ቃልህ እውነት ነው ዘኦርቶዶክስ /Your word is Truth Zorthodox/
432 subscribers
3 photos
2 files
19 links
🔶 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት እንድሁም አጫጭር ትንታኔዋችና ዳሰሳ

🔵 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶች #ከሽልማት ጋር

🔷 የጥያቄዎቻችሁ መልስ

🔶 መጽሐፍ ቅዱሳዊ የቁጥር ዳሰሳዎችና ሌሎችም... #ቤተሰብ ይሁኑ
Download Telegram

የነገር ፍጻሜ ከመጀመሪያው ይሻላል፡፡(7፥8)
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
እባከዎ ለሌሎች ሰዎች ያካፍሉት
፡፡
የሙሴ መጀመሪያ አያምርም ነበር፡፡በውሃ ውስጥ ተጥሏል፡፡
እግዚአብሔር ግን ከተጣለበት አንስቶ ቤተ መንግሥት አስቀመጠው፡፡
የጠላቱን እንጀራ እያበላ አሳደገው፡፡መጀመሪያው ባያምርም መጨረሻውን አሳማረለት፡፡
ሁሌም መጀመርያው ደስ አያሰኝም ነገር ግን ፍጻሜው ከመጀመሪያው መሻል አለበት፡፡በእርግጥም የነገር መጨረሻ ከመጀመሪያው ይሻላል፡፡
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዓለምን ለማዳን ሲል በነበረው ሁኔታ የመጨረሻው ሳምንት ዓርብ ጨለማ ነው፡፡ቅዳሜም ደስ የማያሰኝ ተስፋ የተሟጠጠበት ቀን ነው፡፡
ያ ሁሉ አልፎ የመጨረሻው ቀን እሁድ ግን ደስታ ነበረ፡፡
ሁሌም መፈለግ ያለብን የመጨረሻውን ነገር መሆን አለበት፡፡አንድን ፊልም ወይም ታሪክና ልብ ወለድ ማየት የምንፈልገው መጨረሻውን ነገር ነው፡፡
የአደጋን የጦርነትን የክርክርን የውድድርን የጨዋታንም ለማወቅ የምንጓጓው መጨረሻውን ለማየት ነው፡፡
በመንፈሳዊ ህይወታችንም ይሁን በኑሮ ውጣ ውረድ መፈለግ ያለበን ይህንኑ መጨረሻውን ነው፡፡
የሰዎች ሕይዎት የሚጠቅመን መጀመሪያቸው ሳይሆን መጨረሻቸው ነው፡፡
አዳም ክፉ ሆኖ አልተፈጠረም
የአስቆረቱ ይሁዳ እድሜውን ሙሉ ክፉ ሰው አልነበረም
ዲዮቅልጣኖስና ዱድያኖስ በመጀመሪያ አንስቶ ክፉ አልነበሩም
አርዮስ ንስጥሮስም መጀመሪያቸው ምንፍቅና አልነበረም
ወይም አንተ ወይም አንቺ በክፋታቸው የምታውቂያቸው ሰዎች በመጀመሪያ እንድሁ ክፉ ላይሆኑ ይችላሉ፡፡
መጨረሻቸው ግን እንድህ ሆነ፡፡
መጀመሪያቸው ክፉ ጥሩ ያልነበሩ ሰዎች ደግሞ መጨረሻቸው መልካም የሆነ አለ፡፡
የቅዱስ ጳውሎስ መጀመሪያ ጡሩ አልነበረም
የሙሴ ጸሊም መጀመሪያ ጡሩ አልነበረም
የታላቁ አባት የአብርሃም መጀመሪያ ጡሩ አልነበረም
እነዚህ እና ሌሎችን ስናይ መጀመሪያቸው ጥሩ አልነበረም፡፡ ስቃይና መከራ ጭንቅና ስደት ነበር፡፡
መጨረሻቸው ግን ያማረና ደስታ ሆነ፡፡ቅድስናንም አተረፉ
ወዳጄ ይሄን ነው ቅዱስ ጳውሎስ
"የእግዚአብሔርን ቃል የተናገሩአችሁን ዋኖቻችሁን አስቡ፥ #የኑሮአቸውንም #ፍጻሜ እየተመለከታችሁ #በእምነታቸው ምሰሉአቸው።"(ዕብ13:7) ያለው፡፡
ወዳጄ ለመጀመሪያህ ምንም ይሁን ምን አትጨነቅ አትፍራም ፡፡መጀመሪያህ የማያምር ምንአልባትም ስቃይና ሴቃ የሞላበት ሊሆን ይችላል፡፡መጨረሻህን ግን ተስፋ አድርግ፡፡
መጀመሪያህ በኃጢአት ሊሆን ይችላል፡፡አሁን መጀመሪያህን ተወውና ለመጨረሻህ ተጨነቅ፡፡ከመጀመሪያው ይልቅ መጨረሻህ ወይ ያስደስትሃል ወይ ደግሞ ያስጨንቅሃል፡፡ሆኖም እንደ አንተ ይወሰናል፡፡
የመጀመሪህ መጨረሻ አለው የመጨረሻህ ግን መጨረሻ የለውምና ትጋ፡፡
የቅዱሳኑ መጨረሻ እንዳማረ አንተም የአማረውን የእነርሱን መጨረሻ እንድሆንልህ ጸልይ፡፡ነቢዩ ከሙሴ ጋራም እንድህ እያልክ ጸልይ
<<የጻድቃንን ሞት እኔ ልሙት ፍጻሜዬም እንደ እርሱ ፍጻሜ ትሁን።>>(ዘኁ23፥10) በል፡፡
ስለዚህም ተወዳጅ ሆይ
" የነገሩን ሁሉ ፍጻሜ እንስማ፤ ይህ የሰው ሁለንተናው ነውና፤ እግዚአብሔርን ፍራ፥ ትእዛዙንም ጠብቅ። "(መክ12:13)

በዲ/ን ገብረ ክርሰቶስ ካሳ
እንኳን ለድንግል ማርያም ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፡፡

ጽዮን ድንግል ማርያም በተወደደ ልጇ የዓለምን ታሪክ ቀየረች፡፡
ትናትና ዛሬ የተገናኘባት የማይታየውን ያየንባት ክርስቶስን የስነበበችን ወንጌል መዝገቡ ለቃል ድንግል ማርያም፡፡
ከመላእክት አእምሮ የራቀች በስላሴ ልቡና የታሰበች፡፡

፡፡፡
ዖዛ እጁን ዘርግቶ የእግዚአብሔርን ታቦት ያዘ።
የእግዚአብሔርም ቍጣ በዖዛ ላይ ነደደ፥ እግዚአብሔርም ስለ ድፍረቱ በዚያው ቀሠፈው፤ በእግዚአብሔርም ታቦት አጠገብ በዚያው ሞተ።(2ሳሙ 6:6)
ዖዛ እንድህ ከሆነ አማናዊት ታቦት ድንግል ማርያምንማ ለመሳደብ አፉን የከፈተ ምን ይበቃው ይሆን??

"ዳዊት እግዚአብሔርን ፈራና። #የእግዚአብሔር #ታቦት #ወደ እኔ #እንዴት ይመጣል? አለ። "
(መጽሐፈ ሳሙኤል ካልዕ 6:9)
አስተውል ነቢዩ ምን እንዳለ፡፡

እግዚአብሔር እራሱ የሰራት ንጽሕት አድሲቱ ታቦት እግዚአብሔር ወልድ በአካል የተገለጠባት ድንግል ማርያም ወደ ኤልሳቤጥ ስትሄድ
ኤልሳቤጥ
" የጌታዬ እናት ወደ እኔ ትመጣ ዘንድ እንዴት ይሆንልኛል?"
(የሉቃስ ወንጌል 1:43) አለች፡፡
እንግድህ የዳዊትና የኤልሳቤጥ ቃል አንድ እንደሆነ አስተውል፡፡

እንድህ ሆነ
ታቦተ ጽዮን በአቢዳራ ቤት በረከትን ሞላች
" የእግዚአብሔርም ታቦት በጌት ሰው በአቢዳራ ቤት #ሦስት ወር ያህል ተቀመጠ፤ እግዚአብሔርም አቢዳራንና ቤቱን ሁሉ #ባረከ። "
(መጽሐፈ ሳሙኤል ካልዕ 6:11) እንድል

አማናዊቷ ጽዮን ድንግል ማርያም በኤልሳቤጥ ቤት #ለሦስት ወር ስትቆይ
በኤልሳቤጥ ላይ መንፈስ ቅዱስን ሞላች፡፡
" ኤልሳቤጥም የማርያምን ሰላምታ በሰማች ጊዜ ፅንሱ በማኅፀንዋ ውስጥ ዘለለ፤ በኤልሳቤጥም መንፈስ ቅዱስ ሞላባት፥"
(የሉቃስ ወንጌል 1:41)እንዳለ ሉቃስ፡፡

በቃና ዘገሊላ በአማላጅነቷ ውሃውን ወደ ወይን ቀየረች ድንግል ማርያም
" የወይን ጠጅም ባለቀ ጊዜ የኢየሱስ እናት። የወይን ጠጅ እኮ #የላቸውም አለችው።"(ዮሐ 2:3) አለች የእኛ እናት ወደ ተወዳጅ ልጇ፡፡

ወዳጆቼ፡፡የዶኪማስን ጓዳ በበረከት የሞላች፡፡
በዚህ <<እኔ የለኝም>> እንጂ <<የላቸውም>>የሚል ሰው በለለበት ክፉ ዘመን፡ድንግል ማርያም በምልጃዋ አትለየን፡፡<<መንፈሳዊ ህይዎት መልካም ሥራ በጎነትና ጽድቅ የላቸውምና ይቅር በላቸው>>ትበልልን፡፡
ጓዳችንን በበረከቷ ትሙላልን፡፡
አሜን፡፡

በዲ/ን ገብረ ክርሰቶስ ካሳ
" አትሳቱ፤ ክፉ ባልንጀርነት መልካሙን አመል ያጠፋል።"
(1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 15:33)

🔘" ባልንጀራዬስ ማን ነው? "
(የሉቃስ ወንጌል 10:29)

☑️ሰው በዚች ፈተና በበዛባት አለም ሲኖር ብዙ ነገሮችን ቀድሞ ዋጅቶ ቀጣይ አቅጣጫ ማሰቀመጥ ካልቻለ ለውድቀት ቀርቧል ማለት ነው። መጽሐፍ ቅዱሰ ዘመኑን እንድዋች ይነግረናል። " ቀኖቹ ክፉዎች ናቸውና ዘመኑን ዋጁ።"
(ወደ ኤፌሶን ሰዎች 5:16) ይህ የሚያመለክተው ለቀኖቹ ክፍት መልሱ ዘመኑን መዋጀት መሆኑን ነዉ።
☑️ የሰው ልጅ ኋጢአት ሰርቶ እግዚአብሔር በንፍር ውሃ ትውልድን ካጠፍ በኋላ /ኖህና ቤተሰቡ ሲቀሩ/ እግዚአብሔር ለኖህ እንድህ አለ " በምድር ዘመን ሁሉ መዝራትና ማጨድ፥ ብርድና ሙቀት፥ በጋና ክረምት፥ ቀንና ሌሊት አያቋርጡም። ዘፍ8:22... ይህ ቃል እንደሚያሰረዳን በምድረ ዘመን ሁሉ ሁለት ተቃራኒ ነገሮች እንደሚኖሩ ነው ፤ እውነት ነው አሉም.... ዛሬ ላነሳ የወደድኩት ባልጀርነት ነው። ከላይ እንደጠቀስኩት መልካም ባልንጀራ እና መልካም ያልሆነ ባልንጀራ(ክፉ ባልንጀራ).....ለዛሬ ክፉ ባልንጀራ በሕይወት መጽሐፍ መሰረት ልመለከት ወደድኩ።

☑️ መቸም በሕይወታችን አንድ ጥያቄ መኖሩ አይቀርም። ማን ነው ባልንጀራየ...ይህን ጥያቄ የሕይወት መምህርም ተጠይቋል ምንም እንኳ ጥያቄው ከጠያቂው አንጻር ካየነው መልካም ባይሆንም።
☑️ መልካምም ይሁን ክፉ ባልንጀራ ሕይወታችንን ይቀይራል። መቀየሩ ግን ወይ ለመነሳት ነው ወይም ለመውደቅ ነው። ምናልባት ይህ የሚገባን ካለፈ በኋላ ነው። ለአብነት ያህል በሕይወት መጽሐፍ እንመልከት፦
1⃣ የሄዋንና የሰይጣን ጓደኝነት

ይህ ጓደኝነት ግራ ሊያጋብን ይችላል ግን የሆነ እውነታ ነው። ሄዋን ትክክለኛ ጓደኛ መሆኑን ሳታውቅ በእርሷና በአካሏ በአዳም ያለችን #ምስጢር ለአድሱ ጓደኛዋ ለሰይጣን አካፈለች። እርሱም በተሰጠው መረጃ ተነስቶ የሄዋንንና የአካሏን የአዳምን መውደቅ አመቻቸ።

(ኦሪት ዘፍጥረት ምዕ. 3)
----------
1፤ እባብም እግዚአብሔር አምላክ ከፈጠረው ከምድር አውሬ ሁሉ ይልቅ ተንኰለኛ ነበረ። ሴቲቱንም። በውኑ እግዚአብሔር ከገነት ዛፍ ሁሉ እንዳትበሉ አዝዞአልን? አላት።

2፤ ሴቲቱም ለእባቡ አለችው። በገነት ካለው ከዛፍ ፍሬ እንበላለን፤

3፤ ነገር ግን በገነት መካከል ካለው ከዛፉ ፍሬ፥ እግዚአብሔር አለ። እንዳትሞቱ ከእርሱ አትብሉ አትንኩትም።

4፤ እባብም ለሴቲቱ አላት። ሞትን አትሞቱም፤

5፤ ከእርስዋ በበላችሁ ቀን ዓይኖቻችሁ እንዲከፈቱ እንደ እግዚአብሔርም መልካምንና ክፉን የምታውቁ እንድትሆኑ እግዚአብሔር ስለሚያውቅ ነው እንጂ።

