Abdul Aziz Nur
5.93K subscribers
1.16K photos
246 videos
50 files
1.76K links
في النهاية كلنا سنكون ذكرى

በመጨረሻም ሁላችንም ትዝታ እንሆናለን !
Download Telegram
💪ሰኡዲያ ከጠላቶቻ በላይ ናት !!

💥 እሷን ለማጥፋት የሚንቀሳቀሱ ሁሉ አላህ ያዋርዳቸው ለኢስላምና ለሙስሊሙ ትልቅ ባለ ውለታ ናት ጠላቶቻ ይህን ማንሳት ባይፈልጉም !! አህለሱናን የሱና ሰዋችን ያስጠለለች ያከበረች ልዩ ሀገር !! አላህ ይጠብቃት መሪዋቻቸውኑም አላህ ይጠብቃቸው አላህ ከዚ በላይ ሱናን ጠባቂ ያርጋት ሀገሪቷንም ከዚ በላይ ሸሪኣን ጠባቂ ያርጋት በአለም እንደ ሱዑዲ ኢስላምን ሚያንፀባርቅ ሀገር አታገኝም ሆኖም ኢሄን ለማዳፈን የሚለፉ ብዙ ናቸው አላህ አያሳካላቸው አሚን።
📝......zizu nur
https://t.me/joinchat/AAAAAEPo5jHkW5Ui9vf2CQ
🌐 ሼር ማድረግም እንዳይረሱ
ዘካ የሚሰጠው ለምን አይነት ሰው ነው?
~~~~~~~~~~~~~~~
የዘካ ባለሐቆች 8 ናቸው። በቁርኣን እንዲህ ተዘርዝረዋል:–

(إِنَّمَا الصَّدَقَاتُ لِلْفُقَرَاءِ وَالْمَسَاكِينِ وَالْعَامِلِينَ عَلَيْهَا وَالْمُؤَلَّفَةِ قُلُوبُهُمْ وَفِي الرِّقَابِ وَالْغَارِمِينَ وَفِي سَبِيلِ اللَّهِ وَابْنِ السَّبِيلِ ۖ فَرِيضَةً مِنَ اللَّهِ ۗ وَاللَّهُ عَلِيمٌ حَكِيمٌ)

"ግዴታ ምጽዋቶች (የሚከፈሉት) ለድሆች፣ ለምስኪኖችም፣ በርሷም ላይ ለሚሰሩ ሰራተኞች፣ ልቦቻቸውም (በእስልምና) ለሚለማመዱት፣ ጫንቃዎችንም (በባርነት ተገዢዎችን) ነፃ በማውጣት፣ በባለ እዳዎችም፣ በአላህ መንገድም በሚሰሩ፣ በመንገደኛም ብቻ ነው፡፡ ከአላህ የተደነገገች ግዴታ ናት፡፡ አላህም አዋቂ ጥበበኛ ነው፡፡" [አትተውባ: 60]

መጠነኛ ማብራሪያ

① ድሃ ማለት:– ለመኖር (ልብሱ፣ ጉርሱ፣ ትዳር ለመመስረት፣ ለመማር፣) ምንም ነገር የሌለው ወይም ትንሽ ነገር ያለው ማለት ነው። እነዚህን ፍላጎቶች ለማሟላት ዘካ ሊሰጠው ይችላል።

② ምስኪን ማለት: – ለመኖር የሚሆን ነገር በተወሰነ መጠን ያለው ሲሆን የሚበቃው ግን አይደለም።

③ ዘካ ላይ የሚሰራ ሰራተኞች:– ዘካ እንዲሰበስቡ በመሪ የሚላኩ ሰዎች ናቸው። ዘካ ሶስት ነገሮችን ይፈልጋል። መሰብሰብ፣ መጠበቅና ማከፋፈል። በሶስቱም ዘርፍ ላይ የሚሰማሩ ሰራተኞች ሃብታም ቢሆኑም ዘካ ይሰጣቸዋል።
ልብ በሉ! ለዚሁ ስራ በመንግስት የሚሾሙትን እንጂ የግለሰቦች ወኪሎችን አይመለከትም። ደሞዝተኛ ሰራተኛም እዚህ ውስጥ አይገባም።

④ ልቦቻቸው (በእስልምና) የሚለማመዱ ማለት ሁለት አይነት ናቸው።

አንደኛ/ ካፊር (ሙስሊም ባይሆንም ለተሻጋሪ ፋይዳ ሲባል ነው ሊሰጠው የተፈቀደው): –
– ቢሰጠው ይሰልማል ወይም ሌላ ፋይዳ ይገኝበታል ተብሎ ተስፋ የሚጣልበት ከሆነ፣
– የሚያደርሰው ጉዳት ኖሮ በዚህ ማስቆም የሚቻል ከሆነ

ሁለተኛ/ ሙስሊም:–
– በዲኑ እንዲጠነክር ወይም ለሌላ ሰው መስለም/ መጠንከር ሰበብ ይሆናል ተብሎ ከተገመተ
