ዝክረ ተማሪ
821 subscribers
31 photos
10 videos
17 links
ይህ ዝክረ ተማሪ የተሠኘው ቻናላችን ነው። በዚህም ቻናል ስለ ጥንታዊ ቆሎ ተማሪዎች እናወሣለን ። ይከታተሉ ።
Download Telegram
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ተማሪው በቅኔ ትምህርት ቤት

አንድ ተማሪ በንባብና በዜማ ትምህርት ቤት ሳለ የመጻሕፍትን ምሥጢርና ትርጓሜ አይቶ እንዳይረዳ ከልክሎት ይኖር የነበረውን የድንቁርና መጋረጃ ቀዳዶ ለመጣል ከብዙ ጊዜ ጀምሮ ያስብ ስለ ነበር ሐሳቡ ሁሉ ተፈጽሞለት ወደ ቅኔ ትምህርት ቤት በመግባቱ እጅግ ደስ ይለዋል።
(ከጥንታዊ የቆሎ ተማሪ የተወሰደ)

https://t.me/zkretemari
https://t.me/zkretemari
🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
እናትና አባት ወደ ትምህርት ቤት በሄደው ልጃቸው ያላቸው
ታላቅ ተሥፋ ።
🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
ወላጆች ልጃቸው ወደ ትምሕርት ቤት መሄዱን በእርግጥ ከተረዱ በኋላ ለዕድሜው እንጂ ለልብሱ እና ለጉርሱ አያስቡም እንዲሁም ልጃችን ትምህርቱን ጨርሶ በተመለሠ ጊዜ የእገሌን ልጅ በሕግ አጋብተን ያለንን ሀብት ሁሉ ለእርሱ አውርሠን ፤ብንታመመም ያስታምመናል ፣ ብንሞት ዳዊት ደግሞ ይቀብረናል እያሉ መሠረት ያለው ተሥፋቸውን ጠዋትና ማታ እርስ በእርሳቸው ምክንያቱም "ተስፋ ያላዩትን እዲያዩት ፣ያልያዙትን እንደያዙት " ሥለምታደርግ ነው።
ከዚህም ሌላ ልጃቸው ከ ትምሕርት ከተመለሰ በኋላ እንደ ሽልማት ሆኖ የሚሠጠው ነጫጭ ጥጥተገዝቶ ( ኩታና ሱሪ ) መፈተል ይጀመራል ።
ላሊበላ ቤተ ማርያም ውስጥ በ12ተኛው መቶ ክፍለ ዘመን የተሳለ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከልጇ ከመድሀኔአለም ጋር ስዕለ አድኅኖ።

https://t.me/zkretemari

እንኳን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ልደት አደረሳችሁ።
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#የቆሎ_ተማሪ
........................
ግዕዙን ለማወቅ     ቅኔ ማህሌቱን
ታሪክ ወግ ባህሉን  ሊያስቀጥል ያባቱን
ቁምጣውን አጥልቆ  ኩታውን   ደርቦ
ደግሞም ይለምናል እንዲሠጠው ዳቦ
.....................
   ስለ እመብርሃን   ስለ አዛኝቷ
ይኅው መጥቻለሁ አለው ከዛች ቦታ
እማዬ  እናቴ  እንዳስለመድሽኝ
ቁራሺቷን ዳቦ በጠላ ስጪኝ
............................
  እያለ ቢለምን ከበራፍ ላይ ሁኖ
አያፍርም ነበረ በእርሷ ተማፅኖ
ጠላውን በጣሳ ቂጣውን በሰፌድ
ተብሎ ይሠጣል ቢሆንህ ለመንገድ
...................................
ሲሄድ ሲገሰግስ ሲሄድ በየዋርካው
ደግሞም ይለምናል ቢሆን ለማደሪያው
.............
የቆሎ ተማሪው ተርቦ ቢጠይቅ
የቆሎ ተማሪው ተጠምቶ ሲጠይቅ
ተስፋው ቅኔ ሁኖ አያቅም ዘር ብሔር
ይጣደፋል እንጂ ሠጪውን ለማክበር።

