ቃልህ እውነት ነው ዘኦርቶዶክስ /Your word is Truth Zorthodox/
428 subscribers
3 photos
2 files
19 links
🔶 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት እንድሁም አጫጭር ትንታኔዋችና ዳሰሳ

🔵 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶች #ከሽልማት ጋር

🔷 የጥያቄዎቻችሁ መልስ

🔶 መጽሐፍ ቅዱሳዊ የቁጥር ዳሰሳዎችና ሌሎችም... #ቤተሰብ ይሁኑ
Download Telegram
በመጀመሪያ ቃል ነበረ፡፡ዮሐ ፩፥፩
፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠

#ክፍል #አንድ
፡፡
ኢየሱስ መጀመሪያ የለውም ነገር ግን በመጀመሪያ ነበረ
ኢየሱስ መጀመሪያ የሌለው በመጀመሪያ ተብሎ የሚጠራ አምላክ ነው፡፡
ቤተ ልሔም ለክርስቶስ ልዩ የመገለጥ ስፍራ እንጂ የህልውናው መነሻ አይደለችም። ቅዱስ ዮሐንስም እርሱ ከዘላለም ከአብ ጋር የነበረ መሆኑን በመግለጥ ይጀምራል።
በዘፍጥረትም
" በመጀመሪያ እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን ፈጠረ።"(ዘፍ 1:1)ተብሎ የተገለጸው ዮሐንስ "በመጀመሪያ ቃል ነበረ "ብሎ የገለጸውን ነው፡፡

በመጀመሪያ የሚለው የቃል ስምን እንጂ ጊዜን አመልካች ብቻ አይደለም
ኢየሱስ በመጀመሪያ የነበረ ጌታ ዘመን የማይሰፈርለት ቀናት የማይቆጥርለት ጌታ ነው፡፡
ወይም በሌላ አባባል 'መጀመሪያ ሲል ከአብ መወለዱን ስንናገር ከአብ በዘለዓለማዊ
መገኘት (Eternal Generation) መገኘቱን ለማመልከት እንጂ በጊዜ የተገደበ መሆኑን
ለማመልከት አይደለም፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ኢየሱስ መጀመርያ እንደሌለው ነገር ግን
በመጀመርያ እንደ ነበረ የሚናገር ሲሆን የዓለም ፈጣሪ መሆኑን ያስተምራል (ዮሐንስ 1፡1-18)፡፡ እርሱ የዘለዓለም አባት (ዘለዓለማዊነትን ያስገኘ) እንጂ በጊዜ የተገደበ አይደለም፡፡

ኢየሱስ የአብ አካላዊ ቃል ሆኖ በመጀመሪያ የነበረ ፈጣሪ ነው፡፡፡ክብር ይግባውና ቃልስ ፍጡር አይደለም፡፡
አብ መጀመሪያ "ቃልን ፈጠረ "ማለት አብ ቃልን ከመፍጠሩ በፊት ቃል የሌለው //ሎቱ ስብሐትና// ድዳ ነበረ ያሰኛል፡፡

ሊቀ ነቢያት ሙሴ በመጀመሪያ" እግዚአብሔር ሰማይና ምድርን ፈጠረ"
ብሎ የገለጸውን ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ በሐድስ ኪዳን"" በመጀመሪያ ቃል ነበረ ""አለ
የዮሐንስ የወንጌሉ መጀመሪያ መጀመሪያ የነበረው ቃል ነው፡፡
ስለዚህም ፍጥረት ሁሉ የተፈጠረው መጀመሪያ ተብሎ በተጠራው በመጀመሪያ በቃል/#ሎጎስ /ኢየሱስ ነው፡፡
እንደ ዛሬ ዘመኖቹ አሕዛብና መናፍቃን የእርሱ ማንነት ጠፍቷቸው
" እንግዲህ። አንተ ማን ነህ?? ብለው ለጠየቁት አይሁድ ኢየሱስ ሲመልስላቸው ። ""#ከመጀመሪያ #ለእናንተ #የተናገርሁት ነኝ።" (ዮሐ8:25) በማለት በነቢያት አድሮ ሲአስተምራቸው ሲናገራቸው የነበረው እርሱ ቃል ኢየሱስ እንደሆነ ተናገረ፡፡
ይሄን የሰማው ቅዱስ ጳውሎስም
" ከጥንት ጀምሮ እግዚአብሔር በብዙ ዓይነትና በብዙ ጎዳና ለአባቶቻችን በነቢያት ተናግሮ ነበር አሁን ግን••• ዓለማትን #በፈጠረበት #በልጁ በዚህ ዘመን መጨረሻ ለእኛ ተናገረን፤"(ዕብ 1:2) በማለት ጽፏል፡፡


