ዘውትር አላህን ያስታውሡ
345 subscribers
398 photos
78 videos
7 files
285 links
ከወንድ ወይም ከሴት እርሡ አማኝ ኾኖ በጎን የሰራ መልካም ኑሮን በእርግጥ እናኖረዋለን።ይሠሩትም ከነበሩት ነገር በመልካሙ ምንዳነውን እንመነዳቸዋለን።[ ሱረቱ ነህል: 97]

For any comments•••• @zewtr_allahn_enastaws_bot
Download Telegram
አንዳንድ ጊዜ ህይወት በትንሽ መከራ አትፋታክም ፤ በትንሽ ፈተና አትጠግብክም ፤ላይ በላይ ትኮረኩምሃለች  ይህ ሰው ከዚህ በፊት ያየው መከራ ይበቃዋል ብላ አትተውህም ሁለት ሶስት ጊዜ ትሰብርሃለች ዘመንህን  በሙሉ አንተ ማየት የማትፈልገውን ደጋግማ ታሳይሃለች ፤ ለመከራ ነው እንዴ የተፈጠርኩት እስክትል ድረስ አፈር ታስልስሃለች....... ዱንያን ጀሊሉ ሲፈጥራት እንዲሁ ነች በድርጊቷ ብዙ አትዘን........ የሚገርመው ነገር አንተ ምንም ሆንክ ምንም ከመሄድ አትቆምም ፤የቱንም ያክል ችግር ቢደርስብክም አታዝንልክም ፤ ለአፍታ እንኳን ዞር ብላ አታይክም መጎዳትክን አታስተውልም፤ለብሶትህ ጆሮ አትሰጥም ፤ ለሀዘንህ አትቆዝምም ፤ለሞትህ የሃዘን ቀን አታውጅም፤ አንተ ተጎዳህ ብላ ላንተ አዝና ፀሐይ ብርሃኗን ከመስጠት አትወገድም፤ጨረቃ ፊቷ አይጠቁርም ፤አንተ በህይወት ብትቀጥልም ባትቀጥልም እነሱ ጉዳያቸው አይደለም........... እናማ በተጎዳክ ጊዜ ሁሉ ራስክን አክም ፤በተሰበርክ ጊዜ ሁሉ ራስክን ጠግን ፤ በወደቅክ ጊዜ ሁሉ ተነስ በምንም መልኩ አትስነፍ ተስፋ አትቁረጥ ፤የዱንያን ባህሪ ጠንቅቀህ እወቅ ፤ከነ ቁስልህ ተራመድ ........
መልካም ሚስት ይፈልጋሉ?

"መልካም ሴት በአንተ ጥረት አትመጣም ይልቁንም ጌታውን ለሚፈራ ሰው የተሰጠች ርዝቅ ናት።"

ርዝቅህን ከአሏህ ጠይቅ !
ቁርአን ውስጥ የተጠቀሱ 7 ከንቱ ምኞቶች
=============================

💫🌸 يَا لَيْتَنِي كُنْتُ تُرَابًا

النبأ- (40)
①) «ዋ ምኞቴ! ምነው አፈር በሆንኩ!»
[አ-ን'ነበእ: 40]




💫🌸 يَا لَيْتَنِي قَدَّمْتُ لِحَيَاتِي

الفجر-(24)

②) «ዋ እኔ! ምነው በሕይወቴ (መልካምን ሥራ)
ባስቀደምኩ ኖሮ!»
[አል-ፈጅር: 24]




💫🌸فَيَقُول يَا لَيْتَنِي لَـمْ أُوتَ كِتَابِيَهْ

الحاقة(25)
③) «ዋ ጥፋቴ! ምነው መጽሐፌን ባልተሰጠሁ!»
[አል-ሐቀህ: 25]




💫🌸 يَا وَيْلَتَى لَيْتَنِي لَـمْ أَتَّخِذْ فُلَانًا خَلِيلًا
الفرقان (28)

④) «ዋ ጥፋቴ! እገሌን ወዳጅ አድርጌ
ባልያዝኩ ኖሮ እመኛለሁ!»
[አል-ፉርቃን: 28]




💫 يَوْمَ تُقَلَّبُ وُجُوهُهُمْ فِي النَّارِ يَقُولُونَ يَا لَيْتَنَا أَطَعْنَا اللهَ وَأَطَعْنَا الرَّسُولَا

الأحزاب (66)

⑤) « ዋ ምኞታችን! አላህን በተገዛን፤
መልክተኛውንም በታዘዝን ኖሮ!»
[አል-አሕዛብ: 66]