6፤ ሴቲቱም ዛፉ ለመብላት ያማረ እንደ ሆነ፥ ለዓይንም እንደሚያስጎመጅ፥ ለጥበብም መልካም እንደ ሆነ አየች፤ ከፍሬውም ወሰደችና በላች፤ ለባልዋም ደግሞ ሰጠችው እርሱም ከእርስዋ ጋር በላ።

የክፍ ባልንጀራ ውጤት #ከአምላክ-መለየት-ሞት

2⃣ የአምኖንና የኢዮናዳብ ጓደኝነት/ሙሉ ታሪኩን ያንብቡ 2ሳሙ 13/

ይህ ታሪክ ለእውነተኛ አእምሮ ይከብዳል። ሰው ትክክለኛ ሚዛን ላይ እያለ እንድህም አይመክርም ቢመከርም አይደረግም። ግን እውነታው በዘመኑ እንደምንሰማው ይህ እውነት ነው/የመነሻ ታሪኬም ይህን መስማቴ ነው/

አምኖን እህቱ ትዕማርን ይወዳታል። በዚህ ሰአት ነበር ምክር ሳይጠይቀው ኢዮናዳብ የሚባለው ጓደኛው አምኖን በልቡ የያዘውን #ምስጢር ጠይቆ ጥሩ ያልሆነ መፍትሔ የሰጠው። ምክሩም በአጭሩ እንድህ ይላል፦

(መጽሐፈ ሳሙኤል ካልዕ ምዕ. 13)
----------
4፤ እርሱም። የንጉሥ ልጅ ሆይ፥ ስለ ምን ቀን በቀን እንዲህ ከሳህ? አትነግረኝምን? አለው። አምኖንም። የወንድሜን የአቤሴሎምን እኅት ትዕማርን እወድዳታለሁ አለው።

5፤ ኢዮናዳብም። ታምሜአለሁ ብለህ በአልጋህ ላይ ተኛ፤ አባትህም ሊያይህ በመጣ ጊዜ። እኅቴ ትዕማር እንድትመጣና እኔ የምበላውን እንጀራ እንድትሰጠኝ፥ መብሉንም እኔ እያየሁ እንድታዘጋጅልኝ፥ ከእጅዋም እንድበላው እለምንሃለሁ በል አለው።

6፤ እንዲሁም አምኖን። ታምሜአለሁ ብሎ ተኛ፤ ንጉሡም ሊያየው በመጣ ጊዜ አምኖን ንጉሡን። እኅቴ ትዕማር እንድትመጣና እኔ እያየሁ ሁለት እንጎቻ እንድታደርግልኝ፥ ከእጅዋም እንድበላ እለምንሃለሁ አለው።

7፤ ዳዊትም። መብልን ታዘጋጂለት ዘንድ ወደ ወንድምሽ ወደ አምኖን ቤት ሂጂ ብሎ መልእክተኞችን ወደ ትዕማር ቤት ላከ።

8፤ ትዕማርም ወደ ወንድምዋ ወደ አምኖን ቤት ሄደች፥ ተኝቶም ነበር፤ ዱቄትም ወስዳ ለወሰች፥ እያየም እንጎቻ አደረገች፥ ጋገረችም።



(መጽሐፈ ሳሙኤል ካልዕ ምዕ. 13)
----------
10፤ አምኖንም ትዕማርን። ከእጅሽ እበላ ዘንድ መብሉን ወደ እልፍኙ አግቢው አላት፤ ትዕማርም የሠራችውን እንጎቻ ወስዳ ወንድምዋ አምኖን ወዳለበት እልፍኝ አገባችው።

11፤ መብሉንም ባቀረበች ጊዜ ያዛትና። እኅቴ ሆይ፥ ነዪ ከእኔም ጋር ተኚ አላት።

12፤ እርስዋ መልሳ። ወንድሜ ሆይ፥ አይሆንም፤ እንዲህ ያለ ነገር በእስራኤል ዘንድ አይገባምና አታሳፍረኝ፤ ይህንም ነውረኛ ሥራ አታድርግ።

13፤ እኔም ነውሬን ወዴት ልሸከም? አንተም በእስራኤል ዘንድ ከምናምንቴዎች እንደ አንዱ ትሆናለህ፤ እንግዲህስ ለንጉሡ ንገረው፥ እኔንም አይነሣህም አለችው።

14፤ ቃልዋን ግን አልሰማም፤ ከእርስዋም ይልቅ ብርቱ ነበረና በግድ አስነወራት፥ ከእርስዋም ጋር ተኛ።

15፤ ከዚያም በኋላ አምኖን ፈጽሞ ጠላት፤ አስቀድሞም ከወደዳት ውድ ይልቅ በኋላ የጠላት ጥል በለጠ። አምኖንም። ተነሥተሽ ሂጂ አላት።
የክፉ ባልንጀራ ውጤት እህትን #ማሰነወር.....
❇️በመጽሐፍ ቅዱስ #አሰነወራት ተብሎ ለሁለት ሴቶች ተነግሯል አንዱ ለያዕቆብ ልጅ ዲና የተነገረ ሲሆን እሷም ባልንጀሮቿን ሳታውቅ በመሄዷ ነው። ነገር ግን የዲና የሚያጋጥም ነው ምክንያቱም ከእርሷ በራቁ በአልተገረዙ የተደረገባት ሰለሆነ የትዕማር ግን ልብን ይሰብራል በወንደሟ ሰለሆነ...


ይቀጥላል

ክብር በጣም ለምወዳችሁ ለመልካም ወንድሞቸና እህቶቸ/በመልካም ጓደኝነት ለገነባችሁኝ ለምገነቡኝም/
#መልካም_እረኛ_እኔ_ነኝ
ዩሐ 10:14

❇️ይህን ርዕስ በማንሳት በ29/03/11 የዕለቱን ወንጌል ሰለ ኖላዊ ትምህርት ሰጥቸ ነበር ፤ ከተጠቀምንበት በማለት ወደ ጽሑፍ ቀየርኩት.....

🔘በተነሳው ርዕስ ላይ ሁለት ነገሮችን እናገኛለን #መልካም_እረኛ እና #እኔ_ነኝ የሚሉ ሰፊ ርዕሶች።
🔘ለስም አጠራሩ ክብር ምሰጋና ይሁንና ጌታችን መድሀኒታችን ኢየሱስ ክርሰቶስ በዩሐንሰ ወንጌል ብቻ #እኔ_ነኝ እያለ ያስተማራቸው ትምህርቶች አለ። እነርሱም 6 ናቸው። በአጭሩ አሰቀምጠናቸው ስናልፍ፦
1⃣. " ኢየሱስም እንዲህ አላቸው።። #የሕይወት_እንጀራ_እኔ_ነኝ፤ ወደ እኔ የሚመጣ ከቶ አይራብም በእኔ የሚያምንም ሁልጊዜ ከቶ አይጠማም።"(ዮሐ6:35)..እርሱ የሕይወት እንጀራ ነው እኛ እንበላለን ፤ በመብላችንም ዘላለማዊ እንሆናለን።

(የዮሐንስ ወንጌል ምዕ. 6)
----------
53፤ ስለዚህ ኢየሱስ እንዲህ አላቸው። እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ የሰውን ልጅ ሥጋ ካልበላችሁ ደሙንም ካልጠጣችሁ በራሳችሁ ሕይወት የላችሁም።

54፤ ሥጋዬን የሚበላ ደሜንም የሚጠጣ የዘላለም ሕይወት አለው፥ እኔም በመጨረሻው ቀን አስነሣዋለሁ።

55፤ ሥጋዬ እውነተኛ መብል ደሜም እውነተኛ መጠጥ ነውና።

56፤ ሥጋዬን የሚበላ ደሜንም የሚጠጣ በእኔ ይኖራል እኔም በእርሱ እኖራለሁ።

2⃣. " ደግሞም ኢየሱስ። #እኔ_የዓለም_ብርሃን_ነኝ፤ የሚከተለኝ የሕይወት ብርሃን ይሆንለታል እንጂ በጨለማ አይመላለስም ብሎ ተናገራቸው።"(ዮሐ 8:12)...እርሱ እውነተኛ ብርሃን እኛ ደግሞ በእርሱ ብርሃን ብርሃን ሆነን ለዓለም እናበራለን።

(የማቴዎስ ወንጌል ምዕ. 5)
----------
14፤ #እናንተ_የዓለም_ብርሃን_ናችሁ። በተራራ ላይ ያለች ከተማ ልትሰወር አይቻላትም።

15፤ መብራትንም አብርተው ከዕንቅብ በታች አይደለም እንጂ በመቅረዙ ላይ ያኖሩታል በቤት ላሉት ሁሉም ያበራል።

16፤ መልካሙን ሥራችሁን አይተው በሰማያት ያለውን አባታችሁን እንዲያከብሩ #ብርሃናችሁ_እንዲሁ_በሰው_ፊት_ይብራ


3⃣. " #በሩ_እኔ_ነኝ፤ በእኔ የሚገባ ቢኖር ይድናል፥ ይገባልም ይወጣልም መሰማሪያም ያገኛል።"(ዮሐ10:9)...በክርሰትና ከክርስቶስ ውጭ #የሕይወት_በር የለም። በዚህ ሕይወት በር ከገባን በኋላ ከሕይወት በር እንዳንወጣ እንድሁም መውደቃችን መነሳታችን አይተው የሚራዱን ብዙ ቅዱሳን አሉ ነገር ግን የከበረች በረከታቸውን እርዳታቸውን ለማግኛት ቅድሚያ የሕይወት በርን አውቆ መግባትና መኖር ይገባል። በአጭሩ ይህ #የሕይወት_በር_ምንድን_ነው? ለምትሉኝ አባቶች #በሰይፍ_የተዘጋች_ገነት_በሰይፍ_ተከፈተች እንዳሉን የሕይወት በሩ #በሰይፍ_የተወጋው_ግራ_ጎኑ ነው። ይህ በር ነው የሕይወት ምንጭ...በዚህ በር ለማለፍ በሩ ላይ ያለውን ቅድሚ መቀበል ይቀድማል። በሩ ላይ #ደምና_ውሃ አለ። በደሙ ተገዝተን በውሃው ነጽተናል። " ከአባቶቻችሁ ከወረሳችሁት ከከንቱ ኑሮአችሁ በሚያልፍ ነገር በብር ወይም በወርቅ ሳይሆን፥ ነውርና እድፍ እንደ ሌለው እንደ በግ ደም #በክቡር_የክርስቶስ_ደም_እንደ_ተዋጃችሁ_ታውቃላችሁ።"
(1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 1:18-19)

4⃣. " #መልካም_እረኛ_እኔ_ነኝ፥ አብም እንደሚያውቀኝ እኔም አብን እንደማውቀው የራሴን በጎች አውቃለሁ የራሴም በጎች ያውቁኛል፤ ነፍሴንም ስለ በጎች አኖራለሁ።"(ዮሐ10:14-15)
ይህ መልካም እረኛ ሰለሚወዳቸው በጎች የሚሞት ነው። ይህን ለመረዳት ሶስቱን የጌታችን የእረኝነት ሰሞች እንመልከት፦
❇️#መልካም_እረኛ
" መልካም እረኛ እኔ ነኝ። መልካም እረኛ ነፍሱን ስለ በጎቹ ያኖራል።"(ዮሐ10:11)
👆👆👆ይህ ሰለሚወዳቸው በጎች በፈቃዱ #ስለሚሞተው_ሞቱ የሚናገር ነው (ምዕራፉን ሙሉውን ያንብቡት)

❇️ #ታላቅ_እረኛ
" በዘላለም ኪዳን ደም #ለበጎች_ትልቅ_እረኛ የሆነውን ጌታችንን ኢየሱስን ከሙታን ያወጣው የሰላም አምላክ፥"
(ወደ ዕብራውያን 13:20)
👆👆👆👆ይህ ሰለ ትንሳኤው የሚናገር ነው ተወዳጆች ያሰተውሉ።

❇️ #የእረኞች_አለቃ
" የእረኞችም አለቃ በሚገለጥበት ጊዜ የማያልፈውን የክብርን አክሊል ትቀበላላችሁ።"
(1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 5:4)
👆👆👆ይህ ሰለ ዳግም ምጽአቱ የሚናገርበት ነው።
ይህን ጠቅለል ሰናደርገው ሶስቱም ሰሞቹ የሚናገሩት ሰለ በጎች የተደረገውንና የሚደረገውን ነው። ሰለዚህ እረኛው ለበጎቹ ይህን ካደረገ እኛም ለእረኛው እንመች።

5⃣. " ኢየሱስም። #ትንሣኤና_ሕይወት_እኔ_ነኝ፤ የሚያምንብኝ ቢሞት እንኳ ሕያው ይሆናል፤"(ዮሐ11:25)
🔸ይህ ምሰጢር የሚታመን ወደፊት ከሚፈጸሙ አንዱ ነው።

6⃣. (የዮሐንስ ወንጌል ምዕ. 15)
----------
1፤ #እውነተኛ_የወይን_ግንድ_እኔ_ነኝ፤ ገበሬውም አባቴ ነው።

2፤ ፍሬ የማያፈራውን በእኔ ያለውን ቅርንጫፍ ሁሉ ያስወግደዋል፤ ፍሬ የሚያፈራውንም ሁሉ አብዝቶ እንዲያፈራ ያጠራዋል።

3፤ እናንተ ስለ ነገርኋችሁ ቃል አሁን ንጹሐን ናችሁ፤

4፤ በእኔ ኑሩ እኔም በእናንተ። ቅርንጫፍ በወይኑ ግንድ ባይኖር ከራሱ ፍሬ ሊያፈራ እንዳይቻለው፥ እንዲሁ እናንተ ደግሞ በእኔ ባትኖሩ አትችሉም።

5፤ #እኔ_የወይን_ግንድ_ነኝ እናንተም ቅርንጫፎች ናችሁ። ያለ እኔ ምንም ልታደርጉ አትችሉምና በእኔ የሚኖር እኔም በእርሱ፥ እርሱ ብዙ ፍሬ ያፈራል።
➡️እኛ ቅርጫፎች ነን ለማለምለም ከግንዱ ጋር መጣበቅ ለመድረቅ ከግንዱ መውደቅ ወይም መቆረጥ ይጠበቅብናል። ይህ ነጻ ፈቃዳችን ነው ገር ግን ግንዱ ላይ ሆኖ አለማለምለም አልፎም አለማፍራት አይቻልም። ከግንዱ ስር የሚቆርጥ ምሳር አለ " #አሁንስ_ምሳር_በዛፎች_ሥር_ተቀምጦአል፤ እንግዲህ መልካም ፍሬ የማያደርግ ዛፍ ሁሉ ይቈረጣል ወደ እሳትም ይጣላል።"(የማቴዎስ ወንጌል 3:10) ሰለዚህ በእውነተኛ ልንመላለሰ ግደታችን ነው።

ትምህርቱ እዚህ ላይ አላቆመም ፥ በዚሁ ምዕራፍ እውነተኛ እረኛ ምን ያደርጋል የሚለው ይቀጥላል...

