ ሲተረጎም።

ያንተን ቁጥር በሌላ SIM የተሰጠው ሰው ተመሳሳይ ወጪና ገቢ ጥሪና መልዕክት ይደርሰዋል ማለት ነው። OTPው በእጅህ ባለው ስልክ ሲገባ CLONE በተደረገውም SIM ይገባል ማለት ነው። ያንተን ኮፒ የSIM ቁጥር የያዘ ሰው አንተ በስልክህ የተመዘገብከውን የሞባይል ባንኪንግ መጠቀም ይችላል ማለት ነው።

ማን በአንድ ቁጥር ሁለት SIM ይሰጣል የሚለውን EthioTele ቢጠየቅ ይበጃል እላለሁ።

2️⃣. ሌላው በሀገር ውጥ ህገወጥ Programmerች የተሰራ APK በስልካችሁ ላይ ስትጭኑ አፑ ከፊት ለፊት ከሚታየው አገልግሎቱ ውጪ ከጀርባ መረጃ የመበርበር (ስልክ Dial ማድረግ፣ Text ማንበብ፣ ሰነድ መውሰድ ወዘተ) ተግባር ሊፈጽም ይችላል። ያኔ በስልክ የባንኩ አጭር ቁጥር DIAL በማድረግ ገንዘብ ማስተላለፍ ተሞክሮ  OTP Text ሲገባም ከዛው ከርቀት ሆነው Textን አንብቦ ሞልቶ የወንጀል ተልዕኳቸውን ይፈጽማሉ። RAT ምናምን ይባላል ይሄኛው ዘዴ።

የቴክኖሎጂ እያደገ የሰው እውቀት እየጨመረ በሄዴ ቁጥር የሳይበር ወንጀል ከዚህ ይከፋል።

መፍትሄ:- ለSIM Cloning, SIM Lock ON በማድረግ ስልኮት ሌላ SIM ቢወጣበት እንኳ SIM Lock ስለሚጠይቅ SIMን Access ላያደርጉ ይችላሉ።

ለRAT ችግር እንዳይከሰት ደግሞ ፈጽሞ MODED Apk ወይም ሀገርውስጥ Build ሚደረጉ Apk በስልካችሁ አለመጫንን እመክራለሁ።

ሌላውን የሚመለከተው አካል INSA aND ባንኮች መላ ብያበጁበት ያሻል እላለሁ።

የማይነካ ነገር የነካሁባችሁ ቡድኖች ይቅርታ ብያለሁ"

CC፡
#Ethio_telecom
#Ethiopian_Federal_Police

©ጉማ

*
T.me/TheNewsReports
#BREAKING ፡ የኒውዮርክ ችሎት ዳኛ በዶናልድ ትራምፕ ላይ ብይን ሰጥቷል።

Share | T.me/TheNewsReports
#BREAKING ፡ ዶናልድ ትራምፕ በ34 የወንጀል ክሶች ጥፋተኛ ሆነው ተገኝተዋል።

Share | T.me/TheNewsReports
#UPDATE ፡ የቀድሞ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በፈረንጆቹ ጁላይ 11 ይፋዊ ፍርድ ይተላለፍበታል።

Share | @TheNewsReports
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#NOW ፡ ትራምፕ ከብይኑ በኋላ፦ "ይህ የተጭበረበረ እና አሳፋሪ ችሎት ነው!"

Share | T.me/TheNewsReports
#UPDATE ፡ ዶናልድ ትራምፕ በሁሉም ክሶች ወንጀለኛ ተብሎ ብይን መሰጠቱን ተከትሎ ታዋቂ ሰዎችን ጨምሮ በርካታ ማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ለትራምፕ ያላቸውን እጅግ ከፍተኛ ድጋፍ እያሳዩ ነው።

ማህበራዊ ሚዲያዎች ከመቼውም ጊዜ በላይ ተጨናንቀዋል።

አሜሪካ እንዲህ አይነት ውርደት አይታ የምታውቅ አይመስልም።

Share | T.me/TheNewsReports
#BREAKING ፡ ፈረንሳይ እስራኤልን ከሰኔ 17-21 በፓሪስ በሚካሄደው በዩሮሳቶሪ 2024 ትልቁ የጦር መሳሪያ ኤግዚቢሽን እንዳትሳተፍ አገደች።

Share | T.me/TheNewsReports