https://t.me/zkretemari
ተቀላቀሉ☝️☝️☝️
https://t.me/zkre_temri_group
ዝክረ ተማሪ pinned «በየሳምንቱ አንድ ጀግና ወይም ጀግኒት የአብነት ሊቃውንትን እንዘክራለን🤗🤗🤗። የዚህም ሳምንት ሊቋ የዜማና የቅዳሴ መምህር የሆኑት መምህርት ሶስና በላይ ናቸው።»
ከእለታት በአንድ ቀን ሊቃውንቱ እና መኳንቱ በተሰበሰቡበት ለመሆኑ እኔ ብሸጥ ስንት አወጣለሁ ሲሉ ዳግማዊ አፄ ሚኒልክ ጥያቄ አቀረቡ :- ይሄ ያልተጠበቀ ጥያቄ ስብስቡን ሁሉ ግራ አጋባው እምዬን የሚያክል የዋህ ደግ የተከበሩ ንጉስ በስንት ሊገመቱ እንደሚችሉ የሚናገር ጠፋ ከመሀል በዚህ ጊዜ አንድ የቆሎ ተማሪ ለመናገር አቆብቁቦ ብድግ አለ እምዬ ምኒልክም በል ተናገር አሉት ያ ቆሎ ተማሪም እምዬ እርሶ ቢሸጡ ሃያ ዘጠኝ ብር ያወጣሉ ብሎ መለሰ እምዬ ምኒሊክ በመልሱ ተገርመው ቆጣ ብለው 😣 እንዴት እኔን በ ሃያ ዘጠኝ ብር ገመትከኝ ሲሉ ጠየቁት?🤔 የቆሎ ተማሪውም እየሱስ ክርስቶስ የተሸጠው በሰላሳ ብር ነውና እርሶ ምንም እንኳን ደግ ንጉስ ቢሆኑም ከጌታችን አይበልጡም ብዬ ነው በሃያ ዘጠኝ፥ ብር የገመትኮት አለ በተማሪው መልስ ንጉሱን ጨምሮ ሁሉም ተገርመው ሳቁ 😜

https://t.me/zkretemari
ተቀላቀሉ☝️☝️☝️
https://t.me/zkre_temri_group
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ደብረ አባይ አባ ሳሙኤል ገዳም ።
--የደብረ አባይ ቅዳሴ ማስመስከሪያ ጉባኤ።

የጥንታዊ የትምህርት ሂደታችን እንዴት ልዩ ነበር።

@zkretemari
ተቀላቀሉ☝️☝️☝️

https://t.me/zkre_temri_group
ያ የቆሎ ተማሪ ምንኛ ታድሏል
የልደትዬን በር ሲሳለመው ይውላል
ዳዊትን ከመፃሐፉ ቅኔን ካባቶቹ ሲማረው ከርሞታል
መችስ በቃውና ጊዜና ሰዓቱ
ሁሌ ሲገኝ ኖሯል በድንግል ማህሌቱ
ያ ብልጡ ተማሪ ቅኔው የገባው እለት
አማልጂኝ ይላታል ሁሌ እለት እለት
ቆሎ ሊያዘግኑት ቀለብ ቢሉ አባ
ዘግነው ስጡኝ አለ ሆዱ እንደባባ
በእኔ እጅ ባነሳ ትንሽ ነው አባቴ
እርሶ ዘግነው ይስጡኝ እንደው በእመቤቴ
እያለ ጠየቀ አማላጅነትን ሊገልፅ በሞከረ
ቅኔው ላልገባቸው እንዲሁ መከረ
በማህፀን ሆና ጥላዋ ይፈውስ ነበረ
ኤፍሬምም ደረሰ ጥቂቷንም ነገር ሊገልጽ በሞከረ
እግዜርም አየና የአዳም መዳኛ እንድቶን አረገ
ሰይጣን ይህን አይቶ እንዲው በረገገ
ውልደቷን አየነው
አዳምም ደስ አለው
የመዳኛው ቀንም ሲደርስ ስላወቀ
የሲዖልም ኑሮ እንዲሁ አለቀ
ተንስዑ ለፀሎት ሊልም ተዘጋጀ
ምስለ መንፈስከ እንዲሉ ህዝቡን አዘጋጀ
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ጓንቻ ኳኩርታ  የቀበሌ ዶንቺ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን የምትገኘው የዜማ እና የቅዳሴ መምህርት ሶስና
የጥንት ተማሪ ቁርሱ ጸሎት ያውም በቁመት
የዛሬ ተማሪ ቁርሱ ብስኩት ያውም በወተት