☑️መንፈሳዊ ቻናላችንን ለመቀላቀል
👇👇👇👇👇👇👇👇

📜📜📜📜📜📜📜📜📜📜
📜 @zorthdox 📜
፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧
📜 @Hesychasm 📜
📜📜📜📜📜📜📜📜📜📜
:
:
ለመንፈሳዊ ጥያቄዎ
ለመንፈሳዊ ውይይት
ለአስተያየተዋ
👇👇👇👇👇👇👇👇
፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧
፧፧፧ @Apophatism ፧፧፧፧
፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧
፧፧፧ @Archeanarchos ፧፧
፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧
ሻሎም የቻናላችን ተከታታዩች ሰላምታየ ይድረሳችሁ

በዚች ቻናል የሚለቀቁ ትምህርቶች ለሌሎች ይደርሱ ዘንድ ለወንድም ለእቶቻችሁ እንድታሰተዋውቁ እንማልዳለን
☑️መንፈሳዊ ቻናላችንን ለመቀላቀል
👇👇👇👇👇👇👇👇

📜📜📜📜📜📜📜📜📜📜
📜 @zorthdox 📜
፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧
📜 @Hesychasm 📜
📜📜📜📜📜📜📜📜📜📜
:
:
ለመንፈሳዊ ጥያቄዎ
ለመንፈሳዊ ውይይት
ለአስተያየተዋ
👇👇👇👇👇👇👇👇
፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧
፧፧፧ @Apophatism ፧፧፧፧
፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧
፧፧፧ @Archeanarchos ፧፧
፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧
መልካም ዕለተ ሰንበት ይሁንልን
Forwarded from 💠አይዋሽም መስቀሉ💠


#የኢየሱስ ክርስቶስ ሥዕል ወይስ የአክተር ምሥል ??
✿፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡✿፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡✿፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡✿
ብዙ ሰው የኢየሱስ ክርስቶስን ስእል በማየት በሥዕል የተገለጠው ኢየሱስ ክርስቶስ ነው ብለው ይደመድማሉ፡፡
አንዳንዶቹ ደግሞ <<ሥዕሉ የኢየሱስ ክርሥቶስ አይደለም የፊልም አክተር ምስል እንጂ>> ይላሉ
ቅዱስ ጎርጎርዮስ ሥዕላትን" #የሰማይ መስኮቶች" ይላቸዋል፡፡ምክንያቱም ሰማያውያኑን ነገር አጉልተው በማሳየታቸው ነው፡፡
አንድን መንፈሳዊ ታሪክ ለማስረዳትም ሆነ ለመረዳት ቋንቋ ወሳኝ ነገር ነው፡፡
ሥዕላትን ግን ለማንኛውም የአለማችን ህዝቦች ያለ ቋንቋ ይረዳቸዋል፡፡እነርሱም ያለ ቋንቋ ይናገራሉ፡፡
ይህ ማለት ግን አንድ ስዕል የሚአሳየው የሥዕሉን ባለቤት ወክሎ ተገድሎውንና በተጋድሎ ያገኘውን ጸጋ የአምላክም ሥዕል ከሆነ አምላክነቱን እና ክብሩን ነው፡እንጂ "እገሌ "ማለት ይህ ነው ማለት አይደለም፡፡
እንኳንስ ሥዕል ፎቶ እንኳን የሰውን ማንነት ሙሉ ለሙሉ የመግለጽ አቅም የለውም፡፡
ምክንያቱም ፎቶ አንድ አቅጣቻን ብቻ የሚአሳይ በመሆኑ ነው፡፡ሥለዚህ ሥዕላት የሥዕሉ ባለቤት ወካይ አካል ሲቦል ናቸው፡፡እንጂ ባለቤቱን አይደሉም፡፡

አንድ ሰው የኢየሱስ ክርስቶስን ወይም የቅዱሳንን ሥዕልን ሢሥዕል እነርሱን እነዚህ ናቸው ማለቱ አይደለም፡፡
ስለ እነርሱ ያለውን ክብርና ቅድስና በአዕምሮው ላይ የተፈጠረውን ምስል በወረቀት ላይ በስዕል አስቀመጠው እንጂ፡፡
አንድ አማኝም በአንድ ቅዱስ ሥዕል ፊት ሲሰግድና ሲጸልይም በወረቀት ወይም በሌላ ማቴርያል ላይ ለተሣለው ሰገደ ጸለዬ ማለት አይደለም፡፡፡በሥዕሉ ላይ አድሮ በረከትንና ጸጋን ለሚአሰጠው ለሥዕሉ ባለቤት እንጂ፡፡

የኢየሱስ ክርስቶስን ፊልም መነሻ አድርገው <<አሁን በቤተ ክርስቲያን ያሉት የኢየሱስ ክርስቶስ ሥዕላት አይደሉም የአክተሮች ምስል እንጂ>>ይላሉ፡፡በዚህም ሲተቹና ሲከራከሩ የሚውሉም አልጠፉም፡፡
ሆኖም ኦርቶዶክሳውያን <<ኢየሱስ ማለት አሁን በቤተ ክርስቲያናችን ያሉትን የኢየሱስ ክርስቶስን (መድኃኔ ዓለምን)ሥዕላት ናቸው>>አንልም፡፡ ነገር ግን የአክተር ምስሎች ግን አይደሉም፡፡የኢየሱስ ክርስቶስ ሥዕላት ናቸው እንጂ፡፡
ኢየሱስ ክርስቶስ በኦርቶዶክስውያን ዘንድ እንኳን በሥዕል ከምንገልጠውና ከምንናገረው ከሃሳባችንም በላይ ነውና፡፡

እናም አክተሮቹ አባቶቻችን የሳዓሉትን የኢየሱስ ክርስቶስን ሥዕል መስለው ፊልሙን ሠሩት እንጂ አባቶቻችን አክተሮቹን አስመስለው አልሳሉትም፡፡
ይህ ማለት ለአክተሮቹ የኢየሱስ ክርስቶስን ፊልም ለመስራት መነሻ የሆናቸው አባቶቻችን አስቀድመው የሳሉት ሥዕል ነው፡፡ማለት ነው፡፡

የኢየሱስ ክርስቶስ ፊልም የተሠራው በ1970ቹ ገዳማ ሲሆን የእኛ አባቶች ግን የኢየሱስ ክርስቶስን ሥዕል የሣሉት ገና ክርስትና እንደተመሠረተ በመጀመሪያው መቶ ክፍለ ዘመን ነው፡፡ስለዚህ የመናፍቃኑና የአህዛቦቹ ድርቅና ከንቱ ሆኖ ይቀራል፡፡

ነገር ግን ልክ እንደመናፍቃንና አህዛብ አንዳንዶች የኢየሱስ ክርስቶስን የሥቅለቱን ፊልም በማየት የፊልሙን ተዋናይ ኢየሱስ እንደሆነ አድርገው ያስቡታል፡፡
ሆኖም ኢየሱስ አይደለም የፊልም ተዋንይ እንጂ፡፡
የክርስቶስን እናት ድንግል ማርያምን መስላ የምትሠራውም ሆነ ኢየሱስን መስሎ የሚሰራው ተዋናዮች በመጽሐፍ ቅዱስ የተጻፈውን ትንሽ ነገር አስተላለፉልን እንጂ እነርሱን አይደሉም፡፡
ምስጢረ ሥጋዌ ምስጢር ነው አይመረመርም
የክርስቶስ ሞትና መከራ ርሁቅ ነው ማንም አይናገረውም፡፡፡

#አንዳንዶች

"መልክና ውበት የለውም፥ ባየነውም ጊዜ እንወድደው ዘንድ ደም ግባት የለውም።"
(ኢሳ53:2) የሚለውን በመጥቀስ ይከራከራከራሉ፡፡፡
ይህ የተነገረው በዕለተ ዓርብ ስለደረሰበት መከራና ስቃይ እንጂ ኢየሱስ Normal ደም ግባትና መልክ የለውም ማለት አይደለም፡፡ለእኛ ሲል በግርፋት ደም ግባቱ ጠፍቷልና
ነቢዩ ይህንን ተናገረ፡፡

ኢየሱስ ክርስቶስ ጥቁር ነው ወይስ ቀይ ወይስ ጠይም???
.
የመጀመሪያው ሰው አዳም ምን አይነት መልክና የመልክ ቀለም እንደነበረው መጽሐፍ ቅዱስ በዚህ ጉዳይ መልስ አይሰጥም፡፡
ሆኖም አዳም በእግዚአብሔር አምሳል የተፈጠረ ውብ ፍጡር እንደሆነ ግን ይናገራል፡፡
የከለር ጉዳይ ግን መጽሐፍ ጉዳዩ አይደለም፡፡
ኢየሱስ ክርስቶስ ደግሞ ፍጹም አምላክ ሲሆን የሰውን ሥጋ ለብሶ ፍጹም ሰው ሆኗል፡፡
"የአብርሃምን ዘር ይዞአል እንጂ የያዘው የመላእክትን አይደለም።"
( ዕብ2:16) ተብሎ እንደተጻፈ ኢየሱስ ክርስቶስ የተወለደው ከአብርሃም ዘሮች ከአይሁድ ወይም ከእስራኤላውያን ስለሆነ እስራኤላውያንን ይመስላል፡፡

ኢትዮጵያውያን ኢየሱስ ክርስቶስ ከአይሁድ ከእስራኤላውያን ስለተወለደ ፍጹም እስራኤላውያንን አስመስለው አልሳሉትም፡፡
ኢየሱስ ወደ ዓለም የመጣው እስራኤልን ብቻ ሳይሆን ዓለምን ሊአድን ነውና ኢትዮጽያውያን አባቶቻችን ""ለቀዮቹም ለጥቁሮቹም ሲል ወደ ዓለም መጥቷል"" ሲሉ ጠይም አድርገው ይስሉታል፡፡
አብዛኞቹ ምእመናንም ይህን ስዕል በማየት "መድኃኔ ዓለም ጠይም ነው" ብለው ያስባሉ፡፡
ሌላው በኢትዮጵያውያን ሊቃውንት ኢየሱስ ክርስቶስ የሚሳሉት የችንካሩ ምልክቶች እንድታዩ ሆነው ነው፡፡የራሱ ፀጉሮቹም ኢትዮጵያዊያን ባህታውያንን አስመስለው ይስሉታል፡፡
ፀጉሮቹ የረዘሙና ፂም የተሞላበት ፊት ያለው የእየሱስ ምስል በመካካለኛው
ክፍለ-ዘመን በተለይም በባይዛንታይን ኢምፓየር ከፍተኛ ዕውቅናን አግኝቷል።
ፕሮፌሰር ቼቪታይዝ እንደሚሉት የእየሱስ ምስል የሚሳለው እንደ
ዘመኑ ከነበሩት ነገስታት አካላዊ ገፅታ ሉዓላዊነትን በተጎናፀፈ መልኩ ነበር። የማህበረሰብ አጥኚው ፍራንቼስኮ ቦርባ ሪቤይሮ ኔቶ በሳኦ ፖሎ በሚገኘው የካቶሊክ ዩኒቨርሲቲ አስተባባሪ የነበሩት እሳቸው እንደሚሉትም " በታሪክ ውስጥ የእየሱስ ገፅታ በክርስትና
መጀመሪያ ወቅት እስራኤላውያንን መምሰሉ ለብዙዎች አሳሳቢ ጉዳይ አልነበረም" ይላሉ።

በምስራቃዊ ካቶሊክ ቤተክርስቲያኖች ዘንድ የእየሱስ ገፅታን ለመሳል ጥብቅ የሆነ ህግም በማውጣት፤ ከአለማዊው ውጭም መንፈሳዊ የሆኑ ጥበቦችንም ሊያሳይ ይገባል ተብሎ
እንደሚታመን ይናገራሉ።" ከተለያዩ ሰዎች ጋር በሚሳልበት ወቅት ከሁሉም ተለቅ ብሎ
እንዲታይና ሲሆን ይህም ያለውን ታላቅነት ምሳሌ ነው።

ከዚህም በተጨማሪ በመስቀል ላይ ተሰቅሎም ሲሳልም በህይወት እንዳለና ከአጠቃላይ ፀጋው ጋር ነው የሚሳለው" ይላሉ።

የምዕራቡ ዓለም ቤተክርስቲያን እነዚህን ህግጋትንም ሆነ ባህል ስለማይከተሉ በዘመናትም ውስጥ የእየሱስን ምስል በዘፈቀደና እንደፈለጉት አድርገው ይስሉ ነበር ይላሉ።በእምነቶች ላይ ያሉ ታሪካዊ ሰዎች የባህል የበላይነት ያለበት አካል ነፀብራቅ እየሆኑ እንደመጡ ይናገራሉ።

✿አሁን አሁን ኢየሱስን ተብሎ የሚሳለው ሁሉ የእርሱን ስዕል አይደም፡፡ክብር ለአባቶቻችን ይሁንና እንደት እንደሚሳል አስተምረው አልፈዋል፡፡፡
ፈረንጆች ሁሌ መልካም የሆነውን ነገር የሚስዕሉት እነርሱን አስመስለው ነው፡፡ሰይጣንን የሳሉት ግን ጥቁር አድርገው ጥቁሮችን አስመስለው ስለውታል፡፡
ይህም ጥቁሮችን ከመናቃቸው የተነሳ እንደሆነ ይነገራል፡፡
እናም በስዕል ስም የተለያዪ ሃይማኖታዊ ትውፊታቸውን ያልጠበቁ ብቻ ሳይሆን አስቀያሚ ስዕላትም ብቅ ካሉ ሰነባብተዋል፡፡

በዚህ ጉዳይ ጌታ እንድኖር ከፈቀደ እመለስበታለሁ •••••••••

ማስተዋልና ጥበቡን እግዚአብሔር ያድለን፡፡

By G/kirstos Kasssa.
📜📜📜📜📜📜📜📜📜📜
📜 ዘፍጥረት በጥያቄና መልስ📜
📜📜📜📜📜📜📜📜📜📜
:
:
📜📜📜📜📜📜📜📜📜📜
📜 ክፍል--ስድስት 📜
📜📜📜📜📜📜📜📜📜📜

:
#አዳም_ለሔዋን_ሔዋን_ብሎ_መቸ_ስም_አወጣላት?