ሙሴ ዘፍጥረትን ሲጽፍ<< በመጀመሪያ እግዚአብሔር ሰማይና ምድርን ፈጠረ >>በማለት ብቻ በዝምታ ያለፈውን ቅዱስ ዮሐንስ ግን ዝም ብሎ አላለፈም፡፡ እርሱ ክርስቶስ እግዚአብሔር እንደሆነ ሲያስረዳ
" ሁሉ በእርሱ ሆነ፥ #ከሆነውም አንዳች ስንኳ #ያለ #እርሱ #አልሆነም።"(ዮሐ 1:3)በማለት አምላክነቱንና ፈጣሪነቱን አስረግጦ ነገረን፡፡

ቃል የተባለው ሥጋ የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ እንደሆነም በእራእዩ እንድህ ይለናል፡፡

"በደምም የተረጨ ልብስ ተጐናጽፎአል፥ #ስሙም #የእግዚአብሔር #ቃል ተብሎአል።"
(የዮሐንስ ራእይ 19:13)ይለናል፡፡

አዳምንና ሔዋንን ወንድና ሴት አድርጎ የፈጠራቸው መጀመሪያ የተባለ ቃል ኢየሱስ እርሱ እንደሆነ
"ፈጣሪ በመጀመሪያ ወንድና ሴት አደረጋቸው፥"(ማቴ 19:4) በማለት ሰውን የፈጠረ በመጀመሪያ የነበረው ቃል ኢየሱስ እርሱ እንደሆነም ተናግሯል፡፡


በመጀመሪያ ሲል አንዳንዶች አብ ከፊት ወልድ /ቃል ኢየሱስ/ደግሞ በኃላ የተገኘ ይመስላቸዋል፡፡
መጽሐፍ ግን እንድህ ይላል፡፡
" የእስራኤል ንጉሥ እግዚአብሔር፥ የሚቤዥም የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል። #እኔ #ፊተኛ #ነኝ እኔም #ኋለኛ ነኝ፥ #ከእኔ #ሌላም #አምላክ የለም።"(ኢሳ44:6)
ብሎ እራሱ በብሉይ ኪዳን በነቢያት አድሮ የተናገረውን ቅዱስ ጳውሎስ ጠቅሶ ሲናገር
"#እርሱም #ከሁሉ #በፊት ነው ሁሉም በእርሱ ተጋጥሞአል።"(ቆላ1:17) በማለት ኢየሱስ አምላክ እንደሆነ ከእርሱ በፊትም ሆነ በኀላ አምላክ እንደሌለ አስረዳ፡፡
ኢየሱስም " አንተ ከአብርሃም አትበልጥም ፍጡር ነህ" ላሉት አይሁድ እንድህ መልሶ ነበር
" እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ #አብርሃም #ሳይወለድ #እኔ #አለሁ አላቸው።"(ዮሐ8:58)

የአዳም የአብርሃም የዓለማቱ ፈጣሪ መሆኑን ሲነግራቸው
"እራሱን አምላክ አድርጓል" ብለው በድንጋይ ሊወግሩት ድንጋይ ሲያነሱ ተሰውሮአቸው ሳይሆን በመካከላቸው አልፎ ሄደ ይህ በራሱ ኢየሱስ አምላክ እንደሆነ በቂ ማስረጃ ነው