💫🌸يَقُولُ يَا لَيْتَنِي اتَّخَذْتُ مَعَ الرَّسُولِ سَبِيلًا

الفرقان (27)
⑥) «ዋ ምኞቴ! ከመልክተኛው ጋር ቀጥተኛን መንገድ ይዤ በሆነ!»
[አል-ፉርቃን: 27]




💫🌸 يَا لَيْتَنِي كُنْتُ مَعَهُمْ فَأَفُوزَ فَوْزًا عَظِيمًا

النساء (73)
⑦) « ወይ ምኞቴ! ታላቅ ዕድልን አገኝ ዘንድ
ከነሱ ጋር በሆንኩ!»
[አ-ን'ኒሳእ: 73]


ሁሉም የሟቾች ምኞቶ ናቸው።
ቀብር ውስጥ ያሉት ሰዎች ምኞታቸው
ወደ ዱንያ አንዴ መጥተው ለአኺራቸው
ጥሩን ነገር መስራት ነው። ግን ምን ዋጋ አለው! አልፏል ተቀድሟል!
ቀብር ገብተህ አንተም ይህን
ከምትመኝ ነፍስህ አካልህ ውስጥ
እስካለች ድረስ ለአኺራህ አስቀድም።  ብልህ የሆነ ሰው ከመጸጸቱ በፊት ሥራውን ይሥራ

አላህ ሆይ! ከነዚህ ከንቱ ምኞቶች በእዝነትህ ጠብቀን።
📮👌قال رسول الله ﷺ الدال على الخير كا فاعله

📮👌ወደ መልካም ያመላከተ እንደ ሰሪው ነው ረሱል ﷺ
እንደማታገባት ጠንቅቀክ እያወቅክ አትቅረባት!
ራስህንም እርሷንም አትጉዳ
አሏህ እስኪያገራልህ ራስህን አቅብ! የጌታህን ክልከላ አትዳፈር!


@zewtr_allahn_enastaws
የኩዌቱ ፀሐፊ ዐብደላህ አልጃረላህ አላህ
ይዘንለት፡፡ በአንድ ወቅት እንዲህ ብሎ ነበር፡፡
🌺🌺🌺🌱🌺🌺🌺🌺
- ስሞት አላስብም፣ አልጨነቅም፣
- ገላዬ ፈራሽ ነውና ምን አሳሰበኝ
ሙስሊም ወንድሞቼ መደረግ ያለበትን ሁሉ ያደርጉልኛል፡፡
1- ልብሴን ያወልቃሉ፣
2- ያጥቡኛል፣
3- ይከፍኑኛል፣
4- ከቤቴ ይዘውኝ ይወጣሉ፣
5- ወደ አዲሱ ቤቴ (መቃብር) ይወስዱኛል፣
6- ብዙዎች ጀናዛዬን ለመሸኘት ይመጣሉ፣
7- እኔን ለመቅበር ሥራቸውንና ቀጠሯቸውን ሁሉ ትተው የሚመጡ አሉ፡፡
ከነኚህ መካከል ምናልባት ላንዳፍታ እንኳን ስለኔ አስበው የማያውቁ ብዙ
ናቸው፡፡
8- ቤተሰቦቼ እኔን ላለማስታወስ ያለኝን ነገር ሁሉ አውጥተው ይጥሉ
ይሆናል፤ አሊያም በኔ ሥም ይመፀውቱ ይሆናል
- ቁልፎቼ
- መጽሐፎቼ
- ጫማዎቼ
- ልብሦቼ …..
በአንድ ነገር ግን እርግጠኛ ሁኑ፡፡
- በመሞቴ ይህች ዱንያ ሐዘኗ አልበዛም፣ አለች አልፈረሠችም፣
- የዓለም እንቅስቃሴም ላፍታ አልቆመም፣
- የኢኮኖሚው ቀውስም አልተፈጠረም፣
- በሥራ ቦታዬ ላይ ሰው ለመቅጠር ማስታወቂያ ይወጣል፣
- ንብረቴ የወራሾቼ ይሆናል፣ በትንሽ በትልቁም ኦዲት የምደረገው ግን እኔ
ነኝ፣
- ስሞት መጀመሪያ ከኔ የሚገፈፈው ስሜ ነው፡፡ በሥሜ መጠራቴ
ይቀራል፤
- ጀናዛው የታለ እባላለሁ፡፡ ጀናዛውን ዉሰዱ፣ አምጡ እንስገድበት፣
ጀናዛውን እንቅበር … ይባላል
- ሥልጣኔ፣ ከተከበረ ቤተሰብ መሆኔ፣ ጎሳዬ … ሁሉ ዋጋ ያጣል፤
ዱንያ ይህን ያህል ቀላልና ተራ ነገር ነች፤ የምንሄድበት ዓለም ግን አቤት
ክብደቱ! ማስፈራቱ! …
በሕይወት ያለህ ወዳጄ ሆይ! በመሞትህ ሦስት ዓይነት ሐዘን አለ
1- የሚያውቁህ ዋ ያ ሚስኪን እኮ ሞተ! ይላሉ
2- ባልደረቦችህ ለሰዓታት አለያም ለቀናት ያዝኑና ወደ ሳቅና ጨዋታቸው
ይመለሳሉ፣
3- ትልቁ ሐዘን ያለው ቤትህ ነው፣ ቤተሰብህ ጋ … ሁሌም ያስታውሱህ
ይሆናል፣
የዱንያ ታሪክህ በዚህ መልኩ አበቃ ፤ የመጨረሻው ዓለም ታሪክህ
ተጀመረ
ሁሉ ነገርህ ተወሰደ፣ ፈረሠ፣ አለፈ፣ ጠፋ!!!
1- መልክህ፣
2- ሀብትህ፣
4- ጤናህ፣
5- ልጅህ፣
6- ቪላህ፣
7- ዝናህ፣
8- ሚስትህ/ባልሽ
ካንተ ጋር ሥራህ ብቻ ቀረ
እውነተኛው ሕይወት ተጀመረ፡፡
እዚህ ላይ አንድ ጥያቄ ልጠይቅህ/ሽ
ለአኺራህ ምን አዘጋጀህ!! እስቲ በጥልቀት አስብ፡፡
እናም በርታ፣ በርቺ እህቴ
1- በግዴታዎች፣
2- በሱንና ነገሮች፣
3- በድብቅ መፅውት፣
4- መልካም ሥራ አብዛ፣
5- ሌሊት ተነስተህ ስገድ፣
ትድን ዘንድ ጠንክር፣ ይሳካልህ ዘንድ በርታ፡፡
መልካም ንግግር ምጽዋት ነው፡፡ ምንም የለኝም አትበል፡፡ ሌላ ነገር
ብታጣ ይህችን በእጅህ የገባችውን ፅሑፍ መጽውት፣ ምንም ጉልበትና ጊዜ
አይወስድብህምና አታመንታ፡፡
ምንጭ ፡ ጠሪቁ ተውበህ
#የሆነ ነገር ተመኝተህ እንደተመኘኸው የተሠጠህ እንደሆነ ቀደር ይባላል፤ አላህ ነዉና የሠጠህ ዉሰደው።