– በሙስሊሞች ላይ ጉዳት የሚያደርስ ሆኖ በዚህ ማስቆም የሚቻል ከሆነ። [መጅሙዑል ፈታዋ፣ ኢብኑ ተይሚያ: 28/290]

⑤ እራሳቸውን ከአሳዳሪዎቻቸው በመግዛት ነፃ ለማውጣት የሚጣጣሩ ባሪያዎች ዘካ ከሚገባቸው ናቸው።

የተጠለፉ/ የተማረኩ ሙስሊሞችን ማስለቀቅም ከዚሁ ውስጥ ይካተታል።

⑥ ባለ እዳ:– የተጣሉ ሰዎችን ለማስታረቅ አልሞ እዳ የገባ ሰው ሃብታም እንኳን ቢሆን ዘካ ሊሰጠው ይችላል።
በራሱ ጉዳይ እዳ የተጫነው ከሆነ በኑሮው ባይቸገር እንኳ እዳውን ለመክፈል ሊሰጠው ይችላል።

⑦ በአላህ መንገድ የሚሰራ ማለት:– ለጂሃድ ዘማች ማለት ነው። ለትጥቅ፣ ለስንቅና አጠቃላይ ዝግጅት ዘካ ይሰጣል።

⑧ መንገደኛ:– አገሩ መግቢያ ከዘካ ገንዘብ ይሰጠዋል።
≈≈≈≈≈≈≈
https://t.me/joinchat/AAAAAEPo5jHkW5Ui9vf2CQ
🌐 ሼር ማድረግም እንዳይረሱ

🌹 ባረከላሁ ፊክ
💠 ክፍል አንድ ሼኽ ኢልያስ ስለ ሙብተዲኦች ምን አለ ?

🎙ሼኽ ኢልያስ አህመድ (ሀፊዘሁላህ) ስለ ሙብተዲእ ሰው ስም ማንሳት ሲያወራ እንዲህ ይላል:–

“ ነብዩ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ለአንዲት ሴት የትዳር መስተካከል ብለው የሰሃባዋችን ስም አንስተው ከተናገሩ ዲንን እምነትን ለማስተካከል የአንድን ሰው ስም ለዛውም የሙብተዲእ ሰው ስም ማንሳት የተከለከከ ነው ይባላል ? በፍፁም !! ይህ እንደውም በጣም የተገባ እና የበለጠ ነው።

በዚ ርእስ ላይ ኡለማዋች ያለ አንዳንች ኺላፍ ያስቀመጡት ነገር ነው።...ይህን ልናቅ ይገባል ። ”

🔘 ሙሉ ድምፁን በቴሌግራም ማግኘት ይችላሉ ሰፋ ባለ መልኩ የሙብተዲእን ስም ማንሳት አንደሚፈቀድ እንደውም ግዴታ ሚሆንበት ግዜም አለ ይለናል። ሃሜት ነው ለሚሉ ሰፋ ያለ መልስ አለው ያድምጡት ይጠቀማሉ።
📝......zizu nur
#በቴሌግራም #ለመከታተል👇

https://t.me/joinchat/AAAAAEPo5jHkW5Ui9vf2CQ
🌐 ሼር ማድረግም እንዳይረሱ

🌹 ባረከላሁ ፊክ
2019_05_25_091814.aac
5.8 MB
💠 ክፍል 1⃣ (አንድ)

🎙ሼኽ ኢልያስ አህመድ (ሀፊዘሁላህ)

🔶 ርዕስ: – የሙብተዲእን ሰው ስም ማንሳት
https://t.me/joinchat/AAAAAEPo5jHkW5Ui9vf2CQ
🌐 ሼር ማድረግም እንዳይረሱ
🛑 ከፍረጃ እንጠንቀቅ

አንደ ሰው መቼ ነው እንደ ከሃዲ ወይም ሙብተዲእ አልያም ደግሞ አመፀኛ የሚቆጠረው የሚለውን ጠንቅቆ አለማወቅ ብዙዋችን እጅግ አደገኛ ለሆነ ጥፋት ሲያጋልጥ ይታያል ። አንድ በዳዕዋ ዘርፍ ላይ የተሰማራ ሰው በዚ ረገድ የሚያስፈልገውን መርህና ጥንቃቄ ካልለየ ጥፋቱ ከራሱም አልፎ ወደሌሎች ይሻገራል። ያለ አግባብ እየወነጀለ ክብራቸውን ከሚያጎድፋቸው ሰዋች በተጨማሪ ጥፋቱ ብዙዋችን ውዥንብር ላይ ይጥላል። ሰዋችን ያሳስታል ፣ ለዳዕዋም መሰናክል ይሆናል።
...................................................................................................................................