ዛሬም ኢየሱስ ማን ነህ ?? ለሚሉት ሁሉ
""የቡድሃ መስራች ሳይወለድ እኔ አለሁ የእስልምና መስራች ሙሐመድ ሳይወለድ እኔ አለሁ የእነ #ሙሐመድ ፈጣሪ የእናተም ፈጣሪ እኔ ነኝ"" ይላል፡፡

በሌላ ቦታም
" አልፋና ዖሜጋ፥ መጀመሪያውና መጨረሻው እኔ ነኝ። ለተጠማ ከሕይወት ውኃ ምንጭ እንዲያው እኔ እሰጣለሁ።"(ራእይ 21:6)ይለናል፡፡
በመጀመሪያ ስለነበረው ቃል ኢየሱስ ሲናገር
" ስለ #ሕይወት ቃል ከመጀመሪያው የነበረውንና የሰማነውን በዓይኖቻችንም ያየነውን የተመለከትነውንም እጆቻችንም የዳሰሱትን እናወራለን፤"(1ኛዮሐ1:1)ይላል፡፡

እንደት ደስ ይላል፡፡
ኦርቶዶክሳዊያን የምንሰብከው ኢየሱስ በመጀመሪያ የነበረውን ከዚያም በሥጋ የተገለጸውን እውነተኛውን አምላክ በአይናችን አይተን በጆሮአችን ሰምተን በእጃችን የዳሰስን ነው፡፡እንጂ የሆነ ፈላስፋ የፈለሰፈውን ወይም ተገለጠልኝ የሚል የሐሰተኛ ነቢይን ቃል የተከተልን አይደለም፡፡
ቅዱስ ጴጥሮስ እንዳለን
""የእርሱን ግርማ አይተን እንጂ በብልሃት የተፈጠረውን ተረት ሳንከተል የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ኃይልና መምጣት አስታወቅናችሁ።""(2ኛጴጥ1:16)

እንግድህ ወዳጆች ሆይ ቀኑ ሳይመሽ በእርሱ በእውነተኛው አምላክ በእርሱ በክርስቶስ አምላክነት ታምኑ ዘንድ ቃሉ ቀርቦልሃል

እናም ኢየሱስ በመጀመሪያ ቃል ነበረ ዘለዓለማዊ ቃል እርሱ ክርስቶስ ነው
የሚታየውና የማይታየው ስም ያለውና ስም የሌለው ከመኖሩ ጊዜ ከመፈጠሩ ሰማይና ምድር ከመዘርጋታቸው ከመፈጠራቸው በፊት በመጀመሪያ ቃል ነበረ
በመጀመሪያ ቃል ነበረ፡፡ኢየሱስ ነበረ፡፡

የት ነበረ••••••??? ብለን ለምንጠይቀው ደግሞ
""ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ ""ብሎ ይመልስልናል፡፡
ይቀጥላል•••••••

በአይዋሽም መስቀሉ (ገብረ ክርስቶስ ካሳ)
:
""ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ""ዮሐ 1፥1
:፠፠=፠፠፠፠፠፠፠=፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
•••••••••••••#ክፍል #ሁለት
•••••••••••••••፠፠፠፠፠፠
በክፍል አንድ በመጀመሪያ ቃል ነበረ የሚለውን አይተናል
በክፍል ሁለት ""ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ"" የሚለውን ደግሞ እነሆ

በመጀመሪያ ቃል ሎጉስ ነበረ በመጀመሪያ የነበረ ቃል የት ነበረ ????
ብለን ለምንጠይቀው ቁዱስ ዮሐንስ ሲመልስ "ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ "ይለናል፡፡