የሆነ ነገር ተመኝተህ አብዝተህ አገኘዋለሁ የጠበቅከው እንደሆነ ሶብር ይባላል በመጠበቅህ ዉስጥ ሁሉ አጅር አለህና ጠብቀው ።

የሆነ ነገር ተመኝተህ ከጠበቅከው በታች ሆኖ ከተሠጠህ ሳታጉረመርም ከተቀበልከው ያ ሪዷ ይባላል ፤ አላህ የወደደልህን በመውደድህ እንኳን ደስ ያለህ።

@zewtr_allahn_enastaws
ጥበበኛው ሉቅማን ልጃቸውን ሲመክሩ እንዲህ ይላሉ ፦

" ከኢማን ቀጥሎ ልትደክምለት የሚገባው ትልቁ ነገር መልካም ጓደኛ ይሁን። መልካም ጓደኛ ምኗም እንደማይጣል መልካም ዛፍ ነው። በጥላው ትጠለላለህ። ከግንዱ ቤት ትሠራለህ። ከፍሬው ትመገባለህ።"

@zewtr_allahn_enastaws
ለህይወትህ ስኬትን ከፈለክ አይንህ ሳይሆን!
ልብህ #ያረፈባትን ሴት አግባ!

ምክንያቱም አይን ቀላዋጭ ነውና ብዙ ያምረዋል
ልብህን አድምጥ የአንተ ሚስት ለአንተ ብቻ ቆንጆ ውብ  ልዕልት ናትና።

@zewtr_allahn_enastaws
ሕይወታችንም፣ ሞታችንም፣ ደስታችንም፣ ሐዘናችንም፣ ጤናችንም፣ ሰላማችንም፣ ድክመታችንም፣ ጥንካሬያችንም ሁሉ ነገራችን በአላህ እጅ ነው፡፡ በሰው እጅ እንዳይመስላችሁ፡፡

አምላካችን ሆይ ድህነታችን ወዳንተ ነው፡፡ የምንከጅለው የምንመኘው ካንተ ነው፡፡ መልካሙን ሁሉ ዝነብልን፡፡
ወደኸኝ እንጂ አትውሰደኝ !