☑️ በዚህ ክፍል የምናየው አዳም #ለሴት_ለሔዋን ወይም ለአካሉን #መቸ_እና_ለምን? ስም እንዳወጣላት ነው?
🔘በዘፍጥረት እንደምንረዳው እግዚአብሔር አምላክ ለአዳም ስም የማውጣት ስልጣን እንደሰጠውና አዳምም ሕያው ነፍስ ላለው ሁሉ ስም እንዳወጣላቸው እንረዳለን።

(ኦሪት ዘፍጥረት ምዕ. 2)
----------
19፤ እግዚአብሔር አምላክም የምድር አራዊትንና የሰማይ ወፎችን ሁሉ ከመሬት አደረገ፤ #በምን_ስም_እንደሚጠራቸውም_ያይ_ዘንድ_ወደ_አዳም_አመጣቸው፤ አዳምም ሕያው ነፍስ ላለው ሁሉ በስሙ እንደ ጠራው ስሙ ያው ሆነ።

20፤ #አዳምም_ለእንስሳት_ሁሉ፥ ለሰማይ ወፎችም ሁሉ፥ ለምድር አራዊትም ሁሉ #ስም_አወጣላቸው፤ ነገር ግን ለአዳም እንደ እርሱ ያለ ረዳት አልተገኘለትም ነበር።


☑️ ይህ ተግባር ወይም ስም ማውጣት በዙርያው ባለው ፍጥረት ሁሉ ላይ የበላይነቱን ያሳየበት የመጀመርያ ተግባር እንደሆነም ይጠቁማል።

#ከወንድ_ተገኝታለችና_ሴት_ትባል


(ኦሪት ዘፍጥረት ምዕ. 2)
----------
20፤ አዳምም ለእንስሳት ሁሉ፥ ለሰማይ ወፎችም ሁሉ፥ ለምድር አራዊትም ሁሉ ስም አወጣላቸው፤ #ነገር_ግን_ለአዳም_እንደ_እርሱ_ያለ_ረዳት_አልተገኘለትም_ነበር

21፤ እግዚአብሔር አምላክም በአዳም ከባድ እንቅልፍን ጣለበት፥ አንቀላፋም፤ #ከጎኑም_አንዲት_አጥንትን_ወስዶ_ስፍራውን_በሥጋ_ዘጋው

22፤ እግዚአብሔር አምላክም #ከአዳም_የወሰዳትን_አጥንት_ሴት_አድርጎ_ሠራት፤ ወደ አዳምም አመጣት።
👆👆👆👆👆ከላይ ከጥቅሱ እንደምንረዳው እግዚአብሔር አምላክ የአዳምን ብቸኝነት አይቶ ከግራ ጎኑ አጥንት ወስዶ አካሉ ሔዋን እንደሰጠው ይናገራል። እዚህ ላይ ማስተዋል ያለብን #ሔዋን በዚህ ጊዜ ተፈጠረች ማለት ሳይሆን #በአዳም_ሕልው_ሆና_ትኖር_የነበረችው_ሔዋን_መለየቷን_ወይም_ይፍመሆኗን መረዳት አለብን። ይህ ለመረዳት የሚከተለውን ቃል እንረዳ፦

(ኦሪት ዘፍጥረት ምዕ. 5)
----------
1፤ የአዳም የትውልዱ መጽሐፍ ይህ ነው። #እግዚአብሔር_አዳምን_በፈጠረ_ቀን_በእግዚአብሔር_ምሳሌ አደረገው፤

2፤ #ወንድና_ሴት_አድርጎ_ፈጠራቸው_ባረካቸውም_ስማቸውንም_በፈጠረበት_ቀን_አዳም_ብሎ_ጠራቸው

#አዳም...የወንድ ስም ብቻ አይደለም። ከላይ እንዳየነው #አዳም የወንድም የሴትም መጠርያ ሰም ነበር መጀመርያ ነገር ግን #ሕልው ሆና ትኖር የነበረችው #ሔዋን ይፍ ሰትሆን ስሟ #ሴት ሲባል #አዳም የወንዱ ብቻ መጠርያ እንደሆነ እንረዳለን።

☑️ሰለዚህ #የሔዋንን_ስም በቅደም ተከተል ስናይ

1⃣ አዳም
" ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው፥ ባረካቸውም። ስማቸውንም በፈጠረበት ቀን #አዳም ብሎ ጠራቸው።"(ኦሪት ዘፍጥረት 5:2)

2⃣ ሴት
" አዳምም አለ። ይህች አጥንት ከአጥንቴ ናት፥ ሥጋም ከሥጋዬ ናት፤ #እርስዋ_ከወንድ_ተገኝታለችና_ሴት_ትባል።"(ኦሪት ዘፍጥረት 2:23)

3⃣ ሔዋን
" #አዳምም_ለሚስቱ_ሔዋን_ብሎ_ስም_አወጣ፥ የሕያዋን ሁሉ እናት ናትና። "(ኦሪት ዘፍጥረት 3:20)

☑️ ከሁለተኛው ስም ማለትም ከአዳም ጎን ተገኝታለችና #ሴት ከተባለችው እንነሳ፦

🔘 ምንም እንኳ በሳይኮሎጅ የተወሰኑ ሀሳቦች ቢነሱም ከአዳም ጎን የተገኛችው ሔዋን ስም በእንግሊዘኛው ስናይ፦
#he_s_he...she
#male_fe_male...female

➡️ ይቀጥላል
:
:
☑️መንፈሳዊ ቻናላችንን ለመቀላቀል
👇👇👇👇👇👇👇👇

📜📜📜📜📜📜📜📜📜📜
📜 @zorthdox 📜
፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧
📜 @Hesychasm 📜
📜📜📜📜📜📜📜📜📜📜
:
:
ለመንፈሳዊ ጥያቄዎ
ለመንፈሳዊ ውይይት
ለአስተያየተዋ
👇👇👇👇👇👇👇👇
፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧
፧፧፧ @Apophatism ፧፧፧፧
፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧
፧፧፧ @Archeanarchos ፧፧
፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧
#ሻሎም የቻናላችን ተከታታዮች ልባዊ ሰላምታችን በያላችሁበት ይድረሳችሁ

ዛሬ በውስጥ መስመር ከደረሱን ጥያቄዎች መካከል አንዱን በማብራራት ለመመለስ እንሞክራለን። እርሰዎም በዘፍጥረት አስመልክተን በጻፍናቸው ዙርያ ጥያቄ ካለዎት ይጻፉልን።

☑️ለዛሬ የምንመልሰው ከደረሱን ውስጥ የሚከተለውን ነው
👇👇👇👇👇👇👇
ሰላም የእግዚአብሄር ቤተሰቦች እንደምን ናችሁ
ትምህርታችሁ እጅግ ከምናገረው በላይ አጥጋቢ ነው ቃለ ህይወት ያሰማልን ብያለሁ
ጥያቄ ነበረኝ ዘፍጥረት ላይ
1. ፈጣሪ እንስሳት ሲፈጥር በገነት ነበር ያኖራቸው?
2. ዘፍ 3 ቁ1 .. ላይ እባብ ሲፈጠርም ተንኮለኛ ነበር ወይስ በሰራው ስራ ነው?
3. አሁን በምድር ላይ ያሉት እንስሳ ከአዳም ጋር አብረው የተባረሩ ናቸው ወይስ ሌላ ፍጥረታት ናቸው? አመሰግናለው

ጠያቂያችንን እያመሰገንን ሌሎች ካሉም አድራሻችን ተጠቅማችሁ አድርሱን እንመልሳለን
🔸🔸🔸🔸🔸🔸🔸🔸🔸
🔸 የጥያቄዎቻችሁ መልስ🔸
🔸🔸🔸🔸🔸🔸🔸🔸🔸

#ጥያቄ_ቁጥር_አንድ
☑️ፈጣሪ እንስሳት ሲፈጥር በገነት ነበር ያኖራቸው?

በሥነ-ፍጥረት ትምህርት እንደተማርነው እግዚአብሔር አምላክ የፈጠራቸው #ብዙዉ_እንደአንድ_እየተቆጠረ ወይም #እንደየወገኑ እየተቆጠረ #22_ሰነፍጥረት ተፈጥረዎል። ከእነዚህም መካከል እንስሳቱ ፣ አራዊቱ ይጠቀሳሉ።

(ኦሪት ዘፍጥረት ምዕ. 1)
----------
24፤ እግዚአብሔርም አለ። #ምድር_ሕያዋን_ፍጥረታትን_እንደ_ወገኑ_እንስሳትንና_ተንቀሳቃሾችን_የምድር_አራዊትንም_እንደ_ወገኑ_ታውጣ፤ እንዲሁም ሆነ።

25፤ እግዚአብሔር የምድር አራዊትን #እንደ_ወገኑ አደረገ፥ እንስሳውንም #እንደ_ወገኑ፥ የመሬት ተንቀሳቃሾችንም #እንደ_ወገኑ_አደረገ፤ እግዚአብሔርም ያ መልካም እንደ ሆነ አየ።
🔘ጥያቄው የት ኖሩ? #በምድር_ወይስ_በገነት የሚል ነው። ለዚህ ጥያቄ መልስ የሕይወት መጽሐፍ እንድህ ይላል

(ኦሪት ዘፍጥረት ምዕ. 1)
----------
26፤ እግዚአብሔርም አለ። ሰውን በመልካችን እንደ ምሳሌአችን እንፍጠር፤ የባሕር ዓሦችንና የሰማይ ወፎችን፥ እንስሳትንና ምድርን ሁሉ፥ #በምድር_ላይ_የሚንቀሳቀሱትንም_ሁሉ_ይግዙ
27፤ እግዚአብሔርም ሰውን በመልኩ ፈጠረ፤ በእግዚአብሔር መልክ ፈጠረው፤ ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው።
28፤ እግዚአብሔርም ባረካቸው፥ እንዲህም አላቸው። ብዙ፥ ተባዙ፥ #ምድርንም_ሙሉአት_ግዙአትም፤ የባሕርን ዓሦችና የሰማይን ወፎች #በምድር_ላይ_የሚንቀሳቀሱትንም_ሁሉ_ግዙአቸው
🔘ሰለዚህ የሥነ ፍጥረት አክሊልና ገዥ አዳምና ሔዋን ግዙ የተባሉት በምድር ላይ የሚኖሩት ነው። ይህ ማለት የስነ ፍጥረት መኖርያ ምድር ነች ማለት ነው። ነገር ግን ምድር ስንል #ዓለማተ_ምድርን ሳንረሳ መሆን አለበት። ይህን ከረሳን እንደት ወደ ገነት ሊገቡ ይችላሉ የሚለው ሊያደናግረን ይችላል።
#ዓለማተ_ምድር

☑️እንደ ቤተክርሰቲያናችን አሰተምህሮ ዓለማት ሃያ ናቸው።
1⃣ ዓለማተ ምድር.. 5
2⃣ ዓለማተ ነፍስ... 2
3⃣ ዓለማተ እሳት... 9
4⃣ ዓለማተ ውሃ..... 4 በአጠቃላይ ሃያ ናቸው። ወደ ጥያቄው ሰናጠበው #ዓለማተ_ምድር የሚባሉት /ምድር ፣ ገነት ፣ ሲኦል ፣ ብሔረ ሔዋን እና ብሔረብፁዓን/ ናቸው። ይህ ማለት አምስቱም እግዚአብሔር በሚያውቀዉ ከምድር ጋር የተያያዙ አንድ የሆኑ ናቸው። ሰለዚህ ሰለ #ገነት ስናጠናም " እግዚአብሔር አምላክም #በምሥራቅ_በዔድን_ገነትን_ተከለ የፈጠረውንም ሰው ከዚያው አኖረው።"(ኦሪት ዘፍጥረት 2:8) እንዳለ #ገነት በምስራቅ በኩል የተተከለች የምድር አካል ነች። እግዚአብሔር በፈቀደው አዳም የሚኖርባት ፤ እንሰሳቱም እግዚአብሔር በፈቀደዉ መንገድ የሚገቡባትም ነበረች። " እግዚአብሔር አምላክም የምድር አራዊትንና የሰማይ ወፎችን ሁሉ ከመሬት አደረገ፤ በምን ስም እንደሚጠራቸውም ያይ ዘንድ #ወደ_አዳም_አመጣቸው፤ አዳምም ሕያው ነፍስ ላለው ሁሉ በስሙ እንደ ጠራው ስሙ ያው ሆነ። "(ኦሪት ዘፍጥረት 2:19)
👆👆👆👆👆👆👆
ቃሉ የሚለው ወደ አዳም አመጣቸው ነው የሚለው። አዳም ያለው በገነት ነው ፤ የመጡት ደግሞ መግባት ሰለሚችሉ እንጅ በተአምር አይደለም። በአጭሩ እንሰሳት ይኖሩ የነበሩት በምድር ላይ ነው።