ኢየሱስ መኖር የጀመረው ከድንግል ማርያም ከተወለደ ወድህ አይደለም፡፡
እርሱ ዓለም ሳይፈጠር በእግዚአብሔር አብ ዘንድ በከዊነ ቃልነቱ ነበረ፡፡
ቃል ሆኖም ሰማይና ምድርን ፈጥሯል፡፡
"በእግዚአብሔር #ቃል (በወልድ ) ሰማዮች ጸኑ፥ ሠራዊታቸውም ሁሉ በአፉ እስትንፋስ(በመንፈስ ቅዱስ)፤"(መዝ 33:6)እንዲል፡፡
ዳዊት እንድህ የዘመረውን ቅዱስ ጳውሎስ ደግሞ
" #ዓለሞች በእግዚአብሔር #ቃል እንደ ተዘጋጁ፥ ስለዚህም የሚታየው ነገር ከሚታዩት እንዳልሆነ በእምነት እናስተውላለን።"(ዕብ 11:3)ይለናል፡፡
ይህም በእግዚአብሔር ዘንድ የነበረው በከዊነ ቃልነቱ ዓለምን የፈጠረው አርሱ እንደሆነ ግልጽ ማስረጃ ነው፡፡
"
" አቤቱ፥ አንተ #ከጥንት ምድርን መሠረትህ፥ ሰማያትም የእጅህ ሥራ ናቸው።"(መዝ 102:25)
ከጥንት ሰማይንና ምድርን የሠራ በእግዚአብሔር ዘንድ የነበረ ቃል እርሱ ነው
ኢየሱስ "ፈጣሪ አይደለም" ለሚሉት እንድህ በማለት ይመልሳል፡፡
<<ሰማዮችን በዘረጋ ጊዜ አብሬ ነበርሁ፥ በቀላያት ፊት ክበብን በደነገገ ጊዜ፥ደመናትን በላይ ባዘጋጀ ጊዜ፥ የቀላይን ምንጮች ባጸና ጊዜ፥
ለባሕርም ዳርቻን በወሰነ ጊዜ ውኃ ከትእዛዙ እንዳያልፍ፥ የምድርን መሠረት በመሠረተ ጊዜ፥ የዚያን ጊዜ እኔ በእርሱ ዘንድ ዋና ሠራተኛ ነበርሁ፤ ዕለት ዕለት ደስ አሰኘው ነበርሁ፥ በፊቱም ሁልጊዜ ደስ ይለኝ ነበርሁ፥ >>(ምሳ 8:30) ይላል፡፡

እርሱ በቃልነቱ ለዘለዓለም አለ ይኖራልም፡፡
"ተራሮች ሳይወለዱ፥ ምድርም ዓለምም ሳይሠሩ፥ ከዘላለም እስከ ዘላለም ድረስ አንተ ነህ።"(መዝ ዳዊት 90:2)
ኢየሱስ ዓለም ሳይፈጠር የአብ ልጅ ሆኖ በአብ ዘንድ ነበረ፡፡
"ከአንተ ጋር ቀድሞ በኃይልህ ቀን፥ በቅዱሳን ብርሃን፥ #ከአጥቢያ #ኮከብ አስቀድሞ #ከሆድ #ወለድሁህ።"(መዝ110:3)
ዓለም ሳይፈጠር ከአብ የተወለደ ለልደቱ ጥንት የሌለው እርሱ በብሉይ ኪዳን እንድህ ይላል፡፡

"ወደ እኔ ቅረቡ ይህንም ስሙ፤ እኔ #ከጥንት #ጀምሬ በስውር አልተናገርሁም፤ ከሆነበት ዘመን ጀምሮ እኔ #በዚያ (#በእግዚአብሔር ዘንድ) ነበርሁ፥ #አሁንም ጌታ እግዚአብሔር(አብ ) ና መንፈሱ (መንፈስ ቅዱስ ) #ልከውኛል።"(ኢሳ48:16)ይልል፡፡