ወንጀሌ የበዛ የአላህ ባሪያ መሆኔ ሲታወሰኝ የወዳጅ ውዳሴም ሆነ የጠላት ዘለፋ  ከንቱ መሆኑ የበለጠ ፍንትው ብሎ ይታየኛል !

ፈጣሪየ አላህ ሆይ!

የወንጀል ሸክሜ የገዘፈብኝ ደካማ ባሪያህ ነኝና ይቅር በለኝ ! በሰራሁት አትያዘኝ !

ቀልቤንና ስራየን አጽድተህልኝ እንጂ ሞቴን አታምጣው!

ወደኸኝ እንጂ አትውሰደኝ !

Muhammed sirage
አራት ሴቶች ልብን ያረጋጋሉ

🎙አብዱ ሽኩር አቡ ፈዉዛን

abu_fewzan_abdu_shikur
ለአላህ የምትነግሩት ነገር የላችሁም ¿¿
ብቻችሁን ከእሱ ጋር ብቻ የሚፈታ ሀጃ የለባችሁም እእ ታዲያ ለምን አትነግሩትም አንዴ ጠይቃችሁት አልተቀበለኝም ብላችሁ ነው¿¿
ህፃን ልጅ እኮ የሆነ ነገር ሲፈልግ እርይ ብሎ አልቅሶ የፈለገውን ያስደርጋል
አላህ እኮ ሁሌ እኛን ሰሚ ነው አይሸሸንም አይመቸኝም አይለንም በወንጀላችን ብዛት እንኳን አያባረንም ራህመቱ እኮ ሰፊ ነው ....
ሁልጊዜ ለኛ በሩ ክፍት እኮ ነው




              
አንድ ሰው ሰላት ከጨረሰ በኋላ "አላሁመ አንተ ሰላም ወሚንከ አሰላም ተባረክተ ያ ዘል ጀላሊ ወልኢክራም" ሲል መልዕክቱ ምንድነው?

ሸይኽ ኢብኑ ኡሰይሚን አላህ ይዘንላቸውና እንዲህ ይላሉ:- "አንድ ሰው ይህንን ዚክር ሲል አላህ ሆይ ሰላቴን ሰላም አድርገህ የወንጀሌ መታበሻ እና ደረጃዬን ከፍ የሚያደርግልኝ እንድታደርግልኝ በዚህ በተከበረው ስምህ(አስ-ሰላም በሚለው) ወዳንተ እቃረባለሁ ማለቱ ነው።"

[شرح رياض الصالحين ٤٩١/٥]
ከትልልቆቹም በላይ…

ከአቢ በክራ (ረ.ዐ) ተይዞ፡ ከአላህ መልዕክተኛ (ﷺ) ዘንድ ሆነን ባለንበት እንዲህ አሉ፦

﴿أَلَا أُنَبِّئُكُمْ بِأَكْبَرِ الْكَبَائِرِ - ثَلَاثًا - الْإِشْرَاكُ بِاللَّهِ، وَعُقُوقُ الْوَالِدَيْنِ قَوْلُ الزُّورِ،﴾

“ከትልልቆቹም ወንጀሎች የበለጡ የሆነውን ወንጀል አልነግራችሁምን? ሶስት ግዜ ደጋጋሙት። በአላህ ማጋራት፣ የወላጆችን ሐቅ መቁረጥና የሐሰት ንግግር ናቸው።”

📚 ሙስሊም ዘግበውታል: 87
ጃቢር ረዲየላሁ አንሁ የአላህ መልዕክተኛ ﷺ ተከታዩን ሲናገሩ ሰምቻለሁ በማለት አስተላልፈዋል፡-
"ለሊት ውስጥ አንዲት ወቅት አለች
አንድ ሙስሊም ይህችን ወቅት አግኝቶ አላህን ከዚህችም ከመጭውም ዓለም ጉዳዮች አንዳች በጎ ነገር ከጠየቀ አላህ የጠየቀውን ይሰጠዋል። ይህች ወቅት በሁሉም ሌሊቶች ውስጥ ትገኛለች።