በዚህ ጉዳይ ላይ የሚያስፈልጉ መርሆዋችን ለይቶ አለማወቅ በርካታ ፅንፍ የረገጡ አንጃዋችን እንዲፈለፈሉ ሰበብ ሆኗል። በየጓዳው እየተፈለፈሉ ሙስሊሙን በጅምላ የሚያከፍሩ ወይም ያለ ጥንቃቄ ቅድመ– ሁኔታ ሰዋችን ከሱንና የሚያስወጡ ሰዋች ተራውን ህዝብ ቀርቶ ታላላቅ የሱንና ዑለማዋችንም ጭምር ክብራቸውን መቦጨቅ አለፍ ሲልም በቢድዐና በኩፍር መፈረጅ እንደ ቁድስ ምግባር እየቆጠሩ ነው። ለእንዲህ አይነት የጥፋት ተጣሪዋች ሰለባ ከመሆናችን በፊት በዚህ ረገድ የሚያስፈልጉ መሰረታዊ ነጥቦችን ልንለይ ይገባናል።

[አልበያን:– ገፅ /182]
( ኢብኑ ሙነወር)
📝......zizu nur
#በቴሌግራም #ለመከታተል👇

https://t.me/joinchat/AAAAAEPo5jHkW5Ui9vf2CQ
🌐 ሼር ማድረግም እንዳይረሱ

🌹 ባረከላሁ ፊክ
🌻 የዒድ መልዕክት አለዎት?

🌸 ውድ የነሲሓ ቲቪ ተከታታዮች፤
በነሲሓ ቲቪ ለኢድ አል–ፊጥር የእንኳን አደረሳችሁ እና የመልካም ምኞት መግለጫ ለማስተላለፍ በሚከተለው ቁጥር በዋትሳፕ ወይም በቴሌግራም ከ 1 ደቂቃ ያልበለጠ የድምፅ ወይም የቪድዮ መልእክት መላክ ትችላላችሁ።

ሴቶች የፅሁፍ መልዕክት ላኩልን፤ ከስክሪኑ በታች በኩል በሚገኘው የ sms መደብ ላይ መልዕክታችሁን ለነሲሓ ታዳሚዎች እናደርሳለን

📲+966556044767

🗓 መልዕክት የምንቀበለው እስከ እለተ ጁምዓ ግንቦት 23/2011 ብቻ ይሆናል
#በቴሌግራም #ለመከታተል👇

https://t.me/joinchat/AAAAAEPo5jHkW5Ui9vf2CQ
🌐 ሼር ማድረግም እንዳይረሱ

🌹 ባረከላሁ ፊክ
ﺑﺴﻢ ﺍﻟﻠﻪ ﺍﻟﺮﺣﻤﺎﻥ ﺍﻟﺮﺣﻴﻢ

📛 አላህን ማመፅ ለምን አስፈለገ መልእክት ከጅማ ዩንቨርስቲ !!

🔰 የዐለማት ጌታ ለሆነው አላሕ ሱብሀነሁ ወተዓላ ምስጋና ይገባው፤ የአላሕ ሶላትና
ሰላም በመልዕክተኛው ሰለሏሁ ዐለይሒ ወሠለም በቤተሰቦቹና በባልደረቦቹ
እንዲሁም
የባልደረቦቹን መንገድ በተከተለ ሁሉ ይስፈን።

🌈 አላህን ማመፅ ለምን አስፈለገ አላህን ለማመፅ ነው ብሎ ሁሉም ስራውን ባይጀምርም ስራው አላህን ማመፅ ከሆነ ከስራው ሊቆጠብ ይገባ ነበር ሰዋችን ወደ ዲን ለመጥራት ዲን በሚከለክለው ነገር ላይ ሆነን መጥራት ለምን አስፈለገ እናም ልብ በሉ ከምትሰሩት ሸፍጥ ተንኮል ዲንን ማውደም ጀምኣን መበታተን ተቆጠቡ !!