ይህን በኢሳይያስ የተነገረውን ቅዱስ ዮሐንስም ወስዶ እንድህ ይላል
"በእርሱ በኩል በሕይወት እንኖር ዘንድ እግዚአብሔር አንድ #ልጁን ወደ #ዓለም #ልኮታልና።"(1ኛ ዮሐ 4:9) ይለናል፡፡

ኢየሱስ ዓለም ሳይፈጠር በእግዚአብሐር ዘንድ በከዊነ ቃልነቱ እንደነበረ እራሱ ተናግሯል፡፡
"" አሁንም፥ አባት ሆይ፥ #ዓለም #ሳይፈጠር በአንተ ዘንድ #በነበረኝ ክብር አንተ በራስህ ዘንድ አክብረኝ።"(ዮሐን17:5)

ኢየሱስ <<ሰውን ለማዳን ለሰው ስል ደካማ ሥጋን ተዋሕዶ ስራብ ስጠማ ብታዩኝ ፍጡር አትበሉኝ ዓለም ሳይፈጠር በክብር ነበርኩ >>እያለ ነው፡፡

""አባት ሆይ፥ ዓለም ሳይፈጠር ስለ ወደድኸኝ የሰጠኸኝን ክብሬን እንዲያዩ እኔ ባለሁበት የሰጠኸኝ እነርሱ ደግሞ ከእኔ ጋር ይሆኑ ዘንድ እወዳለሁ።"(ዮሐ 17:24)

,
#ወዳጆቼ እናስተውል!!
በአብ ዘንድ የነበረው ኢየሱስ እርሱ ጌታና የባሕሪ አምላክ ነው፡፡
""መቼም ቢሆን እግዚአብሔርን ያየው አንድ ስንኳ የለም፤ በአባቱ #እቅፍ #ያለ አንድ #ልጁ(ኢየሱስ) እርሱ ተረከው።"(ዮሐ1:18)
በአብ ዘንድ የነበረው የአብ ልጅ ክርስቶስ እርሱ ሁሉን ነገረን፡፡

እስኪ ይሄን የጠቢቡ ሰሎሞንን ጥያቄ አብረን እንመልስለት??

""ወደ ሰማይ የወጣ የወረደስ ማን ነው? #ነፋስንስ በእጁ #የጨበጠ ማን ነው? ውኃንስ በልብሱ የቋጠረ ማን ነው? የምድርን ዳርቻ ሁሉ ያጸና ማን ነው? ይህን ታውቅ እንደ ሆንህ፥ #ስሙ #ማን #የልጁስ #ስም #ማን ነው? ""(ምሳ 30:4)፡፡በማለት ይጠይቀናል፡፡

ጠቢቡ ለጠየቀው ጥያቄ ግን እራሱ ቃል ኢየሱስ መለሰ እንድህም አለ
" ከሰማይም ከወረደ በቀር ወደ ሰማይ የወጣ ማንም የለም፥ እርሱም በሰማይ የሚኖረው የሰው ልጅ(ኢየሱስ) ነው።"(ዮሐ 3:13)
:
በብሉይ ኪዳን እንድህ ጠቢቡን ያስደነቀው በእግዚአብሔር ዘንድ የነበረው ቃል ሥጋ ሆኖ ተገልጦ ተአምር ሲሰራ የአዩት ሕዝቦች ደግሞ በሐድስ ኪዳን እንድህ አሉት
" እጅግም ፈሩና። ነፋስም ባሕርም የሚታዘዙለት ይህ ማን ነው? ተባባሉ።"(ማር4:41)ይላል
:
" ከማኅፀን የሠራህ፥ የሚቤዥህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል ። #ሁሉን #የፈጠርሁ፥ ሰማያትን #ለብቻዬ የዘረጋሁ ምድርንም ያጸናሁ እግዚአብሔር እኔ ነኝ፤ ከእኔ ጋር ማን ነበረ??"(ኢሳ44:24)
በማለት ብቻውን ፈጣሪ እንደሆነ ይናገራል፡፡ይህም ከአንድ አምላክ ውጭ ማንም አለመኖሩን ያሳያል ፡፡እርሱ ወልድ ከአብ ና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር አንድ ነውና፡፡
""#እኔና #አብ #አንድ ነን።"(ዮሐ 10:30) እንድል፡፡