#ጥያቄ_ቁጥር_ሁለት
☑️አሁን በምድር ላይ ያሉት እንስሳ ከአዳም ጋር የተፈጠሩት ናቸው ወይስ አድስ የተፈጠሩ?
🔘እግዚአብሔር አምላክ ሁሉንም ሰነ ፍጥረት ከመጀመርያው ቀን እሰከ ሰድተኛው ቀን ፈጥሯል ከዚያም ከስራው አረፏል።

(ኦሪት ዘፍጥረት ምዕ. 2)
----------
1፤ ሰማይና ምድር ሠራዊታቸውም ሁሉ ተፈጸሙ።
2፤ እግዚአብሔርም የሠራውን ሥራ በሰባተኛው ቀን ፈጸመ፤ #በሰባተኛውም_ቀን_ከሠራው ሥራ_ሁሉ_ዐረፈ።
3፤ እግዚአብሔርም ሰባተኛውን ቀን ባረከው ቀደሰውም፤ እግዚአብሔር ሊያደርገው ከፈጠረው ሥራ ሁሉ በእርሱ #ዐርፎአልና
👆👆👆👆👆👆
#አረፈ ሲል መፍጠሩን አቆመ ማለት ነው። ይህ ማለት ከዚህ በኋላ የተፈጠረ አንድም ነገር የለም። ሰለ እንስሳትም ካነሳን አዳም ከመፈጠሩ በፊት የተፈጠሩ ናቸው።

☑️ #ጥያቄ_ቁጥር_ሶስት
" እባብም እግዚአብሔር አምላክ ከፈጠረው ከምድር አውሬ ሁሉ ይልቅ #ተንኰለኛ ነበረ። ሴቲቱንም። በውኑ እግዚአብሔር ከገነት ዛፍ ሁሉ እንዳትበሉ አዝዞአልን? አላት።"(ኦሪት ዘፍጥረት 3:1)

#ይቀጥላል....

:
☑️መንፈሳዊ ቻናላችንን ለመቀላቀል
👇👇👇👇👇👇👇👇

📜📜📜📜📜📜📜📜📜📜
📜 @zorthdox 📜
፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧
📜 @Hesychasm 📜
📜📜📜📜📜📜📜📜📜📜
:
:
ለመንፈሳዊ ጥያቄዎ
ለመንፈሳዊ ውይይት
ለአስተያየተዋ
👇👇👇👇👇👇👇👇
፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧
፧፧፧ @Apophatism ፧፧፧፧
፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧
፧፧፧ @Archeanarchos ፧፧
፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧
🔸🔸🔸🔸🔸🔸🔸🔸🔸
🔸 የጥያቄዎቻችሁ መልስ🔸
🔸🔸🔸🔸🔸🔸🔸🔸🔸

#ጥያቄ_ቁጥር_ሶስት

☑️ዘፍ 3 ቁ.1 .. ላይ እባብ ሲፈጠርም ተንኮለኛ ነበር ወይስ በሰራው ስራ ነው?

" እባብም እግዚአብሔር አምላክ ከፈጠረው ከምድር አውሬ ሁሉ ይልቅ #ተንኰለኛ ነበረ "ዘፍ 3:1

👆👆#ተንኮለኛ የሚለውን በአማረኛው ፍች ከወሰድነው ስህተት ላይ ይጥለናል።

🔘ለዛሬ ለመነሻ ቃሉን ከእንግሊዘኛ መጽሐፍ ቅዱስ መውሰድ ግድ ሁኖብኛል። ምናልባት እንግሊዘኛ መጽሐፍ ቅዱስ የምትጠቀሙ ካላችሁ ቃሉን የምወሰደው #Holy_BIBLE_king_James እና #GOOD_NEWS_BIBLE ናቸው። #ምክር Holy Bible RSV ካላችሁ ብትጠቀሙ የተሻለ ነው።


#Serpent was more #Subtil than any beast of the filed which the LORD GOD had made. Genesis 3:1/KJV/

Now the #Snake was the most #cunning animal that the LORD GOD had made./GNB/
:
SUBTIL/Hebrew word/

#Wise
2 Samuel 13:3 , "Jonadab was a very subtle (the American Standard Revised Version "subtle") man" (discreet)
" ኢዮናዳብም #እጅግ_ብልህ ሰው ነበረ።" 2ኛ ሳሙ13:3)
Genesis 3:1 "Now the #serpent was more #subtle than any beast of the field,"

የተለያዩ መጽመፍ ቅዱስ እትሞችን ስንፈትሽ #subtle የሚለውን በተለያየ ቃል ቢገልጹትም ትርጉሙ አንድ ነው።
#Cautious-ጥንቁቅ, #Cunning ብልጥ #Crafty ተንኮለኛ #prudent ጠንቃቃ በማለት ያሰቀምጣሉ።

በአማረኛው መጽሐፍ ቅዱሳችን #ተንኮለኛ መባሉ የክፍት ሳይሆን #በማስተዋል#በእውቀቱና #በብልህነቱ ከዱር አራዊትም ሆነ እንሰሳት የተሻለ ሰለሆነ ነው። ይህን ሐሳብ እንድንረዳው አንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ሐሳብ እንይ፦
" እነሆ፥ እኔ እንደ በጎች በተኵላዎች መካከል እልካችኋለሁ ፤ ስለዚህ #እንደ_እባብ_ልባሞች እንደ ርግብም የዋሆች ሁኑ።"(የማቴዎስ ወንጌል 10:16)
“Behold, I send you forth as sheep in the midst of wolves: be ye therefore #wise_as_serpents, and harmless as doves” (Matthew 10:16, KJV).


☑️ #እባብም_ተንኮለኛ_ነበር የሚለው የሚገልጸው #ልባምነቱን_አሰተዋይነቱን_ብልህነቱን እንጅ አማረኛ ትርጉሙን ወስደን እንዳንሳሳት ልንጠነቀቅ ይገባል።
🔘ለአብነት አሰተዋይነቱን ወይም ብስልነቱን በሶስት ነጥቦች እንመልከት
1⃣ እባብ ቆዳውን እንደሚቀይር በሁሉም ዘንድ ተቀባይነት አለው። ነገር ግን ቆዳውን የሚቀይረው ለረጅም ጊዜ በመጾም ነው።
2⃣ እባብ ውሃ ሲጠጣ መርዙን አሰቀምጦ ነው። ይህም መርዙ ራሱኑ እንዳይገለው ጥንቃቄው ነው። /እኛም በዘወትር ጸሎት አቤቱ ይቅር በለን እኛም የበደሉንን ይቅር እንደምንል ብለን እንደምንጸልነው/
3⃣ እባብ አደጋ ሲያጋጥመው ራሱን አሳልፎ አይሰጥም። በተቻለው መጠን ተጠቅሎ ራሱ እንዳይመታ ለመከላከል ይሞክራል።

❇️በነገራችን ላይ የተለያዩ መካነ ድህረ ገጾችን በማየት ሰለ #እባብ ስታጠኑ #ከጥንታውያን_ግብጽ እሰከ #አሁኗ_ሕንድ ድረስ #በእባብ ተፈጥሮ ተሸንፈው እባብን በማምለክ የሚኖሩ ብዙዎች ናቸው።
🔸በዚህ ዘመን እንኳ #በሕንድ #እባብ ይመለካል። #በዓመቱ_እባብን_ለማምለክ_የሚውል_አንድ_የተለየ_ቀንም_አላቸው ። በዚህ ቀን የተለያዩ እባቦች ወተት ይሰጣቸዋል ይመለካሉም።

☑️ እኛ ክርሰቲያኖች ግን እንድናመልካቸው ሳይሆን ምሳሌ እንድሆኑን ወንጌል ይነግርናል። ይኸውም በማስተዋል እንደ እባብ እንድንመላለስ ነው። እባብ በመከራ ጊዜ ራሱን አሳልፎ እንደማይሰጥ እናንተም #ራሳችሁን አሳልፍችሁ አትስጡ ሲለን ነው።

#ማነው_ራሳችን?

" ነገር ግን #የወንድ_ሁሉ_ራስ_ክርስቶስ፥ የሴትም ራስ ወንድ፥ የክርስቶስም ራስ እግዚአብሔር እንደ ሆነ ልታውቁ እወዳለሁ።"(1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 11:3)
👆👆👆👆👆👆👆
ከእባብ ተማሩ ማለት በመከራ ሰአት እባብ ራሱን አሳልፎ እንደማይሰጥ እናንተም #ራሳችሁን_ክርስቶስን አሳልፍችሁ አትሰጡ ማለት ነው።

🙏🙏🙏እግዚአብሔር አምላክ በማስተዋል እንድንመላለስ ይርዳን አሜን
:
☑️መንፈሳዊ ቻናላችንን ለመቀላቀል
👇👇👇👇👇👇👇👇

📜📜📜📜📜📜📜📜📜📜
📜 @zorthdox 📜
፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧
📜 @Hesychasm 📜
📜📜📜📜📜📜📜📜📜📜
:
:
ለመንፈሳዊ ጥያቄዎ
ለመንፈሳዊ ውይይት
ለአስተያየተዋ
👇👇👇👇👇👇👇👇
፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧
፧፧፧ @Apophatism ፧፧፧፧
፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧
፧፧፧ @Archeanarchos ፧፧
፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧
አይዋሽም መስቀሉ:
°°°°°°°°°
ሰላም ለአንተ ይሁንልህ ወንድሜ ግያዝ እንደት ነህ እኔ በዚህ እንደ አንተ አይነት ግያዞች በበዙበት ሃገር እስኬሁን ድረስ ደህና ነኝ፡፡ብትሰማኝ ብትመለስም ብዬ ይህችን መንፈሳዊ ደብዳቤ ልጽፍልህ መልካም ሆኖ ታየኝ፡፡

ለምን በአንተ ዙሪያህን የከበበ ጦር አይተህ ትፈራለህ ?

★ቅዱሳኑን ግን ማየት ለምን ተሳነህ? አንተ ስላላያሃቸውም "የሉም በአጠገባችንም አይሰፍሩም አያድኑንም እያልክ ከመከራከር አልፈህ ለሰውም ተስተምራለህ፡፡ወንድሜ ግያዝ እንደት ዓይነ ስውርነትህን ለሌሎች ታስተምራለህ??

" የእግዚአብሔር ሰው ሎሌ ማለዳ ተነሥቶ በወጣ ጊዜ፥ እነሆ፥ በከተማይቱ ዙሪያ ጭፍራና ፈረሶች ሰረገሎችም ነበሩ። ሎሌውም። ጌታዬ ሆይ፥ ወዮ! ምን እናደርጋለን? አለው። "(ነገሥት ካልዕ 6:15) ተበሎ እንደተጻፈ

ወዴጄ ግያዝ ሆይ በጦርነቱ ስፍራ በገዳሙ "በዚህ መጋደል ለእኛ ምን ያደርጋል" የምትል ለምን ይሆን ?ለምንስ እንሽሽ እንውጣ እዬልክም ታስተምራለህ??

ስሙን የኤልሳዕ ደቀ መዝሙር ነኝ ትላለህ፡፡ ለሰውም ታስተምራለህ ግን ኤልሳዕዊ እምነት ቀርቶ ምግባር የለህም፡፡

ኤልሳዕ የመምህሩ የኤልያስን ፍጹም የሆነ መንገድ ተከትሏልና፡፡
ኤልሳዕ አሥራ ሁለት ጥማድ በሬዎቹን አርዶ ለነዳያን ያበላ ቅዱስ ሰው ነው፡፡
አንተ ግን የሌሎችን መብላት እንጂ ማብላት አታውቅም፡፡ሌሎች እንዲከተሉህ እንጂ አንተ ቅዱሳኑን አትከተልም፡፡

" ከተሻገሩም በኋላ ኤልያስ ኤልሳዕን። ከአንተ ሳልወሰድ አደርግልህ ዘንድ የምትሻውን ለምን አለው፤ ኤልሳዕም። መንፈስህ በእኔ ላይ #ሁለት #እጥፍ ይሆን ዘንድ እለምንሃለሁ አለ። "(መጽሐፈ ነገሥት ካልዕ 2:9) በማለት
ኤልሳዕ የመንፈሳዊ አባቱ የኤልያስ በረከትና መንፈስ እጥፍ ሆኖ በእርሱ ላይ እንዲያድርበት መንፈሳዊ አባቱን የጠየቀ ቅዱስ ሰው ነው፡፡

ወዳጄ ግያዝ ሆይ አንተ ግን እንደዚህ አይነቱን በረከት የማታውቅ አሳዛኝ የኤልሳዕ በረከት እጥፍ ከሚሆንልህ ይልቅ የሚአልፍ የዓለም ብርና ወርቅ እንድበዛልህ የምትፈልግ ሰው ነህ፡፡
ኤልሳዕ በመምህሩ በኤልያስ መጎናጸፊያ የዮርዳኖስን ባህር ተሻግሯል፡፡
ወዳጄ ግያዝ አንተ ግን ""ተራ ጨርቅ ነው መስቀሉን ተራ እንጨት ነው" የምትል አሳዛኝ ሰው ነህ፡፡፡

ኤልሳዕ ያለ ክፍያ የሚፈውስና የሚአድን ነቢይ ነው፡፡
አንተ ግን "ለሰው መልካም መሥራት አያድንም አያጸድቅም""ትላለህ፡፡እንኳን ልትሰጥ የሌሎችን አጭበርብረህ ትቀማለህ፡፡
እውነተኛው መምህር ኤልሳዕ በነፃ የፈወሰውን የሶርያ የሠራዊት አለቃ #የንዕማንን ገንዘብ በውሸት አታለህ ተቀበልከው፡፡

እነ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እነአትናቴዎስ በነጻ በአስተማሩት ንጹህ ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮ አንተ የእነሱ ልጅ ነኝ እያልክ ሀሰትህን ልትዘራ ትፈልጋለህ፡፡

ወዳጄ ግያዝ ሆይ እውነተኞቹ መምህራን ስም እያታለልክ "እፈውሳለሁ አድናለሁ"እያልክ የመበለቶችን ገንዘብ መሰብሰብ አግባብ ነውን??