ሙስሊም ዘግበውታል

@zewtr_allahn_enastaws
🌹ስትናደድ ብዙ አታዉራ ቃላቶችህን ቸቆጣጠር,ቃላቶች እንዲቆጣጠሩክ አታድርግ,ብዙዎቹ በተናደድንበት ቅጽበት የምንናገራቸዉ ቃላት በስተመጨረሻም ተናጋሪዋ ይጸጸታል።
©
@zewtr_allahn_enastaws
↷እራሷን በሒጃብና በአይናፋርነት
የተሸፋፈነች ሴት፦
.
      "ለአባቷ ኩራት፤
      " ለወንድሟ ልቅና፤
     " ለባሏ ያልተነካ ሐብት፤
    " ለሴት ልጆቿ እና ለሙስሊም
    "ሴት ልጆች መልካም ተምሳሌት ናት።
.
           •••⊰✿ ✿⊱•••
.
"እህቴ ሆይ! ከሱና አስተዳደግ ውጪ ተርቢያ
"የተደረጉ ሴቶች አይሸውዱሽ.! የሓያእን ካባ
የሚያለብስሽን ተክክለኛው ሒጃብ ልበሺ.!!
NikabnewWbete
🔎ዱኒያ ላይ ስትኖር  መልካሚስትን አልያም መልካም ጓደኛን ያዝ ...!

قال لقمان الحكيم لابنه: 
يا بني

أول ما تتخذه في الدنيا امرأةٌ صالحةٌ و صاحبٌ صالحٌ، تستريح إلى المرأة الصالحة إذا دخلت
وتستريح إلى الصاحب الصالح إذا خرجت إليه.“

📕 |[أدب النساء للٱلبيري - ١٣٨].
💫 ብቻቹን ትሞታላቹ ብቻቹን ወደ መቃብራቹ ትገባላቹ ብቻቹን ከአላህ ፊት ትቆማላቹ ሞት ያማል መቃብር ጨለማ ነው ጊዜው ከማለፉ በፊት ራሳችንን እናዘጋጅ።
ያስነጠሰ ሰው አላህን ካመሰገነ ከአላህ እዝነትን ለምኑለት! ካላመሰገነ ግን...

وعن أَبي موسى رضي الله عنه، قَالَ: سَمِعْتُ رسول الله صلى الله عليه وسلم، يقولُ:  إِذَا عَطَسَ أحَدُكُمْ فَحَمِدَ اللهَ فَشَمِّتُوهُ، فَإنْ لَمْ يَحْمَدِ الله فَلاَ تُشَمِّتُوهُ  [رواه مسلم]

የአላህ መልእክተኛ(ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ተከታዩን ሲናገሩ ሰምቺያለው በማለት አቡ ሙሳ(ረዲያላሁ አንሁ) አሰተላልፈዋል፦

”ከእናንተ አንዳንቹ ሲያስነጥስ አላህን ካመሰገነ ከአላህ እዝነትን በመመኘት መልሱለት። አላህን ካላመሰገነ አትመልሱለት።” [ሙስሊም ዘግቦታል]

عن أَبي هريرة رضي الله عنه، عن النبيِّ صلى الله عليه وسلم،
  قَالَ:  إِذَا عَطَسَ أحَدُكُمْ فَلْيَقُلْ: الحَمْدُ للهِ، وَلْيَقُلْ لَهُ أخُوهُ أَوْ صَاحِبُهُ: يَرْحَمُكَ الله. فإذَا قَالَ لَهُ: يَرْحَمُكَ اللهُ، فَليَقُلْ: يَهْدِيكُمُ اللهُ وَيُصْلِحُ بَالَكُمْ  [رواه البخاري]

አቡ ሁረይራ(ረዲያላሁ አንሁ) እንዳስተላለፉት ነቢዩ(ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም)እንዲህ ብለዋል፦

"ከናንተ አንዳቹ በሚያነጥስ ጊዜ 'አልሐምዱ ሊላህ' (ለአላህ ምስጋና ይድረሰው) ይበል፡፡ ወንድሙም 'የርሐሙከላህ አላህ ይዘንልህ) ይበለው፡፡ እርሱም መልሶ 'የህዲኩሙላህ ወዩስሊሕ ባለኩም' (አላህ ቅኑን መንገድ ይምራቹ፣ ጉዳያቹንም ያስተካክልላቹ)' ይበል፡፡ [ቡኻሪ ዘግበዉታል]
ውዱዑን አሳምረህ አድርግ!

ረሱል صلى الله عليه وسلم እንዲህ ብለዋል፦

“ውዱዑ አድርጎ ውዱዑን ያሳመረው ሰው፤ ኃጢአቶቹ ከጥፍሮቹ ስር እንኳ ሳይቀር ከአካላቱ ይወጣሉ።”

ሙስሊም ዘግበውታል: 245

@zewtr_allahn_enastaws