💥ወላሂ ወቢላሂ ስለ ምንም ነገር ከነብዩ(ሰ ዐ ወ) የበለጠ አታቁም ከነሱም በላይ ጥበበኛ አይደላችሁም።
ይድረስ [ለዘብተኛ] እስልምና አራማጅ ነን ለምትሉት EMSL (የኢትዮጽያ ሙስሊም ተማሪዎች ሊግ)

💢 እናንተ የነብዩን (ሰ ዐ ወ) የደእዋ አካሄድ ኋላ ቀርና ሒክማ እንደ ጎደለው ምትነግሩን??በዚህ ንግግራችሁ ብቻ እስከ ኩፍር ደረጃ ልትደርሱ ትችላላችሁ።እናንተ ከየት ያመጣችሁት ፍልስፍና ነው ኪታብና ቁርዓን ከማስቀራት ይልቅ ኢስላምን በፊልም በድራማ በቀረርቶና በኮርስ ብናስተምር ውጤታማ እንሆናለን ብላችሁ ምትሰብኩት??በየትኛው ሒክማችሁ ነው ሀራም ላይ የወደቁ ሴት እህቶቻችን በቁርዓንና ሀዲስ ከመምከር ይልቅ እነሱ በሚፈልጉት መልኩ[በጅንጀና,በመተቃቀፍ;በመጨባበጥ) ቀርበን እናሳምናቸው ምትሉት?? በምን መረጃ ነው ሴቶቻችን ከካፊሮች ጋር አብረው መሆን ስላበዙ እንደ ካፊሮቹ እንሁንላቸው የምትሉን??[ለዳእዋ] ብለን ልንጨብጣቸው?ልናቅፋቸው?ልንተሻሻቸው?ተዉ አላህን ፍሩት።አላህ እንዲህ ይላል "የሰው ልጅን እኛው የፈጠርነው ነፍሲያውን ምን እንደሚወሰውሰው እናቃለን"ሱረቱ ቃፍ-16።

ሞዴሎቻችን ካፊሮች ናቸውን?በጭራሽ የኛ ሞዴላችን ረሱል(ሰ ዐ ወ) መመሪያችን ቁርዓን ነው።ስራችን ተቃባይነት ይኖረው ዘንድ ሁለት ነገሮች ሙሙላት ግድ ይላቸዋል ኢኽላስና ኢቲባእ።ታድያ እኛ በፈለሰፍነው አካሄድ ነብዩን ሳንከተል ብንሄድ ደእዋችን ገደል ይከተናል።EMSL(የኢትዮጵያ ሙስሊም ተማሪዎች ሊግ) የተባለው ቡድን ከተመሰረተ አመት እንዳልሆነው እናቃለን።ነገር ግን አሁን በተለያየ ዩኒቨርሲቲዎች ከጀማአው እውቅና ውጪ የራሳቸውን ቡድን በማፍራት [ዘመናዊ]ው [ለዘብተኛ]ው እና [አሮጌ]ው [አጥባቂ]ው እስልምና የሚል አይነት ልዩነት ለመፍጠር እየሰሩ ነው ያሉት።

🛑 የዚህ ሊግ አባላት የትኛውም ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ይኖራሉ ተመሳስለውም ገብተው የራሳቸውን አላማ ለማስፈፀም መሞከራቸው አይቀርም።ሚገርመው እነዚህ ሰዎች ወንዶቻቸው ጀመዓ ሰላት ማናያቸው ኪታብ ከመቅራት ኮርስ ይበልጣል የሚሉ ኢኽቲላጥን ማያቁ ሴቶቻቸው ሂጃብን(ሻርፕና ሚኒስከርት እንጂ) ማያቁ ናቸው(እንዳው ብዙዎቹ ከት/ት እንደሚጋጭ ሚያስቡ ናቸው)። የኛ ጀመዓ በሀገሪቱ ኣሉ ከሚባሉት ግንባር ቀደሙ ነው።በጀመዓችን ከቁርዓን ለፍዝ እስከ ተፍሲር ከአጫጭር ኪታቦች(ሪሳላዎች) እስከ ሱነን ይቀራል።አንድነት ሰባኪዎች አንድነታችንን እየበጠበጡ ስለሆነ ልንጠነቀቃቸው ይገባል በተለይ ሁሉም ዩኒቨርሲቲ ጀመዓህ አሚሮች የበለጠ ሀላፍትና አለባችሁ።ታድያ ይህን ጀመዓ ከመደገፍ ይልቅ ለምን መበተን አስፈለገ??ከስር ያያዝኩት ፎቶ ጅማ ሊዘጋጅ ታስቦ የነበረው ፖስተር ነው።ነገር ግን በጀመዓውና በአካባቢው ዱኣቶች ትብብር ተሰርዟል። ከዚህ አይነት የእስልምና ምልክት እንኳን ከማይታይበት ፕሮግራም ምን ይገኛል ብላችሁ ታስባላችሁ??በቀጣይነት ወደ አርባምንጭ የታሰበ ዝግጅት ኣላቸው የአርባ ምንጭ ዩንቨርስቲ አሚሮች ፣ ተማሪዋች ፣ ዳኢዋች እና የአካባቢው ማህበረሰብ ይህን እኩይ ኢስላምን አፍራሽ ተግባር ነቅታቹ ልትከታተሉ ይገባል ።
[አብደላ ኡመር ሀሰን ከጅማ ዩንቨርስቲ]

📝......zizu nur
#በቴሌግራም #ለመከታተል👇

https://t.me/joinchat/AAAAAEPo5jHkW5Ui9vf2CQ
🌐 ሼር ማድረግም እንዳይረሱ

🌹 ባረከላሁ ፊክ
🌹 ፍትሃዊ ሁኑ አላህ ፍትሃዊ ሰዋችን ይወዳል

💠 በሰሃቦች ግዜ የአቂዳ ልዩነት ነበርን በሱም የተነሳ ሰዋች በአቂዳ ተለያይተው አንድ መሆን ይችላሉን ?