እርሱ ከአብ ጋር የነበረ ወደ እዚህም የመጣ አምላክ ነው፡፡
""ከአብ ወጥቼ ወደ ዓለም መጥቻለሁ፤ ደግሞ ዓለምን እተወዋለሁ ወደ አብም እሄዳለሁ።"(የዮሐ 16:28)
:
በሌላ ቦታ
""የሰጠኸኝን ቃል ሰጥቻቸዋለሁና፤ እነርሱም ተቀበሉት፥ ከአንተም ዘንድ #እንደ #ወጣሁ #በእውነት #አወቁ#አንተም እንደ ላክኸኝ አመኑ።"(ዮሐ 17:8) ይላል፡፡
ስለዚህም እምናመልከው ከአብ ዘንድ የነበረውን ነው፡፡
"#ከአብ #ዘንድ የነበረውንም ለእኛም የተገለጠውን የዘላለምን ሕይወት እናወራላችኋለን፤"(1ኛ ዮሐ 1:2)እንድል፡፡

የምንሰብከው የእምነት ቃል በእግዚአብሔር ዘንድ የነበረው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው
"እግዚአብሔርስ አባታችሁ ከሆነ በወደዳችሁኝ ነበር፤ #እኔ #ከእግዚአብሔር #ወጥቼ #መጥቻለሁና፤ ።"(ዮሐንስ 8:42)
እንድል ከእርሱ ዘንድ የነበረውን ወደ ዓለም የመጣውን ተመልሶም ያረገውን ኢየሱስን በእውነት እንድናመልከውና እንድንገዛው ስለፈቀደልን ስሙ የተመሰገነ ይሁን፡፡

ይቀጥላል••••••••

በአይዋሽም መስቀሉ (ገብረ ክርስቶስ ካሳ)
#ይህን #ያውቁ #ኗሯል??
#ክፍል #አንድ
👉1/የኢትዮጵያ የመጀመሪያው ጳጳስ አቡነ ሰላማ (ፍሬምናጦስ)330 ዓ/ም
👉2/የኢትዮጵያ የመጀመሪያ ዜማ ውርድ ይባለል
👉3/ከመጽሐፍ ቅዱስ መጀመሪያ የተጻፈው መጽሐፈ ሄኖክ ነው
👉4/በዓለም ለመጀሪያ ጊዜ አምና ክርስቲያን የሆነች ቅድስት ድንግል ማርያም
👉5/ለመጀመሪያ ጊዜ ክርስትና ወደ ኢትዮጵያ የገባው 34 ዓ/ም በጃንደረባው ባኮስ
👉6/የመጀመሪያው የኢትዮጵያ ገዳም ደብረ ዳሞ
👉7/የኢትዮጵያ የመጀመሪያው መንፈሳዊ ዩኒበርስቲ ሐይቅ አቡነ ኢየሱስ ሞዐ ገዳም
👉8/የኢትዮጵያ የመጀመሪያው ፓትርያርክ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ባስልዮስ ሰኔ 21 ቀን 1951 ዓ/ም
👉9/በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የዜማ አባት ቅዱስ ያሬድ 505 ዓ/ም ተወለደ፡፡
👉10/ ለመጀመሪያ ጊዜ የኢትዮጵያን ኦ/ተ ቤተ ክርስቲየያንን ለሁለት የመሩ ፓትርያርኮች
አቡነ መርቆሪዎስና አቡነ ማቲዎስ ናቸው፡፡
#ሳምንታዊ_የዓርብ_ምሽት የጥያቄና መልስ ውድድር ዛሬ ማታ ከምሽቱ 3:00 ላይ #ሶስተኛ_ዙር የጥያቄና መልስ ውድድር ይቀጥላል። ከምሽቱ ሶስት ሰአት ላይ ይለጠፋል። ወንድሞች እህቶች ይሳተፋ ዘንድ ጋብዟቸው።
ጥያቄው ከመለቀቁ በፊት በሁለቱ ዙር የነበረውን የሁለት ሳምንት ውጤታችሁን አሳውቃለሁ።
☑️ ሕግና ደንቡን ለማስታወስ ያክል
👇👇👇👇👇
#የውድድሩ_ሕግና_ደንብ