ለስሙ እኔ የኤልሳዕ ደቀ መዝሙር ነኝ ብለህ የኤልሳዕን በትርና ልብስ ይዘሃል፡፡ነገር ግን ሙት አላስነሳህበትም የሱናማዊቷን ልጅ ማስነሳት ተስኖህ ቀረ፡፡
ምክንያቱም የኤልሳዕ በትርና ጨርቅ እንደሚአድን እምነት የለህምና፡፡

ወዳጄ ግያዝ ሆይ ኤልሳዕ ሲጠይቅህ የመለስከው ምን ነበር??
" ኤልሳዕም። ግያዝ ሆይ፥ ከወዴት መጣህ? አለው። እርሱም። እኔ #ባሪያህ #ወዴትም #አልሄድሁም ።"(መጽሐፈ ነገሥት ካልዕ 5:25) እያልክ በእግዚአብሔር ሰው ፊት ዋሸህ፡፡

ወዳጄ ግያዝ ሆይ ዛሬም አማኝ ሳትሆን ነኝ ትላለህ፡፡ከቅዱሳኑ ጋር ሳትኖር አለሁ እያልክ ታጭበረብራለህ፡፡ቦታ ቀይረሃል ስትባል አልቀየርኩም እያልክ ታወራለህ፡፡ወዳጄ ሆይ ይህ ትልቅ በደል አይደለምን?

ያች ሱናማዊተት ሴት
" ወደ ተራራው ወደ እግዚአብሔር ሰው በመጣች ጊዜ እግሮቹን ጨበጠች፤ ግያዝም #ሊያርቃት #ቀረበ፤ የእግዚአብሔርም ሰው። ነፍስዋ አዝናለችና ተዋት፤ እግዚአብሔርም ያንን ከእኔ ሰውሮታል አልነገረኝምም አለ። "
(መጽሐፈ ነገሥት ካልዕ 4:27) ተብሎ እንደተጻፈ፡፡
አማልዱን ብለው ወደ ቅዱሳኑ የሚቀርቡትን ሰዎች ለማራቅ ትጥራለህ ይሄንም ሥሬዬ ብለህ ይዘህዋል፡፡፡ተራራ አትውጡ ከንቱ ድካም ትላለህ፡፡

ወንድሜ ግያዝ ሆይ የበረከቱን እንጀራ (#ቅዱስ #ቁርባን)ህዝቡ እንዳይበላ መከልከልህስ ለምን ነበር??
""አንድ ሰውም ከበኣልሻሊሻ የበኵራቱን እንጀራ፥ ሀያ የገብስ እንጀራ፥ የእህልም እሸት በአቁማዳ ይዞ ወደ እግዚአብሔር ሰው መጣ፤ እርሱም። ይበሉ ዘንድ ለሕዝቡ ስጣቸው አለ። ሎሌውም። ይህን እንዴት አድርጌ ለመቶ ሰው እሰጣለሁ? አለ። እርሱም። ይበላሉ ያተርፋሉም ብሎ እግዚአብሔር ተናግሮአልና ይበሉ ዘንድ ለሕዝቡ ስጣቸው አለ። "
(መጽሐፈ ነገሥት ካልዕ 4:43)

ወዳጄ ግያዝ ሆይ ምንህም ከኤልሳዕ ጋር ስለማይመስል እባክህ የኤልሳዕ ደቀ መዝሙር ነኝ እያልክ አታታለን፡፡

ይህ ውሸትህና ክህደትህ ስለታወቀ ለምጽ በሙሉ በአካላትህ ሁሉ ይወጣብሃል፡፡
እንደ ንዕማን በዮርዳኖስ ተጠምቀህ እንዳትድን "ጠበሉን ተራ ውሃ ነው" ትላለህ
ከባእድ ሃገር የመጣ ንዕማን የሚአድን አፈሩን በሠረገላው ጭኖ እንዳልወሰደ አንተ" ይህ ሁሉ ከንቱ ድካም ነው" ትላለህ፡፡ሌሎቹ ሲድኑ አንተ በለምጥ ተሰቃይተህ ትሞታለህ፡፡

የእሳቱን ባህርስ በምን ትሻገረዋለህ ??

የኤልያስ መጎናፀፊያ [የቅዱሳኑ በረከትና ምልጃ)የለህምና
የሚአበረታታህስ ከክፉ የሚአድንህስ የማን ነው??

የሚጠብቁህን መላእክት ቅዱሳን አይንህ አያይምና፡፡የሉም አይሠሩም እያልክ ካድካቸው፡፡
ወዳጄ ግያዝ ሆይ ኦባክህን ተመለስ
ለአንተ ስለ አልታዩህ እንጅ እነርሱስ በመንፈስ ከእኛ ጋር ናቸው፡፡

ወዳጄ ግያዝ ሆይ ለዛሬው ጨረስኩ በተረፈ እንደ ደመና የከበቡንን ታይ ዘንድ ፈጣሪ አይንህን ያብራልህ፡፡፡

" ኤልሳዕም። አቤቱ፥ ያይ ዘንድ ዓይኖቹን፥ እባክህ፥ ግለጥ ብሎ ጸለየ። እግዚአብሔርም የብላቴናውን ዓይኖች ገለጠ፥ አየም፤ እነሆም፥ በኤልሳዕ ዙሪያ ያሉት የእሳት ፈረሶችና ሰረገሎች ተራራውን ሞልተውት ነበር። "
(መጽሐፈ ነገሥት ካልዕ 6:17)
ተብሎ እንደተጻፈ ጌታ ሆይ ለአንተ ምስክር የሆኑ ቅዱሳን መላእክትን ጻድቃን ሰማዕታትን እና ሊቃውንትን ያዩና ይመለከቱ ዘንድ እባክህ የግያዞችን ዓይን ግለጥላቸው፡፡
አሜን፡፡

By G/kirstos kassa
.................ታኅሳስ 18/5/2011 ዓ/ም፡፡
ውድ የዚህ መንፈሳዊ ቻናል ዓባላት ወዳጆቼ እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሠላምና በጤና አደረሳችሁ፡ አደረሰን፡፡ እያልኩ
በዓሉ መንፈሳዊ እንደመሆኑ ያለልክ በመብላትና በመጠጣት በመስከርና በመዝፈን ሳይሆን ክርስቶስ ኢየሱስ እኛን የወደደበትን ፍቅሩን እያሰባችሁ እንድታከብሩት እያሳሰብኩ
በዓሉ የሠላም የፍቅርና የአንድነት በዓል እንድሆንላችሁ እመኛለሁ፡፡


(የሉቃስ ወንጌል ምዕ. 2)
----------
10፤ መልአኩም እንዲህ አላቸው። እነሆ፥ ለሕዝቡ ሁሉ የሚሆን ታላቅ ደስታ የምሥራች እነግራችኋለሁና አትፍሩ፤

11፤ ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኃኒት እርሱም ክርስቶስ ጌታ የሆነ ተወልዶላችኋልና።

12፤ ይህም ምልክት ይሆንላችኋል፤ ሕፃን ተጠቅልሎ በግርግምም ተኝቶ ታገኛላችሁ።

13፤ ድንገትም ብዙ የሰማይ ሠራዊት ከመልአኩ ጋር ነበሩ። እግዚአብሔርንም እያመሰገኑ።

14፤ ክብር ለእግዚአብሔር በአርያም ይሁን ሰላምም በምድር ለሰውም በጎ ፈቃድ አሉ።

15፤ መላእክትም ከእነርሱ ተለይተው ወደ ሰማይ በወጡ ጊዜ፥ እረኞቹ እርስ በርሳቸው። እንግዲህ እስከ ቤተ ልሔም ድረስ እንሂድ እግዚአብሔርም የገለጠልንን ይህን የሆነውን ነገር እንይ ተባባሉ።

መልካም በዓል
ከእለታት አንድ ቀን አንድ ሰውዬ ወደ ሃኪም ዘንድ ሄዶ "ዶክተር እባክህን ባለቤቴ ከርቀት የመስማት ችግር ጀምሯታል ምን ላድርግ" ይለዋል

ዶክተሩም "ከምን ያህል ርቀት መስማት እንደማትችል ታውቃለህ?" ይለዋል ሰውየውም አላውቅም ሲል ይመልሳል ዶክተሩም በል ከምን ያህል ርቀት መስማት እንደማትችል አጣርተህ ና ይለዋል።

ሰውየውም እንደተባለው ወደ ቤቱ ይሄድና ከ 5 ሜትር ርቀት ላይ ቆሞ ሚስቱን "የእኔ ቆንጆ ዛሬ ምሳ ምንድነው ይላታል ዝም መልስ የለም አሁንም 4ሜትር ላይ ሆኖ "የእኔ ቆንጆ ዛሬ ምንድነው ምሳ ይላል" አሁንም ዝም ትለዋለች።

እንዲህ እያደረገ አጠገቧ ድረስ ይቀርብና "የእኔ ቆንጄ ዛሬ ምንድነው ምሳ?" ይላል ሚስትም በንዴት ዞራ "ምን ሆነሃል ዛሬ ቀን? አሁን እኮ ለ5ተኛ ጊዜ ስጠይቀኝ ምስር ወጥ አልኩህ እኮ" አለችው።

👉👉ለካ የማይሰማው እሱ ኖሯል👈👈
💚💛❤️💚💛❤️💚💛❤️💚💛❤️

ብዙዎቻችን የእራሳችን ችግር አይታየንም ተራራ የሚያህል ጉድፍ ይዘን ነጥብ የምታክል የሰው ነገር ይጎላብናል ።

እንሰብካለን የማንሰማው የማንለወጠው እኛው ነው

እንመክራለን እንገስጻለን ከአጥፊዎች ጎራ በቀዳሚነት እንሰለፋለን።

ፈጣሪ ሆይ ህግጋትህን እንድንጠብቅ የልቦናችን ዓይን ግለጽልን
🔘ሻሎም ተወዳጆች በጌታ ስም ልባዊ ሰላምታየ ይድረሳችሁ።

በተለያየ ምክንያት በቻናሉ የሚለጠፉ ተከታታይ ትምህርቶች ተቋርጠዎለ። እግዚአብሔር ቢፈቅድ ከነገ ጀምሮ እንማማራለን።

(የያዕቆብ መልእክት ምዕ. 4)
----------
13፤ አሁንም። ዛሬ ወይም ነገ ወደዚህ ከተማ እንሄዳለን በዚያም ዓመት እንኖራለን እንነግድማለን እናተርፍማለን የምትሉ እናንተ፥ ተመልከቱ፥ #ነገ_የሚሆነውን_አታውቁምና