⚡️ ኡስታዝ አህመድ አደም በጁምዓ ኹጥባ ላይ ያስተላለፈው መልእክት ከጥላቻ ርቀን ፍትሃዊ ሆነን ከሰማነው ምንም አይነት መርሆን የለቀቀ ንግግር አልተናገረም በመሰረቱ ተሳሳተ ብንል እንኳን ልክ አንድ ሙብተዲእን በምናስተናግድበት ሁኔታ አደለም ማስተናገድ ያለብን አንድ በሱና ምናቀው ከዚ ነገር የተብቃቃ መሆኑን ልናውቅ ይገባናል !! ካለፉ ትምርቶች በአቂዳ ጉዳይ መስማማት እንደማይቻል ቁጥር ስፍር የሌላቸው ሙሃደራዋች አሉት ስለ ሙብተዲኦች የተናገረበት ስለ አህባሽ ሺዓ ኢኽዋን ጭምር አብራርቶ ተናግሮ ሳለ በዛ እሱን መጠርጠር ከእርግጠኝነት በሃላ ቢሆን እንካን አንድ ነገር ነበር !! ግና ያ ባልሆነበት ሁኔታ ለማብጠልጠል መሽቀዳደም ለሱና ያለን ተቀርቃሪነት አናሳ መሆኑን ያሳያል ከትክክለኛው የአህለሱና መንገድ ውጪ ያሉ ሁሉ ከ 72 እንደሚገቡ ተናግራል ስለ ኢክዋን አብራርቶ ከተናገረ በሃላ የኢብን ባዝን ንግግር አጣቅሶ ከ 72 እንደሚመደቡ ያለፉ የሱ ትምርቶች ናቸው። ታዲያ እንዲ በሱና ምታቀውን ባላረጋገጥከው ወሬ እሱን ለማሳጣት መነሳት ለዲን ከመቆርቆር ነው ብዬ አላስብም እንዲያው በተቃራኒ ተሳስቶ ቢሆን እንኳን በጣም ልናዝን ቀርበን ልነመክረው ካለበት ስህተት ልናረመው ነበር ሚገባው ሰለፎች አሳማሪዋች እንጂ አበላሾች አነበሩም።

ወደ ተነሳበት ነገር ስመለስ ሰሃባዋች በአቂዳ ተለያይተዋል በአቂዳ ተለያይቶ አንድ መሆን ይችላል ብሏል በማለት የተነሳ ሀሳብ ነው። በዚ ነገር ላይ የሚነሱ ሃሳቦች ወይ እውነታውን ካለ መረዳት ሲሆን አልያ ደሞ በድፍን አሉባልታ ተመርቶ የሚናፈስ ወሬ ነው ። እውነታው ግን ኡስታዝ አህመድ አደም በኹጥባው ላይ እንደ ገለፀው በሰሃቦች ግዜ የአቂዳ " ሊባል የሚችል " ልዩነት ተከስቶ ነበር በዛ ነገር ላይ ሰሃቦች ተስማምተዋል ብሏል ይህ የአቂዳ " ሊባል የሚችል " ስህተት ሰሃቦች በተጨባጭ የተለያዩበት ነገር ነው ለምሳሌ ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) አላህን አይተዋል አላዩም የሚለው ነጥብ የአቂዳ " ሊባል የሚችል" ልዩነት ነው። ሰሃባዋች በዚ ነገር ላይ ቢለያዩም ተስማምተው ተዋደው ቀጥለዋል ። ከሱ በማስቀጠል በቁርዓን እና በሃዲስ ግልፅ መረጃ የመጣባቸው ሰለፎች ኡለማዋች የተስማሙበት የአቂዳ ርእስ ግን በሱ ላይ ጠንካራ መልእክትን ነው ያስተላለፈው ተምክሮ ማይቀበል ከሆነ አሚር መሪ ካለ ሊገደል ሁሉ ይችላል