የጥንት ተማሪ ወጡ የተልባ ማጣፈጫ አልባ
የዛሬ ተማሪ ወጡ ቀይና ነጭ ያውም በግላጭ

የጥንት ተማሪ የሚበላው ቆሎ ያውም ጦሙን ውሎ
የዛሬ ተማሪ የሚበላው ስጋ እንደባለፀጋ
አኩፋዳ ምን ማለት ነው ትርጓሜውስ ?
እጅግ የሚያስለቅስ የቆሎ ተማሪው ታሪክ
በሊቀ ለቃውንት እዝራ
Join 👉 https://t.me/zkretemari
ልመናን የጀመረው የቆሎ ተማሪ ነዉን ?
""""እነዚህ እኮ እነዚህ ናቸው"""""

ዛሬ ውሻ የሚያባርራቸው
ቁራሽ እንጀራ የምትሰጣቸው
ዛሬ "ተሜ"የምትላቸው
ነገ"አባቴ"የምትላቸው
እነዚህ እኮ እነዚህ ናቸው

አየሀቸው???

በጠባብ ጎጆ...ተቻችሎ መኖርን ያስተማሩ
ዝቅ ብለው ከፍ ያሉ..ለውሻ ጩኸት ያልተበገሩ
ለእውቀት ሩቅ ሂደው...አርቆ ማሰብን የተማሩ
"ቆሎ ተማሪ ብለህ"...ቁራሽ የምትነሳቸው
ሗላ ላይ..."ይፍቱኝ አባቴ" የምትላቸው
እነዚህ እኮ....አነዚህ ናቸው!!
አየሀቸው!!?

ዘመኑን የቀመሩልህ
ስጋውን የቆረሱልህ
ደሙን ያዘጋጁልህ
ምድርን አስጨርሰው ሰማይን የሚያሳዩህ

ከዲያቆኑ
እስከ ካህኑ

ከቆሞሱ
እስከ ጳጳሱ

የበቁ ለክህነቱ...አባቶቼ የምትላቸው
በምስጢር ሲራቀቁ...መምህሮቼ የምትላቸው
እነዚህ እኮ....እነዚህ ናቸው
አየሀቸው???

በል ክብር ስጣቸው
የት አላችሁ በላቸው

አመንኮሱ አጰጵሶ....አባቴ ለማለቱ
ዛሬ ላይ ነው በጎጆ...ተሜ ላይ ነው መሠረቱ!!!

ትኩረት ለአብነት ትምህርት ቤቶች!!!!
Live stream started
Live stream finished (39 minutes)
ምዕራፍ ፩

በአብነት ትምህርት ቤት የሚሰጡት ትምህርቶች እንደየ ተማሪዉ የእድሜ መጠን እና እውቀት ደረጃቸው በምዕራፍ ተከፋፍለው የሚሰጡ ሲሆኑ በዘመናዊው ስርዓተ ትምህርት 1ደረጃ , 2 ደረጃ , መሰናዶ ..እየተባለ ከተዋቀረው ስርዓት ጋር ሊነፃፀር ይችላል ። ይህም ሲባል አንድ የአብነት ትምህርት የጀመረ ተማሪ ወደቀጣዩ ምዕራፍ ለመሸጋገር ይችላል ዘንድ ትምህርቱን በአግባቡ ተከታትሎ በቂ እውቀት ሊገበይ ግድ ይላል ።
በአብነት ትምህርት ቤት ውስጥ የሚሰጡ የትምህርት ዓይነቶች