14፤ ሕይወታችሁ ምንድር ነው? ጥቂት ጊዜ ታይቶ ኋላ እንደሚጠፋ እንፍዋለት ናችሁና።

15፤ በዚህ ፈንታ። #ጌታ_ቢፈቅድ_ብንኖርም ይህን ወይም ያን እናደርጋለን ማለት ይገባችኋል።

#ማስታወሻ በጣም ብዙና ተደጋጋሚ ጥያቄዎች በውስጥ ይደርሱኛል። አሰቸኳይ ናቸው የምለዉን ለጠያቂዎች ብቻ በተቻለ መጠን እየመለስኩ ነው። እንድሁም ለቻናላችን የሚያስተምሩ ከሆነም እየለጠፍኩ ነው ይህ ይቀጥላል ግን ያልተመለሰላችሁ ቅር እንዳይላችሁ ድግግሞሽ ስላለብኝ ነው በተቻለ መጠን እመልሳለሁ ነገር ግን ሌሎች አማራጮችንም ተጠቀሙ።
:
🔘ለዛሬው በቀጣይ እንደት ብንቀጥል መልካም ነው
🔸ዘፍጥረት ይቀጥል ወይስ ወደ ሐዲስ ኪዳን መጽሐፍት ገብተን እንዳስስ... መንፈሳዊ አሰተያያችሁን ለግሱኝ
ለመንፈሳዊ ውይይት
ለአስተያየተዋ
👇👇👇👇👇👇👇👇
፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧
፧፧፧ @Apophatism ፧፧፧፧
፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧
Forwarded from 💠አይዋሽም መስቀሉ💠
+++ ታቦትና ኢየሱስ ክርስቶስ +++
/ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ/
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ታቦታት ላይ
የተጻፈው ምንድር ነው? ተብለው ቢጠየቁ መልስዎ ምን
ይሆን? ‹ዐሥርቱ ትእዛዛት ተጽፈዋል› ካሉ መልስዎ
ትክክል አይደለም፡፡ ትክክለኛውን መልስ ከመመልከታችን
በፊት ጥቂት ነገሮች ስለ ታቦት እንመልከት፡፡ ብዙ ጊዜ ስለ
ታቦት አስፈላጊነት በሚሠጡ ማብራሪያዎች ላይ ሰፊውን
ቦታ የሚይዘው ስለ ብሉይ ኪዳን ታቦት የሚናገሩ
ጥቅሶችን በመጥቀስ በመሆኑ ምክንያት ስለ ታቦት
የሚነሡ ጥያቄዎች እንዳያቋርጡ ያደረገ ይመስላል፡፡
ስለዚህ በዚህች አጭር ጽሑፍ ‹ነገርን ከሥሩ› የሚለውን
አካሔድ ሳንከተል በቀጥታ ስለ ሐዲስ ኪዳን ታቦት ብቻ
እንመለከታለን፡፡
ታቦት በሐዲስ ኪዳን ለምን ያስፈልጋል? የሚለውን ጥያቄ
ለመመለስ ጌታችን በመጨረሻዋ ምሽት ሐሙስ ምሥጢረ
ቁርባንን ባስተማረ ጊዜ ያደረገውን እናስታውስ፡፡ ጌታችን
ሐዋርያቱ በተሰበሰቡበት ‹‹እንጀራውን አንሥቶ ባረከ
ቆርሶም ሠጣቸው እንካችሁ ብሉ ይህ ሥጋዬ ነው አለ፡፡
ጽዋውንም አንሥቶ አመሰገነ እንካችሁ ጠጡ ይህ
ስለብዙዎች የኃጢአት ይቅርታ የሚፈስሰው የሐዲስ ኪዳን
ደሜ ነው አለ›› (ማቴ. 26፡26) ጌታችን አስቀድሞ
‹‹ሥጋዬን የሚበላ ደሜን የሚጠጣ የዘላለም ሕይወት
አለው›› ብሎ በትምህርት የመሠረተውን ምሥጢረ ቁርባን
በተግባር ለሐዋርያቱ በዚህ መልኩ አስተማራቸው፡፡ (ዮሐ.
6፡56) ሐዋርያቱም ከጌታችን ዕርገት በኋላ ወንጌልን
እየሰበኩ ‹‹እንጀራውን በመቁረስ ይተጉ ነበር›› (ሐዋ.2፡
42) ቅዱስ ጳውሎስም ‹‹ከጌታ የተቀበልሁትን ለእናንተ
ደግሞ አሳልፌ ሠጥቻችኋለሁ›› በማለት ሥጋ ወደሙን
እንዴት መቀበል እንደሚገባና ‹ሳይገባው የሚቀበል የጌታ
ሥጋና ደም ዕዳ›› እንዳለበት በማስተማር የቁርባንን
ሥርዓት ደነገገ፡፡ (1ቆሮ. 11፡23-30)
ልብ እንበል የክርስቶስ ሥጋና ደም መሠጠቱን የሚያምን
አንድ ክርስቲያን ይህ የከበረ ሥጋና ደም እንደ ተራ ማዕድ
በየቦታው ፣ በየጠረጴዛው ሊቀርብ ይችላል ብሎ ለማሰብ
እጅግ ይከብደዋል፡፡ ስለዚህም ቤተ ክርስቲያን ዘመነ
ሰማዕታት አልፎ ስደትዋ እስካበቃበት ዘመን ድረስ በሒደት
እየተሻሻለ በመጣ የቤተ መቅደስ ሥርዓት የሐዲስ ኪዳኑን
መሥዋዕት በክብር ለመሠዋትና ለምእመናን ለማቀበል
በቅታለች፡፡ የበግና የፍየል ደም ይሠዋ በነበረበት የኦሪት
ዘመን እንኳን ለብቻው ትልቅ መሠዊያ ተዘጋጅቶ ፣
መሠዊያው ተቀድሶ ሰው በማይገባበት በመገናኛው
ድንኳን ውስጥ በክብር ተቀምጦ ነበር፡፡ በድንኳኒቱ
ውስጥ የሚያገለግሉት አሮንና ልጆቹም የተለየ ልብስ
ለብሰው የበጉን ደም በመሠዊያው ዙሪያ ባለው ቀርነ
ምሥዋዕ (የመሠዊያ ቀንድ) ላይ እየቀቡ ሥርዓቱን
ይፈጽሙ ነበር፡፡ ለበግና ለፍየል መሥዋዕት ይህ ሁሉ
ክብር ከተሠጠ እንደ በግ ስለ ሁላችን ኃጢአት ራሱን
መሥዋዕት አድርጎ ያቀረበው የእግዚአብሔር በግ ፣ እንደ
ሊቀ ካህናትነቱ እጁን በመስቀል ላይ ዘርግቶ የተሠዋውና
ሥጋና ደሙን እንካችሁ ብሉ ብሎ የሠጠን የኢየሱስ
ክርስቶስ ሥጋና ደም መሥዋዕት ሆኖ የሚቀርብበት
መሠዊያ ምንኛ የከበረ ይሆን?
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሥጋ
ወደሙ ‹መሠዊያ› የምትለው ታቦት በቅርጽም ፣
በአገልግሎትም ፣ በክብርም በኦሪት እግዚአብሔር ለሙሴ
ከሠጠው ታቦት ጋር አንድ አይደለም፡፡ የቀደመው ታቦት
በአራት ካህናት የሚያዝ በውስጡ ጽላት የሚቀመጥበት
ሲሆን የአሁኑ ታቦት ግን የጽላት ቅርጽ ያለው ጽሌ (ሰሌዳ)
ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያኒቱ የሐዲስ ኪዳኑን ታቦት በሦስት
ስያሜ ትጠራዋለች - የቃልኪዳኑ ታቦት ፣ ጽላት እና
መሠዊያ ብላ፡፡ የቃልኪዳኑ ታቦት የሚባለው እግዚአብሔር
ከእስራኤል ጋር ስላደረገው ስለ ቀድሞ ቃልኪዳን ሳይሆን
‹‹ሥጋዬን የሚበላ ደሜን የሚጠጣ የዘላለም ሕይወት
አለው›› ተብሎ ስለተሠጠው እና ‹‹ስለብዙዎች የኃጢአት
ይቅርታ የሚፈስሰው የሐዲስ ኪዳን ደሜ ነው›› ብሎ
ጌታችን ስለ ሠጠን አዲሱ ኪዳን ነው፡፡ (ማቴ. 26፡
26-30) የቃልኪዳኑ ታቦት የሚባለው በሥጋ ወደሙ
ስለተሠጠን ሐዲስ ኪዳን ነው፡፡ ታቦት መባሉ ደግሞ
እግዚአብሔር በረድኤት የሚያድርበት ፣ በሥጋ ወደሙ
ደግሞ በአካል የሚገለጥበት ዙፋን ስለሆነ ነው፡፡
ጽላት (ሰሌዳ) የሚባለው ዐሠርቱ ትእዛዛት ተጽፈውበት
አይደለም፡፡ የሕግ ሁሉ ፈጻሚ የሆነው የመድኃኔዓለም
ክርስቶስ ‹‹አልፋና ኦሜጋ›› የሚለው የከበረ ስሙ በታቦቱ
ላይ ስለተጻፈ ነው፡፡ (ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን /ሊቀ
ካህናት ክንፈ ገብርኤል አልታዬ/ ፣ የኢትዮጵያ ቤተ
ክርስቲያን ታሪክ /ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ/)
አንዳንድ ሰዎች ‹‹የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ታቦት ከኦሪቱ
ጋር አይመሳሰልም!›› ብለው እንደ ትልቅ መከራከሪያ
ሲያውጁ ማየት እጅግ ያስገርማል፡፡ አንዴ ‹ኦሪታዊት ነሽ›
አንድ ጊዜ ደግሞ ‹‹ለምን እንደ ኦሪቱ አልሆንሽም›› ብሎ
ንትርክ ግራ ያጋባል፡፡ የኦሪቱን ያልመሰለው አሁን ያለነው
ሐዲስ ኪዳን ላይ ስለሆነና የታቦቱ አገልግሎት የተለየ
ስለሆነ ነው፡፡ የሐዲስ ኪዳኑ ታቦ ት ከቀድሞው አንድ
ታቦት ተለይቶ በቁጥር የበዛውም ለብዙዎች መድረስ
ያለበት የክርስቶስ ሥጋና ደም የሚፈተትበት መሠዊያ
ስለሆነ ነው፡፡ መድኃኒት ቤት የሚበዛው መድኃኒት
የሚያስፈልጋቸው ሰዎች ሲበዙም አይደል? ታቦት የበዛው
በታቦቱ የሚሠዋው መሥዋዕት ለብዙዎች ስለ ኃጢአት
ይቅርታ የሚፈስሰውና ከኃጢአት ሁሉ የሚያነጻው ያለሱ
ሕይወት የላችሁም የተባልነው ሥጋና ደሙ ለኃጢአት
በሽተኞች ስለሚያስፈልገን ነው::
ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ እንዲህ ሲሉ ያብራራሉ ‹‹የኦሪት
ጽላት እግዚአብሔር በደመና ተከናንቦ ሙሴንና አሮንን
የሚያነጋግርበት ለእስራኤል ብቻ በረድኤት የሚገለጥበት
ዙፋን ነበር፡፡ ይህ ግን (የሐዲስ ኪዳኑ ታቦት) የአምላክ
ሥጋና ደም የሚፈተትበት (ጌታችን) ሥጋዬን የበላ ደሜን
የጠጣ የዘላለም ሕይወት አለው ሥጋዬን ብሉ ደሜን
ጠጡ እያለ ያመኑትን የሚጠራበት የምሕረት ምሥዋዕ
(መሠዊያ) ነው፡፡ ክብርና ስግደትም የሚደረግለት ለዚህ
ነው፡፡›› (የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ ገጽ 109)
አንዳንድ ሰዎች የሐዲስ ኪዳኑን መሠዊያ ለመቃወም
"ከእንግዲህ የቃልኪዳኑ ታቦት ብለው አይጠሩትም
አይሹትም አይደረግምም" የሚለውን ጥቅስ ይጠቅሳሉ።
(ኤር 3:16) ልክ ነው። እግዚአብሔር ከእስራኤል ጋር
የነበረውን የቀደመው ቃልኪዳን ስላለፈ ከእንግዲህ
በእስራኤል ዘንድ የቃልኪዳኑ ታቦት አይደረግም። እኛ ግን
ባለ አዲስ ቃልኪዳን ባለቤቶች ነንና ይህ ጥቅስ የሐዲስ
ኪዳን ደሙ መፍሰሻ የሆነውን የቃልኪዳን ታቦት
እንለዋለን።
በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ሥርዓት መሠረት በታቦታቱ ሁሉ
ላይ የተጻፈው ‹‹አልፋና ኦሜጋ›› የሚለው የመድኃኔዓለም
ክርስቶስ ስም ነው፡፡ ከስሙ ጋር ደግሞ በሁሉም ታቦታት
ላይ የሚከተለው ጥቅስ በግእዝ ተጽፎአል፡፡ ‹‹ከመ ለስሙ
ለኢየሱስ ክርስቶስ ይስግድ ኲሉ ብርክ ዘበሰማያት
ወዘበምድር›› ‹‹ይህም በሰማይና በምድር ከምድርም
በታች ያሉት ሁሉ በኢየሱስ ስም ይንበረከኩ ዘንድ›› የሚል
ነው፡፡ (ፊልጵ. 2፡10) በታቦቱ ፊት የሚሰግድ ሰው ለምን
እንደሚሰግድ በታቦቱ ላይ የሚጻፈው ይህ ጥቅስ
ያስረዳናል፡፡ ምክንያቱ ‹‹ጉልበት ሁሉ ለኢየሱስ ስም
ይሰግዱ ዘንድ›› ስለሚገባ ነው፡፡ የክርስቶስ ሥጋ
እንደሚቆረስ ደሙ እንደሚፈስስ የሚያምን ሰው በዚህ
መሠዊያ ፊት በፍርሃት ለክርስቶስ ይሰግዳል፡፡ ሥጋ
ወደሙን ‹‹ተራ መታሰቢያ ብቻ ነው›› የሚል ሰው ግን
በመሠዊያው ፊት እንዲሰግድና መሠዊያውን እንዲያከብር
አንጠብቅም፡፡ የኢየሱስ ክርስቶስ
😊👉👉በዓለ ጥምቀትን አስመልክቶ👈👈😊