ብሏል ልብ በሉ ይህን ጠንካራ አገላለፅ በግልፅ በቁርዓን እና በሃዲስ ከመጡ በሰለፎች በኡለሞች ኢጅማእ ውጪ የሆነ ተገስፆ ካልሰማ ሊገደል ሁሉ ይችላል። ይህ አገላለፅ በአቂዳ አንድ መሆን ይቻላል የሚል አመለካከት ቢኖረው ይህን ቃል እስከ መገደል የሚለውን መጠቀም ለምን አስፈለገ በፊቅህ ጉዳይ የተለያየ ነው የሚል ሙግት አይመጣም በአቂዳ ልዩነት አለ ብሏል ብሎ ለሚሞግት ሰው ፊቂህ ፈልጎበት ነው አይልም በግልፀ አቂዳ ልዩነትን ፈልጎበት ነው። አቂዳ " ሊሆን የሚችል " ስህተት ያለው በግልፅ በቁርዓን እና በሃዲስ ያልተገለፁ የሰለፎች ስምምነት የሌለባቸውን ልክ አላህን አይተዋል አላዩም ብለው እንደተለያዩት በዚ ርእስ ሰዋች ቢለያዩ ሰሃባዋች እንደተስማሙት ሊስማሙ ይገባል ነው።

💥 ኡለማዋች በሰሃቦች ግዜ የአቂዳ ልዩነት የለም የሚል ንግግር ሲጠቀሙ ሚን ኡሱሊዲን በዲን መሰረታዊ ነገሮች ቁርዓን እና ሃዲስ በግልፅ የመጣባቸው ሰለፎች የተስማሙበት እሱን ነው የፈለጉበት እንጂ ግልፅ ባልመጡ ሰለፎች ያልተስማሙበት አቂዳ መሰል ነገሮች እንዳሉ ኡለማዋች እራሳቸው ገልፀዋል ለምሳሌ ኢብኑ ኡሰይሚን ገልፀዋል ፈውዛንም ሸርህ አቂደቱል ዋሲጥያ ላይ አላህን በማየት ላይ ሶስት አመለካከቶች እንዳሉ አንስተዋል እነዚ አቂዳ መሰል የተፈጠሩ ልዩነቶች ናቸው ። በሰለፎች ዘንድ ግልፅ በመጡ በቁርዓን እና በሃዲስ ላይ ልዩነት አነበራቸውም ግልፅ ባልመጡ ነገሮች ላይ በአንዳንድ " አቂዳ መሰል " ነገር ላይ ልዩነት ነበር ይህ ሰሃባዋች የተቻቻሉበት እኛም ልንቻቻልበት የሚገባን ነገር ነው። በግልፅ ቁርዓን እና ሃዲስ ላይ የመጡ ሰሃባዋች ኡለማዋች የተስማሙበት ጉዳይ ደሞ ልዩነትን የማያስተናገድ አርእስት ነው ወላሁ አእለም ። ሙሉውን የአህመድ አደም ኹጥባ በቴሌግራም አድራሻዬ ለቂቄዋለው እና እውነታውን እናተው ፍረዱ አላህ አህለሱናዋችን ከመለያየት ይጠብቃቸው ልባቸውን እዝነት የተሞላ ያርግላቸው አሚን !!
📝......zizu nur
#በቴሌግራም #ለመከታተል👇

https://t.me/joinchat/AAAAAEPo5jHkW5Ui9vf2CQ
🌐 ሼር ማድረግም እንዳይረሱ

🌹 ባረከላሁ ፊክ
ኢድ ሙባረክ
ተቀበለላሁ ሚና ወሚንኩም ሷሊሀል አእማል።
تقبل الله منا ومنكم صالح الأعمال
ወንደሞቼ እና እህቶቼ ፣ አላህ መልካም ስራዎቻቸንን ይቀበለን !
🌷የአረብ ሀገር ሴት ግን ታስደምመኛለች !!

🌷አብሶ እሄን ችግር ብትቀርፈው !!