1⃣ የጥያቄና መልስ ግሩፑ ላይ ቀጥታ መጻፍ ወይም መመለስ አይቻልም።

2⃣ መልስ መመለስ የሚቻለው በውስጥ መስመር ብቻ ነው። ይህም ከጥያቄው ስር ላይ #መልስ የምትለውን በመንካት ብቻ ነው የሚላከው።

3⃣ መልሰወን አንድ ጊዜ መላክ ይችላሉ። ከአንድ ጊዜ በላይ መላክ አይችሉም ነገር ግን የላኩትን መልስ ማስተካከለ ወይም ኢድት ማድረግ ይችላሉ #ግን መረሳት የለሌበት አንድ ጊዜ ይሁን ከአንድ በላይ ኢድት ቢያደርጉም #3_ነጥብ ያስቀንሳል
👆👆👆ነገር ግን እዚህ ላይ መረሳት የሌለበት ነገር መልሰዎን እንደላኩልኝ የተሳሱትን ጥያቄ #አንድ_ጊዜ_ብቻ የተሳሳቱትን ጥያቄ በውስጥ መስመር እናገራለሁ። ለምሳሌ ጥያቄ ቁጥር 1 እና 5 ቢሳሳቱ በአጭሩ ተ.ቁ 1 እና 5 ተሳስተዎል ያስተካክሉ ብየ እጽፍለዋታለሁ።

4⃣ መልስ መመለስ የሚቻለው እስከ ምሽቱ #አምስት_ሰዓት ብቻ ነው። ከዚህ በተጨማሪ መልስ እስከ ቅዳሜ ማታ እስከ ምሽቱ 12:00 መመለስ ይቻላል ነገር ግን ከአርብ ከምሽቱ #አምስት_ሰዓት በኃላ የመለሰ #4_ነጥብ ያስቀንሳል። ምክንያቱም በማግስቱ ቅዳሜ ላይ ጥያቄዎቹን በመጠየቅም መጽሐፍትን በማገላበጥ ሙሉ በሙሉ ሊመለሱ ይችላሉና።

5⃣ የጥያቄና መልስ ከፍተኛ ነጥብ ያስመዘገቡና የመለሱት መልስ በማግስቱ ወይም ቅዳሜ ማታ ላይ #የጥያቄና_መልስ_ግሩፑ ላይ መልሳቸው ፎርዎርድ ይደረጋል ነጥባቸውም ይገለጻል። የጥያቄዎቹም መልስ ግሩፑ ላይ #ይለጠፋል

6⃣ ጥያቄዎቹን ሙሉ ለሙሉ ወይም የሚያውቁትን ብቻ መመለስ ይቻላል ነገር ግን በተቻለ መጠን የጥያቄውን ትዕዛዝ መጠበቅ አለብን።

❇️ #ማስታወሻ ውድድሩ በሳምንት አርብ ማታ ላይ የሚደረግ ሲሆን #ለአራት_ሳምንት ወይም #ለአንድ_ወር ይደረግና በጠቅላላ ድምር #ከፈተኛ_ነጥብ ያስመዘገብ አንድ #ወንድ እና አንድ #ሴት #የመንፈሳዊ_መጽሐፍ ተሸላሚ ይሆናሉ ፤ በቀጣይ ደግሞ እንደ አድስ እየጀመረ ይቀጥላል።

#ዓላማው_መሸለም ሳይሆን በጥያቄና መልስ መማማር ነው።
🔜 #መልካም_ውድድር_ተወዳጆች