# ገሀድ_ምንድን_ነው ?
@abuneestnfas
ገሃድ የቃሉ ትርጉም መገለጥ መታየት ነው፡፡ በጥምቀት መገለጥ መባሉ ሰው የሆነው አምላክ በዓለም ሲኖር እስከ 30 ዓመት እድሜው ድረስ ሰዎችን ለማዳን የመጣ መሲህ ሰው የሆነበት፣ አምላክ ኢየሱስ ክርስቶስ እሱ መሆኑን ሳያውቁ ከኖሩ በኃላ በ 30 ዓመት እድሜው በባሕረ ዮርዳኖስ በእደ ዮሐንስ እጅ ሲጠመቅ አብ በደመና
ሆኖ ‹‹የምወደው ልጄ ይህ ነው›› በማለቱ መንፈስ ቅዱስ
በርግብ አምሳል በራሱ ላይ ሲያርፍ በመታየቱ ነቢያት ይወርዳል ይወለዳል ይሰቀላል ይሞታል ይነሳል ብለው የተናገሩለት መሲሕ እርሱ መሆኑ ተገልጦአልና እንዲሁም ሦስቱ አካላት በአንድ ጊዜ ታይተዋልና ምስጢረ ሥላሴ የተገለጠለት በመሆኑ ገሃድ ይባላል፡፡(ማቴ 3፡13-17) ይህን በማሰብ የምንጾመው ጾም “የገሃድ ጾም” ይባላል፡፡ ቀኑም ጥር 10 ቀን ለ 11 አጥቢያ ነው፡፡ስለዚህ ጥር 10 ቀን ከ ሰባቱ አጽዋማት አንዱ የሆነው የገሀድ ጾም ነው ማለት ነው! ዘንድሮ 2011 ዓ.ም የጌታችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ጥምቀቱ የሚውለው ቅዳሜ ስለሆነ በዋዜማው አርብ ይፆማል።አርብ ደግሞ ራሱን የቻለ የፆም ቀን ስለሆነ እስከ ምሽቱ 12 ሰአት እንዲፆም አባቶች ብዙ ጊዜ ሲያስተምሩ ሰምቻለው።ይሄውም አርብ እስከ 9 ሰአት ራሱን የቻለ ፆም ስለሆነ ቢያንስ 3 ሰአቷ የገሃዱን ፆም ለማሰብ ነው። ለሊት ቅዳሴ ማስቀደስ የሚችል ግን ሀሙስ እህልና ውሃ ቀምሶ ለሊት ቅዳሴውን ያስቀድሳል።ቅዳሴ የሚገባው ከለሊቱ 6 ሰአት ተገብቶ ለሊት 9 ሰአት ቅዳሴው ያበቃል።
@abuneestnfas
#ከተራ_ምንድን_ነው?
ከተራ ከበበ ካለው የግእዝ ግሥ የወጣ ነው፡፡ ፍችው ውኃ
መከተር ፣ መገደብ ማለት ነው፡፡ የጥምቀት ዋዜማ ታቦተ ሕጉ ከቤተ መቅደስ ወጥቶ ውኃ ባለበት አካባቢ ስለሚያድር የየአጥቢያው ሕዝብ እየተሰበሰበ በወንዝ ዳር ወይም በምንጭ አካባቢ ድንኳን ይተከላል፡፡
ድንኳንም ከሌለ ዳስ ሲጥል ይውላል፡፡ የምንጮች ውኃ
ደካማ በመሆኑ እንዲጠራቀም ይከተራል ጉድጓድ እየተቆፈረ ውኃው እንዳይሄድ ይገደባል፡፡
#ምሣሌዎቹ
• በበዓለ ጥምቀት የታቦታቱ ወደ ወንዝ መውረድ መድኃኔዓለም ክርስቶስ በእደ ዮሐንስ ለመጠመቅ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ በዋዜማው የመኼዱ ምሳሌ ነው፡፡ ታቦቱ የጌታችን ምሳሌ ሲኾን ካህናቱ የመጥምቁ ዮሐንስ ምሳሌ ሲኾን መዘምራኑና ሕዝቡ ደግሞ ዮሐንስ
ያጠመቃቸው ሕዝቦች ምሳሌዎች ናቸው፡፡
• በባሕረ ጥምቀቱ ላይ በሚንሳፈፍ ነገር መብራት መደረጉ
በርግብ አምሳል ለወረደው መንፈስ ቅዱስ ምሳሌ ነው፡፡
"የአምላካችሁን የእግዚአብሔርን ቃል ኪዳን ታቦትና
ሌዋውያን ካህናት ተሸክመውት ባያችሁ ጊዜ፥ ከሰፈራችሁ ተነስታችሁ ተከተሉት። " #ኢያሱ_3:3
” ጥሩ እድል ሊሆንም ላይሆንም ይችላል” ጣፋጭ ታሪክ

በአንድ መንደር ውስጥ የሚኖር አንድ ገበሬ ነበር። ከእለታት አንድ ቀን የዚህ ገበሬ ፈረስ ይጠፋል። የመንደሩ ሰው ሁሉ ተሰብስቦ ወደ ገበሬው ቤት በመሄድ ሃዘናቸውን ይገልጹለታል።እንዲህ ሲሉ ” ፈረስህ በመጥፋቱ አዝነናል፤ እንደው ምን አይነት መጥፎ እድል ነው?” ሲሉት። ገበሬው መልሶ “መጥፎ እድል ሊሆንም ላይሆንም ይችላል” ብሎ መለሰላቸው።በበነጋታው የጠፋው ፈረስ ሌሎች ሰባት ፈረሶችን አስከትሎ መጣ። ይህንን የተመለከቱ የሰፈሩ ሰዎች ወሬውን ይሰሙና ወደ ገበሬው ቤት በመሄድ እንዲህ ይሉታል።” የሚገርም እኮ ነው፤ አንድ ፈረስ ነበረህ አሁን ስምንት ፈረሶች ሆኑልህ። እንደው ምን አይነት ጥሩ እድል ነው?” ገበሬውም ” ጥሩ እድል ሊሆንም ላይሆንም ይችላል” ሲል መለሰላቸው።ሲነጋ የገበሬው ልጅ ከስምንቱ ፈረሶች አንዱን ሰርቆ ሊጋልብ ሲሞክር ፈረሱ አሽቀንጥሮ ይጥለውና ልጁ እግሩን ይሰበራል።ወሬውም በሰፈሩ ሁሉ ተሰማ። እንደ ልማዳቸው የሰፈሩ ሰዎች ተሰባስበው ” ውይ የልጅህ መሰበር እንዴት ያሳዝናል ባክህ? እንደው ምን አይነት መጥፎ እድል ነው?” አሉት። ገበሬውም መልሶ ” መጥፎ እድል ሊሆንም ላይሆንም ይችላል” ሲል እንደልማዱ በእርጋታ መለሰላቸው። በቀጣዩ ቀን የመንደሩ የጦር ተቆጣጣሪ፤ ወጣቶችን ለጦር ሜዳ ሊመለምል ወደ መንደሩ ይዘልቃል። የሁሉንም ቤት ወጣት ወንዶች ለጦርነት ሲመለምል ከፈረስ ላይ የወደቀውን የገበሬውን ልጅ ግን እግሩ ስለተሰበረ ሳይወስዱት ቀሩ።ይሄኔ የመንደሩ ሰዎች ተሰባስበው ወደ ገበሬው በመሄድ እንዲህ አሉት “አየህ ልጅህ እግሩን በመሰበሩ ወደጦር ሜዳ ሳይወሰድ ቀረ፤ እንደው ምን አይነት ጥሩ እድል ነው?” ገበሬው ግን አሁንም እንዲህ አላቸው ” ጥሩ እድል ሊሆንም ላይሆንም ይችላል”
እናም .............................................................
ብዙን ጊዜ በኑሮዋችን ውስጥ አንድ ነገር ሲከሰት በችኮላ “መጥፎ” ወይም “ጥሩ” እድል በማለት እንፈርጃለን። መልካም ያልነው ነገር መጥፎ ነገር ይዞ ሲመጣ፤ መጥፎ ያልነው ነገር ደግሞ መልካም ነገር ይዞ ብቅ ሲል፤ ዳኝነታችን መሰረት የሌለው እንደሆነ እንረዳለን። ወደ ኋላ መለስ ብለን የመጣንበትን ብንቃኝ፤ በእርግጠኝነት በአንድ ወቅት መጥፎ እድል ናቸው ብለን የፈረጅናቸው በኋላ ላይ ግን መልካም ነገር ይዘውልን የመጡ የህይወት አጋጣሚዎችን እናገኛለን። እኛ ግን ቀድመን “መጥፎ” እና “ጥሩ” እድል እያልን ነገሮችን ስንከፋፍል፤ አይምሮዋችን አስቀድሞ ነገሮችን ስለሚዳኝ ጭንቀት በጊዜው ከሚሆነው ነገር ጋር እንዳንስማማ ያደርገናል። የገበሬው አመለካከት ግን እጅግ የሚደንቅ ነው። የሚገጥሙት ነገሮች ምን ይዘው እንደሚመጡ ስለማያውቅ “መልካም” እና “መጥፎ” እድል እያለ እራሱን ላልተጠበቀ ሃዘን አያዘጋጅም።የፈረሱ መጥፋት መጥፎ እድል ነው ብሎ ለማለት አልደፈረም። ምክንያቱም የሆነው ነገር ምን ይዞ እንደሚመጣ ስላላወቀ። ፈረሱ ሌሎች ፈረሶችን ይዞ ሲመጣም “መልካም እድል” ብሎ ሊደመድም አልወደደም፤ እንደሰወኛ ብናስብ እነዛ ፈረሶች ባይኖሩ ልጁ አይሰበርም ነበር። የልጁን መሰበርም እንደ መጥፎ እድል ሊወስደው አልፈለገም፤ እንደሰወኛ ግን ልጁ እግሩ ባይሰበር ኖሮ፤ እንደሌሎቹ የሰፈር ወጣቶች ከአባቱ ተነጥሎ ወደ ጦር ሜዳ በተወሰደ ነበር።
እንዲህ አይነት አመለካከት ከአልታሰበ የስሜት መናወጥ ያድናል፤ እርግጥ ነው ቀላል አይደለም። ነገር ግን በህይወት መንገድ ላይ ስንጓዝ የሚገጥሙን ሁኔታዎች ጊዜ ብቻ የሚፈታው ሚስጥር በውስጣቸው አለ። ነገሮች ሁሉ ወደ በጎ እየተቀየሩልን እግዚአብሔርን ባማረርንበት አፋችን እንድናመሰግነው ያደረገን አጋጣሚ በሁላችንም ህይወት ውስጥ አለ። በአንጻሩ በስንት ልመና ያገኘነውን ነገር ምነው ባትሰጠኝ ኖሮ ብለን ያማረርንበትም ጊዜ ይኖራል። በዚህ አለም ላይ
ያለምክንያት የሚሆን ምንም ነገር የለም። ምናልባት አሁን እያለፍነበት ያለው ፈተና እና የኑሮ ጦርነት እድላችንንን እንድንማረር እያረገን ይሆናል፤ ነገ የሚመጣውን ግን አናውቅም። የእኛ ድርሻ መሆን ያለበት ሁሉንም እንደአመጣጡ መቀበልና ነገር ሁሉ ለበጎ ነው ብለን
ለእግዚአብሔር መተው ነው።መጽሐፍ ቅዱስም እንዲህ ይላል “ሁሉም ነገር ለበጎ ነው”ዛሬ ሁሉም ነገር ቢጨልምብህ ለበጎ ነው ብሎ ማለፍ ተረት ብቻ አይደለም፡፡ ጨለማ በጎ ነገሮችን ይዞ ለመምጣቱ ህይወት እራሷ ታስተምረናለችና ፡፡

https://telegram.me/Hesychasm


ሠናይ ቀን ይሁንላችሁ፡፡
Forwarded from Deleted Account
እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የጥምቀት በዓል አደረሰህ/ሽ ?
ሀዳፌ ነፍስ ለጻድቃን የጻድቃንን ነፍስ የሚአሻግረው በምድር ላይ ተገለጠ
ተጠመቀም
ለምን ወደ ዮሐንስ ሄዶ ተጠመቀ??
➊ጌታ የመጣው ለትህትና ነውና ወደ ፍጡሩ ወደ ዮሐንስ ሄዶ ተጠመቀ
➋እናተም ሄዴችሁ ተጠመቁ ለማለት
ለምን በዮርዳኖስ ተጠመቀ??
➊ምሳሌውናን እና ትንቢቱ ይፈጸም ዘንድ በዮርዳኖስ ተጠመቀ
➋ዲያብሎስ በዮርዳኖስ የጣለውን የእዳ ደብዳቤ ይቀድልን ዘንድ በዮርዳኖስ ተጠመቀ
ለምን በሠላሳ ዓመቱ ተጠመቀ?
➊አዳም(እኛ)በሠላሳ ዓመታችን ያጣንውን ልጅነት ይመልስልን ዘንድ በሰላሳ ዓመቱ ተጠመቀ
➋የአጥማቃው የዮሐንስን እድሜ ይጠብቅ ዘንድ
➌የክህነት አገልግሎት በ30 ዓመት ይሰጥ ሲል በ30 ዓመቱ ተጠመቀ
ለምን በሌሊት ተጠመቀ??
➊ከጨለማ ወደ ብርሃን የምትመለሱበት ደረሰ ሲል በሌሊት ተጠመቀ
➋የወረደው ርግብ መንፈስ ቅዲስ እንደሆነ ለማጠየቅ በሌሊት ተጠመቀ
ርግብ በሌሊት መብረር አትችልምና
ጌታ ሲጠመቅ ለምን ዮሐንስ እጁን አልጫነበትም?
➊የኦሪቱ መስዋእት አለፈ የሐድስ ኪዳኑ መስዋዕት አንተ ነህ ሲል
➋አይሁድ ክርስቶስን ያከበረው ዮሐንስ ነው እንዳይሉ
ለምን በውሃ ተጠመቀ??
➊በኖህ ዘመን የሆነውን በማስታወስ ውሃ ለመዓት የተፈጠረ ይሉ ነበረና ውሃ ለምህረትም እንደተፈጠረ ለማስረዳት
➋ውሃ መልክዕ ያሳያል እናተም ብትጠመቁ መልክአ ነፍሳችሁን ታያላችሁ ሲለን
➌ውሃ ልብስ ያጠራል፡፡እናተም በጥምቀት ከኃጢአት ትነጻላችሁ ሲለን
➌ውሃ አትክልት ያለመልማል፡፡እናንተም በጥምቀት ልምላሜ ነፍስን ታገኛላችሁ ሲለን በውሃ ተጠመቀ
በክርስቶስ ጥምቀት ምን አገኘን??
➊ተሰውሮ የኖረው ምሥጢረ ሥላሴ ተገለጸልን
➋የእዳ ደብዴቤአችን ተሻረልን
➌በጥምቀት ልጅነትን የምናገኝበት መንገድ ተከፈተልን ጥምቀት ተመሰረተልን
➍የጥምቀቱ ውሃ ተባረከልን
ጥምቀትን በዓል እንደት እናክብረው??
ብትችል/ይ ሌሊት አስቀድሰህ/ሽ ሥጋና ደሙን ተቀበል/ይ
በመብል በመጠጥ በጭፈራ በዘፈንና በዝሙት እንዳይሆን ተጠንቀቅ
እይታዎችህ ክርስቶስ ለአንተ/ አንቺ የከፈለውን የደም ዋጋ ላይ ይሁን
ዐይንህ/ሽ አይቶ በምኞት እንዳትቃጠል/ይ ኃጢአትም እንዳትሰራ/ሪ አይናችሁን በመስቀሉ ጋርዱ
ከልክ በላይ በመልበስ ሰዎችን እንዳታሰናክል/ይ ተጠንቀቅ/ቂ

በተረፈ ወዳጆቼ ሆይ መልካም የጥምቀት በዓል ይሁንልህ/ሽ /ችሁ፡፡