🌻 እራሷ እንደ ሻማ ቀልጣ ለሌሎች ብርሃን የምትሆን ፣ እራሷን ዝቅ አርጋ ቤተሰቦቻን ከፍ የምታደርግ ፣ ባልተደላደለ ህይወት ለሌሎች መደላለደል የምተለፋ ፣ ለራስ መኖር ትርጉሙን ማታቀው ለሌሎች መኖርን የምትኖር ፣ ለምን ተለየች የአረብ ሀገር ሴት !! በሌላ አህጉር የሚኖሩ በአውሮፖ በአሜሪካ በሌሎችም ሀገራት ያሉ እህቶች ስራቸው በአንፃራዊ አረብ ሀገር ካሉት የተሻለ ስራ ነው ፣ እራሳቸውን ስለመለወጥ ብዙውን የሚያስቡት ለቤተሰብ አያስቡም እያልኩ አደለም በደንብ ያስባሉ ግን ከአርብ ሀገር ሴት ጋር ስታነፃፅራቸው ልዩነቱ ይሰፋል ስራቸውም ያልተመቻቸ ዳገት አሳር የበዛበት ነው ፣ ሰርተውም መላክ እንጂ መለወጥን የሚያስቡት ከስንት አንድ ናቸው !! እንዴት እንዴት ሆነው እንደሚያመጡት አላህ ነው የሚያቀው ያም ሆኖ ከብዙ አመታት ቆይታ በሃላ ወደ ሀገር ሲገቡ ብሩ ተኖ አልቋል ባዶ እጃቸውን ነው የሚገቡት ምን ያክል ቅስም ይሰበራል ከዛም ትዳር በመያዣ በማረፊያ ሰዓታቸው መልሰው ወደ መጡበት ሀገር ትንሽ ቂሪት ልሰብስብ ብለው ይመለሳሉ ለዚ ተጠያቂዋች በጥቂቱ እነዚ አካላት ናቸው ብዬ አስባለው

1⃣ ኛው ቤተሰብ ራሱ የሚል እምነት አለኝ ቤተሰብ እዛ ያለውን ችግር እና ስቃይ አይረዳም ብር ሲቸግረው እየጨቀጨቀ ማስላክ በዚ መልኩ በጣም ተጠያቂነት እናት አባት ሳይሆን ወንድሞች ናቸው እንዲ ሆናል እንዲያ ሆናል ብሎ ከአቅም በላይ ብርን ማስላክ ምንም እንዳትለወጥ ያደርጋል አንዳንድ በቃ አረብ ሀገር እህት አለኝ ፈታ ነው የምለው እያሉ የሷን ብር መጫወቻ የሚያደርጉ ብዙ ናቸው። አንዳንድ ለራስሽ አስቢ አብሽር እያለ የሚያበረታታ ቢኖርም አብዛኛው ግን ወዲያ ነው። እና እህቴ ለቤተሰብ አትለግሺ አይባልም በተለይ ለእናት እና ለአባት መርዳት ያስፈልጋል ግን ነገ መጠሽ የነሱ ሸክም ብቶኚ እሱም ሌላ ጣጣ ነውና ለራስሽም እያሰብሽ ሰርቶ መርዳት ሚችል ወንድም ከሆነ ደሞ እንዲሰራ ማበረታታት እንጂ እሱን እንደ ደሞዝ ብር እየላኩ እሱንም ማንሰፍ እራስሽንም ማዳከም የለብሽም እና አላህ እንዳለው በመለገስ ሰዓት በጣም መዘርጋት ማባከንም በጣም ማጠፍም መሰሰት መሃል ሆነሽ እነሱንም አንቺንም እየረዳሽ ሊሆን ይገባል።

2⃣ ኛው ሃለፍትና እና ሃላፊነት ማይሰማቸው ስግብግብ ወንዶች ናቸው !! በትዳር ስም ተቸግሪያለው በሚል ስም ብር ለመፍለጥ አንሰፍስፈው የሚጠብቁ ወንዶች ናቸው እወድሻለው በሚል ሆን ብለው በቻት እያዋራ በቃ ሀገር ቤት ስንገባ እንጋባለን በሚል ስትመጪ ማረፊያ ለአንዳንድ ነገሮች በሚል ብር እያስላከ እሱ ወይ ጫት ነው ሚቅበት ወይ ሌላ ትዳር ነው ሚመሰርትበት ስንቱን አየን ሰማን እነዛ ተቸገርኩ ወደድኩ ለሚል ሁላ ብር አትላኪ ሆን ብለው ለማጭበርበር የተሰለፉ ስግብግብ ወንዶች ናቸው ከነዚ ተኩላዋች እራስሽን ከቆጠብሽ ለራስሽ መሆን ትችያለሽ ለውጥም ይኖርሻል ከመፀፀትም ትድኛለሽ

3⃣ ኛው የዋህነትሽ ችግር ሆኖብሻል ሲበዛ የዋህ አቱኚ ሲበዛም ተጠራጣሪ አቱኚ መጠራጠር ግን በአንድዚ አይነት ነገር በጣም እርግጠኛ ለመሆን ይዳርጋል። የዋህነትሽን የተረዱ ናቸው በአንቺ ለመጫወት የሚመጡት እና አብዝቶ የዋህነት ችግር ነውና ቀንሺ ስንት ሰዋች ሸውዱሽ ስንት ሰዋች አታለሉሽ ሁሉም የሉም አደል ተነዋል ብርሽም ተናል አንዳንዱ ክብርሽንም ይዞ የሄደ ስንት አለ !! በጣም በዝቶ የዋህነትሽ ስልክ ሲቸግራቸው እንኳን አንድ የአረብ ሀገር ሴት በውስጥ ልጀናጀን እና ስልክ ላስልክ የሚሉ በቀቀን ወንዶች እንዳሉ አታቂም አላገጠመሽም አንቺስ አላክሽም ታዲያ በዚ በትንሹ የዋህ ከሆንሽ እንደው ወደድኩሽ ተቸገርኩልሽ ለሚልሽ አጭበርባሪማ ምን ያክል ነው ሚዘርፍሽ እና የዋህነትን ቀንሺ ለዚ መዳኛው ወደ ዲንሽ ተመለሽ ከአላህ ጋር በደንብ ተዋወቂ የዛኔ ነገሮች ሁላ ይስተካከላሉ ከአላህ በራቅሽ ቁጥር ነገሮች ሁላ ይበላሻሉ ስለዚ አማራጭ የሌለው ምርጫ ወደ አላህ መቅረብ ኢስላምን መኖር ነው ።

🌼 ቀጣይ ሌሎች ችግሮችን ለማየት ሞክራለው ለዛሬ እሄን ተግብረሽ ጠብቂኝ ኢንሻአላህ እንደምተገብሪው ተስፋ አለኝ ማ አሰላም።
📝......zizu nur
#በቴሌግራም #ለመከታተል👇

https://t.me/joinchat/AAAAAEPo5jHkW5Ui9vf2CQ
🌐 ሼር ማድረግም እንዳይረሱ

🌹 ባረከላሁ ፊክ
ብዥታን ማስወገድ ኡስታዝ አሕመድ ኣደም ሰሓቦች በዐቂዳ ተሳስተዋል በመካከላቸውም የአቂዳ ልዩነት ነበረ…
ኡስታዝ አሕመድ ሸይኽ ኣደም
🔊 ብዥታን ማስወገድ

ኡስታዝ አሕመድ ኣደም ሰሓቦች በዐቂዳ ተሳስተዋል በመካከላቸውም የአቂዳ ልዩነት ነበረ ብሏል ለሚለው ሰሞነኛ ወሬ የተሰጠ ማብራሪያ

🎙 በኡስታዝ አሕመድ ሸይኽ ኣደም

@ዛዱልመዓድ

https://t.me/joinchat/AAAAAEPo5jHkW5Ui9vf2CQ
🌐 ሼር ማድረግም እንዳይረሱ
በቃ ጀግንነት ሰለፊያ ይህ ነው

በትነው በታትነው አቤት ወንድነት
አቀጣጢ ወሬ ሆነሸ ከፊት ፊት
መደቆስ መዷቀስ ልኩን ነው ማሳየው
ልልፈራ ላልፈራ መስሚዬ ጥጥ ነው
ስፅፍ ጀግና እኮ ነኝ ወደረም የሌለኝ
ካነሳው አነሳው ከጣልኩኝ ጣልኩኝ
ደሞ ስፈጥን ማንስ ሊደርስብኝ
ዛሬ ተሳስቶ ዛሬ ረድ ሰጠሁኝ
ኡዙር ሚባል ነገር ከቶ አልፈጠረብኝ
ቁምቡርሱን አውጥቼ ባዶ ያስቀረሁኝ
ማንንም አልሰማ ለአዋም አልጨነቅ
ምን ገዶኝ እኔ ቢጨነቅ ባይጨነቅ
ወሬ ማሰራጨት መቧጨቅ ሟባጨቅ
አሽሙሬ ይገድላል ከጦርም ይብሳል
ቅኔውንስ መዝረፍ ከኔ ማን ይልቃል
ወጋ አድርጌ ሳጭቃጭቅ ማዋል
ውስጤ ከራሰልኝ ነፍስያ ከረካች
ጀግነቴ ሰምሮ አደባባይ ከወጣች
ምንም አልፈልግም የቀረው ይቀራል
ኡማው ተበትኖ የኔ ስም ይነግሳል
ለመንገስ ለመንገስ ሁሉም ተራሩጧል
ትንሹም ትልቁም እኩል ተሰልፏል
በርቱ ጠንክሩ የለም ወደ ሃላ
ፍርስርስ እስኪሚል እስኪጠፋ መላ
እስክኖን መሳቂያ ፣ የሰው መሳለቂያ
እኛም እምባ አለን ሌላም ባይኖረን
ይወጣልናል አልቅሰን አልቅሰን
ግን!! ልክ እንደ ሶሪያ ፀፀቱ ይቀራል
ከንብረትም በላይ ልቦች አቁስለሃል
ታዝናለህ የዛኔ ውጤቱን ስታየው
በስሜት ተነድተህ እሳቱን የጣልከው
በስሜት ተነድተሽ እሳቱን የጣልሽው
📝......zizu nur
https://t.me/joinchat/AAAAAEPo5jHkW5Ui9vf2CQ
🌐 ሼር ማድረግም እንዳይረሱ

🌹 ባረከላሁ ፊክ